የጉብሬና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል 🇸🇦

Description
ትክክለኛው እስላማዊ አስተምህሮ ከቁርአንና ከሐዲስ ከደጋግ ቀደምቶች አረዳድ ከታማኝ ዑለሞች ንግግር የሚሰራጭበት ቻናል ነው።
Advertising
We recommend to visit

🎪SERVING YOU THE FUNNIEST MEMES🎪

Join 💡 @Habeshan_memes 💡

©Credit Facebook group የዩኒቨርስቲ ትዝታዎቼ and ግቢ memes


📥DM for credit / removal

Https://Www.instagram.com/Gebi.Memes



😂😛
@gebi_memes

@gebi_memes

Last updated 1 week ago

ዳንኤል ፍቃዱ ተስፋዬ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ
ስልክ - 0913158507 ወይም 0978554559
Daniel Fikadu Tesfaye Certified Attorney of law at all Federal Courts of Ethiopia.
Email- nurotekore@gmail. Com
⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️

Last updated 4 months, 1 week ago

1 year, 5 months ago

#አዲስ ደርስ በጀርሕ ወት-ተዕዲል ዙሪያ

?ክፍል 01

?ርዕስ፡-

?ሁሉም ሊያዳምጠው የሚገባ ወቅታዊ ማብራሪያ⤵️

በጀርሕ ወት' ተዕዲል ዙሪያ የተዘጋጀውን ሪሳላ ማብራርሪያ "
? ጀርሕ ወት-**ተዕዲልን የመሰለ ታላቁን ዒባዳ፣ልክ እንደ ጨው ነው በሚሉ ሰዎች ላይ የተሰጠ ምላሽ፤

? የሙመይዪዓዎች አደገኛና መርዛማ አካሄዳቸው የተጋለጠበት...ወቅታዊ ማብራሪያ።**

? በመረጃ የታጀብ ድንቅ ምላሽ

አዘጋጅ፡- ዶ/ር በሸይኽ አቡ ዓብዲላህ ሑሰይን ሙሐመድ አስ'ስልጤ ሃፊዘሁሏህ

??አቅራቢኡስታዝ ሸምሱ ጉልታ አቡ ሀመውያ ሃፊዘሁሏህ

? በአል-ኢስላሕ መድረሳ* የተሰጠ ወሳኝ ትምህርት*

? ይ --ቀ--ጥ--ላ--ል።
https://t.me/medresetulislah
????
የተለያዩ ትምህርቶችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችን
⤵️* #join *ያድርጉና ይቀላቀሉhttps://t.me/umusaymenhttps://t.me/umusaymen

1 year, 5 months ago

↪️ **አዲስ እና ተከታታይ ደርስ!

➡️ የኪታቡ ርእስ፦ ዶላሉ ጀማአቲል አህባሽ! ክፍል አምት 05

? በወንድም፦ ሙሀመድ አል–ወልቂጢይ**

https://t.me/gubreahlelsunajemea/7114

1 year, 5 months ago

*? ዓሹራእና ምንዳው*

➧ ዓሹራእ ማለት የሙሐረም ወር 10ኛ ቀን ሲሆን ከነብዩላሂ ሙሳ አስገራሚ ታሪኮች አንዱን የሚያስታውሰን ቀን ነው።
ነብዩላሂ ሙሳ ፊርዓውን ህፃናቶችን በሚያርድበት ዘመን ተወልደው በራሱ ቤት እንዲያድጉ አላህ ያሻውን ሰሪ የሆነው ጌታ አደረገ። ይህም ፊርዓውን በይተል መቅዲስ አካባቢ የተነሳ እሳት የግብፅን ምድር ሲያጠፋ በህልሙ ያይና ለጠንቋዮቹና ድግምተኞቹ ሲነግራቸው ከእስራኤላዊያን የሚወለድ ህፃን የንግስናው መጥፊያ ሰበብ እንደሚሆን ነግሩት። ፊርዓውንም ከሚወለዱት ህፃናት ሴቶቹ ቀርተው ወንዶቹ እንዲታረዱ አዘዘ።
ይህ ነገር አገልጋይ እንዳያሳጣቸው የፈሩት ግብፃዊያን ፊርዓው ዘንድ ሄደው አቤቱታ ሲያቀርቡ አንድ አመት የሚወለደው ተትቶ በሌላኛው አመት የሚወለደው እንዲታረድ አዘዘ። የአላህ ፍላጎት ሆነና ነብዩላሂ ሙሳ ወንድ ህፃናቶች በሚታረዱበት አመት ተወለዱ። የእስራኢላዊያን ህፃናት መወለድ የሚጠባበቁ ሰራዊቶች በመኖራቸው የነብዩላሂ ሙሳ እናት ጊዜዋ በመድረሱና አመቱ ወንድ ህፃናት የሚታረዱበት በመሆኑ ጭንቅ ውስጥ ገባች። የተፈራው አልቀረም ህፃኑ ተወለደ። እናት ምን ይዋጣት!!!?

↪️ አላህ ሁሉን ቻይ መሆኑን ሊያሳያት በሳጥን አድርገሽ ወደ ቀይ ባህር ወርውሪው የሚል መልእክት እንዲመጣላት አደረገ። ወረወረችውም። ወደ አላህም ፍፁም ተማፀነች። አላህም ልጇን እንደሚመልስላት ቃል ገባላት። ባህሩ ሳጥኑን ወደ ፊርዓውን ቤተመንግስት እየነዳ አደረሰው። የፊርዓው አገልጋይ ሴቶች ሳጥኑን አገኙት ሲከፍቱት የሚያምር ህፃን ነው!!!። ወደ ቤተመንግስት ተወሰደ። ኣሲያ የፊርዓው ባለቤት የአይናችን ማረፊያ ይሆናል ልጅ አድርገን እንያዘው አትግደለው አለችው ተቀበላት።

ረሃብ ይዞት ሲያለቅስ የሚቀርብለት ጡት በሙሉ እንቢ አለ። ምናልባት የሚስማማው ጡት ከተገኘ ብለው ሴቶችን ሲፈለጉ እህታቸው ማንነቷን ደብቃ አንድ ህፃናት በሙሉ ጡቷን የሚጠቡላት ሴት ላመላክታችሁ ወይ ብላ ጠየቀች አው አሉ። እናታቸው ወደ ቤተመንግስት መጣች!!!። ሱብሃናላህ በፊርዓውን ቤተመንግስት በእሱ ተንከባካቢነት በእናታቸው ጡት እንዲያድጉ አላህ አደረገ። በወቅቱ እስራኤላዊያን በቂብጦች የመከራ ገፈት ይጎነጩ ነበር። አላህ በሙሐረም 10ኛ ቀን ፊርዓውንን ከነሰራዊቱ አጥፍቶ እሳቸውንና ህዝቦቻቸውን ነጃ አወጣ።
የአላህ መልእክተኛ ነብዩ ሙሐመድ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ወደ መዲና ሲሄዱ አይሁዶች ይህን ቀን ሲፆሙ አገኙዋቸው። ለምንድነው የምትፆሙት ብለው ሲጠይቁዋቸው ይህ ቀንማ አላህ ፊርዓውን አጥፍቶ ሙሳን ያዳነበት ቀን ነው። ለዚህ ነው የምንፆመው አሉዋቸው። እሳቸውም ለሙሳማ እኔ ከናንተ የቀረብኩኝ ነኝ ብለው መፆም ጀመሩ ተከታዮቻቸውንም እንዲፆሙ አዘዙ። ያለውንም ምንዳ ሲናገሩ እንዲህ አሉ:–

"صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ وَصِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ"
رواه مسلم   ( 1162).

"የዓረፋ ቀንን መፆም ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። የዓሹራእ ቀንን መፆም ደግሞ ያለፈውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።"

♻️ አዩዶችን ለመኻለፍ አላህ ካቆየኝ የሚመጣውን አመት ዘጠነኛውን የሙሐረም ቀን እፆማለሁ ብለው ነበር። ከዚህ በመነሳት የሙሐረምን ዘጠነኛና አስረኛ ቀን መፆም ይወደዳል። አብዛኛዎች ፉቀሃዎች ዘጠነኛ አስረኛና አስራ አንደኛውን ቀን መፆም ሱና ነው ይላሉ። ነገር ግን ከመረጃ አንፃር ዘጠነኛና አስረኛው ነው። ይህ ካልተቻለ አስረኛና አስራ አንደኛውን በመፆም አይሁዶችን መኻለፍ ይቻላል።
አላህ ይወፍቀን።

ከተወሰነ ማስተካከያ ጋር በድጋሚ የተለቀቀ።

http://t.me/bahruteka

Telegram

ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

***👉*** ዓሹራእና ምንዳው ➧ ዓሹራእ ማለት የሙሐረም ወር 10ኛ ቀን ሲሆን ከነብዩላሂ ሙሳ አስገራሚ ታሪኮች አንዱን የሚያስታውሰን ቀን ነው። ➧ ነብዩላሂ ሙሳ ፊርዓውን ህፃናቶችን በሚያርድበት ዘመን ተወልደው በራሱ ቤት እንዲያድጉ አላህ ያሻውን ሰሪ የሆነው ጌታ አደረገ። ይህም ፊርዓውን በይተል መቅዲስ አካባቢ የተነሳ እሳት የግብፅን ምድር ሲያጠፋ በህልሙ ያይና ለጠንቋዮቹና ድግምተኞቹ ሲነግራቸው ከእስራኤላዊያን…

1 year, 6 months ago

የዙል ሒጃ 11,12,13ኛ ቀናቶች

روى نبيشة الهذلي أن النبي ﷺ قال:-
«أيام التشريق أيام أكل وشرب وذكر الله »
.
أخرجه مسلم

وفي رواية الإمام أحمد
«من كان صائماً فليفطر فإنها أيام أكل وشرب»
صحيح مسلم

➡️ ኑበይሻ አል ሁዘልይ የተባለ ሶሓብይ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላል፦

"አያመ ተሽሪቅ (የዙል ሒጃ 11,12,13ኛ) ቀናቶች የሚበላባቸውና የሚጠጣባቸው እንዲሁም አላህ የሚዘከርባቸው ቀናቶች ናቸው።"
በሌላ ዘገባ ደግሞ እንዲህ ብለዋል፦
"ፆመኛ የሆነ ሰው ያፍጥር እነዚህ ቀናቶች የሚበላባቸውና የሚጠጣባቸው ቀናቶች ናቸው።"

↪️ በየወሩ ሶስት ቀን (አያመል ቢድ የሚፆም ሰው በዙልሒጃ ወር ሁለት ቀን ነው የሚፆመው (14 ኛና 15) ቀን 13 ኛው ቀን አያመ ተሽሪቅ ውስጥ ስለሚገባ መፆም አይቻልም።

አላህ ዒዳችንን ይቀበለን።

https://t.me/bahruteka

Telegram

ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

የዙል ሒጃ 11,12,13ኛ ቀናቶች روى نبيشة الهذلي أن النبي ﷺ قال:- «أيام التشريق أيام أكل وشرب وذكر الله ». أخرجه مسلم وفي رواية الإمام أحمد «من كان صائماً فليفطر فإنها أيام أكل وشرب» صحيح مسلم ***➡️*** ኑበይሻ አል ሁዘልይ የተባለ ሶሓብይ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላል፦ "አያመ ተሽሪቅ…

1 year, 6 months ago

، عَن عبدِ اللهِ بنِ قُرْطٍ -رضيَ اللهُ عنهُ- قالَ : قالَ رسولُ اللهِ ﷺ :

«إِنَّ أَعْظَمَ الْأَيَّامِ عِنْدَ اللَّهِ تَبَارَكَ وَتَعَالَى يَوْمُ النَّحْرِ، ثُمَّ يَوْمُ الْقَرِّ »،

أخرَجَهُ أحمدُ وأبو داودَ،

والمُرَادُ بِيومِ القَرِّ اليومَ الحادِيَ عَشَرَ

ዐብዱላሂ ኢብኑ ቀርጢን – ረዲየላሁ ዐንሁ – የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – እንዲህ ብለዋል ይላል : –

" አላህ ዘንድ ትልቅ ቀኖች ማለት የውመ ነሕርና ከዛ ቀጥሎ የውመል ቀር ( የዙል ሒጃ 10 ኛውና 11 ቀን) ናቸው " ።

የውመል ቀር በማለት የተፈለገው 11ኛው ቀን ነው ።

https://t.me/bahruteka

Telegram

ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም https://telegram.me/bahruteka

، عَن عبدِ اللهِ بنِ قُرْطٍ -رضيَ اللهُ عنهُ- قالَ : قالَ رسولُ اللهِ ﷺ :
1 year, 6 months ago

አሰላሙ አለይኩም ውድ የሱና ቤተሰቦች
ዒድ ሙባረክ ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊኸል አዕማል እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን በተለይም
1 ሌራ እና አከባቢዋ
2 ወራቤ እና አከባቢዋ
3 ቡታጀራ እና አከባቢዋ
4 አረቅጥ እና አከባቢዋ
5 አዲስ አበባ እና አከባቢዋ
6 ባህርዳር እና አከባቢዋ
7 ሀራ እና አከባቢዋ
8ኮምቦልቻ እና አከባቢዋ
9 ሸዋሮቢት እና አከባቢዋ
10 መርሳ እና አከባቢዋ
11 አልከሶ እና አከባቢዋ
12 ቅበት እና አከባቢዋ
13 ሁልባረግ እና አከባቢዋ
13 ጉብሬ እና አከባቢዋ
14 ሀዋሳ እና አከባቢዋ
15 ሚቶ እና አከባቢዋ
16 ሳንኩራ እና አከባቢዋ
17 አዳማ እና አከባቢዋ
18 ቆሼ እና አከባቢዋ
19 ጉንችሬ እና አከባቢዋ
20 የሀረር እና የአፋር እንዲሁም
በተለያዩ የሀገራችንክፍሎች እና የውጭ ሀገራት የምትገኙ ሰለፍዮችእንኳን አላህ ለ1444 የዒድል አድሐ አረፋ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን በዓሉየኢማን የሰላም የጤና የመተዛዘን እንዲሆንልን እመኛለሁ።
ወንድማችሁ ሙከረም
ኢብኑ ሽፋ ።።።።።።።ከጉንችሬ ።።።።።።።።።።

https://t.me/abuzekeryamuhamed
https://t.me/abuzekeryamuhamed

Telegram

ሙሐመድ አል-ወልቂጢይ ((አቡ ዘከሪያ))

***✍***አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱ ላሂ ወበረካቱ። ውድ እና የተከበራቹ የዚህ ቻናል ተከታታዮች ይህ ቻናል ረመዳን 29 1442 አ.ሂ የተከፈተ ቻናል ሲሆን አላህ ካለ የሀገራችን ሙስሊም ማህበረሰብን በተለይ ደግሞ ወልቂጤ ላይና ዙሪያዎቿ የሚገኙ ማህበረሰቦችን ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ እስላማዊ ትምህርቶች የሚለቀቁበት ቻናል ነው።

**አሰላሙ አለይኩም ውድ የሱና ቤተሰቦች**
1 year, 6 months ago

? ከፓኪስታን - መካ በእግር . . .

የፓኪስታኑ ተማሪ ኡስማን አርሻድ ለሃጅ ሃይማኖታዊ ጉዞ ጃንጥላ እና በጀርባ ላይ የሚታዘል ሻንጣ ይዞ 4,000 ኪሎ ሜትር በእግሩ በመጓዝ ሳዑዲ አረቢያ መካ ደርሷል።

አቅሙ ያለው ሙስሊም በሕይወት ዘመኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ ለማሳካት የሚመኘውን የሃጅ ጉዞ ኡስማን አርሻድ በእግሩ በመጓዝ አውን አድርጎታል።

ጉዞውን የጀመረው ፤ ከትውልድ ከተማው የፓኪስታኗ ኦካራ ሲሆን፣ ስድስት (6) ወራትን ተጉዞ ነው መካ የደረሰው።

ቅዱሱን የሃይማኖታዊ ጉዞ በእግሩ የፈጸመው ኡስማን በሺዎ የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች በእግር በመጓዝ ሳዑዲ አረቢያ መካ ለመድረስ የተለያዩ አገራትን ማለትም ኢራን ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስን (UAE)  አቆራርጧል።

ኡስማን አርሻድ ስለ ጉዞው ምን አለ ?

" ሁሉም ሙስሊም በሕይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ #መካ መጥቶ የፈጣሪን ቤት ማየት ይነኛል።

የእኔ ምኞች ደግሞ በእግር ተጉዤ የፈጣሪንና የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)  መስጂድ ማየት ነበር።

ጉዞው ከባድ ነበር የኢራቅ ቪዛን ማግኘት ስላልቻልኩ ከኢራቅ ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ለመግባት ጀልባ ነበር የተጠቀምኩት።

አንዳንድ ችግሮች ነበሩ መጥፎ የሆነ የአየር ሁኔታ እና በጉዞው ምክንያት እግር መቁሰል አጋጥሞኛል።

አብዛኛው መንገድ ሰው የማይታይበት እና መንደርም ሆነ ከተማ ያልነበረው ነው።

ጉዞዬን እንድቀጥል ያደረጉኝ መንገድ ላይ ያገኘኋቸው ሰዎች ናቸው። ረጋ ብዬ ጉዞዬን መጨረስ እንዳለብኝ አበረታተውኛል።

ባገኘሁበት ቦታ ነበር የማድረው፣ በመስጂድ  ፣ በፍተሻ ጣቢያ ፣ በሆቴል፣ ወይም እንዳርፍ ከፈቀዱልኝ ሰዎች ጋር ሊሆን ይችላል። አማራጭ ሳጣ ድንኳን ጥሬ በረሃ ላይ ብዙ ጊዜ አድሬያለሁ።

በመጨረሻም ከ6 ወር በኃላ ያሰብኩበት ደርሻለሁ።

ምንም ነገር ማድረግ ብትፈልጉ በራሳችሁ ተማመኑ።  ማንኛውንም ጉዞ እንድትፈፅሙ ፈጣሪ ይረዳችኋል። "

ምንጭ በተለያዩ ሚዲያዎች ተሰራጭቷል

https://t.me/bahruteka

Telegram

ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም https://telegram.me/bahruteka

***?*** ከፓኪስታን - መካ በእግር . . .
1 year, 6 months ago

? ከዒድ አዳቦች

☑️ ሰውነትን መታጠብና ካለ ልብስ ውስጥ ጥሩ የሆነውን መልበስ
ቅባት ወይም ሽቶ መቀባት
☑️ ምንም ነገር ሳይቀምሱ መውጣት
ወደ ዒድ ቦታ ከተቻለ በእግር መሄድ
☑️ ወደ ዒድ ቦታ ተክቢራ እያደረጉ መሄድ
ቤተሰብን ህፃናትንም ጨምሮ ወደ ዒድ ቦታ ይዞ መሄድ (ከዱዓኡ ነረካ እንዲካፈሉ)
☑️ ሶላት እንደተሰገደ ተምር መብላት
ሲመለሱ ከሄዱበት መንገድ በሌላ መመለስ
☑️ እቤት እንደ ደረሱ ሁለት ረካዓ መስገድ
እንደ ተመለሱ ቶሎ ኡድሒያውን አርዶ ቁርስ ከስጋው መብላት

➧ እነዚህ ከዒድ ኣዳቦች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው አላህ ለስራው ይወፍቀን።

https://t.me/bahruteka

Telegram

ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

***👉*** ከዒድ አዳቦች ***☑️*** ሰውነትን መታጠብና ካለ ልብስ ውስጥ ጥሩ የሆነውን መልበስ ***✅*** ቅባት ወይም ሽቶ መቀባት ***☑️*** ምንም ነገር ሳይቀምሱ መውጣት ***✅*** ወደ ዒድ ቦታ ከተቻለ በእግር መሄድ ***☑️*** ወደ ዒድ ቦታ ተክቢራ እያደረጉ መሄድ ***✅*** ቤተሰብን ህፃናትንም ጨምሮ ወደ ዒድ ቦታ ይዞ መሄድ (ከዱዓኡ ነረካ እንዲካፈሉ) ***☑️*** ሶላት እንደተሰገደ ተምር መብላት ***✅*** ሲመለሱ ከሄዱበት መንገድ በሌላ መመለስ…

1 year, 6 months ago

ቀደም ሲል የተለቀቀው አልሰራ ላላችሁ ይህን ተጠቀሙ
➘➘➘
https://t.me/AbuImranAselefy/7056

#አዲስ_ኪታብ_ስለ_ሙመይአዎች

↩️التحذير البديع من دعاة ومنهج التمييع

↪️ ከተምይዕ ተጣሪዎች እና አካሄድ ልዩ ማስጠንቀቅ
? للشيخ محمد بن علي بن حزام الفضلي البعداني حَفِظَهُ اللهُ وَرَعَاهُ
? በሸይኽ ሙሐመድ ብን አልይ ብን ሂዛም አላህ ይጠብቃቸው

https://t.me/AbuImranAselefy/7054

1 year, 6 months ago

? ወ ድ የሱና ቤተሰቦቻችን አላህ እንኳን ለዒደል አድሓ በሰላም አደረሳችሁ

تقبل الله منا ومنكم

አላህ ዒዱ የሰላም የፍቅርና የአላህን ውዴታና እዝንት የሚያስገኝ ያድርግልን ።

የዘንድሮ ዒድ ከሌላ ጌዜ ለየት ባለ መልኩ የሚዘረፍበት ነውና እንጠቀምበት ። ብዙ ወንድምና እህቶች በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ያሉበት ነው ። ከሞቀ ቤታቸው ከተረጋጋ ህይወታቸው አላህ ለሒክማው በፈለገው ነገር ሜዳ ላይ ወድቀው ህፃናቶቻቸውን ይዘው የሰው እጅ እያዩ ነው ። የዚህ አይነት ፈተና ይገጥመናል ብለው አስበውት በማያውቁት ፈተና ውስጥ ናቸው ። በርግጥ ሶብር ካደረጉ መጨረሻው ያመረ መሆኑ ጥርጥር የለውም ።
እናስታውሳቸው አብሽር እንበላቸው ሐዘናቸውን እናስረሳቸው ። ዒዱ የደስታ እንዲሆንላቸው እንድረስላቸው እንዘይራቸው ። የዱንያ ህይወት ፈተና አያጣውምና የኛም ሁኔታ አይታወቅም ስለዚህ የዛሬ መልካም ስራችን ለነገ ስንቃችን ነውና እንሰንቅ ።

https://t.me/bahruteka

Telegram

ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም https://telegram.me/bahruteka

***?*** ወ ድ የሱና ቤተሰቦቻችን አላህ እንኳን ለዒደል አድሓ በሰላም አደረሳችሁ
We recommend to visit

🎪SERVING YOU THE FUNNIEST MEMES🎪

Join 💡 @Habeshan_memes 💡

©Credit Facebook group የዩኒቨርስቲ ትዝታዎቼ and ግቢ memes


📥DM for credit / removal

Https://Www.instagram.com/Gebi.Memes



😂😛
@gebi_memes

@gebi_memes

Last updated 1 week ago

ዳንኤል ፍቃዱ ተስፋዬ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ
ስልክ - 0913158507 ወይም 0978554559
Daniel Fikadu Tesfaye Certified Attorney of law at all Federal Courts of Ethiopia.
Email- nurotekore@gmail. Com
⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️

Last updated 4 months, 1 week ago