Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

Addis Standard Amharic

Description
አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago

3 weeks, 2 days ago
Addis Standard Amharic
3 weeks, 2 days ago
Addis Standard Amharic
3 weeks, 2 days ago
አትሌት መዲና ኢሳ በ5 ኪሎ ሜትር …

አትሌት መዲና ኢሳ በ5 ኪሎ ሜትር ከ20 ዓመት በታች የሩጫ ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረች

የአዲዳስ ኩባንያ ባዘጋጀው አዲዜሮ የ5ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት መዲና ኢሳ ከ20 ዓመት በታች የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር አሸነፈች፡፡

የ19 ዓመቷ አትሌት መዲና ርቀቱን 14 ደቂቃ ከ38 ሰከንድ በማጠናቀቅ ነው የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር ጭምር ያሸነፈችው፡፡

በዚሁ ውድድር አትሌት መልክናት ውዱ ሁለተኛ እንዲሁም ፎቲየን ተስፋይ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡

በወንዶች ዮሚፍ ቀጄልቻ በ13 ደቂቃ በመግባት ሲያሸንፍ ይሁኔ አዲሱ በ5 ሴኮንዶች ዘግይቶ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡

(ፋና)

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek

1 month ago

ዜና: #ከአላማጣ ከተማ እና አከባቢዋ ተፈናቅለው ቆቦ እና ሰቆጣ የተጠለሉ ሰዎች ቁጥር 29 ሺ እንደሚጠጋ ተመድ አስታወቀ

በቅርቡ በራያ አላማጣ አከባቢ ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት ሳቢያ ከቀያቸው ተፈናቅለው በሰሜን ወሎ ዞን #ቆቦ ከተማ እና በዋግ ህምራ ዞን #ሰቆጣ ከተማ ተጠልለው የሚገኙ ሰዎች ቁጥር 29 ሺ እንደሚጠጋ የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ቢሮ (ኦቻ) አስታወቀ።

አብዘሃኛዎ ህጻናት እና ሴቶች የሆኑ 23ሺ ተፈናቃዮች ቆቦ፣ 5ሺ 980 የሚሆኑት ደግሞ ሰቆጣ ከተማ ተጠልለዋል ያለው ቢሮው በአከባቢው ያለው ሁኔታ አሁንም የተረጋጋ ባለመሆኑ ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል ሚያዚያ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት ጠቁሟል።

የምግብ እና ውሃ እጥረቱ አሳሳቢ ነው ያለው ቢሮው አፋጣኝ የነፍስ አድን እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አስታውቋል።
https://wp.me/pfjhHd-16P

Addis standard

ከአላማጣ ከተማ እና አከባቢዋ ተፈናቅለው ቆቦ እና ሰቆጣ የተጠለሉ ሰዎች ቁጥር 29 ሺ እንደሚጠጋ ተመድ አስታወቀ - Addis standard

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12/2016 ዓ.ም፡- በቅርቡ በራያ አላማጣ አከባቢ ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት ሳቢያ ከቀያቸው ተፈናቅለው በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ እና በዋግ ህምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ ተጠልለው የሚገኙ ሰዎች ቁጥር 29 ሺ እንደሚጠጋ የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ቢሮ (ኦቻ) አስታወቀ። አብዘሃኛዎ ህጻናት እና ሴቶች የሆኑ 23ሺ ተፈናቃዮች ቆቦ፣ 5ሺ 980 የሚሆኑት ደግሞ ቆቦ ከተማ…

ዜና: [#ከአላማጣ](?q=%23%E1%8A%A8%E1%8A%A0%E1%88%8B%E1%88%9B%E1%8C%A3) ከተማ እና አከባቢዋ ተፈናቅለው ቆቦ እና ሰቆጣ የተጠለሉ ሰዎች ቁጥር 29 ሺ እንደሚጠጋ ተመድ አስታወቀ
1 month ago
ዜና: [#ኢትዮጵያ](?q=%23%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB) ለአይኤምኤፍ ከጠየቀችው አዲስ ብድር …

ዜና: #ኢትዮጵያ ለአይኤምኤፍ ከጠየቀችው አዲስ ብድር ጋር በተያያዘ አሁንም ልዩነቶች መኖራቸው ተጠቆመ

ኢትዮጵያ አይኤምኤፍ እንዲሰጣት በጠየቀችው ብድር እና በኢኮኖሚ ማሻሻያ ፓኬጅ ዙሪያ አሁንም ከአይኤምኤፍ ጋር ልዩነቶች መኖራቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል የተቋሙ ከፍተኛ ባለስልጣን እንደነገሩት አስታወቀ።

ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ ድጋፍ ማግኘት ከፈለገች መገበያያ ገንዘቧ ብር ከዶላር ጋር ያለው ምንዛሬ በከፍተኛ ሁኔታ እንድታዳክም መጠየቋን የጠቆመው ሮይተርስ በሀገሪቱ መደበኛ ምንዛሬ አንድ ዶላር ከሚመነዘርበት በ50 በመቶ ተዳክሞ በጥቁር ገበያ እንደሚመነዘር አመላክቷል።

ኢትዮጵያ በዚህ ደረጃ የመገበያያ ገንዘቧን ማዳከም እንደሚጠበቅባት በባንኩ በኩል እንደ ቅድመ ሁኔታ መቀመጥ አለመቀመጡን ማረጋገጥ አለመቻሉን የዜና አውታሩ ገልጿል፤ ተቋሙ ተለዋዋጭ የሆነ በገበያ ሁኔታ የሚወሰን የውጭ ምንዛሬ ተመን መኖር አለበት ብሎ እንደሚያምን ጠቁሟል።

“ልዩነቶች ቢኖሩም አሁንም ድርድሩ እንደቀጠለ ነው” ሲሉ የአይኤምኤፍ የኢትዮጵያ ልዑክ አልቫሮ ፒሪስ ድርድሩ በሚካሄድበት በዋሽንግተን ለጋዜጠኞች መናገራቸውነ ያስታወቀው ሮይተርስ “አስቸጋሪ ቢሆንም ስምምነት ላይ ለመድረስ ተስፋ አለ” ማለታቸውን ጠቁሟል። በኢትዮጵያ መንግስት እና በአይኤምኤፍ በኩል ስላሉ ልዩነቶች ዝርዝር ጉዳዮች ከመጥቀስ መቆጠባቸውን አመላክቷል።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek

1 month ago
[#ቻይናዊውን](?q=%23%E1%89%BB%E1%8B%AD%E1%8A%93%E1%8B%8A%E1%8B%8D%E1%8A%95) ሆን ብለው እንዲያሸንፍ ያደረጉ የ …

#ቻይናዊውን ሆን ብለው እንዲያሸንፍ ያደረጉ የ #ኬንያና #ኢትዮጵያ አትሌቶች ሜዳሊያቸውን ተነጠቁ

በቤጂንግ ግማሽ ማራቶን ከስፖርታዊ ጨዋነት ባፈነገጠ መልኩ ቻይናዊውን አትሌት ሆን ብለው እንዲያሸንፍ አድርገዋል የተባሉ የኬንያ እና የኢትዮጵያ አትሌቶች ያገኙት ሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት ተነጠቀ።

ባልተገባ መንገድ ውድድሩን እንዲያሸንፍ የተደረገው ቻይናዊ አትሌትም ሽልማቱን ተነጥቋል።

ኬንያውያኑ አትሌቶች ዊሊ ምናንጋት እና ሮበርት ኬተር እንዲሁም ኢትዮጵያዊው ደጀኔ ሃይሉ ቢቂላ ማሸነፊያው መስመር ላይ ሆን ብለው ቻይናዊው እንዲያሸንፍ ፍጥነታቸውን ሲገቱ እንደነበር መታየታቸው ተገልጿል፡፡

ባለፈው እሁድ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ሩጫ ውድድር ላይ የተፈፀመውን ያልተገባ ድርጊት የተመለከተው የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ ጉዳዩን እየመረመረ መቆየቱን ገልጿል፡፡

ኬንያዊው ምናንጋት መጀመሪያ ላይ የእስያ ጨዋታዎች ሻምፒዮናን እንዲያሸንፍ ያደረገው ጓደኛው በመሆኑ ነው ቢልም፤ ነገር ግን በኋላ ላይ ለማሯሯጥ እንደተቀጠረ ተናግሯል።

ይህንንም ተከትሎ የቤጂንግ ግማሽ ማራቶን ውድድር አዘጋጁ የአሸናፊውን ሂ ጄ እና የሦስቱን አትሌቶች ሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት መንጠቁን ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት ዘግቧል፡፡

(ፋና)

1 month, 1 week ago
**በ** [**#አማራ**](?q=%23%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AB) **ክልል** [**#ምስራቅ\_ጎጃም**](?q=%23%E1%88%9D%E1%88%B5%E1%88%AB%E1%89%85_%E1%8C%8E%E1%8C%83%E1%88%9D) **ዞን 38 …

#አማራ ክልል #ምስራቅ_ጎጃም ዞን 38 ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ ጀመሩ

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን በተፈጠረዉ “የፀጥታ ችግር ምክንያት” ተቋርጦ የነበረው ትምህርት በዞኑ በሚገኙ 10 ወረዳና ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ 33 የመጀመሪያ ደረጃና በ5 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መጀመሩን የዞኑ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ በዞኑ ከወላጆች፣ መምህራንና ተማሪዎች፣ በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች፣ አጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር በተካሄደ ውይይት የመማር ማስተማር ስራው መጀመሩን ገልጿል።

ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት በሁሉም ወረዳዎች ለማስጀመር ባለፉት ሁለት ሳምንታት ባካሄደዉ የንቅናቄ መድረክ 17 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ 2 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ማስተማር እንደጀመሩ ተገልጿል።

አሁን በንቅናቄ ወደ ማስተማር ስራ የገቡት በአብዛኛዉ በከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሲሆኑ በገጠር የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ወደ ማስተማር እንዲገቡ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን መምሪያው ገልጿል።

ባሳለፍነው ወር የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ኑርልኝ ብርሃኑ አስተዳዳሪ ለወራት በዘለቀው ግጭት ምክንያት በዞኑ ከ500 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን ገልጸዋል።

================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek

1 month, 1 week ago

ዜና: #ኤርትራ በእስር ላይ የነበሩ 46 የ #ትግራይ እስረኞችን ለቀቀች፤ ከፊሎች ከአንድ አመት በላይ በእስር ላይ የቆዩ ናቸው

ኤርትራ ከሁለት ወር እስከ ከአንድ አመት በላይ በእስር ላይ ያቆየቻቸውን 46 የትግራይ እስረኞችን በትላንትናው ዕለት መልቀቋ ተገለጸ። አብዛኞቹ አስረኞች የተወሰዱት ከትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን #ታህታይ_አዲያቦ ወረዳ ነው።

የታህታይ አዲያቦ ወረዳ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ መብራህቶም ገዛኢ፤ በትላንትናው እለት የተፈቱት እስረኞች ወደ ኤርትራ ተወስደው ከመታሰራቸው በፊት ታግተው እንደነበር ለአዲስ ስታንዳርድ አብራርተዋል።

በትግራይ ውስጥ በኤርትራ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች በሚገኙ ግለሰቦች ላይ የሚፈጸመው እገታ ተባብሶ መቀጠሉን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ተጨማሪ ለማንበብ፡ https://wp.me/pfjhHd-166

Addis standard

ኤርትራ በእስር ላይ የነበሩ 46 የትግራይ እስረኞችን ለቀቀች - Addis standard

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5/2016 ዓ/ም፦ ኤርትራ ከሁለት ወር እስከ ከአንድ አመት በላይ በእስር ላይ ያቆየቻቸውን 46 የትግራይ ተወላጆችን  በትላንትናው ዕለት መልቀቋ ተገለጸ።  አስረኞቹ መለቀቃቸውን ያረጋገጡልን ምንጭ እንደገለጹት፤ አብዛኞቹ አስረኞች የተወሰዱት ከትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን ታህታይ አዲያቦ ወረዳ ነው። የወረዳው የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ መብራህቶም ገዛኢ ከአዲስ ስታንዳርድ…

**ዜና:** [**#ኤርትራ**](?q=%23%E1%8A%A4%E1%88%AD%E1%89%B5%E1%88%AB) **በእስር ላይ የነበሩ 46 የ** [**#ትግራይ**](?q=%23%E1%89%B5%E1%8C%8D%E1%88%AB%E1%8B%AD) **እስረኞችን ለቀቀች፤ ከፊሎች ከአንድ አመት በላይ በእስር ላይ የቆዩ ናቸው**
1 month, 1 week ago
Addis Standard Amharic
1 month, 2 weeks ago

ዜና፡ አቶ #ክርስቲያን ተደለ እና #ዮሐንስ ቧያለዉን ጨምሮ 14 የሽብር ተከሳሽ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ

#ኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት ጠርጥሮ ካሰራቸዉና ክስ ከመሰረተባቸው 52 ተጠርጣሪዎች መካከል፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ክርስቲያን ታደለ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ዮሐንስ ቧያለዉን ጨምሮ 14 ተከሳሾች ትላንት መጋቢት 27፣ 2016 ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት የቀረቡት የእምነት ክሕደት ቃላቸዉን ለመስጠት የነበረ ቢሆንም፤ በደል ደርሶብናል በማለታቸዉ ችሎቱ ተከሳሾች ያቀረቡትን አቤቱታ ሲያደምጥ መዋሉን ዶቸ ቬለ ዘግቧል።

በዚህም መሰረት አቶ ክርስትያን ታደለም በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት፤ “ወርቅ የአንገት ሃብል፣ ሁለት የጣት ቀለበት እንደተወሰደባቸው” ትላንት በዋለው ችሎት ላይ ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል ሲሉ አቶ ጠበቃ አቶ ሰለሞን ገዛኸኝን አስረድተዋል።

በተጨማሪም የሞባየላቸውን ቁልፍ እንዲከፍቱ “በሽጉጥ እንዳስፈሯሯቸው እና ጣታቸውን እንደተመቱ” አክለው አስረደተዋል ትብሏል።

ተጨማሪ ለመመልከት ሊንኩን ይከተሉ፦ https://wp.me/pfjhHd-15r

Addis standard

ዜና፡ አቶ ክርስቲያን ተደለ እና ዮሐንስ ቧያለዉን ጨምሮ 14 የሽብር ተከሳሽ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ - Addis standard

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 28/ 2016 ዓ/ም፡\_ የኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት ካሰራቸዉና ከከሰሳቸዉ 52 ተጠርጣሪዎች መካከል፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ክርስቲያን ታደለና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ዮሐንስ ቧያለዉን ጨምሮ 14ቱ ትላንት መጋቢት 27፣ 2016 ለሁለተኛ ጊዜ በፌዳራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት የቀረቡት የእምነት ክሕደት ቃላቸዉን ለመስጠት የነበረ…

**ዜና፡ አቶ** [**#ክርስቲያን**](?q=%23%E1%8A%AD%E1%88%AD%E1%88%B5%E1%89%B2%E1%8B%AB%E1%8A%95) **ተደለ እና** [**#ዮሐንስ**](?q=%23%E1%8B%AE%E1%88%90%E1%8A%95%E1%88%B5) **ቧያለዉን ጨምሮ 14 የሽብር ተከሳሽ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ**
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago