Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 5 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 15 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 week, 5 days ago
" እንኳን ለጾመ ነቢያት በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ"
ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው ነብያት የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ የፆሙት ታላቅ ፆም ነው።
ዛሬም እኛ ክርስቲያኖች የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በፆምና በፀሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የምናስብበት ነው።
ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል፤ በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡፡ እነርሱም፤
፩. ጾመ አዳም:- አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገት ከተባረረ በኋላ; በፈጸመው በደል አዝኖ ፥ ተክዞ፤ አለቀሰ (እንባ ቢያልቅበት እዥ እስከሚያፈስ፤ እዥ ቢያልቅበት ደም በዓይኑ እስከሚፈስና ዓይኑ ይቡስ ወይም ደረቅ እስከሚሆን ድረስ አለቀሰ) ፥ ጾመ፣ ጸለየ፡፡ ከልብ የሆነ ጸጸቱን፣ ዕንባውን፣ በራሱ መፍረዱንም እግዚአብሔር አይቶ ተስፋ ድኅነት ሰጠው፡፡ ‹‹ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ፣ በደጅህ ድኼ፣ በዕፀ መስቀል ተሰቅዬ፣ ሞቼ አድንሃለሁ፡፡›› የሚል ነው፡፡ /ገላ. ፬፥፬፣ መጽ.ቀሌምንጦስ/ ስለዚህ ጾሙ የተሰጠው ተስፋ ፥ የተቆጠረው ሱባኤ ስለተፈጸመበት ‹‹ጾመ አዳም›› ይባላል፡፡
፪. ጾመ ነቢያት:- ነቢያትም የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር ተገለጦ ስለታያቸው፣ ክርስቶስ ለሰው ልጅ የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ በትንቢት ተመልክተው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡፡ ይህ ጾም ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች: ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው:: በተለይ አባታችን አዳም: ቅዱስ ሙሴ: ቅዱስ ኤልያስ፣ ቅዱስ ዳንኤል ና ቅዱስ ዳዊት በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው:: (ዘዳ 9:19, ነገ. 19:8, ዳን. 9:3፣ መዝ. 68:10, 108:24) ቅዱሳን ነቢያት በጭንቅ በመከራ ሆነው የጾሙት ጾም ወደ መንበረ ጸባኦት ደርሶ: ወልድን ከዙፋኑ ስቦታል:: ለሞትም አብቅቶታል::
፫. ጾመ ሐዋርያት:- ሐዋርያት ‹‹ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብራለን፣ ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብረዋለን?›› ብለው ከልደተ ክርስቶስ በፊት ያሉትን ፵፫ ዕለታት ጾመዋልና፡፡
፬. ጾመ ማርያም:- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ቅድስናዋን አይቶ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ አምላክን ያለ ሰስሎተ ድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ ጸንሳ እንደምትወልደው ቢነግራትም የትሕትና እናት ናትና ‹‹ምን ሠርቼ የሰማይና ምድርን ፈጣሪ እችለዋለሁ?›› ብላ ጌታን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማለችና ‹‹ጾመ ማርያም›› ይባላል፡፡
፭. ጾመ ፊልጶስ:- ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ እያስተማረ ሳለ በሰማዕትነት ሲሞት፤ አስክሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ፤ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስክሬን እንዲገለጽላቸው ከኅዳር ፲፮ ጀምረው ጾመው በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስክሬን ተመልሶላቸዋል፤ ነገር ግን አስከሬኑ ቢመለስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል፡፡
፮. ጾመ ስብከት:- የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት፥ የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት፥ የምስራች የተነገረበት ስለሆነ ጾመ ስብከትም ይባላል፡፡
፯. ጾመ ልደት:- የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት ስለሆነ ‹‹ጾመ ልደት›› ይባላል፡፡
ጾምን ትእዛዝ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን የፍቅርና የበረከት ምንጭ በመሆኑ ጭምር ደስ እያለን ብንጾመው የቅዱሳኑ በረከት ያድርብናል፡፡
( ፆመ ነብያት ወይም የገና ፆም ማክሰኞ ህዳር 15 ይጀምራል. ታህሳስ 29 በዕለተ ሐሙስ ይፈታል። ይህ ማለት የዘንድሮ የገና ፆም ቅበላ እስከ ሰኞ ነው ከማክሰኞ ጀምሮ የፍስክ ምግቦች አይበሉም። )
https://t.me/gitim_menfesawi
አንድ ሰው መፍትሔ የሌለው የሚመስል መከራ ሊገጥመው ይችላል። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ መከራው የገጠመው ጥቂት ኃጢአቶችን ስለ ፈጸመ መሆኑን ከማስጠንቀቂያ ጋር ይነግረዋል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ቃሉ ንስሓ ከገባህ መከራው ፍጻሜ ያገኛል እያለ ውስጡን ሲመክረው ይሰማል። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ስለ ንስሓው ሲል ለሰውየው ይራራለታል።
የእግዚአብሔር ድምፅ አንድ ሰው ሲታመም ወይም እርሱ የሚወደው ሌላ ሰው ሲታመም ሊመጣ ይችላል። በዚህ ጊዜ እንዲጸልይ ወይም ስእለት እንዲሳል የሚመክረውን ድምፅ ከውስጡ ይሰማል ይህ ድምፅ የእግዚአብሔር ድምፅ ነው።
የዮሴፍ ወድሞች እህል ሊገዙ ወደ ግብጽ ከወረዱ በኋላ በዚያ ችግር ሲገጥማቸው እርስ በእርሳቸው እንዲህ በማለት ተነጋግረው ነበር፦ "በእውነት ወድማችንን በድለናል እኛን በማማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውና ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን።"/ዘፍ 42፥21/ ከዚህ በኋላ ለዮሴፍ እንዲህ ብለውታል፦ "ለጌታዬ ምን እንመልሳለን? ምንስ እንናገራለን? ወይስ በምን እንነጻለን? እግዚአብሔር የባሪያዎችህን ኃጢአት ገለጠ"/ዘፍ 44፥16/ ኃጢአታቸውን እንዲያስታውሱ ኋላም እንዲገሰጹ ያደረጋቸው የእግዚአብሔር ድምፅ ነው።
ነቢዩ ዳዊት የጌራ ልጅ በሆነው በሳሚ ሲሰደብ የእግዚአብሔር ድምፅ ውስጡ ስላለፈ ኃጢአቱ እየወቀሰው መሆኑን አዳምጧል። ስለሆነም በዙሪያው ለነበሩ ሰዎች "እግዚአብሔር ዳዊትን ስደበው ብሎታልና ይርገመኝ።" /2ኛ ሳሙ.16፥10/ በማለት በግልጽ ተናግሯል።
ረሀብና የመሬት መንቀጥቀጥ በዓለም ሲደርስ የእግዚአብሔር ድምፅ በመላው ዓለም ውስጥ ይሰማል። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ የሚናገረን "ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ።" /ሚል 3፥7/ እያለ ነው። ይህ ድምፅ በረሀቡ ወይም በመሬት መንቀጥቀጡ ጉዳት ለደረሰባቸው ሀገሮች የሚሆን የእርዳታ ጥሪ ለማሰማት ወይም ሌሎቹ ከእነርሱ ትምህርት በመውሰድ ንስሓ እንዲገቡ ለማድረግ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኝት ዝግጅት እንዲያደርጉ ነው።
ስለዚህ ማንኛውም ዓይነት መከራ ውስጥ ስትገቡ ከውስጣችሁ ያለውን የእግዚአብሔር ድምፅ አድምጡት እርሱ ለእናንተ ሊነግራችሁ የሚወደው ምን እንደ ሆነ ታውቃላችሁና።
ደብረዘይት በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የተወደደ አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ደብረዘይት በተናገረበት ድርሳን እንዲህ አለ፦
"የክርስቶስ ተቃዋሚ እንዴት እንደሚመጣ ከነገራቸው በኋላ እርሱ (ጌታ) ራሱም እንዴት እንደሚመጣ እንዲህ ሲል ነገራቸው፡- “መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይኾናልና፡፡”
መብረቅ አለ! ስለ መብረቅ ብልጭታ ማንም እንዲመሰክር አይፈለግም፡፡ በእልፍኝ ለተቀመጡም፣ በቤት ውስጥ ላሉም፣ በአጠቃላይ በዓለም ኹሉ ላሉት በቅጽበት ይታያልና፡፡ ክርስቶስ ክብሩን እየገለጠ እንዲህ ድንገት ይመጣል፡፡ ሌላ ምልክትም አለው፡፡ በድን ወዳለበት በዚያ አሞራዎች እንዲሰበሰቡ ክርስቶስ ሲመጣም አእላፍ መላእክት፣ ቅዱሳን ሰማዕታት፣ ቅዱሳን ሐዋርያት፣ ቅዱሳን ነቢያት፣ ጻድቃን ኹሉም ይሰበሰባሉ።
ከዚያ በኋላ በጣም አስፈሪ ድንቅ ይፈጸማል፡፡ በክርስቶስ ተቃዋሚ፣ በሐሰተኞች ነቢያት የሚደረገው የማታለል ሥራ ካለቀ በኋላ፣ ብዙዎች ሃይማኖታቸውን ከለወጡ በኋላ ወዲያው ተፈጥሮ መልኳን ትለውጣለች፤ ፀሐይ ይጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፡፡ በዚያ ቅጽበት በጨለመው ዓለም ፋንታ የክርስቶስ ብርሃነ መለኮት ይተካል፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ሌሊት የለም፡፡ ከዋክብት በተፈጠሩ ጊዜ መላእክት በታላቅ ድምጽ እግዚአብሔርን እንዳመሰገኑ (ኢዮብ.38፡7) የዚያን ጊዜም ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በጠፈር ሠልጥነው የነበሩ ፀሐይ ስትጨልም፣ ጨረቃ ብርሃኗን ስትከለክል፣ ከዋክብት ሲወድቁ አይተው የሰማያት ኃይላት (መላእክት) ይናወጣሉ፤ ይደነቃሉ።
በዚያን ጊዜም የወልደ እጓለ እመ ሕያው ክርስቶስ ምልክቱ፣ አሠረ ቅንዋቱ በሰማይ ይታያል፡፡ በሌላ አገላለጽ መስቀሉ ከፀሐይ ብርሃን ይልቅ ደምቆ ይታያል፡፡ ዳግመኛ ላትታይ ፀሐይ ጨልማለችና ብርሃነ መስቀሉ ይንቦገቦጋል፡፡ ከእናንተ መካከል “ስለ ምን መስቀሉ በዚያ ሰዓት ይታያል?” ቢል ጌታ የሰቀሉትን አይሁድ ይወቅስ ዘንድ ነው ብለን እንመልስለታለን፡፡
ከዚህ በኋላ ንጉሡ በፍርድ ወንበሩ ይቀመጣል፡፡ የቆሰለውን ቁስል ብቻ ሳይኾን የሞት ተግሣጽንም እያሳየ መጥቶ ይቀመጣል፡፡ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች የሚያምኑበት ሰዓት አይደለምና በወልደ እግዚአብሔር ባለማመናቸው ኹሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፡፡ ሊያከብሩትና ሊታመኑት ሲገባ ሲሳለቁበት ኑረዋልና ላይጠቅማቸው ዋይ ዋይ ብለው ያዝናሉ፡፡ የምድር ወገኖች የራሳቸውን ኃጢአት እያነበቡ ዋይ ዋይ እያሉ ያለቅሳሉ፡፡ በመዋእለ ሥጋዌው ወደ ኢየሩሳሌም በአህያ ላይ ተጭኖ ሲገባ በጌታ ስም የሚመጣ ብሩክ ነው እንዳላሉ አሁን ግን ዋይ ዋይ ይላሉ፡፡
የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤ መላእክቱንም ከታላቅ የአዋጅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፡፡ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ሙታን ይሰበስባሉ።
"ወዮ! በዚያች አስፈሪ ቀን ለእኔ ወዮታ አለብኝ! የመለከቱን ድምጽ ስሰማ መደሰት ሲገባኝ ስቃይ ይሰማኛልና ወዮታ አለብኝ፡፡ ስለዚያች ቀን ሳስብ ውስጤ በረዓድ ይመላል፤ አምርሬ አለቅሳለሁ፤ በውስጤም እቃትታለሁ፡፡ 'ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን' ከሚላቸው ከጻድቃን ጋር የሚያስደምር መልካም ሥራ የለኝምና፤ እንደ አምስቱ ሰፎች ቆነጃጅት፣ መክሊቱን እንደቀበረ ታካች ባርያም ኾኛለሁና አለቅሳለሁ፤ ፊቴ በእንባ ይታጠባል፡፡ የማጣውን ክብር፣ የሚቀርብኝን የድል አክሊል፣ ለጊዜው ሳይኾን ለዘለዓለም እንደማጣው ሳስብ አነባለሁ፡፡
ልጆቼ! ይህን የሚሰማን እኔ ብቻ እኾን ወይስ እናንተም ይሰማችኋል? ከማን ወገን ናችሁ? ደስ ከሚላቸው ወይስ ላይጠቅማቸው ዋይ ዋይ ከሚሉቱ ወገን?"
(በገብረ እግዚአብሔር ኪደ)
@gitim_menfesawi
የሚፈውስ እንባ
/በቅዱስ ኤፍሬም /
ሰውን የምታድን ክርስቶስ ሆይ! ከአንተ በቀር ማን ያድነኛል? የድኅነት ምንጭ ከኾንከው ከአንተ በቀር የታመመችውን ነፍሴን ማን ይፈውሳታል? አቤቱ ሆይ! እንኪያስ የታመመችውን ችግረኛ ሴት እንደፈወስካት እኔንም ከጥፋት ከምረረ ገሃነም አድነኝ፡፡ ምሕረት ቸርነትኅ በእኔ ላይ ትኹን፡፡ ጠላቴን ድል አደርገው ዘንድ እርዳኝ፡፡ ብርቱ በምትኾን ክንድህ ደካማ የምኾን እኔን አበርታኝ፡፡ አበርታኝና ለተጋድሎ የተዘጋጀኹ እንደኾንኩ ዐይቶ ጠላቴ ይራድ፤ ይንቀጥቀጥ፤ ይፈርም፡፡ አበርታኝና ጠላቴ የተዋረደ ይኹን፡፡ አበርታኝና ጠላቴ (ዲያብሎስ) በሐፍረት ከፊቴ ይመለስ፡፡ አበርታኝና እኔም ስምኽን ከፍ ከፍ ላድርገው፡፡
አቤቱ ሆይ! ጐስቋላ የምኾን እንባዬን ተቀበልልኝ፤ ዕዳዬንም ፋቅልኝ፡፡ ፍቅርኅ የእኔን የበደለኛውን የክፉ ምግባሬ ፍሬ ይደምስስልኝ፤ ምረረ ገሃነምም አያግኘኝ፡፡ ቸርና ሰው ወዳጅ ሆይ! ዕዳዬን ደምስስልኝና ጠላቴ ይፈር፡፡ ፈተናውን ድል አደርግ ዘንድ፥ ድል አድርጌም ዘወትር ከአንተ ጋር እኖር ዘንድ ምሕረት ቸርነትህ ከእኔ ጋር ትኹን፡፡
አቤቱ ሆይ! አልቅሳ ሰምታኻታልና፥ በሚፈውስ እንባ አጥበኻታልና፥ ፍጥረትን ኹሉ ለፈጠርከው ለአንተም ቤተ መቅደስህ አድርገኻታልና በደለኛ የምትኾን ሰውነቴ፥ ከባሕርይ አባትህ ከአብ ከባሕርይ ሕይወትህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ታከብርኻለች፡፡ አሜን!!!
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 5 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 15 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 week, 5 days ago