Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

Inspire Ethiopia

Description
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ Youtube.com/inspireethiopia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago

1 month ago

እስኪ አንድ ደስ የሚል ሀሳብ ላጫውታችሁ። አንድ ፋብሪካ ምርት ሲያመርት ምን እንዲሆን ነው? ብስኩትም ያምርት ዳቦ፣ ሞባይልም ያምርት መኪና አንድና ከዚያ በላይ ጥቅም እንዲሰጡ ታስቦ ነው።

እርግጠኛ መሆን የምንችለው የትኛውም ፋብሪካ እንዲሁ ምንም ጥቅም የማይሰጥ ምርት አያመርትም። ታዲያ የሰው ልጅ የፈጠረው ምርት ሁሉ ቢያንስ ለአንድ ምክንያት ከሆነ፤ ፈጣሪ እኛን ዝምብሎ ያለምክንያት አይፈጥረንም ማለት ነው።

እኔ አልረባም፣ አልጠቅምም የትም አልደርስም ልትል ትችላለህ ግን ፈጣሪ ከንቱ የሚሆን ምርት የለውም! ትንሽ ተረጋግተህ ማሰብ ነው የሚጠበቅብህ ያንተ መኖር በጣም የሚያስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች አሉ።
ታስፈልጋለህ ወዳጄ! ታስፈልጊያለሽ እህቴ!

ድንቅ ሰኞ ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

2 years, 10 months ago

አይምሮህ

ከምትፈልገው ነገር ሊያስቆምህ የሚችለው አይምሮህ ብቻ ነው! ሌሎቹን ፈተናዎች ረስቼ አይደለም ግን ካንተ አይበልጡም ብዬ ነው።

ሰዎች እና ሁኔታዎች መጀመሪያ ባንተ ተቃራኒ ቢቆሙም ሲሳካልህ ሲያዩ ግን ከጎንህ ይቆማሉ፤ አይምሮህ ግን ከመጀመሪያውም ካንተ ጎን መቆም አለበት!

ደማቅ ሰኞ ተመኘንላችሁ
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

2 years, 10 months ago

መነሻህን እወቅ

የስኬት የመጀመርያው መንገድ መነሻህን ማወቅ ነው ልክ መነሻህን ያወቅ ሰዓት ምን ማድረግ እንዳለብህ እየተገለጠልህ ይመጣል ። አሁን ምን ደረጃ ላይ ነው ያለኸው ?

በስራህ ፣ በእውቀት ፣ በአስተሳሰብ ፣ በገንዘብ ፣ በፍቅር ምን አይነት ደረጃ ላይ ነው ያለኸው ? ቁጭ ብለህ አስብ እና የስኬት የመጀመርያውን መንገድ ጀምር

ሰናይ ቀን ተመኘን 🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

2 years, 10 months ago

መንጋቱ አይቀርም!

ጓደኞችህ ሲሳካላቸው ስታይ እኔስ ግን መቼ ነው የምቀየረው ብለህ አትዘን፤ ፀሀይና ጨረቃ እኩል አይወጡም ልፋትህ እንደ ፀሀይ የሚያበራ ከሆነ ጨረቃዋ እስክትገባ ታገስ! ጥረትህን ካላቆምክ መንጋቱ አይቀርም!

ልዩ ሰንበት (እሁድ) ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

2 years, 10 months ago
አብዛኞቻችን "ምንድነው የጎደለህ?" ብንባል የብዙዎቻችን መልስ …

አብዛኞቻችን "ምንድነው የጎደለህ?" ብንባል የብዙዎቻችን መልስ "በራስ መተማመን" የሚል ነው። ቤተሰቦች ይህ ቪዲዮ ግን የልበሙሉነትን ጥግ ያሳየናል፤ የህይወታችንን ወሳኙን ጥያቄ አብረን እንመልሳለን💪

ነገ ሰኞ ጠዋት 2 ሰዓት በዩቲዩብ ቻናላችን እንገናኝ✌️****

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

2 years, 10 months ago

*🧤ህይወት እየቀለለ እንዲሄድ አትመኝ! እንደውም አንተ እየጠነከርክ መሄድ ነው ያለብህ። አየህ ትልቅ ነገር የሚፈልግ ሰው ትልቅ ዋጋ ይከፍላል! አይምሮህን ለትናንሽ ድሎች ሳይሆን ለታላቅነት* አዘጋጀው።

ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

2 years, 10 months ago

ራስን መቀየር!

የማትቆጣጠራቸው ነገሮች ላይ ጊዜህን ልታጥፋ ስትል ንፋስ ልትጨብጥ እየሞከርክ እንደሆነ አስብ፤ የሰዎችን ፀባይ፣ የሀገርህን ሁኔታ፣ የኑሮ ውድነቱን፣ የአለቃህን ወይ የአሰሪዎችህን ፀባይ መቀየር አትችልም!

ግን እንደምትችለው እርግጠኛ የምትሆንበት አንድ ነገር አለ...ራስህን መቀየር ግን ትችላለህ! እመነኝ ወዳጄ አንተ ከተቀየርክ ነገሮች ሁሉ ይቀየራሉ፤ ካንተ የሚጠበቀው ለራሴ ያለሁት ራሴ ነኝ ብሎ ማመን እና የተግባር ሰው መሆን ነው።

አስገራሚ ቅዳሜ ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

2 years, 10 months ago

የፈጣሪ ውድ ስጦታዎች!

2 years, 10 months ago

ሁሉም ጥሩ ይሆናል!

ሰዎች ሁሉ ላንተ ፍቅር ይሆናሉ፤ ስራው ትምሀርቱ ምርጥ ይሆናል፤ ሳሩ ቅጠሉ ፀሀዩ ነፋሱ ላንተ ያደሉ እስኪመስልህ ድረስ ያስገርሙሀል ይሄ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ግን አንድ ነገር አትርሳ👇

"የፈጣሪ ድንቅ ስራ መሆንህንና ወደዚህ ምድር ያመጣህ አምላክ ካንተ በላይ እንደሚወድህ እና የሚያስፈልግህን እንደሚሰጥህ" ከዛ ሁሉም ጥሩ ይሆናል!!

የሚያስደምም ጁምአ(አርብ) ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!

2 years, 10 months ago
***🧤*** ቤተሰቦች ከዚህ ቪዲዮ በኋላ ፍርሃት …

🧤 ቤተሰቦች ከዚህ ቪዲዮ በኋላ ፍርሃት የሚባል ነገር ከምንፈልገው ነገር አያስቀረንም!

ቪዲዮው በ Inspire Ethiopia ዩቲዩብ ቻናል ነገ አርብ ጠዋት 2 ሰዓት ይለቀቃል።

የተባረከ ምሽት ተመኘን🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ😊

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago