Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад
✝እንኳን አደረሰን!
✝ማኅበረ በኩር ወአቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ!
☞ዛሬ (ነሐሴ ፲) ጻድቁ ጎንደርን ከአራዊት ለመጠበቅ ቃል ኪዳን ከመድኃኒታችን የተቀበሉበት ቀን ነው!
#ጎንደሬ(?) ቢዘነጋውም እኛ በደብራችን እናከብራቸዋለን።
✝ማኅበረ በኩር ወሰማዕት ተአይነ ማርያም ወወልዳ፤
ወዓቢየ እግዚእ ጻድቅ ገባሬ መንክራት በበዳ፤
ዘከፈሎ ለተከዚ ወለአድያመ ጎንደር ዘዖዳ፤
ቢካቦስ ወዮሐንስ ወመጥራ ዕንቆ ባሕርይ ጸአዳ፤
ወሐርስጥፎሮስ ዘጾረ ለሕማም ክበዳ!
(አርኬ - ዝክረ ቅዱሳን ርቱዓነ ሃይማኖት)
ከአባታችን በረከት አይለየን !
ጩጌ ማርያም
አጽማቸው የማይፈርስ ፍየሎች የሚገኙባት ገዳም።
ጩጌ ማርያም ከጎንደር ከተማ በስተሰሜን በኩል 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ተጉዘን በወገራ ወረዳ አካባቢ የኮሶየ አምባ ራስ ቀበሌን አልፈን ወደ ገዳማቱ ለማምራት የዘጎል አምባን፡የጅብ ዋሻን ጥቅጥቅ ያሉ ደኖችን አልፈን ወደ ምስራቅ ስንታጠፍ በተፈጥሮ ክብ ቅርፅ ያለውን ቤተ ክርስቲያን መስሎ የሚታየውን ተራራ እናገኛለን።
በዚህ ተራራ ላይ አባ ምዕመን ድንግል የገዳም ህይወታቸውን እንዳሳለፉ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ።
በተራራው ማየ ዮርዳኖስ ፀበልና ዋሻ ቅዱስ ሩፋኤል ክርስቲያን እናገኛለን ቤተ ክርስቲያኑ ቅድስትና መቅደስ ያለው ሲሆን በቅድስቱ ማየ ዮርዳኖስን ያለ ሲሆን ይህን በመጠጣታቸው ስጋቸው ያልፈረሰ የፍየል አፅሞች ይገኛሉ። በዚህም በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ጳጉሜ 3 ይቀደሳል።
የጩጌ ማርያም ገዳም በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተመሰረተ ጥንታዊ ገዳም ሲሆን የመሰረቱትም አባ ምእመነ ድንግል የተባሉ ጻድቅ ናቸው፡፡ ገዳሙም ጻድቁ የጸለዩበት እና ከጌታችን ከመድኀኒታች ከኢየሱስ ክርስቶስ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ቅዱስ ቦታ ሲሆን የጻድቁ በዓት መጸለያ ዋሻም በስማቸው “ምእመነ ድንግል” እንደተባለ አለ፡፡
ጻድቁም በሕይወት እንደነ ሄኖክ፣ ኤልያስ፣ ቅዱስ ያሬድ እና አባ ዮሃኒ በህቡእ አሉ ተብሎ ይታሰባል ፡፡የጻድቁ መጸለያ ቦታ በተፈጥሮው የተሸነቆረ መስኮት አለው፡፡ በዚህ ቦታ ላይ መኻን የሆኑ ሁሉ በመስኮቱ ወጥተው ሲመለሱ ማየ ዮርዳኖሱን ጠጥተው ሲሳሉ ልጅ ለማግኘት ይበቃሉ፡፡ ይህን ቃል ኪዳን የሚያውቁ ጳጉሜን በሙሉ በማየ ዮርዳኖሱ በመጠመቅ ትልቅ ሐብተ ፈውስ ያገኛሉ፡፡
የዮርዳኖሱን ጸበል የጠጣ ሲሞት ሥጋው አይፈርስም፣ አይበሰብስም፡፡ እንኳን በአርአያ ሥላሴ የተፈጠረው ሰው እንስሳቱ እንኳን አካላቸው ሳይፈርስ ይቆያል፡፡ ለማስረጃ ያህል እንኳን 16 የሚሆኑ ፍየሎች አካላቸው ሳይፈርስ 400 ዘመን ያስቆጠሩ አሉ፡፡
ገዳሙ የወንዶችና የሴቶች ተብሎ በሁለት የተከፈለ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኑ በወንዶች ገዳም በኩል ሲገኝ ወደ ሴቶቹ ገዳም ስናመራ ደግሞ አንድ ትልቅ የችብሀ ዛፍ ወድቆ እንደተነሳ ይኸውም ከሰው ልጅ ሞቶ መነሳት ጋር የተያያዘ እግዚአብሔር ተአምራትን አሳይቶበታል። ዛፉ ከ15ዓመት በሗላም እንደገና እንደወደቀና በስሩ የፈለቀው ፀበልም ህመምተኞችን እየፈወሰ እንደሚገኝ አባቶች ያስረዳሉ።
የገዳሙን ተራራ የወጣ ሰው እስከ 3000 እንደሰገደ ይቆጠርለታል የሚል ቃልኪዳን አላቸው።
✥#ከጩጌ_ማርያም ገዳም ረድኤት በረከት ያሳትፈን። ደጇን ተሳልመን በረከት እንድናገኝ የአምላካችን ቅዱስ ፍቃድ ይሁንልን።
ዓመታዊ ክብረ በዓሏም በነገው እለት ሰኔ 21 በደማቅ ይከበራል።
❤አንብቡት_ይጠቅማቹሃን‼
#ልጹም ትላለህ ፤ ተው አትጹም ይልሃል!አንተም ትተወዋለህ።
#ልመጽውት ትላለህ ፤ ተው አትመጽውት ይልሃል። አንተም ትተወዋለህ።
#ንስሐ ልግባ ትላለህ ፤ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ያለንስሐ ትሞታለህ።
#ልቁረብ ትላለህ ፤ ገና ነህ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ሳትቆርብ ትሞታለህ
#ላስቀድስ ትላለህ ፤ ተው ትንሽ ተኛ ይልሃል። አንተም ሳትሄድ ታረፍዳለህ።
#ጸበል ልግባ ትላለህ ፤ ጤነኛ ነህ ይልሃል። ገዳም ልባረክ ልሂድ ትላለህ ፤ ተው ስራን
ስራ ይልሃል፡፡ አንተም ሳትሄድ ስትቆጭ ትኖራለህ።
#አስራት በኩራት ልስጥ ትላለህ ፤ ተው አትስጥ የለህም ይልሃል። አንተም
ትተወዋለህ።
#በአንድ ልወሰን ትላለህ ፤ ተው ቆንጆዎቹ ያልፉሃል ይልሃል። አንተም በዝሙት
ትወድቃለህ። የሞዐ Aklilu
#በመጨረሻም_የተወሰነልህ_ግዜ_ያልቃል ። ነፍስህን አጋንንት እንደ ኳስ እየተቀባበሉ
ይወስዷታል።
#ልጠጣ ስትል ፤ ጠጣ ይልሃል። ያሰክርሃል።
#ልዝፈን ስትል ፤ዝፈን ይልሃል። ያስጨፍርሃል!
#ልስረቅ ስትል ስረቅ ይልሃል። ያሰርቅሃል!
#ልጣለው ስትል ተጣላ ይልሃል። ያጣላሃል።
#ልዋሽ ስትል ዋሽ ይልሃል። ያስዋሽሃል! ስጋዊ ተድላን ይሰጥሃል። ይመችሃል፡ስጋህ ወፍሮ
፣ ቀልቶ ፣ ወዝቶ በጓደኞችህ ‹ ተመቸህ እኮ ! › ያስብልሃል። አንተም ደስ ይልሃል! በዛው
ትገፋበታለህ።
#ሃሳብህ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ቀርቶ ወደ ጅምናዝየም ቤት መሔድ
ይሆናል።
#ሃሳብህ ሁሉ የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ ይሆናል። ሃሳብህ ሁሉ ሳውና ባዝ ፣
ስቲም ቤት ፣ማሳጅ ቤት ሂደህ መታሸት እና መዝናናት ይሆናል።
#እግርህ ሁሉ ወደ ሲኒማ ቤት ፣ ወደ ናይት ክለብ ቤት ፣ ወደ ሆቴል ቤት ፣ ወደ
ግሮሰሪ ቤት ፣ ወደ ሱፐር ማርኬት ፣ ወደ ምናምን ቦታ ይሆናል።
#በእነዚህ_ሁሉ_ስጋህ_ሲመቸው
#ቁሞ መጸለይ ይደክምሃል።
#መስገድ ያቅትሃል።
#መጾም ይከብድሃል።
#ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይጨልምሃል።
#ስጋህ በአጋንንት መረብ ይጠመዳል።
#ደም ብዝት አስይዞ ሴት ያዝልሃል።
#ደም ብዛት አሲይዞሽ ወንድ ያዝልሻል።
#የነርቭ በሽታ አስይዞ መቆምና መሄድ ያስቅትሃል።
#ስኳር በሽታ አሲይዞ ከጾም ይከለክልሃል።
#ጨጓራ በሽታ አስይዞ ጾምን ይከለክልሃል።
#ምላስህ እግዚአብሔርን ማመስገንን ሳይሆን ዘወትር ስለ በሽታህ እንድትዘምር
ያደርጋታል።
በጣም ብዙዎች ሃብት ሞልቷቸው በሽተኛ ያደርጋቸዋል። ገና ከጥዋቱ እነዚህ ሰዎች
የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትለው ቢሄዶ ኖሮ ፤ እንደ አብርሃም ፣እንደ ይስሐቅ እና እንደ
ያዕቆብ በምድር ሃብታም እንደ ሆኑ ሁሉ በሰማይም እንደ ቅዱሳኑ የገነት ባለቤት በሆኑ
ነበር።
#ሰይጣን ክፉ ነው! ሃብታሙን በሽተኛ ፣ ድሃውን ደግሞ ጤነኛ አድርጎ አምላክን ወቃሽ
ያደርገዋል።እንዲህ እንዲህ እያለ የመሰናበቻ ጊዜ ይደርሳል። በኃጢአት የዳበረው ስጋችን
አፈር ነውና በቅጽበት እሬሳ ተብሎ ወደ አፈር ይገባል። ነፍስ ግን እያዘነችና እየተፀፀተች
ወደ ሲዖል ትወረወራለች።
#የምናያቸው ቆንጆ ሴቶች ፣ የምናያቸው ቆንጆ ወንዶች ፣ የምናየው የልኳንዳ ስጋ ፣
የምናየው መጠጥና ምግብ ሁሉ ያምረናል። ስጋችን ያሸንፈናል፥ ነፍሳችን ትሸነፋለች።
ለገነት ተፈጥረን ለሲዖል እንሆናለን።
ሁላችንም ወደ እግዚአብሔር ተመልሰን ንሰሀ እንግባ።።
?የቅዱሳን አምላክ ለንስሃ የተዘጋጀ ልብ ይፍጠርልን
?ለንስሃ ሞት ያብቃን አሜን?
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን ይቆየን?
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад