🧕ʜ ɪꜱʟᴀᴍɪᴄ Ⓣⓤⓑⓔ👳‍♀

Description
ኢንሻአላህ በዚቻናል

- ኢስላማዊ ታሪኮች
- የተለያዩ ፅሁፎች
- ቁርአናዊ መልዕክቶችን..

የምንለቅ ይሆናል

* Cross
* promotion
@husni50

September 19,2023
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 Jahr, 5 Monate her

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 2 Wochen, 5 Tage her

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 1 Tag, 12 Stunden her

hace 6 días, 2 horas

[ሱብሃነላህ

እጁ ከፍርስራሹ መሐል ይታያል። ከአፈሩ በላይ ትበያ ለብሷል።  በወራሪዋ ሚሳኤል ተደብድቦ የሞትን ፅዋ ከተጎነጨ ሶስት ወራት ተቆጥሯል። ጀናዛው ሲገኝ አካሉ ምንም አልሆነም ነበር። አዲስና ትኩስ ሰውነቱም አይሸት በምስጥም አልተበላ። ሊያፈጥርባት በእጁ የያዛት ቴምር ከጭብጡ ስር ችግኝ ሆና በቅላለች። 
ያ አላህ 🥹😭

@H_Islamic_tube
@H_Islamic_tube](https://t.me/H_Islamic_tube)

hace 6 días, 3 horas

ደስታህን ከሰዎች አትፈልግ... ከፈጠረህ ከ አለማቱ ጌታ ቢሆን እንጂ💚❤️‍🔥

hace 6 días, 13 horas

☆Anahira☆ ♡ @H_Islamic_tube ♡ by semira 🎀 ክፍል 3 ☆በውስጤ ያለውን ያወቀችብኝ ስለመሰለኝ ተስተካክዬ ተቀመጥኩ እሷም ቀጠለች <<……ካስታወስሽ ባለፈው የሆነ ነገር ብለሺኝ ነበር ዝምታው በጣም ያስጠላል አስታወስሽ?( አለቺኝ ፈገግ አልኩና መለስኩላት) ስለዝምታው ምን ታውቂያለሽ?>>ግራ ተጋብቼ <<ማለት?¿>>አልኳት <<ማለትማ ዝምታ ብዙ አይነት ነገር…

hace 1 semana, 5 días

Anahira የተሰኘ አዲስ ልብ እንጠልጣይ ታሪክ

ያንን ስላነበባቹት ሌላ የትም ያልተነበበ አዲስ ታሪክ በ ሰሚራ .

ዘሬ ማታ 3:00 ይጠብቁን 🙂

@H_Islamic_tube
@H_Islamic_tube

hace 1 semana, 6 días

🦋«እንደ አቅል ሐብት የለም .. እንደአላዋቂነት ድህነት የለም..  እንደ አደብ ውርስ የለም» አሉ። 

🩵💕ሰይዲና ዐሊይ ቢን አቢ ጣሊብ💕🩵

hace 1 semana, 6 días

°°°@H_Islamic_tube

Written By Semira°°°

°°°Ahil & Ferah 🍂

🌺ክፍል አንድ

Ahil ነኝ•••ከዱባይ ዋና ከተማ አቡዳቢ በስተሰሜን ወይስ በስተደቡብ በስተምሥራቅ አይ በስተምዕራብ ነው መሰለኝ አላውቅም ቻርጊያ ውስጥ ነው የምኖረው የምኖርበትን ከተማ ለመግለፅ የተወዛገብኩት በጣም በቅርቡ ከካሊፎርኒያ ስለመጣሁ ነው ለትምህርት ነበር የሄድኩት አሁን ግን የሚጠበቅብኝን ጨርሼ መጥቻለሁ

ብዙ ነገር አወራሁ አይደል አፍወን ትንሽ ስለእኔ አንዳንድ ሃሳብ ላጋራችሁ ብዬ ነው ሆስፒታል ከነበረኝ የእለቱ ቀጠሮ ተመልሼ ተኝቻለሁ ባባ እና ወንድሜ ስለእኔ በጣም ተጨንቀዋል መሞት ምንም አይደለም የትኛውም የአደም ልጅ ሊጋፈጠው ስለማይችል ግን ለእኔ ግን ከበደኝ ከደቂቃዎች በፊት <<አሂል የምርመራው ውጤት የሚያሳየው በሃያት ለመቆየት የሚቀሩህ ጊዜያት ቢበዛ ሁለት አመት ቢያንስ አመት ከስድስት ወር ነው>> ለባባ ጓደኛው ለእኔ ደግሞ የግል ዶክተሬ ነበር ያለን

ምንም አልመሰለኝም ወንድሜ እና አባቴ ግን እንዳዘኑ በሚያሳብቅ መንገድ በየተራ <<ላኢላሃ ኢለሏህ•••ላኢላሃ ኢለሏህ>> ይላሉ ባባ አይኖቹ የስስት አነቡ አኺ አቀፈኝ ያው የሃዘን ነው ለእኔ ግን ምንም አልነበረም እየቆየሁ ስመጣ ግን የሞት ምንነት ይገለጽልኝ ጀመር የእውነትም ፈራሁ ምን ይዤ ነው ጌታዬን የምገናኘው? ምን የሰራሁት ነገር አለናነው? ውስጤ ፈራ ይህን እያሰብኩ ዙሁር ሷላት አቅራቢያችን ካለው መስጂድ አዛን አለ የጌታዬን የመዳኛ ጥሪ ሰማሁት <<•••ሃያ አለል ሷላት••• •••ሃያ አለል ሷላህ•••>>

የመኝታ ክፍሌ በር በትንሹ ተንኳኳ <<አሂል•••ሃቢቢ ልጄ ወደ መስጂድ እንሂድ>> ባባ ነበር <<እሺ አባቴ መጣሁ ብዬ ከአልጋው ተነሳሁ እና ያንን ውድ አባቴን ተከተልኩት የእኔ አባት(ዘይድ) ይባላል እኛ ወንድ ልጆች ከፈጠረን አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) በታች አባቶቻችን አዛዦቻችን ናቸው ጀግናዎቻችን ናቸው ብቸኛ ምሳሌዎቻችን ናቸው

ከውዱ አባቴ ጋር ውዱእ አድርገን ወደ መስጂዱ ገባን ወደ መዳኛው ስፍራ ለስግደት ጌታችን ወደ ጠራን ቦታ ••••
የጀመዓ ሷላታችን ተጠናቆ
በዛውም ሱና ሷላታችንን ከባባ ጋር ሰግደን ወደ መኖሪያ ቤታችን ተመለስን በዚህ ሰሞን ባባ ወደ ድርጅቱ ሄዶ አያውቅም አለብህ የተባልኩትን የጭንቅላት ካንሰር ቀዶ ጥገና ሊያደርጉ የሚችሉትን ውድ ዶክተሮችን መሽቶ እስከሚነጋ በስልክም በአካል ማናገር ሆኗል ስራው ወደ ድርጅቱ የሚሄደው ወንድሜ (ጀሚል) ብቻ ነው እስከ ሆነ ጊዜ ድረስ እኔም ልረዳው እሄድ ነበር ከአንድ ታዋቂ ድርጅት ጋር ሽርክና ከጀመረ በኋላ ግን መሄድ አቆምኩ እዛ በስራ ስውል ህመሜን እንደምረሳው አስበው ቢሆንም እኔ ግን የግድ ማቆም ነበረብኝ ለመሞት ከየትኛውም ሰው በላይ ተረጋግጦ የየተነገረኝ ሰው በማይሆንና ልርቀው በምችለው ጉዳይ ወንጀለኛ መሆን አልፈለግኩም ለእነዛ ሁለት ሳምንታትስ ቢሆን አይኖቼ ያዩበት ይማሩ ይሆን? ልቤ እጅግ ፈራ በዛም ፍርሃት ውስጥ እንዲህ አለኝ <<አሂል አሁን የሸሸህበትን ምክንያት ማውጣት ሳይኖርብህ አይቀርም>> የሆነ የጥሪም ደውል መሰለኝ

ከበረንዳው ተንደርድሬ ወደ ባባ ክፍል አመራሁ °°°እንደተለመደው ከአንድ ዶ/ር ጋር በስልክ እያወራ ነበር

ከ 70 like በኅላ ይቀጥላል •••

Share and like
@H_Islamic_tube
@H_Islamic_tube

hace 2 semanas, 4 días

👩‍🍼እናት 10 ልጅቿን በደንብብ
መንከባከብ ስትችል🪷
10ሩ ልጆች ግን...
አንዲት እናታችንን🤰
መንከባከብ ያቅተናል😭😔

hace 2 semanas, 5 días

ሐሊመቱ አሰዕዲየህ ስለ ነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) የልጅነት ዘመን ስትናገር «ጽልመት በወረሰው ሌሊት ብርሃን የሚሆነን የነብዩ ሙሐመድ (ﷺ) ብሩህ ፊት እንጂ መብራት አልነበረም» ትላለች።
                             ﷽
اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ

hace 2 semanas, 5 días

"የኔ ውድ በቃ ለኔም ልክ ነሽ አትሸሺኝ በቃ አታርቂኝ ልክ ነሽ እሺ"አለች ፌሩዝ እንባዋን እያንጠባጠበች ሂባ አንገቷን ወደጎን ዘንበል አርጋ አቀርቅራ ምርር ብላ አለቀሰች በጣም ከፋት።የምትቆጭበት ሌላ ነገር ያለ ይመስላል
"እማ አየሽኝ እኔኮ አሁን ታምሚያለሁ ሞት በሩን ከፍቶ እየጠበቀኝ ነው....አጬስ ነበር ይሀው ረይሁ ትንገርሽ እንደ ዱርዬ ሱስ ስጋት አድር ነበርኮ"የአለቃ ፊት በንዴት ቱግ አለ።
"ልክ ነሽ እኔም በቦታው ብሆን ያን ነበር ማረገው"ፌሩዝ ሂባን በፍቅር እያየች።ውስጧ ያለውን የሀዘን ስሜት ደብቃ ፈገግ ለማለት ትጥራለች
"ዝም በይ!!"አለቃ ፌሩዝ ላይ ጮኸባት"በቃሽ እሺ ከዚ በላይ ለሷ አንድ ዘለላ እንባ እንዳታፈሺ!!"ቀወጠው ወደ ሂባ ዞሮ ሊመታት ተንደረደረ ሂባም በፍጥነት ከሱ ሸሸች
"አባዬ አትጠጋኝ!!"ጉርምስና የመሰለ ቁጣ ሆኖ ለሁሉም ቢሰማም ለኔና ለአለቃ ግን የተማፅኖ ድምፀት
እንደሆነ ቶሎ ነበር የተረዳነው
"ሂባ ቆይ ለምን???"አላት እንባውን አፍስሶ
በዝምታ እንባዋን እያፈሰሰች አቀረቀረች
"እኛ ላንቺ ስንል አልነበር ስንቱን የተውነው..."መናገር አቃተው ሲቃ ጉሮሮውን ደፈነው።ምንም ሳይናገር ወጣ ፌሩዝም በዝምታ ቆመች።ፋሪስ አቀርቅሮ ከኔ ጎን ቆሟል።ፌሩዝን አረጋግተን ይዘናት ከወጣን ቡኋላ እኔና ፋሪስ እሷው ጋር ቆየን።ነስሯ የተንጠባጠበበትን ቦታ ፅድትድት አርጋ ራሷም ሻወር ወስዳ ከኛ ቅርብ ርቀት ተቀመጠች ያን ዕለት የባጥ የቆጡን ስንዘለባብድባት መሸ
.
.
.
ሂባ ሻል ታመም ማለቷን ቀጥላለች።እኔም ቢሆን እሷን ሁሌ ለማጠንከር ጎኗ ነኝ።ዛሬ የመርዋ የሰርግ ፕሮግራም ስላለ ወደዛ አምርተናል።ሚዜዎቿ ከሲትር ውጪ ሁለቱም ቀበጥ ነገር ናቸው።አይናቸው ላይ የቀጠሏት ሽፋሽፍት ርዝመት ታስደነግጣለች
<<አይኗ ላይ ረዥም ሽፋሽፍት ቀጥላ ስታያት
.
.
.
#ኳስ ተጫዋች ብትሆኚ ኖሮ እግርሽ ሳይሆን የአይን ቆቦችሽ ነበር ቀድመው ኦፍሳይት ሚገቡት>>የተባለው ለነሱ ይመስላል።የነገራቶች መገጣጠም በጣም አስደነገጠኝ።የሁዜ ወንድም ያኔ ሲያላግጥብኝ የነበረው ሴት ያተረማምሳል የተባለው በቅርቡ ደሞ አደብ ገዝቶ እኔን የመከረኝ አሚር ነበር የመርዋ ሃላል ለመሆን የተዘጋጀው።ያ ማለት ግዴታ በሰርግ ፕሮግራሙ ላይ ሁዜ አይቀርም ማለት ነው ብዬ ራሴን አሳመንኩት አካባቢውን እየዞርኩ ቃኘሁት

ሁዜን ሳገኘው ደስታ ከእግር ጥፍር እስከ አናቴ ድረስ ውርር አረገኝ።ሄጄ ብጠመጠምበት ስል ሁላ ተመኘሁ ከሩቁኑ ተያይተን ስፈግግለት እሱም በመጠኑ ደካማ ፈገግታ ችሮኝ ወደኔ መጣ
"ሀፉ"አለኝ አጠገቤ ደርሶ
"ሰላም ነህ ሁዜ"አልኩት አይን ለመስበር እየጣርኩ
"አልሃምዱሊላህ አለሁ አንቺ ደና ነሽ"
"ደና ነኝ አልሃምዱሊላህ ወንድምህን እየዳርክ ነዋ?" ሚያስደስተው መስሎኝ የተናገርኳት ነበረች እሱ ግን አቀረቀረና
"አ...አዎ ነው!ግን ያኔ እኔ ከሱ በፊት ነበር ያን ፀያፍ ህይወት የተውኩት እሱም በለውጤ ድምፁን ከፍ አርጎ እየሳቀ
'በቃ ከበረደልህማ አንዷን እንድርህና መደበኛ ኑሮህን ትጀምራለህ'ይለኝ ነበር።ግን አልሆነም በለውጡ ቀርፈፍ ብሎ የገባበት ወንድሜ ቀድሞኝ አገባ"
"እምም እና ለምን አሁን አንተ አታገባም ቆይ?"
"አ...አ..አያስፈልግም...ሚገርም ነገር ታዘብኩ ሁለት እህታታሞች የሁለት ወንድማማቾች የህይወት መንገድ ማስቀየራቸው"በመጠኑ ፈገግ ሲልልኝ
"የአላህ ውሳኔ ሆኖ ነው"እኔም ፈገግ አልኩለት።የሰርግ ስነስርአቱ ፏ ደመቅ ብሎ አለፈ።

ቀናት ሲነጉዱ እኔም ሂቡን በጣም ስቀርባት ምንም ሳልደብቅ ልክ እንደ አቡኪና እንደ መሩ ሳያት ቀረቤታችን የብረት ያህል ሲጠነክር ቀኑ እየሄደ ነው። ዛሬም እንደ አንድ ቀኑ ለሊት አሟት ደውላ በለሊቱ ክፍሏ ሄድኩ።
"ሂቡ ምን ሆንሽ በረቢ"ውሃ ቀድቼ እየሰጠኋት
"እ...ግንኮ አንቺ ትክክለኛዋ ረይሃን ነሽ"አለች ውሃውን ተቀብላኝ ጎን ካለው ኮመዲኖ እያስቀመጠችው
"ከሷም በላይ ልሆንልሽ ብችል ደስተኛ ነኝ"ጎኗ ተቀምጬ በጎን አቀፍኳት
"ልጠዪኝ ሞክሪ እሺ ረይሃን....እኔ አሁን ፊቴ ያለው እጣፋንታ ሞት ብቻ ነው ብሞት ረይሃን እኔን እንደጎዳችኝ አንቺም ትጎጃለሽ"
"ሂቡ እንደዛ አትበይ የሁላችንም አጣፋንታ ሞት ነውኮ"
"ቢሆንም የኔው ቅርብ መሆኑ ያስታውቃል"
"እኔ ይሄን ማሰብ አልፈልግም"ጥብቅ አርጌ ሳቅፋት ምን ያህል እንደምወዳት የተረዳች ይመስለኛል።እንባ ይወርዳት ጀመር።መላ ሰውነቷ ተንቀጠቀጠ
"ረይሁ አንቺኮ ለኔ አትገቢኝም በጣም ትበዢብኛልሽ እኔ በጣም መጥፎ ሰው ነኝ ስታቀርቢኝ ማሸሽ ስትሸሺኝ
በማቅረብ የማንገላታ ክፊ ነኝኮ"
"ሂባ በአላህ በቃ እንደዛ አትበዪኝ..."በስጨት ብዬ
"ረይሁ ስሚኝስ እ..."ለመናገር ምፈልገው ግን ያቃታት ነገር እንዳለ ሁሉ እየተርበተበተች
"እሺ ምን ልስማሽ ያሳመመሽን እየተሰማሽ ያለውን ነገር ንገሪኝ ውዴ አትፍሪ...."እጆቿን ይዤ በፍቅር ሳያት
"አትርቂኝም....እ....አሸሺኝማ ረይሁ"አለች
"ቃሌ ነው ሁቢ..."ለማዳመጥ ተመቻችቼ ስቀመጥ ፋሪስ ሳያንኳኳ ገባ።እሷም ለመጀመር ያሰበችውን ዋጥ
አርጋ
"ባልዬው ልውጣልህ እንዴ ሚስትህ የናፈቀችህ ትመስላለህ"ፈገግ ስትልለት ከጎኗ ተቀምጦ የቀልድ መታ እያረጋት
"ምን እያወራቹ ነበር እ ሳትዋሹ"አለ።የወሬ ፍቅሩ አስቆን
በአሳሳቃችን እስኪስቅ ድረስ ሳቅን
"በሉ ልተኛበት ውጡልኝ"አለች ስናወራ ቆይተን በመጨረሻ....ልነግረኝ ያሰበችውን ባነግረኝም ስለማይቀርላት አላስጨነቀኝም ነበር....

የተጠበቀችዋ ቀን ከች አለች።ፋሪሴ የኔ መሆኑ ሚረጋገጥበት ቀን እኔም የሱ መሆኔ ሚረጋገጥበት ቀን ሰርጉ እየተከናወነ ነው።ጨዋታው ደርቷል ሂባም ጎኔ ሆና አሪፍ ስታጫውተኝ ነበር ወደ መጨረሻው ሰዓት ፋሪሴ ይዞኝ እስኪወጣ ድረስ የነበረው ጊዜ እጅግ አሪፍ
ነበር።ግን በመሀል ሂባ
"ከሊፋ???!"ብላ በመጠኑ ስጮህ ተሰማኝ።እኔም ምን እንደተፈጠረ ለማየት ወደሷ ዞር ስል ዝልፍልፍ ብላ ራሷን ስታ ወደቀች ያኔ
"ሂቡ..."ሚል ጆሮ ሚስብ የወንድ ድምፅ ተሰማ። ከሊፋ ይሁን????

ክፍል 25 ይቀጥላል......
ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ እናመሰግናለን።

70like🥰

hace 3 semanas, 4 días

ነገ ሰኞ ነዉ የቻልን እንፁም 🤝 . . ያልቻለ 1 ሰውም ቢሆን ያስታውስ 🙌

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 Jahr, 5 Monate her

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 2 Wochen, 5 Tage her

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 1 Tag, 12 Stunden her