ASTU Muslim Students Jeme'a

Description
The aim of this Channel is to broadcast information and to assist muslim students in ASTU by sharing info about Qur'an and kitab derses,remembering others.So,please share it to muslim students
For any questions,comment use this bot
@ASTUMSJ_SUGGESTION_BOT
We recommend to visit

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads:

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ ስራ 👉 @Abusheymc

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

1 year, 7 months ago
ASTU Muslim Students Jeme'a
1 year, 7 months ago
*****📢*** ማስታወስ

*📢* ማስታወስ

🔶 ነገ ከመግሪብ ሰላት በኃላ በአላህ ፈቃድ በአዳማ ከተማ ፣ በቦሌ (ኸዲጃ) መስጂድ እና በቀጥታ ስርጭት በቴሌግራም እና በዩቱብ ትምህርት ይኖረናል።

📚 #كلمة_التوحيد_لا_إله_إلا_الله (فضائلها ومدلولها وشروطها ونواقضها)
لفضيلة الشيخ أ.د.  عبدالرزاق بن عبدالمحسن البدر

📚 #የተውሒድ_ንግግሯ_ላኢላሃኢለላህ ትሩፋቷ
በሸይኽ አብደረዛቅ ኢብኑ አብደ ሙህሲን አል- በድር 

          •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
🗓  እሮብ ሸዕባን 06/1446 ሂጅሪ, (ጥር 28,2017)
ሰዓት: 12:30 (ከመግሪብ እስከ ኢሻ) (በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር)።     
🕌 ቦታ: አዳማ ከተማ፣ ቦሌ (ኸዲጃ) መስጂድ።           
            •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•

🎙 الأُسْتَاذُ أَبُو مُسْلِمٍ عُمَرُ بنُ حَسَنٍ الْعَرُوسَيّ

🎙 በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ኡመር ሐሰን  አልአሩሲ አል-አይመሮ (ሀፊዘሁላህ)

📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ
👇👇👇

🌐** https://t.me/AbumuslimAlarsi

1 year, 7 months ago
ቋንቋችን በቁርኣን አቀራራችን ላይ ተፅእኖ እንዳያሳድርብን

ቋንቋችን በቁርኣን አቀራራችን ላይ ተፅእኖ እንዳያሳድርብን
~
ቋንቋዎች በአካባቢና በዘመን መለያየት የተነሳ ልዩነቶችን ያንፀባርቃሉ። ዐረብኛን እንደ ምሳሌ ብንወስድ በተለያዩ ሃገራት የተለያዩ ዘዬዎች አሉ። አንዳንዶቹ ለኛ ቀርቶ ለዐረቦቹም የሚከብዱ ናቸው። የሆነ ቦታ አንድ ግብፃዊ ያወራኛል። እኔ ከአንዳንድ ቃላት በስተቀር የሚያወራው አልገባኝም። የሌላ ሃገር ዐረብ ቦታው ላይ ነበርና ሁኔታዬን የተረዳ መሰለኝ " የተናገረው ገብቶሃል?" አለኝ። "አልገባኝም" አልኩት። አጠቃላይ የሚናገራቸው እንደሚከብዱኝ ነገርኩት። "እኛም እነሱ ስላስተማሩን ነው ቋንቋቸውን የለመድነው" አለኝ። እንዲያውም የሚገርም ገጠመኝ ነገረኝ። ልጁን ትምህርት ቤት እንዳስገባው ጥቂት ቀን ከሄደ በኋላ "ከዚህ በኋላ እዚያ ትምህርት ቤት አልሄድም። በዐረብኛ ሳይሆን በእንግሊዝኛ ነው የሚያስተምሩት። እኔ እየገባኝ አይደለም አለኝ። ለህጃቸው (ዘያቸው) እንግዳ ስለሆነበት ነበር እንደዚያ ያለው" አለኝ።

ወደ ራሳችን ስመልሰው በየቋንቋው አካባቢን መሰረት ያደረገ ሰፊ የዘዬ ልዩነት አለ። አንዳንዴ ታዲያ ቋንቋችን ወይም ዘያችን የቁርኣን አቀራራችን ላይ ተፅእኖ ሊኖረው ይችላል። ለምሳሌ ያክል
ሀምዛ (أ) እና ዐይን (ع)፣
ሓእ (ح)፣ ኻእ (خ) እና ሃእ (هـ) ፣
* ዛል (ذ) እና ዛይ (ز)
ወዘተ በቋንቋ ተፅእኖ ምክንያት ብዙ ሰው ያለ ልዩነት አደባልቆ ያወጣቸዋል። خير ለማለት ከይር ወይም ሀይር የሚለው ብዙ ነው። {غَیۡرِ ٱلۡمَغۡضُوبِ عَلَیۡهِمۡ وَلَا ٱلضَّاۤلِّینَ} ለማለት "ገይሪል መግዱቢ አለይሂም ወለድዷልሊን" የሚለው ብዙ ነው። 0ረብኛ ደግሞ ጥልቅ የድምፅ አጠቃቀም አለው። ثم፣ سم እና صم አንድ አማርኛ ተናጋሪ በአንድ ድምፅ ሊያወጣቸው ይችላል። ሶስቱም ቃላት ግን የተለያየ ድምፅ እና የተለያየ ትርጉም ነው ያላቸው። እነዚህ ቀላል የሚመስሉ ነገሮች ቁርኣን አቀራራችን ላይ በትክክል ካልተማርን ትርጉም በሚቀይር መልኩ ግድፈት እንድንፈፅም ሊያደርጉን ይችላሉ። ሁለት አካባቢዎችን እንደምሳሌ ልጥቀስ። አዲስ አበባ እና ወሎ።

  1. አዲስ አበባ፦

በአብዛኛው የሃገራችን ህዝብ ዘንድ የዐረብኛዋ ض ድምፅ የለችም። (ሁሉም ያላልኩት ለምሳሌ ዐፋር እና ምስራቁ የወሎ ክፍል አነጋገር ላይ ይሄ ድምፅ እንዳለ ስለማውቅ ነው።)
እና ይሄ ድምፅ (ض) የሌላቸው ተናጋሪዎች { وَوَجَدَكَ ضَاۤلࣰّا فَهَدَىٰ } የሚለውን "... ዳለን ... " ብለው ቢያነቡት ትርጉም የሚቀይር ግድፈት ነው። ضر እና در የተለያየ ድምፅ ያላቸው የተለያዩ ቃላት ናቸው። ትርጉማቸውም ፍፁም የተለያየ ነው። በተመሳሳይ
ضال እና دال
ضرس እና درس
ضرب እና درب
እያልን ብንዘረዝር ብዙ ድምጻቸውም ትርጉማቸውም የሚለያዩ ቃላትን ማየት እንችላለን። ضን በትክክል የማያወጣ ሰው እነዚህን ቃላት ትርጉም በሚቀይር መልኩ ነው የሚያወጣቸው።
ይሄ ክፍተት የአዲስ አበባ ልጆች ላይ በሰፊው ይታያል። ልጆች ቁርኣን ሲቀሩ ይቸገራሉ። ከዱዓቶች ራሱ እንዲህ አይነት ግድፈቶች የሚታዩባቸው አሉ። {سَنَشُدُّ عَضُدَكَ بِأَخِیكَ} የሚለውን የቁርኣን አንቀፅ "0ዱደከ" እያሉ የሚቀሩ አሉ። {أَنقَضَ ظَهۡرَكَ} የሚለውን "አንቀደ ..." ብሎ መቅራት ስህተት ነው። አዲስ አበባን በቅርብ ስለሚገጥመኝ በምሳሌነት አነሳሁት እንጂ ችግሩ ሌሎችም ጋር ይኖራል።

  1. ወሎ፦

የወሎ አማርኛ የቃላት ሃብቱ ስፋት አለው። እጅግ በርካታ ቃላት ከዐረብኛ እና ከኦሮምኛ አስገብቷል። ከሌሎችም አጎራባች ቋንቋዎች በስሱም ቢሆን ይዋዋሳል። ቁልምጫዎቹ፣ ስሜትን (ፍቅርን፣ መቆርቆርን፣ ሃዘንን፣ ...) ገላጭ የሆኑ ለየት ያሉ ቅላፄዎቹ ለቋንቋው ተጨማሪ ውበት ናቸው።

እዚህ ላይ ማንሳት የፈለግኩት ግን ከቁርኣን ጋር በተያያያዘ የተለመደው የ "ዴ" ድምፅ ተፅእኖን ነው። የወሎው አማርኛ ዘዬ ላይ "ደ"ን "ዴ"፣ "ድ"ን ደግሞ "ዲ" አድርጎ ወይም ወደዚያ አቅርቦ ማውጣት የተለመደ ነው። ችግር የሚሆነው ይሄ የአነጋገር 'ስታይል' ወደ ቁርኣን አቀራር ሲመጣ ነው።
ከላይ ያቀረብኳትን ኣያ {وَوَجَدَكَ ضَاۤلࣰّا فَهَدَىٰ} ብንወስድ አንድ ሰው "ወወጀዴከ ... ፈሀዲያ" ብሎ ቢቀራ ልክ አይሆንም። "ወወጀደከ ... ፈሀዳ" መሆን አለበት። {عَبۡدًا إِذَا صَلَّىٰۤ} የሚለውን "ዐብዴን ኢዛ ሶልላ" ብሎ ቢቀራው ልክ አይደለም።
እንዲሁም {قُلۡ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ} የሚለውን "... አሐዲ" በሚል፣ {وَمَاۤ أَدۡرَاكَ} የሚለው "ወማ አዲራከ" በሚል መቅራት ስህተት ነው።
ተመሳሳይ ሁኔታዎች በጣም ብዙ ናቸው። ይሄ መታረም ያለበት ነው።

በሌላ በኩል አንዳንዶች ይህንን በመሸሽ ሌላ ግድፈት እያመጡ ነው። "ዴ" እና "ዲ" እኮ የራሳቸው ቦታ አላቸው። ስህተት የሚሆነው ያልቦታቸው ሲውሉ ነው። በቦታቸው አለመጠቀም ሌላ ስህተት ነው። "እንዴት ነህ?" ለማለት "እንደት ነህ?"፣ "አዲስ" ለማለት "አድስ"፣ "ወልዲያ" ለማለት "ወልድያ" ማለት ልክ አይደለም። ተመሳሳይ ቅርፅ ያላቸው ብዙ ስህተቶች አሉ። የትም ቦታ በቋሚነት "ዴ" እና "ዲ" ላለመጠቀም ይጠነቀቃሉ። ይሄ ስህተት ነው። በርእሴ እንደጠቆምኩት የኔ ትኩረት ከቁርኣን አነባበብ ጋር ያሉ ግድፈቶችን ማስታወስ ነው። ስለዚህ አንድ ሰው {وَٱلۡعَـٰدِیَـٰتِ ضَبۡحࣰا} የሚለውን "ወልዓድያቲ " ብሎ ከቀራ ስህተት ነው። ትክክለኛው "ወልዓዲያቲ " ነውና።

አዲስ አበባንና ወሎን ለማሳያ መዘዝኩ እንጂ በየቋንቋው የተለያዩ የተለመዱ ግድፈቶች አሉና ትኩረት እንስጣቸው። አላማዬ ቁርኣንን በትክክል እንድንማር እና በአቀራራችን ላይ አነጋገራችን ተፅእኖ እንዳያሳድርብን ማስታወስ ነው። ተጅዊድን በጥልቀት እንደተማረ ሰው ባንሆን እንኳ ቢያንስ ትርጉም በሚቀይር መልኩ እያዛነፍን እንዳንቀራ መጠንቀቅ ይገባል።

የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

1 year, 7 months ago

🛑ሰካራም ምሁሮች ፈገግ የምታደርግ ግጥም

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሐፊዘሁሏህ

1 year, 7 months ago

የተጠናቀቀ ደርስ 📚 #شرح_حديث_إنا_كنا_في_جاهلية   لفضيلة الشيخ د. صالح بن فوزان الفوزان حفظه الله تعالى 📚 #ሸረህ_ሀዲስ_ኢናኩና_ፊልጃሂሊያ (እኛ መሀይምነት ውስጥ ነበርን) የሚለው የሑዘይፋ ሓዲስ ማብራሪያ። የሸይኽ ሷሊህ ብን ፈውዛን አል`ፈውዛን (ሃፊዞሁሏህ) ➡️ክፍል ➞ ❶ https://t.me/AbumuslimKitaboch/2315 ➡️ክፍል…

1 year, 7 months ago

School of Mechanical, Materials and Chemical Engineering!!!!

1 year, 7 months ago

↪️ በጨለማ ወደ መስጊድ ተጓዦችን አበስራቸው

‏قال النبيﷺ :- " بشر المشائين في الظلم إلى المساجد بالنور التام يوم القيامة "

በጨለማ ወደ መስጂድ ተጓዦችን የውመ-ል-ቂያማህ በሙሉ ኑር (ብርሃን) አበስራቸው።»

صلاة الفجر يرحمكم الله |🌻🪞

Copy

@ASTU_MSJ

1 year, 7 months ago

Important Reminder: Mandatory Mark Check for Freshers!

AssalamuAlaikum,

Congratulations on completing our final exams! 🎉

This is a crucial reminder for all students, especially our freshers: checking your marks—both in person and online—is extremely mandatory. It’s important to ensure everything is accurate, and if you notice any discrepancies, please reach out to your teachers for corrections as soon as possible.

Wishing you all a blessed and enjoyable break!

@astu_msj

1 year, 7 months ago
ቁርኣን የመቅራት ፍላጎታችን ምን ያህል ነው?

ቁርኣን የመቅራት ፍላጎታችን ምን ያህል ነው?
~
አቡል ጀውዛእ አሪብዒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
نَقلُ الحِجارةِ أهْوَنُ على المُنافِق مِن قِراءَةِ القُرآن!
{ለሙና*ፊቅ ሰው ቁርኣን ከመቅራት ይልቅ ድንጋይ መፈንቀል ይቀለዋል።}

📕 [ተህዚቡ ሒልየቲል አውሊያእ፡ 1/459]

የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

We recommend to visit

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads:

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ ስራ 👉 @Abusheymc

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik