ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

Description
ፍልስፍና  እውነትን በመፈለግ- ሀሳዊ እምነቶችን በማጋለጥ እና ጭፍን አመለካከቶችን በጥበብ በመመርመር ወደ ላቀ አሰተሳሰብ ያሻግራል።

በዚህ ቻናል አለም ላይ ያሉ ፍልስፍናዎች ፤ ርዕዮት አለሞች ፤  ሀይማኖቶች እና አስተሳሰቦች በነፃነት ይዳሰሳሉ።
Advertising
We recommend to visit

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated hace 3 días, 10 horas

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated hace 3 días, 17 horas

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated hace 2 meses

1 week ago

LIMITLESS
By JIM KWIK

UPGRADE YOUR BRAIN,LEARN ANYTHING FASTER AND UNLOCK YOUR EXCEPTIONAL LIFE

@Zephilosophy
@Zephilosophy

1 week ago

ቀላሉን ነገር አታካብደው
ደራሲ:- ዶክትር ሪቻርድ ካርሰን
ትርጉም:- ዶክትር ዮናስ ላቀው

@zephilosophy
@zephilosophy

1 week, 3 days ago

ማህበራዊ ሴሰኝነት -2

‹‹ለአያሌ ዘመናት ወንድ ሴትን ሲጨቁን ስለኖረ፣ ሴቶች ነፃነትን በተጎናፀፉ ማግስት ያደረጉት ነገር ወሲብ ቀስቃሽ ልብሶችን በመልበስ ወንድን በወሲብ ስሜቱ ማሰር ነው፡፡››
ሊዮ ቶልስቶይ

ለምንድን ነው ግን የሴቶችን ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስ መቃወም ያለብን? ይሄንን ማድረግስ ግለሰባዊ ነጻነታቸውን መጋፋት አይሆንም? ለወንዶች ተብሎስ ሴቶች የፈለጉትን ልብስ የመልበስ ፍላጎት መስዋእት መሆን አለበት?

የግለሰብ ነፃነት የሚጠበቀው የብዙኃኑን ደህንነት እስከጠቀመና ማኅበራዊ እሴቶች ላይ ጉዳት እስካላደረሰ ድረስ ብቻ
ነው፡፡ ‹‹እያንዳንዱ ሰው በራሱ አካል፣ መንፈስና አእምሮ ላይ በማንም የማይደፈር ሉዓላዊ ነፃነት አለው፡፡ ሆኖም ግን ይህ ሉዓላዊ ነፃነት የማህበረሰቡን ደህንነት የሚጎዳ መሆን የለበትም፡፡››
ይላል እንግሊዛዊው ፈላስፋ ጆን ስትዋርት ሚል፡፡ የሴቶችን ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስም የምንቃወመው ግላዊ ነፃነታቸውን ለመጋፋት ብለን ሳይሆን አለባባሳቸው ማህበራዊ እሴቶችን በመገዝገዝ ማህበራዊ አለመረጋጋትን ስለሚያመጣ ነው፡፡

ማህበራዊ ሴሰኝነት የእንስሳነት ደረጃና ባህሪ ነው፡፡ እንስሳት የሚኖሩት በርሃብ፣ በውበትና በወሲብ ስሜቶቻቸው ብቻ ነው፡፡ መላው የሕይወት ሃይል በእነዚህ ሃሳቦች ላይ ብቻ የሚውል ከሆነ ደግሞ ሌሎች ሰብአዊ እሴቶች (እምነት፣ ፍቅር፣ ፍትህ፣ እኩልነት፣ ክብር፣ ነፃነት፣ ሠላም፣ ሳይንስ. . ወዘተ) ሁሉ ዋጋ ያጣሉ፡፡

በማህበራዊ ሴሰኝነት ውስጥ የሴቷ ውበት ለሁሉም ወንዶች ሲሆን፣ እያንዳንዱ ወንድም የሁሉም ሴቶች ነው፡፡ የሴቶች ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስና የወንዶች ልቅ የወሲብ ስሜት ከሰብአዊ የአኗኗር መርህ ጋር የሚጣላው ለዚህ ነው፡፡ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስን የመብት ጉዳይ አታድርጉት፡፡ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስን የመብት ጉዳይ ካደረጋችሁት የምትሟገቱትና የምትቃረኑት ከሰብአዊ ባህሪያችሁ ጋር ነው፡፡ ወሲብ ቀስቃሽ አለባባስን የመብት ጉዳይ ካደረጋችሁት እንግዲያውስ ወንዶችም በእናንተ አለባባስ ያለመተንኮስ መብት አላቸው፡፡ ውበትና ወሲብ የተሳሰረ ተፈጥሮ አላቸውና እንዲሁም የወንዱን የወሲብ ስሜት የሚቀሰቅሰው የሴቷ ውበት ነውና ወንዶችም በእናንተ አለባባስ ባለመብት ናቸው፡፡ ወሲብ ቀስቃሽ ልብሶችን ስትለብሱ በወንዶች የምታገኙት ደመነፍሳዊ እውቅና ወሲባዊነትን እንጂ እናንተ እንደምታስቡት ከፍ ያለ የውበት አድናቆትና ሰብአዊ ክብርን አይደለም፡፡

‹‹ለአያሌ ዘመናት ወንድ ሴትን ሲጨቁን ስለኖረ፣ ሴቶች ነፃነትን በተጎናፀፉ ማግስት ያደረጉት ነገር ወሲብ ቀስቃሽ ልብሶችን በመልበስ ወንድን በወሲብ ስሜቱ ማሰር ነው፡፡››ሴቶች በወንዳዊ ባህል ውስጥ ለዘመናት ተጨቁነው ነበር በሚለው አመለካከት ላይ አብዛኛው ሰው ይስማማል፡፡ ‹‹የዚህ ጭቆና ምንጭ ደግሞ ወንዱ ሴቷን ከሰውነት ይልቅ በዙሪያው ከሚገኙ ግዑዝ ነገሮች መካከል እንደ አንዱ ስለሚቆጥራት ነው።" ትላለች ፈረሳይቷ ሲሞን ደ ቦውቨር

በርግጥ ሴቶች ወሲብ ቀስቃሽ አለባበሶችን የሚለብሱት የወንዶችን ወሲባዊ ባህሪ ተከትለው እንደሆነ እርግጥ ነው፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት ሴቶች ይሄንን የሚያደርጉት የወንዱን የንቀት ስሜት ለመበቀል ብቻ ሳይሆን ሴቶች እርስበርስ ካላቸው ተፈጥሯዊ ግንኙነት በመነሳትም ነው፡፡ ሴቶችን የሚረብሻቸው እርስበርስ ያላቸው ተፈጥሯዊ ግንኙነት ነው፤ ይሄም መቀናናት ነው፡፡ ሴቶች በሴቶች ላይ የሚያሳድሩት ተጽእኖ እጅግ የበረታ ነው፤ ተፈላጊ መሆን፣ የሰውን አትኩሮት መሳብና በውበቷና በኑሮዋ ከሌሎች የአካባቢው ሴቶች የተሻለ ሆኖ መገኘት ስለሚፈልጉ ሁል ጊዜ እርስበርስ በሃይለኛ ፉክክር ውስጥ ናቸው፡፡ ይሄ ደመነፍሳዊ ፍላጎቷ ነው ውበቷን በተመለከተ ወደ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስ እንድታዘነብል የሚያደርጋት፡፡ ምክንያቱም በወሲብ ቀስቃሽ አለባበስ መላውን የአዳም ዘር ማስደንገጥ ያስችላታልና፤ ይሄ ድርጊት ደግሞ ለሌሎች ሴቶች የቅናት ደወልን ያጭርባቸዋል፡፡ እነሱም እንደ ዘመናዊቷ ሴት ሆነው ካልተገለጡ ስነልቦናዊ ጉዳቱ እረፍት ያሳጣቸዋል፡፡

በአንፃራዊነት ሴቶች በባህሪያቸው በቀላሉ ተሰባሪ ናቸው፤ ስነ ልቦናዊ ልስላሴያቸው ደግሞ ከአካላቸው(ከማህፀናቸው) ልስላሴ የመጣ ነው፡፡ የስነ ልቦናቸው ደረጃ እርስበርስ በሚያደርጉት የፉክክር ውጤት ላይ የተመሰረተነው፡፡ ወንድ በአካሉ አይፎካከርም፤ ሴቶች ግን በእያንዳንዱ የሰውነት ክፍላቸው ይፎካከራሉ፡፡ በፉክክሩ፣ እኩል ወይም የበላይ እንደሆኑ ካልተሰማቸው ስነልቦናቸው ይጎዳል፡፡

ይህ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስ የሴተኛ አዳሪዎች አለባበስ ነው፡፡ ሴተኛ አዳሪዎችስ እንዲህ የሚለብሱት የወንዶችን ስሜታዊነት ስለሚፈልጉት ነው፡፡ እናንተስ ምን ፈልጋችሁ ነው? ራሳችሁን ከሴተኛ አዳሪዎች የምትለዩበት የተለየ አለባበስ አያስፈልጋችሁም ወይ? የሴተኛ አዳሪዎችን የአለባበስ ስታይል የቀረፀው የወንዱ የወሲብ ስሜት ነው፡፡ እናንተም እንደ ሴተኛ አዳሪዎች ከለበሳችሁ በተዘዋዋሪ የእናንተም የአለባበስ ስታይል የወንዱን የወሲብ ስሜት የተከተለ ነው ማለት ነው፡፡ የአለባበሳችሁ ስታይል ምንጩ የራሳችሁ ፍላጎት ቢመስላችሁም ተሳስታችኋል፤ ስታይላችሁን እየወሰነ ያለው የወንዶች የወሲብ ስነልቦና ነው፡፡ በጣም የሚያሳስበው ነገር ደግሞ ለወንዶች የወሲብ ስነ- ልቦና የተመቹ ሴቶች በገንዘብ፣ በስራ እድል፣ በጌጣጌጥና በቁሳቁስ የተሻሉ መሆናቸውና በሌሎች ሴቶች ላይም የስነ- ልቦና የበላይነት ማግኘታቸው ነው፡፡ ወንዶች ገንዘብ፣ ንብረትና ስልጣን ስላላቸው ለወሲባዊ ፍላጎታቸው የተመቹ ይሆኑ ዘንድ ሴቶች ላይ የተለያዩ ጫናዎችን ያሳድራሉ፡፡ ለወንዶች ወሲባዊ ፍላጎት የተመቻቹ ሴቶችም በሕብረተሰቡ ውስጥ በስራ እድል፣ በአልባሳት፣ በመዋቢያ ዕቃዎች፣ በገንዘብና በቁሳቁስ የተሻሉ እየሆኑ መሄድ፣ ሌሎች ሴቶችም የወንዱን የወሲብ ስነ-ልቦና የተከተለ የአኗኗር ዘይቤ እንዲከተሉ ያስገድዳቸዋል፡፡ የወንዱ የወሲብ ባህሪ ደግሞ ወደ እንስሳነት ስለሚያዘነብል፣ ሴቶች በተለያዩ ጥቅሞችና ጫናዎች እየተገደዱ አኗኗራቸው የወንዱን የወሲብ ስነ-ልቦና መከተል ሲጀምር በሕብረተሰቡ ውስጥ ማኅበራዊ ሴሰኝነት ይስፋፋል፡፡

ምንጭ-ፍልስፍና 1
ፀሀፊ- ብሩህ አለምነህ

@zephilosophy
@zephilosophy

2 months, 3 weeks ago

የትኛው ደስታ ይቅደም?

......... ካለፈው የቀጠለ

" ........ ሀድሰን በባህር ውስጥ ሰጥሞ ህይወቱን ከማጣቱ በፊት የእርዳታ ጩኸቱን አሰማ .... ከፊት ለፊቱ ቢያንስ በመቶ ሜትር ርቀት ላይ የህይወት አድን ጀልባ ትታየዋለች:: .... ጀልባዋ ላይ ያሉትም ሰዎች በጥንቃቄ ከሱ ርቀው እየሄዱ ነበር " ...... አላስቻለውም እርዱኝ ሲል የጣር ጩኸቱን አሰማ .... "እዚህ ጋር እባካችሁ እርዱኝ" ሲል ደጋግሞ ጮኸ። ሰዎቹ ጩኸቱን መደሰሙበት አቅጣጫ መብራታቸውን አበሩ፡፡ ይሄኔ ‹‹እባካችሁ ፍጠኑ እርዱኝ›› የሚል የእርዳታ ጥያቄ አቀረበ፡፡ አሁን ሀድሰን የህይወት አድን ሰራተኞችን ምልከት በማየቱ ትንሽ ተስፋ ስላገኘ ከበፊቱ በበለጠ ትንፋሹን ሰብስቦ "እባካችሁ ፍጠኑ እርዱኝ፣ ሲል ተጣራ፤ ዓይተውታል . . . መብራታቸውንም በእርሱ አቅጣጫ ቦግ እልም አድርገው አብርተውለታል። አሁንም በድጋሚ በሱ አቅጣጫ የሚለቀቀው መብራት አይኑን አጥበረበረው፡ ፡ ድምፁን ሰምተውታል፤ ታዲያ ለምን በፍጥነት አልደረሱለትም? "ኦ አምላኬ" ሀድሰን አጉረመረመ፡፡ ጀልባዋ በመጣችበት አቅጣጫ ተመልሳ ሄደች፡፡ .... በዚህን ጊዜ ሀድሰን ከአጠገቡ በጣም እየራቁ መሆናቸውን አስተዋለ፡፡ አሁንም ተስፋ አልቆረጠም .... ተከትሏቸው ለመሄድ ሞከረ . . . አልደረሰባቸውም!፡፡ . . . ለጥቂት ደቂቃዎች በዝምታ ተውጦ መጨረሻውን መጠበቅ ጀመረ፡፡ ከጀርባው ፀሀይ የእንቁላል አስኳል መስላ የአህያ ሆድ የመሰለውን ሰማይ እየገላመጠች ብቅ ማለት ጀምራለች .... ይህች ፀሀይ የቀኑን ጅማሬ ልታበስር የሀድሰንን የሙት እንጉርጉሮ ልታደምቅ ስራዋን ጀመረች፡፡ ሀድሰን በትንሽዋ ጀልባው የያዘውን ሻንጣ፤ የተዝረከረኩ ልብሶችን፣ ጫማውን ሲመለከት ዳግም የመኖር ፍላጎቱ ጨመረ፡፡ . . . እናም ተጣራ "እርዱኝ አባካችሁ ለሞት አሳልፋችሁ አትስጡኝ" እያለ ለመነ፡፡ በነፍስ አድን ጀልባ ላይ ያሉት ሰዎች ያዩታል ነገር ግን ለሰቆቃው ምላሽ አልሰጡትም፡፡ ተስፋ የቆረጠው ሀድሰን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መራገም ፈለገ . . . እንደገና ፀለየ . . . ፀሎቱ ግን ለእግዚአብሄር ሳይሆን ለሰዎችና ለህይወት አድን ጀልባዋ ነበር . . . አለቀሰ ... እንደገና ለመነ ... ››

በፍልስፍና ታሪክ ውስጥ የዚህን ፍልስፍና እሳቤ በጣም እንዳጎሉት የሚነገርላቸው ጄርሚ ቤንትሀም (Jeremy Bentham) እና ጆን ስቱዋርት ሚል (John Stuar Mill) ሲሆኑ ቤንትሀም ደስታን በተመለከተ በጥራት ሳይሆን በብዛት ላይ እንድናተኩር ሲመክረን በአንፃሩ ሚል "ከብዛት ይልቅ ጥራት ይቀድማል" ይለናል፡፡ እስቲ ሁለቱንም በዝርዝር እንመልከት . . .

የዩቲሊቴሪያኒዝምን ሀሳብ መጀመሪያ እንዳገኘ የሚነገርለት ጄርሚ ቤንታም "መልካም ስነምግባርን ለማሳየት ስትፈልግ በቅድሚያ ለአንተ የቀረቡልህንና ልትፈፅማቸው የምትፈልጋቸውን ተግባራት አጢን፡፡ ከዚያም ድርጊቴ እኔን ጨምሮ ምን ያህል ሰዎችን ሊያካትት ይችላል ብለህ አስብ ። ቀጥሎም በዚህ ድርጊቴ ምን ያህል ደስታን አልያም ምን ያህል ሀዘንን አተርፋለሁ የሚለውን ከግምት ውስጥ አስገባ፡፡ በስተመጨረሻም ደስታህ ከህመም በልጦ ካገኘኸው ያኔ መልካም ነገርን ሰርተሀል" ሲል ንፅፅራዊ እሳቤውን ይገልፃል፡፡ ቤንታም ይህንን ሲል ደሰታን በቁጥርና በሂሳብ ስሌት ቀመር ወስኖ እንዲያልፍ እያደረገው ነው፡፡ " አብላጫው ደስታ ለአብላጫው ቁጥር" ማለቱም ይህንኑ አያረጋገጠለት ነበር፡፡ "ለምሳሌ ማንኛውም አንተን ሊያዝናናህ የሚችል ጨዋታ (game) በመጀመሪያ ከሙዚቃ ፣ ከስዕልና ከግጥም ጋር እኩል ዋጋ አለው ነገር ግን ጥቅም ላይ ስናውለው ጨዋታው የበለጠ ደስታን ከሰጠን ዋጋውም ያንኑ ያህል ይጨምራል" ይለናል፡፡ ታዲያ እዚህ ጋር አብላጫ ደስታ የሚሰጠንን ነገር እንዴት ልናውቅ እንችላለን? ብለን መጠየቃችን አይቀሬ ነው፡፡ ቤንትሀም ለዚህ ምላሽ ሲሰጥ "አንድ ነገር አብላጫ ደስታን ልናገኝበት እንችላለን የምንለው በቅድሚያ ጥንካሬውን፣ የቱን ያህል ጊዜ መቆየቱን፣ እርግጠኛነቱን፣ ቅርበቱን፤ ሌላ ደስታን መጨመር መቻሉን፣ ከህመም ነፃ ማውጣቱን፣ አና ለምን ያህል ሰዎች ሊዳረስ መቻሉን ጠይቀን ካመዛዘንን በኋላ ነው" በማለት መስፈርቱን ይናገራል፡፡ ቤንትሀም በተጨማሪም "ምን ማድረግ እንዳለብን በማወቅና ተግባራዊ በማድረግ መካከል ከፍተኛ ልዩነት መኖሩን ልብ በሉ ምክንያቱም ይህንን ማወቅህ የሌላ ደስታ ምናልባትም ለአንተ መስዋዕትነት ሊያስከፍል አልያም ህመምን ሊያስከትል ስለሚያስችል ነው፡፡ በእርግጥም አንድ ነገር በምናደርግበት ጊዜ አራት ማዕቀቦች ሊያጋጥሙን ይችላሉ፡፡ እነዚህም ማዕቀቦች የተፈጥሮ ህግ ፣ የሰው ሰራሽ ህግ፣ ከሌሎች ሰዎች የሚመጡ አስተያየቶችና እግዚአብሄር ናቸው፡፡ እናም ድርጊታችንን ስንፈፅም ከእነዚህ አራት ነገሮች ጋር እያነፃፀርን ሊሆን ይገባል።"በማለት ሀሳቡን በዝርዝር ያስቀምጣል፡፡

ከዚህ ፈላስፋ ቀጥሎ በስራው በጣም እውቅናን ያተረፈው ጆን ስቱዋርት ሚል ሲሆን እንደሱም አገላለፅ "የጄርሚ ቤንታም ሀሳብ ደስታን ከማስተዋወቅ ጋር ሲነፃጸር ምናልባትም ትክክል ሊሆን ይችላል ግን ተግባራዊ ስናደርገው የደስታን ተቃራኒ ልናገኝበት እንችላለን" በማለት ለምሳሌ "የወሲብ ደስታ ከነፍስ ደስታ ጋር ሊነፃፀር ይችላል?" ሲል ጥያቄን ይሰነዝራል፡፡

ልክ እንደ ቤንታም ሁሉ ሚልም አብላጫ ደስታ ለአብላጫ ቁጥር በሚለው ቢያምንም ለቤንታም አብሳጫ የሚለው ቃል ብዛትን ሲያመለክት ለሚል ግን ጥራት የሚለውን ይተካል፡፡ ታዲያ የደስታ ጥራት(quality) እንዴት ያለው ነው? የደስታን ጥራት መለየት የሚችለውስ ማን ነው? ብለን ብንጠይቅ "ሁለት ደስታዎች በብቃት ሊለያዩ ይችላሉ ፤ ያንን ሊናገር የሚችለው ሰው ደግሞ ሁለቱንም አይቶ ወይም በድርጊቱ ተፈትኖ ያለፈው ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም ዓይተውት ያለፉት እነሱ ከፍተኛውንና በጣም ጥራት ያለውን ደስታ መመዘን ወይም መምረጥ ይችላሉ" ብሎ ይናገራል፡፡ እናም እንደ ሚል አባባል ከሆነ 'የጠገበ አሳማ ከመሆን ይልቅ የራበው ሶቅራጠስ መሆን ይሻላል። (better be a starved Socrates than a satisfied pig)::'

ስለዚህም "ደስታን መሻት ከግላዊ ጥቅም አንፃር ብቻ ከታየ ሀድሰን ባዶውን ይጮሀል፡፡ በመከራ ጊዜም አብዝቶ ይጣራል . . . " እንደ ዩቲሊቴሪያኒስቶች አባባል፡፡

ምንጭ ፦ ፍልስፍናና ዘላለማዊ ጥያቄዎቹ
ፀሀፊ ፦ ቤተልሔም ለገሠ

@Zephilosophy
@Zephilosophy

2 months, 3 weeks ago

የትኛው ደስታ ይቅደም? የግለሠብ ወይስ የማህበረሠብ?

አንድ ሰው መልካም ነገርን የሚያደርገው ገሀነምን በመፍራት እና ገነት ለመግባት ካለው ጉጉት? ወይስ ግዴታ ስለሆነ? ውጤትን አስቀድሞ አያሰበ ወይስ ዝም ብሎ? ወይስ መልካም ነገር መስራት በራሱ ደስታን ስለሚሰጥ? የሰው ልጅ ሁሌም - በእነዚህ ሁለት የተለያዩ አመለካከቶች ተጠምዶ የሚገኘው የበጎ አመለካከት አሳቤዎች (morality) ወደ ምድር ወርደው በእያንዳንዳችን የዕለት ተዕለት ክንውኖች ውስጥ ጣልቃ መግባት ሲጀምሩ ቋሚ የሆነ መገለጫ ላይኖራቸው በመቻሉ ነው፡፡ ለዚህም ነው አንዱ መልካም ብሎ ያሰበውን ሌላው መጥፎ ብሎ የሚፈርጀው፡፡ ይህም ፅሁፍ የሚያጠነጥነው ሔዶኒዝም (Hedonism) ተብሎ በሚጠራው የፍልስፍና ዘርፍ ሲሆን የዚህ ፍልስፍና ተከታይ የሆኑት ‹‹አንድ ሰው መልካም ነገር የሚያደርገው ደስታን ለማግኘት ነው፡፡ ድርጊቱም ጥሩ ወይም መጥፎ ተብሎ የሚመዘነው በውጤቱ ሲሆን ውጤቱም የደስታው ምንጭ ሊሆን ይገባል” ብለው ያምናሉ፡፡

የዚህ ፍልስፍና አራማጆች ሲቀጥሉም ‹‹ደስታ ስራህ ትክክልና መልካም መሆኑን መመዘኛ ነው፡፡ ስለሆነም አንድ ሰው አንድን ድርጊት ሲፈፅም ስጋውንና ነፍሱን ማስደሰት ከቻለ የሰራው ስራ ከጅምሩም መልካም አንደነበር ማረጋገጥ ይቻላል” ይሉናል። ታዲያ የዚህ ፍልስፍና አራማጆች ራሳቸው ደስታን መፈለግ (መሻትን) በተመለከተ የራስን ደስታ መሻት (egoistic hedonism) እና የህብረተሰብን ደስታ መሻት (social hedonism) በማለት በሁለት ጎራ ተከፍለው እናገኛቸዋለን፡፡ በእርግጥም እነዚህ ሁለት ተቃራኒ የሆኑ ሀሳቦችን በመያዝ በተለያየ ጎራ የምናገኛቸው የተቃርኖ ሀሳብ ፈላስፎች ግባቸው ደስታን ማግኘት ቢሆንም ‹‹የማን ደስታ?›› ብለን በጠየቅን ጊዜ ግን ሁለቱም የተለያየ ምላሽ ይሰጡናል፡፡

በቅድሚያ እስቲ የራስን ደስታ ብቻ መሻት (egoistic hedonism) ወይም ቅድሚያ ለራስህ ቦታ መስጠት አለብህ የሚሉንን ፈላስፎች እንመልከት፡፡ ይህንን ሀሳብ ይዘው የሚራመዱ ፈላስፎች ‹‹ሰው በቅድሚያ የራሱን ፍላጎት ማሟላት አለበት፡፡ አንድ ነገር መልካም ነው ብለን የምንናገረው በቅድሚያ የራሳችንን ደስታ ማሟላት ስንችል ብቻ ነው›› በማለት ይከራከራሉ፡፡ ቀጥሎም ደስታው የነፍስ ወይም የስጋ? ብለን ስንጠይቅ በሲሬኒሲዝም (cyrenisism) ጎራ ተሰልፈው የምናገኛቸው “ደስታማ የስጋ ነዉ!፡፡ አናም ብሉ፣ ጠጡ፣ ጨፍሩ፣ አግቡ፤ ለነገ አታስቡ . . . ነገ ምናልባትም ልትሞቱ ትችላላችሁ፡፡ በተጨማሪም የምትሰሩት ስራ ደስታችሁን እጥፍ ድርብ የሚያደርግላችሁ ሊሆን ይገባል›› በሚለት “በትንሹ ልንረካ የምንችልበትንና በተቻለ አቅም ቶሎ ልናገኘው የምንችለውን ደስታ ልንፈልግ ይገባል» ብለው አበክረው ያስተምራሉ።

በአንፃሩ የኢፒኩሪያኒዝም (epicurianism) ሀሳብ አራማጆች የዚህ ዓይነት ደስታ ‹‹የአሳማ ፍልስፍና›› (pig's philosophy) ነው ይሉናል። በእርግጥ የኢፒኩሪያኒዝም አስተሳሰብ አራማጆች ደስታ የግል ሊሆን ይገባል ብለው ቢያምኑም ደስታ ሰውነትን ለማርካት ሳይሆን ለዓዕምሮ ሰላም ልንጠቀምበት እንደሚገባ አበክረው ይገልፃሉ፡፡ ሲቀጥሉም ‹‹አንድ ሰው ደስታን መሻት የሚገባው ለአጭር ጊዜ ብቻ ሳይሆን ለብዙ ጊዜ የሚቆየውን ሊሆን ይገባል፡፡ ለምሳሌ ለአንድ ሰው ወደ ጥርስ ሃኪም መሄድ በራሱ ህመም ሊሆንበት ይችላል፡፡ ግን እንደምንም ሄዶ ጥርሱን ቢታከምና ከጥርስ ህመም ነፃ ቢወጣ ለረጅም ጊዜ ሰላምን የሚያገኝበትን ዋነኛ መንገድ ተጎናፀፈ ማለት ነው፡፡ እናም ሰው ትኩረቱን መብላትና መጠጣት ላይ ካደረገና የአካሉ ጤንነት ካላሳሰበው አንድ ቀን ህመሙ ይህን የአጭር ጊዜ ደስታውን ደብዛውን ሲያጠፋበት ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ዓዕምሮ በጭንቀትና በፍርሀት ከተሸበረ በሽተኛ መሆኑ አይቀርም፡፡ አዕምሮ ሰላም ከሌለው ሰው በትክክል ሲያስብና የዘላለም ደስታን ሊጎናፀፍ አይችልም፡፡ ስለዚህም ደስታን መሻትት ከሰውነት ጤንነትና ከዓዕምሮ ሰላም ጋር ሊስተካከል ይገባዋል " ይሉናል፡፡ እነዚህ የኢፒኩሪያኒዝም አስተሳሰብ አራማጆች ዋነኛ ግባቸው ህመምን ከማስወገድ ጋር የተያያዘ በመሆኑ ጋብቻ ፣ ቤተሰብ ፣ ፖለቲካ አልያም ጓደኝነት ከዓዕምሮ ደስታ በኋላ ሊመጡ የሚችሉ ነገሮች ናቸው ብለው ያምናሉ ። ለምን ቢባል እነዚህ ነገሮች ለጨጓራ ህመም ለአዕምሮ ጭንቀትና ለመሳሰሉ ህመሞች ሊዳርጉ ስሰሚችሉ በተቻለ አቅም ልናርቃቸውና ልናስወግዳቸው ይገባል የሚል ምላሽ አያይዘው ይሰጣሉ ፡፡

በሌላ በኩል እነዚህ ፈላስፎች ‹‹የአጭር ጊዜ ፍላጎትን ለማሟላት ከመሮጥ የሚመጣ ህመም ሊወገድ ይገባል» ይሉናል፡፡ ይህንንም ሲያብራሩ «እርግጥ ነው ዳቦና ውሀ ሰው በጣም በተራበና በተጠማ ጊዜ ከፍተኛ የደስታ ምንጭ ሊፈጥሩለት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን እህልን አብዝተን ስንወድ ቁንጣን እንዳያመጣብን ልንጠነቀቅ ደግሞ ይገባል። እናም ደስታን ለመፍጠር ብለን ለህመም ሳንዳረግ ለመጨረሻ ግባችን ልንሮጥ ይገባል፡፡ ይህ የመጨረሻው ግባችን ታዲያ ከስሜት ህዋሶቻችን የመነጨ ብሎም የስሜት ህዋሶቻችንን ብቻ ለማርካት መሆን የለበትም:: ሳያቋርጡ መጠጣት፣ መጨፈር ፣ ማመንዘር ፣ ከምግቦች ሁሉ ለቅንጦት ስጋን መምረጥ፣ ወዘተ እነዚህ ለጊዜው ደስታ ሰጥተው ... ምክንያታችንን ግን ሊያከሽፉ፣ ምርጫችንን አስተካክለን እንዳንመርጥ ሊከለክሱ፣ አስተያየታችንን ሊያጨናገሩ ስለሚችሉና ነፍሳችንንም አቆሽሸው ዘላቂ ሰላማችንን ስለሚያደፈርሱ በተቻለን አቅም ቅንጦትን ልናስወገድ ይገባናል በማለት አበክረው ይመክራሉ::

አንደ ኤጎይስቲክ ሄዶኒዝም (egoistic hedonism) ሁሉ የዩቲሊቴሪያኒዝም (utilitarianism) አስተሳሰብ አራማጆች ‹‹አንድ ሰው ስራው ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ የስራውን ውጤት ሊመለከት ይገባል፡ ፡ ወይም የሰራው ስራ መልካምነቱን ማረጋገጥ የሚቻለው በፍሬው ነው በሚለው ሀሳብ ቢስማሙም ‹‹አንድ ሰው ሊጨነቅ የሚገባው ለራስ ደስታ አልያም ከራስ ወዳድነት ለመነጨ ስሜት ሳይሆን ለማህበረሰቡ ( ለብዙሀን ደስታ) ነው›› በሚለው ሀሳብ ላይ ልዩነታቸው ይጀምራል፡፡ በዚህም « አብላጫው ደስታ ለአብላጫው ቁጥር›› (the greatest happiness for the greatest number) የሚል መፈክርን አንግበው ይጓዛሉ፡፡ እስቲ ወደ ዝርዝር ሀሳባቸው ከመግባታችን በፊት የዚህን ፍልስፍና እሳቤ በደንብ ይገልፀዋል የተባለውን ታሪክ እናንብ፡-

ምንጭ ፦ ፍልስፍናና ዘላለማዊ ጥያቄዎቹ
ፀሀፊ ፦ ቤተልሔም ለገሠ

ይቀጥላል

@Zephilosophy
@Zephilosophy

2 months, 4 weeks ago

አልበርት አንስታየን
.....✍️የቀጠለ

የአይንስታይንን የእምነት ፍልስፍና ላጤነት ግን ወዳጆቹ የፈላስፋነት ካባ ሊደርቡለት መከጀላቸው እምብዛም አይደንቀውም፡፡

እ.ኤ.አ. በ1915 በእንግሊዞች ላይ ደርሶ ስለነበረው እልቂት የሚገልፅ አንድ ደብዳቤ ከስዊዘርላንዳዊ ወዳጁ ኤድጋር ሜየር ደረሰው፡፡ ሜየር በደብዳቤው፡- "እግዚአብሔር እንግሊዞችን በመቅጣቱ ደስ ሊልህ ይገባል" አለው:: አይንስታይን ለወዳጁ በፃፈው የመልስ ደብዳቤ፡- " ለምን ይኸን ደብዳቤ እንደፃፍክልኝ አልገባኝም፡፡ እኔ ከእግዚአብሔርም ሆነ ከእንግሊዞች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለኝ በሚገባ ታውቃለህ። የሰውን ዘር በምድር ላይ እየቀጣ ያለው እግዚአብሔር ከሆነ ኃላፊነቱን ሊወስድ ይገባ ነበር፣ እግዚአብሔር የሚባል ነገር አለመኖሩ ግን በራሱ ይቅር አስብሎታል" በማለት መልሶለታል፡፡

"እስከዛሬ በምድር ላይ ስኖር ለአንድም ቀን አለ ብዬ አስቤው የማላውቀው ነገር እግዚአብሔር ነው" የሚለው አይንስታይን አንድ ወቅት በተማሪዎቹ፡- "ራስህን ከእግዚአብሄር በላይ ታየዋለህን?" ተብሎ ተጠይቆ ነበር፡፡

እሱም ሲመልስ፡- "አዎን! ከኢየሱስ በላይ ማድረግ ከቻልኩ እንዴት ከእግዚአብሔር ማነስ እችላለሁ፡፡ 'እኔ ከማደርገው በላይ ታደርጋላችሁ' አላለም እንዴ?" በማለት መልሶላቸዋል፡፡

የቅርብ ወዳጁ አይሁዳዊው ሄይል ፍሬድማን፦ "የአይሁድ ዘር ሆነህ በእግዚአብሔር አለማመንህ ምናልባት መጽህፍ ቅዱስ ያለማንበብህ ውጤት ይሆናል" በማለት ለፃፈለት ደብዳቤ ደግሞ በላከለት መልስ፡- "መጽሀፍ ቅዱስ ያነበብኩት ኮፒውን ነው:: በሙሴ የተፃፈው ኦሪጅናሉ ካለህ እባክህ ላክልኝ... በእግዚአብሔር መኖር የማላምን ሀይማኖተኛ መሆኔን ግን አሁንም የረሳኸው አይመስለኝም" ብሎታል፡፡

አንስታይን ምንም እንኳን ይህን ይበል እንጂ እምነት በጥቅም ላይ የተመሰረተ ሊሆን እንደማይገባ ደግሞ እንዲህ አሳስቧል፡- "የሰው ልጅ ምግባር ሊመሰረት የሚገባው በርኅራኄ፣ በትምህርትና በማኅበራዊ ትስስር እንጂ በሀይማኖት መሆን የለበትም:: እንዲያውም የትኛውም ሀይማኖታዊ መሠረት አስፈላጊ አይደለም:: ሰው ከሞት በኋላ በሚጠብቀው የቅጣት ፍርሀትም ሆነ የሽልማት ተስፋ ራሱን ካሰረ በእርግጥም ደካማ ፍጡር ነው::"

አይንስታይን በሕይወት ጉዞው በርካታ መሰናክሎችንና ፈተናዎችን አልፎ ለታላቅነት የበቃ ሰው መሆኑን አይዘነጋውም:: ታዲያ ከፈተናዎች ሁሉ የከፋ ፈተና የሚለው፡- "ታላቅ መንፈስ ያላቸው ሰዎች ሁሉ ፅኑ ፈተና የሚገጥማቸው ደካማ አእምሮ ካላቸው ሰዎች መሆኑ ነው" ይላል:: በእንዲህ ዓይነቱ ፈተና ታዲያ አንዳንዴ ታላላቅ መንፈስ ያላቸው ሰዎች በደካሞቹ ተጠልፈው ሲወድቁ አስተውሎ፡- "አንዳንድ ጊዜ ጠንካራው ሰው ብዙ ድካም ከፍሎ ያገኘውን ነገር ደካማው በከንቱ ሲቀበለው ከመመልከት በላይ የሚያስከፋ ነገር የለም" አለ::

አብዛኛዎቹ የሰው ልጅ ችግሮች መፍትሄ ያለማግኘታቸው ምክንያት ምን እንደሆነም አንስታይን ተጠይቋል:: እሱም ሲመልስ፡- "ችግሮቹን በፈጠርንባቸው መንገድ መፍትሔአቸውንም ለማግኘት በመሞከራችን ነው" አላቸው::

አንስታይን ለሳይንስ በተፈጠረ አእምሮው መጨረሻቸው የማይታወቅ የሚላቸውንና ለዚሁም በማስረጃ የደረሰባቸውን ተናግሯል፡- "በእኔ መረዳት ሁለት ነገሮች መጨረሻቸው አይታወቅም፤ እነሱም ይኸ ዓለም /universe/ እና የሰው ድድብና /man's stupidity/ ናቸው፤ ይሁንና ስለዓለም እርግጠኛ ሆኜ መናገር አልችልም::"

አንስታይን በ76 ዓመቱ በምደረ አሜሪካ ሕይወቱ ስታልፍ አስከሬኑን የመረመረው የፕሪንስተን ዩኒቨርስቲ ሐኪም ማንንም ሳያስፈቅድ የአንጎሉን ክፍል ቀዶ በማውጣት ወሰደ:: ሐኪሙ ይኽ ድርጊቱ ሲታወቅ የአንስታይንን ልጅ ፍቃድ ጠየቀ:: (የአባትህ አንጎል መቼም ልዩ እንደነበር ታውቃለህና እባክህ እንድመራመርበት ፍቀድልኝ.. ያለው ይመስለኛል::) ምንም እንኳን ሐኪሙ የአንስታይንን ልጅ ፍቃድ ቢቸርም ዩኒቨርስቲው ግን ሀኪሙ የአንስታይንን አንጎል ለመመለስ ፍቃደኛ አለመሆኑን ተከትሎ ከሥራው አባረረው:: ሐኪሙ ግድ አልሰጠውም፤ ለ40 ዓመታት ያህል የአንስታይን አንጎል ከሌላው የሰው ልጅ አንጎል የሚለይበትን ጉዳይ ሲመራመር ቆይቶ በ1998 እ.ኤ.አ. ወደነበረበት መልሷል::

አንስታይን በሳይንሳዊ ግኝቶቹ በዘመኑ ሁሉ ታላቅ ክብርና ዝናን ተቀዳጅቶ ያለፈ ቢሆንም "ከዚህስ በኋላ ምን አዲስ ነገርን ለማወቅ ትሻለህ?" ተብሎ መጠየቁም አልቀረም:: እሱም እንዲህ መለሰ፦ "የእኔ ፍላጎት የፈጣሪን ሀሳብ ማውቅ ነው፤ ሌላው ሁሉ ዝርዝር ጉዳይ ነው!"

ምንጭ ፦ ተዐምራትና ጣዖታት
ፀሀፊ ፦ ሀይለጊዮርጊስ ማሞ ( ጲላጦስ )

@Zephilosophy
@Zephilosophy

5 months, 1 week ago

አብዘርዲዝም - ካምዩ

ምንጭ ፦ ፍልስፍና ከዘርዓያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ
ምንጭ ፦ ፍሉይ አለም

መጠለያ ባጣህበት ሁኔታ በዝናብ እየተደበደብክ እየተጓዝክ ሳለ፣ መሳቅ ጀምረህ አታውቅም? የሆነ ጉዳይ በእጅጉ ተበላሽቶብህ ከዚህ በላይ ምን ሊመጣ አይነት ስሜት ፈገግ ብለህ አታውቅም? በችግሮችህ ውስጥ ሳለህ እያንዳንዷን ደቂቃ ወደህ አታውቅም? ይህን አልበርት ካምዩ አብሰርዲቲ ይለዋል፡፡

ካምዩ ፈረንሳያዊ የኤግዚስታንሻሊዝም (ህላዌነት) ፈላስፋ ነው፡፡ በቀላል ታሪክም ፍልስፍናውን ይጀምራል፡፡

ሲሲፈስ የተባለ የጥንታዊቷ ግሪክ ንጉስ አማልክቱን የሚያስቆጣ ተግባር ፈጸመ። ሲሲፈስ ሞትን በሰንሰለት አሰረው፡፡ ይህንንም በማድረጉ የሰው ልጅ ዘላለም ኗሪ ሆነ። በመጨረሻም አማልክቱ ሲሲፈስ ያደረገውን አወቁ፤ በርሱ ላይም ዘላለማዊ ቅጣት ፈረዱበት፤ የሞትንም ሰንሰለት በጠሱ፡፡ እናም ሲሲፈስ ለመቀጣጫ እንዲሆነው ዘላለም ድንጋይ ሲያንከባልል እንዲኖር ተፈረደበት። ግዙፍ ቋጥኝ እየገፋ ወደ ተራራ አናት ያደርስዋል፤ ወዲያውም ቋጥኙ ወደ ተራራው ስር ተንከባሎ ይወርዳል፤ ሲሲፈስም እንደገና ከታች ጀምሮ ወደ ላይ ቋጥኙን ይገፋዋል፡፡ ቋጥኙም ተመልሶ ወደ ተራራው ግርጌ ይወርዳል...

ይህ የሲሲፈስ ዘላለማዊ ቅጣቱ ነው። ያንተስ ሕይወት ከርሱ ይለያልን? የሲሲፈስ እልፍ ጊዜ እየተመላለሰ ቋጥኝ ማንከባለሉ ትርጉም አልባ እንደሆነ ይሰማሃል? ሆኖም ያንተ ሕይወት ትርጓሜው ምንድን ነው?

ሕይወትህን ልክ እንደ ሲሲፈስ ትርጉም አልባ ቋጥኞችን ስትገፋ ነው የምታሳልፈው፡፡ የማይሞላ ሆድ አለህ... ሚልዮን ጊዜ መግበኸው ሚልዮን ጊዜ ጎድሎብሃል፤ የማይሞላ ፍላጎት አለ... ሚልዮን ጊዜ ተደስተህ ሚልዮን ጊዜም ተከፍተሃል። በጠዋት ከእንቅልፍህ ትነሳለህ፤ ገንዘብን ፍለጋም ወደ ስራ ትሄዳለህ... ቀኑ ይመሻል ዳግም ይነጋል... በጥዋት ወደ ስራ ትሄዳለህ. ከእለታት በአንዱ ቀንም ራስህን በሞት አልጋ ላይ ታገኘዋለህ፡፡ እናም በሕይወት ዘመንህ የምታደርገው ነገር ሁሉ ልክ እንደ ሲሲፈስ ቋጥኝ መግፋት- ዘበት ነው!

የሰው ልጅ ህልቆ መሳፍርት በሌለው ሁለንተና ላይ ራሱን ሲያገኘው፤ “ለምን?” የሚል ጥያቄን ይጠይቃል። ለምን ተፈጠርኩ? ለምን እኖራለሁ? የሕይወቴ ትርጉምስ ምንድን ነው? ሆኖም እውነታው ይህ ነው... ያንተም የኔም የመኖር ሁኔታ በአጋጣሚዎች የተፈጠረ እንጂ ትርጓሜ ያለው ነገር አይደለም በጸጥታ ውስጥ ባለው በግዙፉ ሁለንተና ውስጥ አንተ ማን ነህና ሕይወትህ ትርጉም ይኖረዋል? ሁለንተናም ስላንተ ግድ የለውም... ለጥያቄህም መልስ የለውም፡፡ ሆኖም ይህ መሆኑን ብናውቅም፤ ሰው ነንና የሕይወታችንን ትርጉም መፈለጋችንን አናቆምም የሞትን ቀን ያበቃለታል። ሞት በሕይወታችን የኖርንላቸውን ተግባራቶች በሙሉ ዋጋ ያሳጣቸዋል፡፡ ይህንን ነው አብሰርዲዝም ወይም የሕይወት ዘበትነት ሲል የሚጠራው፡፡

እና ዘበት በሆነ ዓለም ላይ እንዴት እንኑር?

ታይታኒክ በተባለው ፊልም መጨረሻ ላይ መርከቧ እየሰመጠች ሳለ ሙዚቀኞች ቫዮሊን ሲጫወቱ ይታያል፡፡ እንደሚሞቱ ቢያውቁም፣ ቅጽበታቸውን ብቻ መኖር ጀመሩ፤ የሚወዱትንም ሙዚቃ ከልባቸው ተጫወቱ፡፡

ካምዩ በአንደኛው መጽሐፉ ላይ እንዲህ ይለናል - "የምር የሆነ አንድ የፍልስፍና ጥያቄ ብቻ ነው ያለው፤ ጥያቄውም - ራሴን ላጥፋ ወይስ ቡና ልጠጣ?”

እንደ ካምዩ እሳቤ የሰው ልጅ የሚኖርበት ምክንያት ከሌለው ሶስት ነገሮች ያደርጋል፡

የመጀመሪያው ራሱን ያጠፋል፡፡ ማለቂያ አልባ በሆነው ሁለንተና ውስጥ የምትበራ አንድ ሻማ የርሷ ጭል... ጭል ማለት ትርጉም የለውምና ራሷን እፍ ብላ ታጠፋለች፡፡ ይህን ካምዩ የዓለምን ዘበትነት ማምለጫ ይለዋል።

ሁለተኛው philosophical suicide ይፈጽማል፡፡ ይህም ማለት ሕይወት ትርጉም ባይኖራትም ትርጉም እንዳላት አድርጎ ማሰብ ይጀምራል። ለዚህ ዋነኛ ተጠቃሽ የሚሆኑት ጭፍን አማኞች ናቸው፡፡ በእምነት ውስጥ መመርመር የለም... የምትኖርበት አላማ እንዳለህ እና የምታምንበት ሀይል ለዚህ አላማ እንደፈጠረህ ያለምንም መጠራጠር በጭፍን ትቀበላለህ፡፡ ስለሆነም መኖርህ ዋጋ አልባ ወይም ዘበት እንደሆነ አይሰማህም፡፡

በሶስተኛነት የምናገኘው ካምዩ absurd hero ይለዋል። ይህ ሰው ሕይወቱ ትርጉም እንደሌላት ያውቃል፤ ለሌሎች ሰዎች ትርጉም የማይሰጥ ነገር ግን ለእርሱ ብቻ ዋጋ ያለው ... ለእርሱ ብቻ የሚሰራ የሕይወት ትርጉምንም ይፈጥራል። ይህ የትርጉም ፈጠራ ሂደትም በራሱ ደስተኛ ያደርገዋል። ለሲሲፈስም ድንጋዩን ወደ ተራራ ማንከባለሉ ለእርሱ ትርጓሜ አለው፡፡ ይህ ለስው ልጆች የከፈለው መስዋእትነት ምልክት ነው. ይህ አማልክቱ ለእርሱ የሰጡት ቅጣት ምንም እንዳልሆነ ማሳያ መንገዱ ነው... ፈገግ ብሎም ድንጋዩን ይገፋል... የእርሱ ፈገግታም አማልክቱን እንደሚያስቆጣቸው ያስባል። እናም ድንጋይ ማንከባለሉ ብቻ ልቡን በደስታ ይሞላዋል።

ካምዩም ሕይወት ትርጉም አልባ እንደሆነች ቢያውቅም እንኳ እንደ ሲሲፈስ ሁን ይልሃል። በዝናብ ውስጥ ደንስ... ትርጉም አልባ በሆነች ዓለም ላይ ለራስህ ብቻ እውነት የሆነ የመኖር ትርጉም ፍጠር፡፡

@Zephilosophy
@Zephilosophy

5 months, 1 week ago

ክቡር ሰው - ካንት

ምንጭ ፦ ፍልስፍና ከዘርዓያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ
ፀሀፊ ፦ ፍሉይ አለም

ከጓደኞችህ ጋር እራት እየበላህ፣ አንዱ ተስተናጋጅ ከመጠን በላይ እያጨበጨበ አስተናባሪውን ይጣራል “እዚህ ጋር አንድ ምግብ፡፡” አንዳንድ ሰውም በሰላም ላደረሰው ሾፌር “እንዴት ነህ፣ ቻው ወይም አመሰግናለሁ” ሳይል ከታክሲ ወርዶ ወደ ጉዳዩ ያቀናል፡፡ ወንጀለኞች ህጻናትን ሰርቀው እንደ እቃ ይሸጣሉ፡፡ መንግስትም አገሩን ከዳ ብሎ ያስበውን ግለሰብ ያስገድላል፡፡ እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች በጋራ የያዙት ነገር ምን አለ?

ኢማኑኤል ካንት አስተናጋጁን የሚያመናጭቀው ጓደኛህም፣ ለሾፌሩ ግድ የሌለው ተሳፋሪም፣ ልጆች የሚጠልፉ ወንጀለኞችም፣ አስገዳዩ መንግስትም... ሁሉም የሰውን ልጅ አግባብ ባልሆነ ሁኔታ አስተናግደዋል ይለናል።

ካንት በምክንያታዊነት ላይ ባለው የጸና አቋም በእጅጉ ይታወቃል። ለእርሱ ምክንያታዊነት ከሁሉ የላቀ ንብረታችን እንደሆነ ነው የሚነግረን። ከዚህም በላይ ምክንያታዊነት ምን ልክ ምን ስህተት ምን ኃጢአት ምን ጽድቅ እንደሆነ ይለይልናል፡፡

ካንት የሞራል ህግጋት አይለወጤ እና የጸኑ ናቸው ብሎ ያስባል። የሚደረስባቸውም በምክንያት እና ምክንያታዊነት ብቻ ነው። ይህንንም ምክንያታዊ ግብረገብነትንም ለማስረዳት ካንት ባለ ብዙ ገፅ መጽሐፎችን አሳትሟል።

ካንት ሁሉም ሰው ሊነካ የማይገባው
ክብር አለው ይለናል። እናም የሁላችንም ድርጊቶች ይህን ክብር የጠበቁ ሊሆኑ ይገባል። በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ብንሆንም የሰውን ክብር መንካት የለብንም፡፡ ሰዎች የምንገለገልባቸው ቁሳዊ መሳሪያዎች አይደሉም፡፡ ሁሉም የራሳቸው ዋጋ አላቸው። ለሁሉም ሰው ግድ ሊኖረን ይገባል።

ሁላችንም እንደ ግለሰብ ዋጋ እንዳለን እናስባለን፡፡ ዓለም የግለሰቦች ጥርቅም ናትና ለራሳችን የምንሰጠውን ዋጋ ለሁሉም ሰው መስጠት የተገባ ነው፡፡ እኛ ምንም አይነት ጥያቄ እና ምክንያት ሳንደረድር፣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለራሳችን ከፍ ያለ ዋጋን ከሰጠን፣ እንደ ማህበርም ለሌሎች ሰዎች ዋጋ ሊኖረን ይገባል።

አዎ በማህበረሰብ ውስጥ አንደኛው ተገልጋይ፣ ሌላኛው አገልጋይ ሊሆን የተገባ ነው፤ ሆኖም በዚህ ሂደት ውስጥ ሰዎችን እንደ ሰውነታቸው ልናከብራቸው የተገባ ነው፡፡ አስተናጋጁም፣ የታክሲ ሹፌሩም ሆነ ሀገር ከዳተኛው ሰው ናቸው። ሁሉም ለራሳቸው ዋጋን ይሰጣሉ፡፡ ካንት ከእርሱ በኑሮ ደረጃ ዝቅ ያሉትን አገልጋዮቹን በታላቅ ክብር ይመለከታቸው ነበር፡፡

በቀጣይም ሰውን እንዴት ማዋራት እንዳለብህ ስታስብ ይህን “እንደ ሰው እያከበርኳቸው ነው ወይንስ እንደ መሳሪያ እየተጠቀምኩባቸው?” ይህም ቀላል እና ሊተገበር የሚገባው ግብረገባዊ ህግ ነው፡፡

@Zephilosophy
@Zephilosophy

5 months, 4 weeks ago

ማራኪ የዜን ትረካዎች
በግሩም ተበጀ

@Zephilosophy
@Zephilosophy

7 months, 1 week ago

ወደ መለኮት የሚወስድ መሰላል

ምንጭ ፦ የህይወት ኬሚስትሪ (ሳድጉሩ)
ትርጉም ፦ ሀኒም

“ግንዛቤ” ለተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ነገሮች ማለት የሆነና ግልጽ ያልሆነ ቃል ነው። “ግንዛቤ” ስትል ከአእምሮ ንቃት ጋር እንዳታምታታው፡፡ የአእምሮ ንቃት በተሻለ ሁኔታ ለመኖርና የመኖርህን ሂደት በትንሹ ከፍ ባለ መንገድ እንድትመራ ይረዳሀል:: ግንዛቤ አንተ የምታደርገው ነገር አይደለም፤ ሕያውነት ነው፡፡ የአንተ ሕያውነትህ በአንተ ግንዛቤ ምክንያት ብቻ ነው። ሙሉ በሙሉ ግንዛቤ የሌለህ ከሆንክ ህያው መሆንህን አታውቅም፡፡ በሕይወት የምትኖረው ባለህ ግንዛቤ መጠን ብቻ ነው። የግንዛቤህ መጠን የሚለካው ደግሞ፣ አንድ ነገር በተሞክሮህ ውስጥ ባለው መጠን ነው፡፡

“ግንዛቤን መለማመድ የምችለው እንዴት ነው?” ብለህ ትጠይቅ ይሆናል፡፡ ግንዛቤን መለማመድ አትችልም፡፡ ሕይወትንስ እንዴት መለማመድ ትችላለህ? አሁን ለምታስበውና ለሚሰማህ ነገር ትልቅ ቦታ የምትሰጥ ከመሆንህ የተነሳ፣ ለህያውነትህ ብዙ ቦታ አትሰጥም፡፡ የስነ ልቦና ሂደትህም ከሕይወት ሂደትህ የበለጠ አስፈላጊ ሆኗል፡፡ አእምሮህ ጫጫታ ውስጥ ባይሆን፣ ግንዛቤ ተፈጥሯዊ መንገድ ነበር፤ ነገር ግን አእምሮህ ማለቂያ ወደሌለው ሁካታ ውስጥ እንዲገባ ስላደረግክ ግንዛቤ ከባድ የሆነ ይመስላል።

ሰዎች የአስተሳሰባቸውን ሂደት በጣም አስፈላጊ ከማድረጋቸው የተነሳ “አስባለሁ፣ ስለዚህም አለሁ” እስከማለት ደርሰዋል። ግን እውነቱ የትኛው ነው፤ የምታስበው ስላለህ ነው ወይስ ያለኸው ስለምታስብ ነው? ሀሳብ ማፍለቅ የቻልከው ስላለህ ነው፣ አይደል? በየትኛውም መንገድ በስነ ልቦና ሂደትህ መጫወት ትችላለህ፤ ነገር ግን ማሰብ የምትችለው ህያው ስለሆንክ ብቻ ነው፡፡ ህያው መሆን ከማይረባ የአስተሳሰብ ሂደትህ ይልቅ እጅግ ትልቅ ሂደት ነው፡፡

ከፈለግክ ሙሉ በሙሉ መኖር፣ ግን አለማሰብ ትችላለህ። እንዲያውም ብታስተውል በሕይወትህ ውስጥ በጣም ቆንጆዎቹ ጊዜዎች ስለ ምንም ነገር ሳታስብ የቆየህባቸው ጊዜያት ናቸው፡፡ የደስታ ጊዜያት፣ የሀሴት ጊዜያት፣ ፍጹም የሆኑ የሰላም ጊዜያት... ብለህ የምትጠራቸው ጊዜያት ስለ ምንም ነገር ሳታስብ የኖርክባቸው ጊዜያት ናቸው፡፡

ታዲያ ይበልጥ አስፈላጊው የትኛው ነው፤ መኖር ወይስ ማሰብ? ህያው ፍጡር መሆን ትፈልጋለህ ወይስ የምታስብ ፍጡር? መወሰን አለብህ፡፡ አሁን ዘጠና በመቶ የሚሆነውን ጊዜ የምታሳልፈው ስለ ሕይወት በማሰብ እንጂ ሕይወትን በመኖር አይደለም፡፡ እዚህ የመጣኸው ግን ሕይወትን ለመለማመድ እንጂ ስለ ሕይወት ለማሰብ አይደለም፡፡ ሕይወትን መለማመድ ትፈልጋለህ፣ በሃሳብህ ከጠፋህ ግን ሕይወትን መለማመድ አትችልም፡፡ ሕይወትን የምትለማመደው በስሜት ህዋሳትህ እንጂ በማሰብ አይደለም፡፡ ሃሳቦችህ ከእውነታው ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው በመሆኑ የምታስበው ነገር ምንም ትርጉም የለውም፡፡ ማሰብ ከእውነታው ጋር ግን ምንም ግንኙነት ስለሌለው፣ ሁሉም ሰው በፈለገው መንገድ የራሱን የማይረባ ነገር ማሰብ ይችላል።

የስነ ልቦና ሂደትህ ከሕይወት ሂደት ጋር ሲነጻጸር በጣም ትንሽ ክስተት ነው፡፡ አሁን አንተ ማሰብን በሕይወት ከመኖር በላይ አስፈላጊ እንደሆነ ስለምታስብ፣ ከአንተ ሃሳብ ጋር በጥቂቱም ቢሆን ብጋጭ ለእሱ ስትል ልትሞት እንኳን ፍቃደኛ ነህ። ሰዎች ለሀሳባቸው፣ ለሚያምኑበት ነገር ይሞታሉ፡፡ ሰዎች በሕይወት መኖር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ስላላስተዋሉ ማሰብ ከሕይወት ሂደት የበለጠ አስፈላጊ ሆኗል፡፡ ሕይወት በመኖር እንቅስቃሴ ስለተዋጠ፣ ማሰብ ከሕይወት የበለጠ ታላቅ ይመስላል፡፡ ግን እንደዚያ አይደለም። አስተሳሰብ ከሕይወት ሂደት ጋር ሲወዳደር ትንሽ ክስተት ነው፡፡

አርስቶትል የዘመናዊ አመክንዮ አባት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ የእሱ አመክንዮ በጣም ቀላል እና ቀጥተኛ ነው፤ A መሆን የሚችለው A ብቻ ነው፤ B መሆን የሚችለው B ብቻ ነው፡፡ A፣ B ሊሆን አይችልም፤ Bም A ሊሆን አይችልም፡፡ በዚህ መከራከር ትችላለህ? ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ትክክል ይመስላል፡፡ ግን እስቲ ይህን እንይ፡-

እዚህ ወንድ ወይም ሴት ሆነህ ተቀምጠሃል፡፡ ግን እንዴት ወደዚህ መጣህ? ሴት ነሽ እንበል፣ አባትሽ ለአንቺ መምጣት ምንም አላዋጣም ማለት ነው? በአንቺ ውስጥ አለ፣ አይደለም እንዴ? ወንድ ከሆንክም እናትህ ምንም አላዋጣችም ማለት ነው? እናትህ በአንተ ውስጥ የለችም? እውነት ነው አንተ ወንድ ወይም ሴት ነህ፤ ሀቁ ግን ሁለቱንም መሆንህ ነው። እውነት በምክንያታዊነት ሊገለጽ የማይችል ልኬት ነው᎓᎓ እውነት ከአመክንዮ ጋር አይገጥምም፤ ምክንያቱም አመክንዮ ሁልጊዜ የሚከፋፍል ሲሆን፣ እውነት ግን አንድ አድራጊ ነው፡፡ ታዲያ ይህ አመክንዮ ከሕይወት ጋር የሚገጥመው የቱ ጋ ነው?

የአንተን አመክንዮ በሕይወትህ ላይ ከልክ በላይ የምትተገብረው ከሆነ፣ ሁሉም ሕይወት ከውስጥህ ተጨምቆ ይወጣል፡፡ የአእምሮ አመክኗዊ ቁሳዊ እውነቶችን ገጽታ የሚጠቅመው የሕይወት ለመቆጣጠር ብቻ ነው፡፡ በመሰረታዊነት ሕይወትህን ፍፁም በሆነ አመክንዮ የምትመለከት ከሆነ ሕይወት ምንም ትርጉም አይኖረውም፤ ስለዚህ ራስህን በአመክንዮ ለመያዝ የምትሞክር ከሆነ ሙሉ በሙሉ ምስቅልቅል ያልክ ትሆናለህ ማለት ነው፡፡ ነገ በማለዳ ከእንቅልፍህ ስትነቃ የፀሐይ መውጣትን፣ በሰማይ ላይ  የሚበሩ ወፎችን አትመልከት፤ የምትወደውን ሰው፣ የልጅህን ፊት ወይም በአትክልቱ ውስጥ ያሉትን አበቦች አታስብ፤ ዝም ብለህ በፍፁም አመክንዮ አስብ።

አሁን፣ በትክክል ከአልጋ መውጣት አለብህ ያ ትንሽ ስራ አይደለም፡፡ ወደ መጸዳጃ ቤት ትሄዳለህ፣ ጥርሶችህን ትቦርሻለህ፣ ምግብ ትበላለህ፣ ከዚያ አንዳንድ ስራዎችን ትሰራለህ፣ ትበላለህ፣ ትተኛለህ፤ ነገ ጠዋትም ተመሳሳይ ነገር ታደርጋለህ፡፡ ይህን ነገር ለሚቀጥሉት አርባና ሀምሳ አመታት ደጋግመህ ማድረግ አለብህ። የሕይወት ተሞክሮህን ሳትመለከት መቶ በመቶ በምክንያታዊነት አስብ፡- በእርግጥ ጠቃሚ ነው? እባክህ የከፍተኛ አመክንዮ ጊዜያት ራስን የማጥፋት ጊዜዎች መሆናቸውን ተመልከት፡፡ ስለ ሕይወት መቶ በመቶ ምክንያታዊ በሆነ መንገድ የምታስብ ከሆነ፣ ለመኖር ምንም ምክንያት አይኖርም፤ እኔና አንተ እዚህ የምንኖርበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ነገር ግን በሕይወትህ ውስጥ አንድ የሚያምር ቅጽበት ከተመለከትክ፣ በድንገት ሁሉም ነገር ብሩህ ይሆንና መኖር ትፈልጋለህ፡፡ የሕይወትህ አመክንዮአዊ ገጽታና የሕይወት ተሞክሮህ ስፋት አንዳቸው ከሌላኛቸው ጋር ተቃራኒ ናቸው።

ሕይወትን በተሞክሮ አይን የምትመለከት ከሆነ፣ ለመኖር፡የሚያበቃ ምክንያት ይኖርሃል፡፡ ሕይወትን በምክንያታዊነት የምትመለከት ከሆነ ደግሞ ለመኖር ምንም ምክንያት አይኖርም፡፡ ሰዎች በበርካታ ምክንያቶች ራሳቸውን ያጠፋሉ፡፡ በአጠቃላይ ግን ሰው ራሱን የሚያጠፋው የነበረውን ተሞክሮ መልሶ ለማየት ፍቃደኛ ባለመሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ በጤና ምርመራ ሲወድቅ፣ የትዳር አጋር ጥሎት ሲሄድ ወይም ንብረቱን ሲያጣ ራሱን ሊያጠፋ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ዛሬ ባልሽ ወይም ሚስትህ ጥሎሽ ወይም ጥላህ ሄደዋል እንበል። በምክንያታዊነት የምታስብ ከሆነ፣ “መላ ሕይወቴ ይህንን ሰው መውደድና ከዚህ ሰው ጋር መሆን ነበር፤ አሁን ይህ ሰው ትቶኝ ሄዷል። የምኖርበት ምክንያት ምንድነው?” ብለህ ታስብና ራስህን ታጠፋለህ። ነገር ግን ባልሽ ወይም ሚስትህ ትተው ከሄዱ ምናልባት በሕይወትህ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ አዲስ እድል ሊሆን ይችላል፡፡ ነፃ ስለሆንክ ብቻ ከአንድ የሕይወት ገጽታ ምናልባትም ያልገመትካቸው ነገሮች ያጋጥሙህ ይሆናል።
@Zephilosophy

We recommend to visit

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated hace 3 días, 10 horas

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated hace 3 días, 17 horas

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated hace 2 meses