Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

Description
የአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ለማንኛውም ጥያቄ
@Finotebrhan
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 2 days ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago

6 months, 4 weeks ago
[#ምስጋና](?q=%23%E1%88%9D%E1%88%B5%E1%8C%8B%E1%8A%93)

#ምስጋና
የሰንበት ትምህርት ቤቱን የአገልግሎት ክፍላት ግንባታ ዕቅድ የሰማች አጸደ ማርያም የተባለች ቀደምት የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባል በተማሪ ቃልኪዳን ጌትሽ በኩል አስር ሺህ ብር (10,000) ድጋፍ አድርጋ ለሰንበት ትምህርት ቤታችን ጽ/ቤት ገቢ ሆኗል፡፡

ስለዚህም ስለተደረገው ሥጦታ የሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት በእጅጉ ያመሰግናል!!!

“ለቅኖች ምስጋና ይገባል።” መዝ ፴፫ ፥ ፩

7 months ago
በኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የፈረንሳይ ማርሴይ እና …

በኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የፈረንሳይ ማርሴይ እና ቱሎን ከተሞች ሊቀ ጳጳስ  ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ !

ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

+++

ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ እ.ኤ.አ በግንቦት 1933 በፈረንሳይ ተወለዱ። በግንቦት 5 ቀን 1974 በዋዲ ኤል-ናትሮን በሚገኘው የቅዱስ ቢሾይ ገዳም ሥርዓተ ምንኩስናን ፈጽመዋል።

ከዚያም እ.ኤ.አ ሰኔ 2 ቀን 1974 በኮሪ ኤጲስቆጶስ (ረዳት ጳጳስ) በመሆን ተሹሟል። እ.ኤ.አ ሰኔ 19 ቀን 1994 ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተሹመዋል፣ ከዚያም የፈረንሳይ ኮፕቶች ጳጳስ ሆነው ተመድበዋል። እ.ኤ.አ ሐምሌ 13፣ 2013 ጀምሮ በሀገረ ፈረንሳይ የማርሴይ እና የቱሎን ሊቀ ጳጳስ  ሆነው አገልግለዋል።

ብፁዕነታቸው ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ90 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

7 months ago
ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት
7 months, 1 week ago

የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት

https://eotc-gssu.org/a/ብሔር_ተኮር/

7 months, 1 week ago

ቤተ ክህነቱ ታሟል
ጎሣን መሠረት ያደረገው የሀገራችን ፖለቲካ ኢትዮጵያዊነት ዕሴቶችን በማፈራረስ ሀገር የቆመበትን መሠረት ለመናድ መዶሻውን ካነሣ ምእተ ዓመት ሊያስቆጥር የመጨረሻው ሩብ ክፍለ ዘመን ብቻ ቀርቶታል፡፡ በሀገረ ምሥረታው ሒደት ምትክ የለሽ ሚና የተጫወተችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥፋቱ ሰለባ የሆነችው ገና ከጅምሩ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን አሐቲነት አደጋ ላይ የወደቀበት እና በከፋ የፈተና ማዕበል እየተናጠች የምትገኝበት ዘመን ላይ መሆናችን ፀሐይ የሞቀው እውነት ነው፡፡
በኦሮምያ ክልል የሚገኙ ጥቂት የቤተ ክርስቲያኗ አገልጋዮች ፖለቲካውን ተገን አድርገው አሐቲነቷን በሚፈታተን መንገድ ክልላዊ ቤተ ክህነት በማቋቋም ውስጣዊ አንድነቷን ለመስበር ፈታኝ ዘመቻ አደረጉ፡፡ እነርሱን አርአያ ያደረጉ በትግራይ የሚገኙ ጥቂት አገልጋዮችም በቤተ ክርስቲያን ላይ የቀደመውን ተጨማሪ ፈተና ለመሆን የምእመናንን አንድነት ለመክፈል በመሞከራቸው ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዟቸዋል፡፡ መሠረቱን ዘውግ ያደረገው ፖለቲካ በትግራይ ክልል የሚገኙ አፈንጋጮችን አቅፎ ደግፎ ይዟል፡፡ ለገለልተኛ አካልን ጭምር በሚያሳዝን መልኩ መንግሥት መንግሥታዊ ሓላፊነቱን ቸል ብሎ በሕግ ዕውቅና ያላትን የሀገር አድባር፣ የነፃነት ፈር ቀዳጅ፣ የሥልጣኔ ማእከል የሆነችው ጥንታዊትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ከባድ ችግር ላይ እንድትወድቅ አድርጓል፡፡ ሕግ የማስከበር ሓላፊነት ያለበት ማእከላዊ መንግሥት መንፈሳዊ አባትነታቸውን በፖለቲካዊ እሳቤ ገድበው ምድራዊ ዘውገኝነትን የመረጡ ውጉዝ ጳጳሳት ከፖለቲካ አመራሩ ጋር በቅንጅት የሚያደርጉትን ለሀገር የሚተርፍ አፍራሽ ተግባር ቤተ ክርስቲያን ብቻዋን እንድትጋፈጥ ትቷታል፡፡ ይህ አእምሮ ላለው ታሪክ ታዛቢ ሁሉ በሚያሳፍር እና የሚያሳዝን ተግባር ነው፡፡
ውስጣዊው የቤተ ክርስቲያን ፈተና ሁሌም የተዳከመች ቤተ ክርስቲያንን የማየት ዓላማ አንግበው ለሚንቀሳቀሱት የውጭ ጠላቶች ምቹ መደላድል ፈጥሮላቸው ውሻ በቀደደው ዘው ብለው ገብተዋል፡፡ የትግራይን ቤተ ክህነት ለማዋለድ፣ አዋልደው ለማሳደግ ጎምበስ ቀና የሚሉ መናፍቃን ከመጋረጃው ጀርባ በዝተው የታዩት በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ ከመጀመሪያውም ፖለቲካውን እና ፖለቲከኞችን ተከልለው ይህን አጀንዳ በኦሮምያ ለሚገኘ ጥቂት አልጋዮች የሸጡት መናፍቃን ናቸው፡፡ እነዚህ ፀረ ቤተ ክርስቲያን ኃይሎች ጥቃታቸውን የከፈቱት በሰዓቱ መሥራት የሚገባንን እንዳንሠራ አሥሮ የያዘንን ቤተ ክህነታዊ ደዌ ተከልለው ነው፡፡ ይህም ቤተ ክህነቱ ለወንጌል አገልግሎት ድንዙዝ ለግለሰቦች ብልጽግና ደግሞ ንቁ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ለማስፈጸም ልፍስፍስ የግለሰቦችን ኪስ ለሚያደልብ ሥራ ፍጡን መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ነው፡፡ ለዚህ በሽታው በጊዜ መድኃኒት ካልተገኘለት ለወንጌል ሥምሪት እንዲያገለግል የተሠራው ቤተ ክህነታዊው መዋቅር ለወንጌል አገልግሎት መሰናክል ሆኖ ይቀጥላል፡፡
ቤተ ክርስቲያንን ከግራ ቀኝ የሚያዋክባትን ውጫዊና ውስጣዊ ማዕበል አሸንፋ አራራትን ፍለጋ በምታደርገው አድካሚ ጉዞ የቤተ ክርስቲያን መሪ የሆኑት ጳጳሳት የመሪነት ሚና፣ የአመራር ክህሎት ወሳኝ ነው። እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ከብዙ ምእተ ዓመታት በኋላ አሁንም የሚታወሱትና አብነት ተደርገው እንዲታወሱ ካደረጓቸው በርካታ ምክንያቶች አንዱ በመከራ ሰዓት ሕዝበ ክርስቲያኑን ለመታደግ በፈጸሙት አይረሴ መንፈሳዊ ተጋድሎ ነው። በዚህ ዘመን ግን መርከቧን በማዕበልና ወጀቡ መካከል አሳልፈው አራራት ላይ መልኅቋን እንድትጥል ለማድረግ ከልብ የሚተጉ አባቶች ቁጥር አንሶ ውጥንቅጡን አክፍቶታል፡፡ የምእምናንን አንድነት ለመጠበቅ መንፈሳዊ ሥልጣን የተሸከሙ ጥቂት የማይባሉ ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት የሚቀዝፉበት መቅዘፊያ በአድልዎና በወገተኝነት የተሠራ በመሆኑ መርከቧን ወደ ወደብ ሳይሆን ወደ ጥልቁ ለመውሰድ እየተፍጨረጨሩ ነው፡፡
ዛሬ ሁሉም በዘውግ መረብ ተጠልፎ ያለ አድልዎ ለመንጋው ሁሉ የሚራራ እረኛ ከንፍሮ ጥሬ ለማግኘት እንደ መድከም ተቆጥሯል፡፡ ቤተ ክህነቱ በዘውገኝነት በሽታ ከተጠቃ ቆየት ቢልም በዚህ ዘመን በሽታው የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በተለይ መንፈስ ቅዱስ ለመንጋው ሁሉ እንዲጠነቀቁ የሾማቸው ጳጳሳት በዚህ በሽታ መጠቃት አራራትን የማይደረስበት ተምኔታዊ ወደብ አድርጎታል፡፡ ይህን መሰል መታመም የምሥራቅ አውሮፓ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችም ታመውት ነበር፡፡
በኦቶማን ተጽዕኖ ሥር የነበሩ ከምሥራቅ ቤተ ክርስቲያን ወገን የሆኑት የባልካን ኦርቶዶክሳውያን ከቱርክ አገዛዝ ራሳቸውን ነጻ ለማውጣት ከፍ ያለ ብሔርተኝነት የተንፀባረቀበት ትግል አድርገው ነበር፡፡ እነዚህ ሕዝቦች በብሔር ተኮር ሃይማኖታዊ ስብከት ተፈትነው እንዳለፉ ታሪክ ይነግረናል፡፡ ሀገራቱ ያለፉበትን ተመሳሳይ ችግር ደብተራ በአማን ነጸረ ተኀሥሦ በተሰኘ መጽሐፋቸው በጨረፍታ ዳስሰውታል፡፡ በዳሰሳቸው ቤተ ክርስቲያንን በየብሔሩ መሸንሸን ኩላዊነቷን የሚጋፋ፣ ቤተ ክርስቲያንን በየብሔሩ ልክ የሚሠፋና የሚያጠብ እንደሆነ በማሥረጃ ይሞግታሉ፡፡ እንዲሁም ወንጌልን ሳይሆን ብሔርን መነሻ ያደረገ ሃይማኖታዊ ማንነት የመገንባት እንቅስቅሴ ቤተ ክርስቲያንን ከመሠረታዊው ተልእኮዋ የሚያናጥባት አደገኛ ነገር መኾኑን በመረዳት የምሥራቅ አውሮፓ ኦርቶዶክሶች መንገዱን በጉባኤ አውግዘው አካሔዳቸውን ማረማቸውን ደብተራው በመጽሐፋቸው ያስረዳሉ፡፡
በጎሳ ላይ የተመሠረተው ፖለቲካ ከፍ ባለ ዲሞክራሲያዊ ባህል በሌለበት ሀገር ውስጥ ሊተገብሩት የሚያስቸግር ነጽሮት እንደሆነ በርካታ ዓለም አቀፍ ልኂቃን በተደጋጋሚ ሲገልጹ ይደመጣሉ፡፡ በተለይ ደግሞ ዘር ቀለም ሳያግዳት ለዓለም ሁሉ የሞተውን የክርስቶስ ኢየሱስን ወንጌል ለሁሉም የማድረስ ሐዋርያዊ ተልእኮ ከተሸከመችው፣ ድንበር ተሻጋሪ ቤተ ክርስቲያን ባሕርይ ጋር ፍጹም አይስማማም፡፡ እንኳን በአንድ ብሔረሰብ በአንድ ሀገር ጥላ ሥር መገደብ ከኩላዊነት ባሕርይዋ ጋር ይጣላል፤ በብሔር መከፋፈሉ ከአሐቲነቷ ጋር ይጋጫል፤ ከማይሻር ቅድስናዋ ጋር አይሔድም፡፡ ይህን እውነት መቀበል ያልፈለጉ፣ ከክርስትናቸው ይልቅ በብሔር ተኮር ሃይማኖታዊ ስብከት ይገኛል ብለው ያሰቡት ሹመት ወይም ሌላ ምድራዊ ጥቅም ያማለላቸው አገልጋዮቿ በሞከሩት ስዒረ-ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያን ታወከች፡፡ አፅራረ ቤተ ክርስቲያን አጋጣሚውን ተጠቅመው በልጆቿ መካከል የመለያየትን አጥር በእሾህ ለማጠር እየተረባረቡ ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያን አሁንም እንደ ክርስቶስ እንደራሴነታቸው ለሰው ልጅ ሁሉ ሊኖራቸው የሚገባውን ወገንተኛነት ቸል ብለው በዘውገኝነት በሽታ ጥላ ሥር የተሰባሰቡ ጳጳሳትን ጉዳይ ፈር ማስያዝ ካልቻለች የመጭው ጊዜ ፈተና ከባድ ይሆንባታል፡፡ ይህን የማድረግ ሓላፊነት ደግሞ የሲኖደሱ ብቻ አይደለም፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሁላችን ናትና የእያንዳንዱ ምእመን ሱታፌ ወሳኝ ነው፡፡ ከዛሬ ብንዘገይም ከነገ ለመቅደም እንዲቻል የምእመናን ሱታፌ በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ወደ ነበረበት መንበር መመለስ አለበት፡፡ ምእመናንን በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እና በወሳኝ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ከነበራቸውን ሕጋዊ፣ ጥንታዊ እና ትውፊታዊ የውሳኔ ሰጭነት ሚና አራቁቶ ቤተ ክርስቲያንን በዘውገኝነት ለታመሙ ጳጳሳት አሳልፎ መስጠት በመጭው ዘመን ተልእኮዋ ላይ መሰናክል ማስቀመጥ ነው፡፡ ለዚህ ነው የለውጥ ጅማሬ መሆን የሚገባው ለምእመናን ሱታፌ ዕድል ፈንታ የሚነፍገውን በቅርቡ “የተሻሻለውን” ሕገ ቤተ ክርስቲያን በመከለስ ነው፡፡

7 months, 1 week ago

የአዲስ አበባ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በ2015 ዓ.ም በ4 በ6ና በ10ኛ ክፍል ያስተማራቸውን ከ4500 በላይ ተማሪዎች አስመረቀ

የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በ2015 ዓ.ም በ4 በ6 እና በ10ኛ ክፍል በተዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት ያስተማራቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም እና ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ካቴድራል አስመረቀ። በመርሐ ግብሩ ላይም ብጹዕ አቡነ አብርሃም የባህርዳር ሀገረስብከት ሊቀጳጳስና የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ የሰሜን አሜሪካ የኒውዮርክ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብጹዕ አቡነ ቀለሜንጦስ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትና የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ሊቃነ ጳጳሳት የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች የጠቅላይ ቤተክህነት የየመሪያው ኃላፊዎች ፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና የክፍለ ከተማ ቤተክህነት  የየክፍሉ ኃላፊዎች የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አመራሮች ተመራቂ ተማሪዎችና  ወላጆቻቸው በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።

የምርቃት መርሐ ግብሩ ልጅህን በሚሄድበት መንገድ ምራው በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በመጀመሪያ በብጹዕ አቡነ ቀለሜንጦስ መሪነት በጸሎተ ወንጌል ተከፍቷል። በመቀጠልም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ሰብሳቢ ላዕከ ኄራን መንክር ግርማ የመግቢያ ንግግር የተደረገ ሲሆን በንግግራቸውም በአዲስ አበባ ከሚገኙ 250 አድባራት 157 የሚሆኑት በ2015 ዓ.ም ሥርዓተ ትምህርቱን መተግበራቸውንና በዛሬው ዕለት ግን 77 የሚሆኑ አድባራት በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ እርከኖች ተማሪዎቻቸውን ማስመዘናቸውን ገልጸዋል። በዚህም ከተፈተኑት 4500 ተማሪዎች ውስጥ 4030 የሚሆኑት ወደ ቀጣይ ክፍል መዘዋወራቸውን አብስረዋል። በ2016 ዓ.ም በ205 ደብራት 72,000 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንዲማሩ እንደ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የዕለቱን ወንጌል የሰንበት ትምህርት ቤት ፍሬ የሆኑት ዲያቆን ህሊና በለጠ "እኔ የሳሮን ጽጌሬዳ የቆላም አበባ ነኝ" መኃ 2:1 በሚል ቃል መነሻነት ቃለ እግዚአብሔር አስተላልፈዋል። በመቀጠልም ብጹዕ አቡነ አብርሃም ለተመራቂ ተማሪዎችና ለወላጆች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም "የሳንቲም ውርስ ልጆችን ያጋጫል የሃይማኖት የእውቀት የምግባር ውርስ ግን እስከ መጨረሻው ለወላጆች የሚጠቅሙ ሀገርን ሀገር የሚያሰኙ  የነገዋን ቤተክርስቲያንን የሚገነቡ ተስፋዎች ያደርጋችዋል። ስለዚህም ቤተክርስቲያንን እንጠብቃት እንታዘዛት አገልግሎታችሁ ከጥቅማ ጥቅም የተነሳ ሳይሆን በነጻ የምታገለግሉበት ነውና ብዙ ጸጋና ሀብትን ይሰጣችኋል በዚህም ቤተክርስቲያናችሁ እጅግ ትደሰታለች።" ሲሉ አባታዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተዋል።

በመጨረሻም የሽልማትና የምስጋና መርሐግብር የተካሄደ ሲሆን ከ77 አድባራት በብዙ የተማሪዎች ቁጥር ያስፈተኑንና ከተፈተኑት ውስጥ የደረጃ ተማሪዎች የነበሩትን ከብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት እጅ የማበረታቻ ሽልማት ተሰቷቸዋል። በብጹዕ አቡነ ቀለሜንጦስ የመጨረሻ አባታዊ ቡራኬ እና መልእክት የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።

(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት)

7 months, 1 week ago
**“በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት …

“በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤” ሮሜ ፲፪፥፲፪

የአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት
ወርሃዊ የጸሎት መርሐግብር ረቡዕ መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ማታ 11:30 ላይ በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ ይከናወናል።

ሁላችሁም የሰንበት ት/ቤታችን አባላት በጸሎት መርሐግብሩ በመገኘት ስለሀገራችን፣ ስለቅድስት ቤተክርስቲያን፣ ስለሰንበት ት/ቤታችን ስለአገልግሎታችን ሁሉ በጋራ እንድንጸልይ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በመላው አለም ያላችሁ የሰንበት ት/ቤታችን አባላት ባላችሁበት በጸሎት አብራችሁን እንድትሆኑ እና ሀገራችንን፣ ቅድስት ቤተክርስቲያንን፣ ሰንበት ት/ቤታችሁን እንድታስቡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የጸሎት መርሐ ግብሩ በየወሩ ከቀን 23 በኋላ ባለው ረቡዕ በቋሚነት ይካሄዳል።

ለጸሎት ሲመጡ  መዝሙረ ዳዊትና ውዳሴ ማርያም ይዘው ይምጡ

የሰንበት ትምህርት ቤቱ ጽ/ቤት
 
ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ

▭▭▭  ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝  ▭▭▭
🔎ፌስቡክ ገፅ https://www.facebook.com/finotebrhans
@finote brhan
🔎ዩቲዩብ ገፅ፡ https://youtube.com/channel/
@finote brhan
🔎 ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@
@finotebrhan
🔎ቴሌግራም ገፅ፦
ትምህርትና መረጃዎች፡ https://t.me/finottebirhan

@finotebrhanl

7 months, 1 week ago
***✨***ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው በሸመገለም ጊዜ …

ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።''
                        መጽሐፈ ምሳሌ 22÷6

ልጆችዎን ወደ ሰንበት ት/ቤት ይላኩ

ቤተክርስትያን ዘላለማዊ የሆነውን የአምላክን ቃል ለተተኪው ትውልድ ከምታስተላልፍባቸው መንፈሳዊ ተቋማት አንዱ ሕፃናትን፣ ወጣቶችን እና ጎልማሳዎችን በሕብረት ሆነው የሚማሩበት የቤተክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ትውፊትን እና  ስርዓትን አውቀው ጠብቀው የሚያቆዩበት ለቀጣይም ትውልድ የሚያስተላልፉበት ለቤተክርስትያን የሚጠቅም ትውልድ የሚፈራበት “በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተተኩልሽ” የሚለው የቅዱስ ዳዊት የትንቢት ቃል የሚፈፀምበት መንፈሳዊ ተቋሟ አንዱ የሰንበት ትምህርት ቤት ነው፡፡ 

በመጽሐፍ ቅዱስ ልጆችን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ልኮ ማስተማር እንደሚገባ ስርዓቱም እንደነበር በብሉይ ኪዳንም በሐዲስ ኪዳንም ሰፍሮ የሚገኝ ሲሆን ይህም በዘመናችን ላለቸው ቤተክርስቲያን የሕጻናት፣ ወጣቶች እና ጎልማሶች ማስተማሪያ ለሆነችው ሰንበት ትምህርት ቤት መነሻ የሆነ እና መሠረትነቷም መፅሐፍ ቅዱሳዊ እንደሆነ ማረጋገጫ ነው።

ልጆቻችንን ወደ ሰንበት ት/ቤት በመላክ የነገውን ማንነታቸውን ዛሬ እንስራ

የአቃቂ መ/ሕ/መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት የህጻናት እና ማዕከላውያን ክፍል
  ▭▭▭▭  ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝  ▭▭▭▭
🔎ዩቲዩብ ገፅ፡ https://youtube.com/channel/
@finote brhan
🔎 ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@
@finotebrhan
🔎ቴሌግራም ገፅ፦
ትምህርትና መረጃዎች፡ t.me/@finotebrhan
🔎 ፌስቡክ ገፅ፡ fb.me/@finotebrhan

@finotebrhan

7 months, 1 week ago

#Result

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ማክሰኞ በ29/01/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ ብሏል።

ተፈታኞች የሚከተሉትን 3 አማራጭ አድራሻዎችን #ብቻ በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ሲል ገልጿል።

👉 በዌብ ሳይት፡- eaes.et
👉 በአጭር የጽሁፍ መልዕክት፡- 6284
👉 ቴሌግራም አድራሻ፡- @eaesbot

አገልግሎቱ ከላይ ከተገለጹት የውጤት መግለጫ አማራጮች ውጪ ሌላ የውጤት መግለጫ መንገዶች የሌሉ መሆኑን አሳውቋል።

ተማሪዎች በማመሳሰል " ውጤት እንገልጻለን " ከሚሉ ከማንኛውም አጭበርባሪዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት ተላልፏል።

በተጨማሪ ተቋሙ ውጤት ለማሳየት ምንም ክፍያ የማይጠይቅ መሆኑን አስገንዝቧል።

እንዴት ውጤት ልመልከት ?

በዌብ ሳይት ለማየት ፦
1. eaes.et ብለው ብሮውዘር ላይ ይጻፉ
2. በመቀጠልም በሚመጣው ገጽ ላይ የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) እና የመጀመሪያ ስም ይጻፉ
3. Check Result የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማግኘት ይችላሉ።

በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ፦

  1. 6284 የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) ብቻ ጽፎ አንዴ ብቻ በመላክ መልስ እስኪያገኙ ይጠብቁ።

በቴሌግራም ቦት ፦

  1. @eaesbot ይፈልጉ

  2. የሚመጡ አማራጮችን በመከተል የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) ያስገቡ በመቀጠልም መልስ እስኪያገኙ ይጠብቁ፡፡

7 months, 3 weeks ago

መስከረም ፳፩

**እንኳን ለብዙኃን ማርያም ለግሸን ደብረ ከርቤ መስቀሉ ላረፈበትና ለከበረበት በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!!

የበረከት በዓል ይሁንልን**!!!

ብዙኃን ማርያም
በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው።

ጉባዔ ኒቅያ
በ፫፻፳፭ ዓ.ም አርዮስ የሚባል መናፍቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አርዮስ ክህደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአርዮስ ክህደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአርዮስ ክህደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡

በዚህም መሠረት ከሚያዝያ ፳፩ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፩ ቀን ድረስ ፳፫፻፵፰ (ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ዐርባ ስምንት) ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡

ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን "ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ" ባላቸው ጊዜም ከ፳፫፻፵፰ቱ (2348) መካከል ፫፻፲፰ (318) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው" ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም "ሃይማኖት እንደ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ይኹን" ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት ፫፻፲፰ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው /ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡

፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት "ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን" የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት "ብዙኃን ማርያም" እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡

ዕፀ መስቀል/ግሸን ማርያም
በሌላ በኩል መስከረም ፳፩ ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤

ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው "የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል" አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር "የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ" የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ "ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት" ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡

ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡ መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡

መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ፲፬፻፵፮ (1446) ዓ.ም የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡

ከዚህ በኋላ ንጉሡ ‹‹መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!›› ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም ፳፩ ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ኀጢአታቸውን ለካህን ተናዘው፣ ንስሐ ገብተው በዚህ ዕለት ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ በመሔድ የሚጸልዩና የሚማጸኑ ምእመናን ኹሉ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የምሕረት ቃል ኪዳን እንደሚያገኙም ጤፉት በተባለው መጽሐፍ ተጠቅሷል፡፡ መጽሐፉ እንደሚለው በሃገራችን ያለው ግማደ መስቀሉ (የቀኝ እጁ) ብቻ ሳይሆን ሙሉው ዕፀ መስቀል ነው።

የእመቤታችን ማርያም ምልጃና ጥበቃ አይለየን!

©ማኅበረ ቅዱሳን

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 2 days ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago