A place to learn English easily.
Owner - @Samson_G
Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian
Last updated 4 months, 1 week ago
NGO, የመንግስት እና የግል ድርጅቶች የስራ ማስታወቂያ እና ነፃ የትምህርት እድሎችን ያገኛሉ ቤተሰበ ይሁኑ ሌሎችንም ይጋብዙ
ለማስታወቂያ @Human133 ላይ አናግሩን
We need promoters
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12
Last updated 2 months, 4 weeks ago
ሰሁር ስበላ ስለሚያመኝ ሰሁር አልበላም አትበል!! በሚስማማህ መልኩ ሰሁር ብላ!።
—————
አንዳንድ ወንድምና አህቶች "ሰሁር ስበላ ስለሚያመኝ ሰሁር አልበላም**" ሲሉ ይደመጣሉ፣ እርግጥ ነው፣ አንድ ሰው ሚታመምበትን ምክንያት አውቆ አመጋገቡ ላይ ማሻሻያ ካላደረገ ሊታመም ይችላል። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ሰዎች ከተመገቡ በኋላ ሊያቅራቸውና ጨጓራቸውን ሊያሳምማቸው የሚችለው በዋናነት በሁለት ምክንያት ነው።
1ኛ, እንደተመገቡ ወዲያው መተኛት። ይህ ለጨጓራ በሽታና ለአለስፈላጊ ክብደት (ውፍረት) መጨመር ይዳርጋል። ይህ በየትኛውም ጊዜ ከባድ የሆነ አደጋ ነው። የጤና ባለ ሞያዎች እንደተመገቡ መተኛትን በጥብቅ ይከለክላሉ ያስጠነቅቃሉ!። በመሆኑም አንድ ሰው ሰሁር ከበላ በኋላ ማረፍ (መተኛት) ከፈለገ ቢያንስ ከ30 ደቂቃ በላይ መቆየት አለበት። አንዳንድ ሰዎች እንደበሉ አዛን ሳይጠብቁና ሱብሂያቸውንም ሳይሰግዱ ወዲያው ይተኛሉ፣ ይህ ትልቅ አደጋ ነው። አንድም የሱብሂ ጊዜ ያመልጣቸዋል፣ በተለይ ወንዶች ከሆኑ ደግሞ መስጂድ ሄደው በጀመዓ መስገድ ይጠበቅባቸዋልና ይህን ግዴታም ያስመልጣሉ።
2ኛ, ከልክ በላይ መመገብ። ከመጠን በላይ መብላት ጨጓራን አጨናንቆ ለመፍጨት እንዲቸገር ያደርገዋል። ከመጠን በላይ መብላት በየትኛውም ጊዜ አይፈቀድም!። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አንድ ሰው ሲመገብ ሆዱን ለ3 ነገር መካፈል እንዳለበት አስቀምጠዋል፣ 1,ለምግብ 2,ለሚጠጣ ነገር 3, ለመተንፈስ። ከልክ በላይ በጣም ጠግቦ ከበላ ጨጓራው ይጨናነቃል፣ ይህ ደግሞ ጤናው ላይ ከሚያሳድረው ተፅእኖ ባሻገር ዒባዳ ለማድረግም ነፃነት አይሰጠውም።
3ኛ, የተለያየ አይነት ምግብ በአንድ ጀንበር መብላት። ይህ አንድ ሰው ከጨጓራው የሚስማማው ከሆነ ከሁሉም አይነት በትንሽ ትንሹ መብላት ብዙም አደጋ ላይኖረው ይችላል። ነገር ግን የትኛው ምግብ እንደማይስማማው ማወቅ ካልቻለ ይቸገራልና በተቻለ መጠን ቀለል ባለ መልኩ ከሚስማማው አይነት አንዱን መመገብ ነው።
አንድ ሰው ከላይ የተጠቀሱ ጥንቃቄዎችን አድርጎ የማቃርና የህመም ስሜት የማይወገድለት ከሆነ ሌሎች አማራጮችም አሉ። አንድ ሰው ሰሁርን ግዴታ እስኪጠገብ ብዙ መመገብ አይጠበቅበትም። ዋናው ነገር በሰሁር በረካ ስላለበት ተፈላጊውም በረካው ነውና ቀለል ያለ ነገር መጠቀም ይችላል።
ከአነስ ኢብኑ ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- “ሰሁርን ተመገቡ በሰሁር በረካ አለ!።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
ዋናውና ተፈላጊው ነገር በረካውን ማግኘት ነውና ተምርና ውኃ… መሰል ቀለል ያሉ ነገሮችን በመጠቀም በረካውን ማግኘት ነው።
ከአቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- “የአማኝ ምርጡ ሰሁር ማለት ተምር ነው።” [አልባኒ፣ አቢዳውድ 2345 ላይ ሶሂህ ብለውታል።]
ተምር ያላገኘ ሰው በውሃም ቢሆን እንኳን ሰሁር ማድረግ አለበት።
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- “ሰሁርን መመገቡ በረካ ነውና አትተውት!፣ አንዳችሁ አንዴ የሚጎነጯትን ውሃ ቢሆን እንኳን በመጎኝጨት (ይተግብረው)፣ አላህና መላኢካዎች ሰሁር በሚጠቀሙ ሰዎች ላይ ሶለዋት ያወርዳሉ።” [በሶሂህ አት-ተርጊብ 1070 ላይ አልባኒ ሀሰን ብለውታል]
ከነቢዩ ባልደረቦች የሆነ አንድ ሰው ወደ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ቤት ሰሁር እየበሉ ገባ፣ ነቢዩም እንዲህ አሉ:- “እርሷ በረካ ናት፣ አላህ እርሷን ሰጥቷችኋልና እንዳትተውዋት!።” [ነሳኢይ 2162 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]
ሰሁርን መብላት ከከሃዲዎች ፆም እና ከእኛው ፆም አንዱ መለያ ነው። ሙስሊሞች ሆይ! ሰሁርን በመብላት ፆማችሁን ከከሃዲዎች ፆም ከመመሳሰል ለዩት!።
ከዐምር ኢብኑል ዓስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- “በእኛ ፆምና በመፅሃፉ ባለ ቤቶች ፆም መካከል ያለው መለያ ሰሁር መብላት ነው።” [ሙስሊም 1096 ላይ ዘግበውታል]
ከጠቀስኳቸው ሀዲሶች ውጭ ሌላ ሰሁር ላይ የሚያበረታቱና የሰሁርን ደረጃና ትሩፋት የሚገልፁ በርካታ ሀዲሶች መጥተዋልና ለሰሁር ልዩ ትኩረት እንስጥ!!
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! "ተሰሀሩ ፈ ኢንነ ፊ ሰሁሪ በረከ!፣ ሰሁርን ተመገቡ በሰሁር በረካ አለ!።"
✍🏻ኢብን ሽፋ: (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ**https://telegram.me/IbnShifahttps://telegram.me/IbnShifa
✅ነገ በአላህ ፍቃድ ከሱብሂ ቡሃላ የሸርሁ ሉምዓቱል ኢዕቲቃድ ኪታብ የሚቀጥል ይሆናል❕
https://t.me/hutemariwochchannel
ሀቅን ያዝ ፣ለሀቅ ወግን፣እውነትን ተናገር ።ግን ሁሉም ሰው ካላመነኝ ብለህ አትጨነቅ፣ሁሉም ሰው ካልተቀበለኝ ብለህ አታስብ❗️ውሸታም ነው እያሉ ቢያወሩም አትጨናነቅ ምክኒያቱም ነብያችንም عليه الصلاة والسلام ከአላህ የመጣውን ወህይ እየተናገሩ ሰወች ውሸታም ሲሏቸው ነበር።https://t.me/hutemariwochchannel
ተጨማሪ ፕሮግራም ነገ አድስ ደርስ ይጀመራል።
የሚጀመረውም ኪታብ القواعد الفقهية የሙሀመድ ሷሊህ አልዑሰይሚን ሲሆን ዘወትር ሰኞ እና ማክሰኞ ከመግሪብ–ኢሻእ ይቀራል።
? ቂርአቱም የሚሰጠው
በቲቲሲ መድረሳ ነው።
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ለእውቀት ፈላጊወች እንኳን ደስስስ አላቹህ እያልን ይህንን በላጭ የሆነ እውቀት፣የዱንያም የአኼራም የደስታ እና የስኬት ቁልፍ የሆነውን ሸሪዓዊእወቀት እንዲትሳተፉ ስንል ለመጠቆም እንወዳለን።
? ሸሪዓዊ እውቀትን መፈለግ በሁሉም ሙስሊም ላይ ግደታ ነው።
لما روى ابن ماجه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال: طلب العلم فريضة على كل مسلم. وهذا الحديث صححه الألباني
?ስለዚህ በተቻለን መጠን ሠዓታችንን በአግባቡ በመጠቀም ከዚህ እውቀት ድርሻ ሊኖረን ይገባል❗️
?ሌሎችም ከመግሪብ–ዒሻእ የተጀመሩ ደርሶች ስላሉ እነሱንም መካፈል
ትችላላቹህ።
1⃣ ሽርሁ አሱ–ና የበርበሀሪይ የፈውዛን ሸርህ ( ቲቲሲ መድረሳ)
2⃣ ዐቂደቱ አሰ–ለፍ… የሷቡኒይ (ዳቶ)…
?ሌሎችም ስለሚኖሩ ወደፊት እናሳውቃለን።
ሀሳብ &ጥያቄ ካሎወት በኮሜንት ያሳውቁ!
https://t.me/hutemariwochchannel
ኮንፈረንሱ የሚካሄድበት ቀን መተላለፉን ስለማሳወቅ
ጥቅም 3 አዲስ አበባ ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ የነበረው ታላቁ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ በፕሮግራም መደራረብ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።
ኮንፈረንሱ የሚካሄድበትን ጊዜ ወደ ፊት የምንገልፅ መሆኑን ከይቅርታ ጋር እናስታውቃለን።
የኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር
كن على بصيرة
? ሰበር የምስራች
የታላቁ ኮንፈረንስ ቀንና ቦታ
በኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር የተዘጋጀውና በአይነቱ ልዩ የሆነው ታላቁ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ፣ አዲስ አበባ ላይ ይካሄዳል።
ቀን:- ጥቅምት 3/2017
ቦታ:- በሚሊኒየም አዳራሽ (ቦሌ ኤርፖርት አጠገብ)
የኮንፈረንሱ መሪ ሀሳብ:-
ዲናችንን ማወቅ፣ መተግበርና ማስተማር
የመግቢያ ትኬትዎን ቶሎ ከእጅዎ ያስገቡ!
የኢትዮጵያ አህለሱና ኢስላማዊ ማህበር
كن على بصيرة
#አዲስ_መፅሐፍ
? ተለቀቀ
? «مَتَى يَخْرُجُ الرَّجُلُ مِنَ السَّلَفِيَّةِ؟»
? ❝አንድ ሰው ከሰለፍያህ የሚወጣው መቼ ነው?❞ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ? كَتَبَهُ الشَّيْخ أَبُو طَلْحَةَ أَبُو ذَرّ بْنُ حَسَنِ بْنِ إِمَامٍ الْإِتْيُوْبِي الْوَلَّوِي عفا الله عَنْهُ وَعَنْ وَالِدَيْهِ أَمِينِ
? ዝግጅት፦ የተከበሩ ሸይኻችን ሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን ኢማም አቡ ጦልሃ አል`ወሎውይ አላህ ይጠብቃቸው!
? ለማንኛውም ጥቆማ ➴➷➴
https://t.me/AbuImranAselefybot
➚➶➹ ብቅ ይበሉ
? የኪታቡ pdf ↙️↙️↙️
➷➴➷➴➷➴➷
https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha/11022
? ወንድማዊ ምክር
በአንድ የዋትሳፕ ወይም ሌላ ግሩፕ ላይ ለምትሳተፉ ወንድና ሴት ሙእሚኖች ። የዚህ አይነቱ በአንድ ግሩፕ ላይ መሰባሰብ በጣም አስፈላጊ ለሆነ ሁኔታ ነው ። እሱም በሚከተለው መልኩ ከሆነ ነው :–
-- ስለ ዲናዊ ጉዳይ ለመነጋገር ።
-- ከዲናዊ ጉዳይ ውጪ አላስፈላጊ የሆኑ ወሬዎች ከሌሉ ።
-- ሴቶች ሃሳባቸው አጠር ባለ መልኩ ማስተላለፍ ከተቻለ ሴት መሆናቸው እንዳይታወቅ ቢያደርጉ ይመረጣል ።
-- በየ ሀሳቡ እየገቡ ታዕሊቅ አለማድረግ ።
-- በግል ወይም በውስጥ መስመር አለ መፃፃፍ ። ለሸሪዓዊ ጉዳይ ከሆነ የሚፃፈው ነገር ማንም ሰው ሊያየው የሚችል ሆኖ ምንም አይነት ወደ ሌላ የሚወስድ ነገር የሌለ ከሆነ ።
-- ምንም አይነት የፈገግታ ምልክት ወይም ሌላ አይነት ተቃራኒ ፆታን የሚስብ ነገር አለመጠቀም ።
-- የሳቅ ምልክት የሆኑ ፊደሎችን አለመላክ ።
-- በምንም መልኩ በቅላፄ ወይም በለሰለሰ ድምፅ አለ ማናገር ።
-- በተሳትፎ ላይ የወንዶችን እይታ ለመሳብ የሚደረግ ነገር እንዳይኖር ማድረግ ።
እነዚህና የመሳሰሉትን ገደቦች ተጠብቆ ነው መሆን ያለበት ።
ከመሆኑም ጋር በጣም የተመረጠውና የሚወደደው ሴቶች በሴቶች ግሩፕ ወንዶችም በወንዶች ግሩፕ ለብቻ ብቻ መሆኑ ነው ።
በአሁኑ ጊዜ ለቁርኣን ተብለው የሚከፈቱ ግሩፖች የፈሳድ ምንጭ እየሆኑ እንደሆነ ብዙ እህቶች እየተናገሩ ነው ። ሴቶች ቁርኣን መቅራት ያለባቸው በሴቶች ነው ። ምክንያቱም በቁርኣን ድምፅን ማሳመር አስፈላጊ ስለሆነ ። አንዲት ሴት ለአጅ ነብይ ወንድ ድምፇን እያሳመረች መቅራት አይፈቀድላትም ። የሴት ልጅ ድምፅ አውራ ነው የሚሉ ዑለሞች እንዳሉ የሚታወቅ ነው ። በዚህ ላይ ቅላፄና ማሳመር ሲጨመር የሚመጣውን ፊትና ማሰብ አይከብድም ።
የሚገርመው የቁርኣን ግሩፕ ተብሎ ወንድና ሴት መሰብሰቡ ነው ። የዚህኛው ፊትና በጣም የከፋ ነው የሚሆነው ። እህቶችም እያማረሩ ያሉት ለቁርኣን ተብሎ ተከፍቶ በውስጥ መስመር እያስቸገሩን ለመቅራት አልቻልንም እያሉ ነው ።
ይህ ጉዳይ በጣም ለሱና የቀረቡ ጠንካራ የሚባሉ እህትና ወንድሞች የተፈተኑበት ጉዳይ ነው ። በመሆኑም እህቶች አላህን ፈርታችሁ ከእንደዚህ አይነት ግሩፕ ውጡ ። የዚህ አይነት ግሩፕ የምትከፍቱ ወንድሞች ከአህን ፍሩ ከማለት ውጪ የሚባል ነገር የለም ።
ንፁህ የሆነው ሸሪዓ የመጣው ወደ ፊትና ( መፍሰዳ ) የሚያደርሱ መንገዶችን ለመዝጋት ነው ።
እኔ አልፈተንም የሚል የተፈተነ ሰው ብቻ ነው ።
ስለዚህ ይህንን ጉዳይ በቀላሉ ማየት በራስ ዲን ላይ መጫወት መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል ።
ለደርስና ለሙሀደራ የሱና ወንድሞች ቻናሎች ስላሉ በግሩፕ አንድ ላይ ለመሆን የሚያስገድድ ነገር መኖሩ በደንብ ሊታይ የሚገባው ጉዳይ ነው ።
አላህ መልካሙን ሰምተው ከሚከተሉት ያድርገን
A place to learn English easily.
Owner - @Samson_G
Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian
Last updated 4 months, 1 week ago
NGO, የመንግስት እና የግል ድርጅቶች የስራ ማስታወቂያ እና ነፃ የትምህርት እድሎችን ያገኛሉ ቤተሰበ ይሁኑ ሌሎችንም ይጋብዙ
ለማስታወቂያ @Human133 ላይ አናግሩን
We need promoters
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12
Last updated 2 months, 4 weeks ago