Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 6 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 month ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 weeks ago
ይመጣል የተባለው ምናባዊው ንጉሥ "ቴ "
..
ከቅርብ ግዜ ወዲህ በብዛት እየሰማናቸው ካሉ የቆረፈዱ የምኞት ተረቶች መካከል
- ንጉሥ "ቴ" የተባለ ኢትዮጵያን የሚገዛ ንጉሥ ይነግሣል
- ኢትዮጵያ የዓለም ገዥ ትሆናለች
-ሁሉም ነገር በቁጥጥሩ ስር ይሆናል
- የዓለም መንግስታት በሙሉ ይታዘዙታል
- ያለ ንጉሡ ፈቃድና ትዕዛዝ ዓለም ላይ ሚደረግ አንዳች ነገር የለም እና የመሳሰሉ የፈጠራ ተረቶችን መስማት የተለመደ ሆኗል።
.
ለዚህ ተረት አስረጅ ሆኖ የሚቀርበው ገድለ ፊቅጦር ፣ ራእየ ሳቤላ ፣ የማቴዎስ ወንጌል 24 ፣ 14 አንድምታ ፣ ራእየ ሲኖዳ እና ድርሳነ ዑራኤል ይገኙበታል። የድርሳነ ዑራኤል ትንቢት እንዲህ ይላል፦
.
« በኢትዮጵያ ሰዎች በአገራቸው ዘመን አቈጣጠር ዓለም በተፈጠረ በሰባት ሺ ሁለት መቶ ዘጠና ስምንት ዓመት በሰኔ ፲፯ ቀን በወንጌላዊው በሉቃስ ዘመን በዓለም ሁሉ ከሰማይ እንደ ብላጊ ዝናም አመድ ይዘንማል »
(ድርሳነ ዑራኤል ዘጥቅምት ገጽ 328 ቁጥር 31)
.
እንደ ቤተ ክርስቲያን የጊዜ አቆጣጠር ከአዳም እስከ ኢየሱስ መወለድ ያለው ዘመን 5500 ሲሆን ከልደቱ እስከ አሁን እስካለንበት የኛ የኢትዮጵያዊያን ጊዜ ሲቆጠር 2013 በአጠቃላይ 7513 ይሆናል። ድርሳነ ዑራኤል በዓለም ሁሉ ላይ ከሰማይ አመድ ይዘንባል ያለን ዓለም በተፈጠረ በ7298 ወይንም በኛ ዘመን አቆጣጠር 1798 ዓ.ል ማለትም ከዛሬ 215 ዓመት በፊት ነበር ማለት ነው። ሆኖም ግን ምንም የዘነበ አመድ የለም። ስለዚህ የድርሳነ ዑራኤል የተረት ትንቢት ውሃ በላው ማለት ነው ።
.
«አመድ ከዘነመ ከአራት ዓመት በኋላ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስማዕት የሆነ በፊቅጦር በገድሉ መጽሐፍ እንደተነገረው የስሙ ምልክት «ቴ » ተብሎ የተመለከተው ይነግሣል ከወንጌላዊው ማርቆስ ወንበር ተሹሞ ከወጣ ጳጳሳቸው ጋር ቅዱሳን የሆነ የኢትዮጵያ ካህናት ይወጡና በግብጽ ምድር በአባ ሲኖዳ ደብር ውስጥ የሃይማኖት ጉባኤ ያደርጋል » (ድርሳነ ዑራኤል ዘጥቅምት ገጽ 330 ቁጥር 44_45)
.
ሲቀጥል እንደ ድርሳነ ዑራኤል ዘገባ መሠረት የስሙ ምልክት « ቴ » ተብሎ የተመለከተው ንጉሥ ይነግሣል የተባለው አመድ ከዘነመ ከአራት ዓመት በኃላ ነበር። ይህ ማለት ከዛሬ 211 ዓመት በፊት 1794 ነበር በአገራችን የነገሥታት ታሪክ ከዛሬ 211 ዓመት በፊት የዘመነ መሳፍንት ጊዜ ነበር። ጉልበት ኖሮት ማሸነፍ የቻለ ከነጋሲ ዘሮች መርጦ ለወጉ ንጉሥ ብሎ ሾሞ ያስቀምጣል እነዚህ ነገሥታቶች ንጉሥ ተብለው ከመጠራትና ግንብ ከመጠበቅ ውጭ በራሳቸው ሊወስኑ ሚችሉት አንዳች ነገር አልነበረም። በዚህ ጊዜ ስሙ በቴ የሚጀምር ንጉሥም በጭራሽ አልነገሠም።
.
እዚሁ ድርሳን ገጽ 330 ላይ « ከወንጌላዊው ማርቆስ ወንበር ተሹሞ ከወጣ ጳጳሳቸው ጋር ቅዱሳን የሆነ የኢትዮጵያ ካህናት ይወጡና በግብጽ ምድር በአባ ሲኖዳ ደብር ውስጥ የሃይማኖት ጉባኤ ያደርጋል » ይላል። እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ተሹሞ ይመጣላት የነበረው ከማርቆስ ወንበር ( ከግብጽ ) ነበር በዚህም ለ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ዓመታት ያህል ቤተ ክርስቲያኗ በግብጽ ቅኝ ግዛት ስር ነበረች። ምክኒያቱም ፍትሐ ነገሥት « የኢትዮጵያ ሰዎች ከዐዋቂዎቻቸው ወገን በራሳቸው ፈቃድ ሊቀ ጳጳሳትን ለራሳቸው አይሹሙ » ብሎ ስለከለከለ ነው (ፍትሐ ነገስት ገፅ 30 ቁጥር 50 )። አሁን ላይ ግን ይህ ሐሰተኛ ቀኖና በመሆኑ ተወግዶ ኢትዮጵያዊያን በራሳቸው ፈቃድ ሊቀ ጳጳሳትን መሾም ከጀመሩ ከ50 ዓመት በላይ ተቆጥሯል
.
ታዲያ ጳጳሳት ከግብጽ ሳይሆን ከራሳችን ከኢትዮጵያዊያን መሾም ከተጀመረ በኃላ ይመጣል የተባለው ንጉሡ «ቴ» በምን ሒሳብ ነው ከግብጽ ተሹሞ ከሚወጣ ጳጳስ ጋር የሃይማኖት ጉባኤ ያደርጋል የሚለን? ካሁን በኃላስ ከግብጽ የሚሾም ጳጳስ አለ?
.
? ሲጠቃለል
.
1/ ትንቢቱ ይፈጸማል የተባለው ከዛሬ 200 ዓመት በፊት ነበር ነገር ግን ምንም የተፈጠረ ነገር የለም።
2/ ጊዜውም ኢትዮጵያ የራሷን ጳጳሳት የምትሾምበት ጊዜ እንጅ እንደድሮው ከግብጽ ጳጳስ ተቀብቶ የሚላክላት ጊዜ አይደለምና ከትንቢቱ ጋር ሆድና ጀርባ ነው።
▣ ይህን ያረጀ ተረት ተሸክሞ ዛሬም ድረስ "ይመጣል" እያሉ ማላዘን ያውም ማኅበር ሳይቀር አቋቁሞ አስከመትጋት የሚያደርስ ልፋት ተገቢ አይደለም። ይመጣል የተባለው ንጉሥ «ቴ» እውነት የሌለው ተራ ቅዥት መሆኑን በግልፅ መረዳት ያስፈልጋል።
እውነተኛው ኦርቶዶክሳዊ ፊት
ጠላትህ ውደድ ፣ ቀኝህን ለመታህ ግራህን ስጥ የሚሉት ትምህርቶች ተራ መደለያ የቃላት ጫወታወች ናቸው ከሌሎች ጋር እንዴት መኖር አለብን እውነቱን እነ አባይ ነህ ካሴ ( አባይ « ላልቶ ይነበብ ☺ ) በዚህ መልኩ ይነግሩናል ኦርቶዶክስ ካልሆኑት ጋር መአድ መጋራት ያለው አደጋን በማስመልከት ፍትሐ ነገሥትን ጠቅሰው ያስረዳሉ እውነት በፍትሐ ነገሥት የሚያምኑ ከሆነ ለምን ይህን የፍትሐ ነገሥት ሕግ ካዱት? ለምን ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስን ስትሾም አልተቃወሙም?
« የኢትዮጵያ ሰዎች ከዐዋቂዎቻቸው ወገን በራሳቸው ፈቃድ ሊቀ ጳጳሳትን ለራሳቸው አይሹሙ »(ፍትሐ ነገስት ገፅ 30 ቁጥር 50 )
አማልክትና ትንሣኤያቸው...
ብዙ አማልክት ተሰቅለዋል፥ ተነሥተዋል (ተረት ቢኾንም) ። ከኢየሱስ በፊት ተሰቅለው ከሞት ስለተነሡ አማልክት እስኪ እንመልከት።
1. የፍሪግያው አቲስ (1170 ቅ.ኢ)
ይህ አምላክ ተብዬ ለኀጢአት ስርየት ነፍሱን የሰጠ ነው ይባልለታል። ላቲኑ “suspensus lingo” ይለዋል፤ “በዕንጨት የተንጠለጠለ” ማለት ነው። ከሞተ በዃላ ተቀበረ፥ ከሞት ተነሣ፥ ዐረገ።
2. የግብጹ ቱሊስ (1700 ቅ.ኢ)
ይህ ግብጻዊ አዳኝ (አምላክ ተብዬ) ልክ እንደ ኢየሱስ ከተሠቃየ በዃላ ሞተ፥ ተቀበረ። ነገር ግን ሞት ሊይዘው አልቻለም። ከሞት ተነሣ፥ ወደ ሰማያትም ዐረገ።
3. (ኤስኺሉስ) ፕሮሜቴዉስ (547 ቅ.ኢ)
ይህ አምላክ ነኝ ባይ እንደ ኢየሱስ በዕንጨት ላይ ተቸነከረ። ሲሞት ተፈጥሮ ተዘባረቀ። መሬት ተናወጠች፥ ዐለቶች ተሠነጠቁ፥ መቃብሮች ተከፈቱ። ይህ አምላክ ተብዬ የተሠቃየበት ምክንያት “ለሰው ልጅ ፍቅር” የሚል ነበር። ግና ርሱም ተነሣ።
4. የሮሙ ቊሪኑስ (506 ቅ.ኢ)
ይህ አምላክ ተብዬ እንዲህ ተብሎለታል፡—
1. ከድንግል ተፀነሰ፤
2. እናቱ ከነገሥታት ዘር ትወለዳለች፤
3. በእኩያን እጅ ተሰቀለ፤
4. ሞቶ ነፍሱን በሰጠ ጊዜ ምድር መላዋ በጨለማ ተዋጠች።
ይህ አምላክ ተብዬ ታዲያ ከሙታን ተነሣ፥ ወደ ሰማያትም ዐረገ።
5. የሶርያው ታሙዝ (1160 ቅ.ኢ)
ይህ አምላክ ተብዬ ለኀጢአት ስርየት የተሰቀለ ነው ይባልለታል። ዩልዩስ ፊርሚኩስ “ለዓለም ድኅነት ሲል ከሙታን የተነሣ” ይለዋል። በ400 ቅ.ገደማ ክቴሲያስ የተባለ ገጣሚ ተቀኝቶለታል፡—
“ታመኑ ቅዱሳን፥ ተመልሷል ጌታችኹ
ታመኑ በጌታ፥ በተነሣላችኹ
ታሙዝ በታገሰው ሕማማት
አግኝተናል እኛ ድኅነት።”
(ተመሳስሎ የተተረጐመ)
6.የህንዱ ክሪሽና (1200 ቅ. ኢ)
ይህን አምላክ ተብዬ ሳታውቁት አልቀራችኹም። በዕንጨት የተሰቀለ ነው። እግሮቹ ኹሉ የተበሱ ናቸው። ታሪኩም የሚከተለው ነው፡—
1. ከድንግል ተወለደ፤
2. ርሱና እናቱ በእረኞች፥ በጠቢባንና በመላእክት ተጐብኝተዋል፤
3. ጨቋኙ ገዥ ካንሳ የበኵር ልጆች ኹሉ ይገደሉ አለ፤
4. በበረሓ ተፈተነ፤
5. በጋንጅስ ወንዝ ተጠመቀ፤
6. አርድእት (ደቂቆች) ነበሩት፤
7. በምሳሌ ያስተምር ነበር። ማሃብሃራታ የተባለ የህንድ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚያትተው ይህ ከአምላክ ተብዬ ከሞት ተነሣ። ከዚያም ወደ ሰማያት ዐረገ።
እንግዲህ እኒህ ኹሉ አምላክ ተብዬዎች ሞተው የተነሡ መኾናቸው ነው። ከእነዚህ ኹሉ ተረቶች መኻል ግን ኢየሱስ አስከነዳ። ለምን? አይሁዳዊ ነውና። (ናምሩድ)
አልገደሉትም
@ገቢር አንድ
https://t.me/Wahidcom/656
@ገቢር ሁለት
https://t.me/Wahidcom/658
@ገቢር ሦስት
https://t.me/Wahidcom/667
@ገቢር አራት
https://t.me/Wahidcom/679
@ገቢር አምስት
https://t.me/Wahidcom/681
ስለ ስቅለት እና በስቅለት ዙሪያ ማብራሪያ ነው። ያንብቡ!
የወንጌላት የእርስ በእርስ ተፋልሶ ኢየሱስ ሞቶ ተቀበረ ከተባለ በኃላ ወደ መቃብሩ ሲሄዱ ያገኙት ማንንና እንዴት ነበር? 1ኛ የማቴዎስ ወንጌል ላይ አንድ መልአክ ብቻ የመቃብሩ በር ላይ ዲንጋው ላይ ተቀምጦ አገኙ እነሆም፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም #ድንጋዩን #አንከባሎ #በላዩ #ተቀመጠ መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ።(የማቴዎስ ወንጌል…
ዕለተ ዓርብ በተአምር ሁለት ቀንና ሁለት ሌሊት ሆነች
“ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ #በምድር #ልብ #ሦስት #ቀንና #ሦስት #ሌሊት #ይኖራል።”
— ማቴዎስ 12፥40
ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በክርስትና ሊመሱ ከማችሉ አወዛጋቢ ትርክቶች አንዱ ነው አንዳንድ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ሶስት ቀን እና ሶስት ሌሊት ለመሙላት ኢየሱስ የተሰቀለው ከሐሙስ ጀምሮ ነው ከሐሙስ እስከ እሁድ ሶስት ቀን ስለሚሆን ይሞላል ብለው ዓርብ ተሰቀለ ሚለውን መጽሐፍ ቅዱሱን ሽምጥጥ አድርገው ይክዱታል
የኦርቶዶክስ መምህር የሆነው ዶ/ር ዘበነ ለማም መጽሐፈ አሚን ወስርዓተ ጸሎት በሚለው መጽሐፉ ገጽ 58 ላይ ሶስት ቀንና ሶስት ሌሊት ለመሙላት አዲስ የሒሳብ ስሌት አሳይቶናል በእርግጥ ይህ ጽንሰ ሀሳብ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲየሰ የተዘጋጀ የማቲዎስ ወንጌል አንድምታ ላይም አስቀምጠውታል
የተሰቀለ ዓርብ ነው ፦
ከጠዋት እስከ ስድስት ሰዓት ― » 1 ቀን
ከስድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ―» 1 ሌሊት
ከዘጠኝ ሰዓት እስከ ማታ ― » 1ቀን
ለዚህ ሒሳብ ይረዳኛል ብሎ ያስቀመጠው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል “ከስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።” (ማቴዎስ 27፥45)
በዚህ መሰረት ዓርብ ቀን «ከስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ጨለማ» ስለነበር እንደ አንድ ቀንና አንድ ሌሊት ከዘጠኝ ሰዓት በኃላ ደግሞ ጸሐይ በመውጣቱ ተጨማሪ አንድ ቀን ሆኖ ተቆጥሯል በአጠቃላይ በኦርቶዶክስ የሒሳብ ስሌት ተጨምቆ ሁለት ቀንና አንድ ሌሊት ይወጣዋል ማለት ነው ይህ ማለት ዓርብ ሙሉ ቀን ( በኦርቶዶክስኛ ሁለት ቀን እና አንድ ሌለሊት) ከዓርብ ሌሊት ጋር ሲደመር 2 ሌሊት 2 ቀን ቅዳሜ ቀን ከማታው ጋር ተደምሮ ሶስት ቀን ሶስት ሌሊት ሞላ ማለት ነው ገራሚ ስሌት ነው!
ችግሩ ግን ቃሉ ሚለው « በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል » ነው ተቀበረ የተባለው ደግሞ ከመሸ በኃላ ነው ማርቆስ 15፥42 —47 ስለዚህ ሁለቱም ወገን ሶስት ቀንና ሶስት ሌሊት ለመሙላት ከሒሳብም ከመጽሐፍ ቅዱስም ውጭ የሆነ የፈጠራ ስሌት በመጠቀም ሚዳክሩት ኢየሱስ ተያዘ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን በመቁጠር ነው ይህ ደግሞ የሞኝ ሙግት ነው
ይህን ሁሉ የተምታታ አስተምህሮ ለማስታረቅ ሁለት ምርጫ አለን አንደኛ ኢየሱስ ዋሽቷል ካልሆነ ኢየሱስ አልተሰቀለም አልሞተም ብለን መቀበል አለብን እውነቱ ኢየሱስ አልተሰቀለም አልሞተም ነው ።
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 6 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 month ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 weeks ago