Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

መጽሐፍ ቤት

Description
ለማንኛውም አስተያየት @book_comment
👇👇👇👇👇👇join @metsihafbet👈
Advertising
We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

● Welcome to Ethio music Channel

➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !

Last updated 2 weeks, 1 day ago

🇪🇹 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ ቆየት ያሉና አዳዲስ👇👇

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት 🎻 የበገና መዝሙራት  
👑 የቅዱሳ መዝሙራት ⛪️ የንግስ መዝሙራት
💍 የሠርግ መዝሙራት 🌦 ወቅታዊ መዝሙራት መገኛ


📢ለ ማስታወቂያ ስራዎች @Miki_Mako

1 год назад
1 год назад
1 год назад
1 год, 1 месяц назад

🔍~~~ጥያቄ ቁጥር ፩ ~~~🔎

1⃣/ ኪርያላይሶን ማለት ምን ማለት ነው

1 год, 1 месяц назад

የዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ስብከቶች መከታተል ይፈልጋሉ

1 год, 1 месяц назад

አለማወቅ// አለመኖር የተባለ ድንቅ የሆነ ቻናል ይዘንላችሁ ቀርበናል ከናንተ የሚጠበቀው JOIN እና ሼር ማለት ብቻ ነው !!

1 год, 1 месяц назад

🫧"ስለ አፍሪካ አንዳንድ የማታውቋቸው እውነታዎች!!"

  1. የዘመናችን ሰዎች ባለፉት 200,000 ዓመታት ውስጥ ከቦትስዋና🇧🇼 እንደመጡ ይታመናል።

  2. ኢኳቶሪያል ጊኒ 🇬🇶 ከአፍሪካ ብቸኛዋ የስፓኝ ተናጋሪ ሀገር ነች።

  3. ሞሮኮ 🇲🇦 በአፍሪካ በብዛት የምትጎበኝ ሀገር ነች።

  4. ናይጄሪያዊው ባለሀብት 🇳🇬 አሊኮ ዳንጎቴ ከአፍሪካ ቀዳሚው ጥቁር ሰው  ነው።

  5. ሳሙኤል ኤቶ 🇨🇲 ቀደም ሲል በአለም ላይ ከፍተኛ ተከፋይ የእግር ኳስ ተጫዋች ነበር በ2011 ሩሲያ ውስጥ በየሳምንቱ £350,000 ይቀበል ነበር።

  6. የሰሜኑ አብዛኛው የአፍሪካ ክፍል ኬፕ አንጄላ በቱኒዚያ 🇹🇳 ነው።

  7. ሌሴቶ🇱🇸 በአለም ላይ ከ1,000 ሜትር (3,281 ጫማ) ከፍታ ላይ የምትገኝ ብቸኛ ነጻ ሀገር ነች።

  8. በኒጀር 🇳🇪 ዳይኖሰር ከ115 እስከ 105 ሚሊዮን አመታት በፊት እንደነበረ ይታመናል።

  9. ቡርኪናፋሶ 🇧🇫 በአፍሪካ ጥበብ እና ባህል መሪ ስትሆን በአፍሪካ ትልቁን የእደ ጥበብ ገበያ ታስተናግዳለች።

  10. ናይጄሪያ 🇳🇬 ከእንግሊዝ በላይ ብዙ የእግር ኳስ ዋንጫዎችን አሸንፋለች።

  11. የዚምባብዌ 🇿🇼 የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሮበርት ጋብርኤል ሙጋቤ 7 የዩኒቨርስቲ ዲግሪ ያላቸው የአለማችን እጅግ የተማሩ ፕሬዝዳንት ሲሆኑ ሁለቱ ማስተርስ ናቸው።

  12. የግብፁ🇪🇬 አል አህሊ በአፍሪካ ቀዳሚው የእግር ኳስ ክለብ ነው።

  13. የቼልሲው ዲዲየር ድሮግባ 🇨🇮  በአውሮፓ ውድድር ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው።

  14. ጆሃንስበርግ፣ ደቡብ አፍሪካ 🇿🇦 ከአፍሪካ እጅግ ሀብታም ከተማ ነች።

  15. ዚነዲን ዚዳን ለአልጄሪያ 🇩🇿 መጫወት ፈልጎ ነበር ነገርግን አስመራጩ በቡድኑ ውስጥ እንደ እሱ ያሉ ብዙ ተጫዋቾች ናቸው በማለት ውድቅ አድርጎታል።

  16. ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ 🇿🇦 በአለም ላይ ታዋቂ ሰው ተደርገው ይወሰዳሉ።

  17. ፕሬዚደንት ሮበርት ሙጋቤ 🇿🇼 ለነጻነት በመታገል 11 አመት ታስረዋል።

  18. ግብፅ 🇪🇬 የመጀመሪያዋ ወረቀት እና ቀለም ፈልሳፊ ነች።

  19. ኢኳቶሪያል ጊኒ 🇬🇶 ከአፍሪካ ከፍተኛ የተማረ ዜጋ አላት 95% (2020)።

  20. በሩዋንዳ 🇷🇼 ከእንግሊዝ 🇬🇧 እና አሜሪካ 🇺🇸 የተሻለ የፆታ እኩልነት አለ።

  21. ሶማሊያ 🇸🇴 የመጀመሪያውን ኤቲኤም ያገኘችው በጥቅምት 7 ቀን 2014እኤአ ነው።

©ሳይንስኛ (anteneg)

1 год, 1 месяц назад

ማንነት-ፍሮይድ

በተለያዩ ቀናት፣ በተለያዩ ሳምንታት ወይም በተለያዩ አመታት ውስጥ የተለያዩ ማንነቶች እንዳሉህ ተሰምቶህ አያውቅም? በአንደኛው ቀን ጨዋታ ወዳድ ተጫዋች ትሆንና በሌላኛው ቀን ቁጥጥርን የሚያበዛ ቁጡ ሰው ትሆናለህ፡፡ ሲግመንድ ፍሮይድ ስለ ባህሪ መለዋወጥ የሚለን ነገር አለ፡፡
ከእርሱ በፊት ስለ ሰው ልጆች ስነ-ልቦና ያጠና የለም ባንልም ፍሮይድ ግን በእጅጉ በተለየ ሁኔታ ተመራምሯል እና ዛሬም ድረስ የምንከተላቸውን የሳይኮሎጂ አስተምህሮዎችን ፈልስፏል።
ፍሮይድ የእኛ ማንነት በሶስት ይከፈላል ይለናል፡፡

#ኢጎ; ይህ አሳቢውና ምክንያታዊው ማንነታችን ነው፡፡ ይህን መጽሐፍ የሚያነበውና በአእምሮህ ውስጥ የሚተርክልህም ይህ የማንነት ክፍልህ ነው፡፡ ከሶስቱ ማንነቶችህም በመሃል ላይ ይገኛል።

#ኢድ; ይሄኛው የእንስሳነት ባህሪህን ያጎላዋል፡፡ ወሲባዊ ፍላጎቶችህ፣ በስሜትህ የምትመራባቸው ውሳኔዎችህ እና ሌሎችም ግልፍተኛ ድርጊቶችህ በዚህ የማንነት ክፍልህ ይመራሉ። ልክም እንደ ሰይጣን ሆኖ ውሳኔዎችን እንድትወስን ያጣድፍሃል። የሰደበህን ሰው እንድትደበድብ ወይም ድንጋይ እንድትወረውርበት ያበረታታሃል። ልክ ህጻን ልጅ ሲርበው እንደሚያለቅሰው ይህ ማንነትህ ድርጊቶችህ ስለሚያስከትሉት ውጤት
ሳይጨነቅ ምሱን እንድታመጣለት
ያለቅሳል።

#ሱፐር_ኢጎ; ይህ በአእምሮህ የተቀመጠ ዳኛ ነው፡፡ እንዲህ አታድርግ ነውር ነው፤ ይህን ማድረግህ አንተን እንድትዋረድ ያደርግሃል እያለ ሃሳቦችህ እና ድርጊቶችህ ላይ ሂስ ይሰጣል፡፡ ስለ ማህበረሰቡ ህግ እና ከድርጊትህ በኋላ ስለሚከሰት መጥፎ ነገር አበክሮ ይጨነቃል። ይህ ልክ ነው፤ ይህ ልክ አይደለም እያለ ይመክርሃል።

ለምሳሌ ለፈተና ልታጠና ተቀመጥክ፡፡ ኢድ መጨናነቅ አይወድም፤ እናም በቀስታ ፈታ በል አትጨናነቅ ይልሃል። ወይ ስልክህን አንድታነሳና ፌስቡክ እንድትጠቀም አልያም ከጓደኞችህ ጋር ሄደህ እንድትዝናና ይመክርሃል።

ሱፐር ኢጎ፤ ከኢድ በተቃራኒ፣ ነገሮችን አጋኖ እና መጥፎ አድርጎ ያቀርብልሃል። ዛሬ ካላጠናህ ፈተና ትወድቃለህ፤ ፈተናንም ከወደቅክ ይህን አመት ትደግማለህ... እያለ ያስፈራራሃል።

በመሃል ወይም ምክንያታዊ ማንነትህ ለማስታረቅ ይመጣል፡፡ ራሴን እስክጥል ድረስ መጨናነቅ የለብኝም፤ ሆኖም ግን ለአንድ ሰዓት ያህል አጥንቼ ወደ ጫወታ እሄዳለሁ ይላል፡፡

ፍሮይድ የማንነት ቀውስ የሚመጣው ሶስቱን አጣጥመን ሳንሄድ ስንቀር ነው ይለናል። ሰካራም፣ ሴሰኛ ሰው አይተህ ታውቃለህ ይሄ ሰው የኢድ (የእንስሳነት) ማንነቱ በርትቶበታል፡፡ በተቃራኒው ስለ ሁሉም ነገር የሚጨነቅ እና ፍጹም ለመሆን የሚጥር ሰው ያውቃል? ቋጣሪ፣ ጥንቁቅ አልያም አብዝቶ የሚጨነቅ ይሆናል ... ይህ ሰው የሱፐር ኢጎ (የዳኛው) ማንነት በርትቶበታል፡፡

ሁሌም ቢሆን በሁለቱ ማንነቶቻችን ውስጥ እንዳንዋጥ ራሳችንን ልንቆጣጠረው ይገባል፡፡ ነገር ሁሉ በጊዜው እና በአግባቡ ሲሆን ያማረ ይሆናል። ጠቢቡ ሰለሞን እንዳለው፡-
“ለማልቀስ ጊዜ አለው፥
ለመሳቅም ጊዜ አለው፤
ዋይ ለማለት ጊዜ አለው፥
ለመዝፈንም ጊዜ አለው።“

@metsihafbet
@metsihafbet

1 год, 1 месяц назад

ፀሎቴን ባሰማ ፥ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ፥ ወሰዱት መሰለኝ
.......
የእቴሜቴ ጀምበር
©ሲራክ ወንድሙ
.
እረኛ አይዘምርም ፥ ዝም ነው አድባሩ
ፋኖስ ክሩን አጥቷል ፥ መሸ ደህና እደሩ
ቡሬ መንደር ራቃት ፥ የለችም ከቤቷ
በሌት አልዘመረች ፥ ከፍቷታል ወፊቷ
ማልዶ ሌት ሚያነቃኝ ፥ ዶሮ በጉድ ወጣ
የሌት ድምፁን ሸጦ ፥ መውዜር ይዞ መጣ
ወዲያም ወደ ሰማይ
ከጎጆዬ በላይ
ፀሎቴን ባሰማ እንደሰው ዝም አለኝ
እሱንም ዘመቻ ወሰዱት መሰለኝ
.
የዛች የእዝነት አርማ ፥ የህዋ ላይ ሰንደቅ
እንዴት ቀን ከፍቶባት ፥ ውብ ጀምበሯ ትጥለቅ
ከዛች ከገራገር ፥ ከደጊቱ ዳሴ
እንደምን ብርቅ ይሁን ፥ ሰላም ለእለት ጉርሴ
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን
እኔን አፈር ይብላኝ ፥ ለእኔ ቀኑ ይክፋ
አንቺን ያሳጣችሽ ፥ ያች አለም ትደፋ
እስከ መች አስከ መች ፥ የአረር ሙዳይ ቋጥረን
እንደጃኖ ኩታ ፥ ዝናር ጥለት አርገን
ሀገር እያጠፋን ፥ ያልፋል እንላለን ?
እንዴት ነው መሰንበት ?
መውዜር እንደነዶ በሚመዘዝበት?
ኧረ እንደምን በምን
ኧረ እንደምን በምን
አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን?
.
ከጩኸትሽ ማዶ ፥ ካኮረፈው ሰማይ
ቄራ ከመሰለው ፥ ከአድማስሽ ሸራ ላይ
እብሪት ያጠላበት ፥ ምስል ድንገት ካየው
ለቸር አንመስለኝም ፥ ያን ጊዜ ፈራለሁ
አርብ አርቡን አመሻሽ
የሰማዩ ገላ ሲመስል የደም ሻሽ
ንትብ የለበሰ
ከወደ አንገቱ ዘሞ የተዘለሰ
ይሁዳሽን ባላይ ፥ ወድቆ ሲያንሰራራ
መስቀል ሆኗል ለሻጭ ፥ ገዢ ራሱን ያኩራ
ከክርስቶስ ይልቅ ፥ ይሁዳ ነውና ሚረከብ መከራ
ምክኒያቱም ......
ዘመን እያሰፉ
ትውልድ ለሚነቅፉ
ነገር ጠንቷል ዛሬ ፥ አውቀውት ይረፉ
ለሻጭ መስቀል  ሊሆን ፥ ምሏልና ዛፉ
.
በኑረት ቀራንዮ ፥ በህይወት ጎለጎታ
ከገዳይሽ ቀዬ ፥ አንቺ ሆነሽ ጌታ
በሰማያ አኮርባጅ ፥ ወዲያ ስትላጊ
የመከራን መስቀል በሌት ተሸክመሽ ፥ መንገድ ስትፈልጊ
ጨረቃዋ ገባች ፥ ከደመና ጉያ
ከዋክቶች ሸሽተው ፥ እንደሰደድ ቋያ
ጠረንሽን ገፍተው ፥ ከገላሽ ሲርቁ
በንቄት ሸምቀው ፥ ሊጥሉሽ ዘለቁ
.
ዞር ብንል ወዲያ ፥ አራራይ መረዋ
ቀና ብንል ኦና ፥ የጠቆረ ህዋ
የፀሎትሽ ጩኸት ፥ ካልደረሰው ያ ' ቃል
እሱም እንደሰዉ ዘምቶልሽ ይሆናል።
..................... //// ..............
©ሲራክ ወንድሙ 

t.me/metsihafbet

1 год, 2 месяца назад

ሁለት የሚገራርሙ ቻናሎች እንሆ

We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

● Welcome to Ethio music Channel

➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !

Last updated 2 weeks, 1 day ago

🇪🇹 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ ቆየት ያሉና አዳዲስ👇👇

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት 🎻 የበገና መዝሙራት  
👑 የቅዱሳ መዝሙራት ⛪️ የንግስ መዝሙራት
💍 የሠርግ መዝሙራት 🌦 ወቅታዊ መዝሙራት መገኛ


📢ለ ማስታወቂያ ስራዎች @Miki_Mako