Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 6 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 month ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 weeks ago
ትላንትና አንዱ ፌስቡክ ላይ ዳኜ ዋሌ ያወጣው ዘፈን አንደኛ ነው < አይዞሽ ኢትዮጵያውያዬ> ከሚለው ዉጪ አለ ከዛ comment ገብቼ ንዴቴን ገልጬ block አረኩት ከዛ ስለ ሃገሬ ማሰብ ጀመርኩ እንዴት በዚ ልክ ሚጠሉዋት ልጆችን ልታፈራ እንደቻለች ስለ እሱዋ ሲወራ ከሰሙ የሚያማቸው ልጆችን እንዴት ልታፈራ ቻለች እሺ ከምንስ የመጣ ነው አልኩ ጥያቄ ብቻ አሁንም እንደ አባቱ የሚያስብ ልጅ እራሱን ያጣ ነው የ አባቱን ድንቁርና እያስቀጠለ ነው የሰው ልጅ ውደ ምድር የመጣው እሱን እንዲሆን እንጂ የ አባቱን እንዲኖር አደለም ከአባቶቻችን ብልሃትን እንጂ ክፋትን አንዉሰድ መልካም የ አድዋ ድል በአለ ይሁንልን ?
አመሰግናለሁ
@fonkabcha1
@fonkabcha1
By the way ትቶሽ እረስቶሻል ግን አንቺ እስካሁን ልረሺው ኣልቻልሽም ሌላ ሰው ልትቀርቢ አልቻልሽም እሱ ሂወቱን እያጣጣመ እየኖረ ነው ያንቺ ሂወት ግን እዛው ላይ ነው what the fuck are u doing with ur past sis የትላንትናው ሂወትሽ የዛሬን ሂውትሽን ለምን እንዲያበላሽብሽ ትፈቅጃለሽ ያ ሰው እኮ ሌላ ሴት እያቀፈ ነው እየሳመ ነው ዋጋ ለማይሰጥሽ ሰው ሂወትሽን ለምንድን ነው ምትከፍዪው ደደብ አቱኚ ከሂወትሽ አውጪው ከዛ ላንቺ ሚገባሽን ሂወት ኑሪ እሱን ያጣሺው ስለማይገባሽ ነው አለቀ sigma girl ሁኚ ?
አመሰግናለሁ?
@fonkabcha1
@fonkabcha1
ወንድሜ እህቴ በሰዎች ዘንድ respect እንዲኖርህ ሰዎች ዘንድ value እንዲኖርህ ትፈልጋለህ so ታዳ ለምን ሰዎችን በደምብ ትቀርባለህ ሁሉንም ሰው ለምን በ አንድ አይነት መንገድ ትቀርባለህ በሰዎች ዘንድ value respect ወይም እነሱ ዘንድ ክብር እና ዋጋ እንዲኖርህ ከፈለክ ግንኙነትህን ገድብ hi hi ? ከመባባል ዉጪ ብዙ አታውራ ስላንተ እንዲያቁ አትፍቀድላቸው Classic man መሆን ከፈለክ ክብር ዋጋ እንዲኖርህ ከፈለክ እንዳትናቅ ከፈለክ ማንነትህን Open ክፍት አርገህ አትቅረብ ይህ ንግግር ዝም ብሎ ሊመስልህ ይችላል ነገር ግን አለመናቅ መከበር ዋጋ እንዲኖርህ እርካሽ አለመሆን ከፈለክ የኔ ከምትላቸው ሰዎች ዉጪ ከሌሎች ጋር ያለህን ግንኙነት ገድበው ይህ መልእክት ላንቺም ጭምር ነው እህቴ
አመሰናለሁ ?
አጀብ ነው
ሁሉም ይዘርፋል ስለራበኝ ፍቅር
ይናገሩታል ይተነብዩታል ፍቅርን ያዩት የኖሩት እያላቸው ምርር
ቀን መቶ አንስቷቸው ሲወድቁ ላያቸው
ደስታ በስቶባቸው አለም ሲርቃቸው
እንዴት አይብጠለጠ ክፉ ሰራቂ ሂወት
ይሉታል እርኩስነው ሰራቂ የደስታ የከባድ ሀዘን ቋት
አይ ፍቅር ስንቶች ይዘልፉታል በማያልቁ ቃላት
እንዲ እንዳ እያሉ ምን ያክል ያሳዝናል አዙረው አንስተው ሲያፈርጡት
ግን ሁሉም አልገባቸው በተለይ ላላዩት
ከውጭ ቆመው በአሉባልታ የፍቅርን ስም ለሚሰጡት
አንድ ነገር አለ አንተ ማትረዳው እነሱ ያዩት
ባዶ ሆኖባቸው እኮነው ሲመጡ ወዳንተ ሂወት
ብጠይቃቸው የተጎዱትን
ፍቅር አውሯቸው በከተማው ሰው ሚባል ማይታያቸውን
እንዲ ነው መልሳቸው አዎ ተጎድተናል ተጎሳቁለናል
ከሰውነት ማረግ ሹልክ ብለን ወተናል
ግን አሁንም ምንድን ነው መፍትሄው ብለህ ብጠይቀው
መቼም ጠልተሀታል ብለህ ብጠይቀው
እብድ ነው ምትመስለው ስላጣት ተጎድቶ ጠላሀት ስትለው
ብር የጠፋበት ሰው ሲናደድ ካየኸው ወይም ሲያለቅስ
ምን ያህል ነው ሚደሰተው ብሩ ቢመለስ
በፍቅር ተጎድቶ የጨለለውም
ፍቅሩ ቢመለስለት ደስታው ገደብ አይኖረውም
አዎ ጠልሽቷል የፍቅር ስም ጠፍቷል
እንደዛም ሆኖ ግን እየዋለ እያደር ይጣፍጣል ሚገቡበት በዝተዋል ብዙዎቹም ለመግባት አሰፍስፈዋል
ለዛም ነው ያፃፈኝ ያስገረመኝን
የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ፍቅር ሆኖብን
✍ አሚር አደም
11/8/2015
@fonkabcha1
@fonkabcha1
ረመዳን
ረመዳን እክ ማመስገኛችን ነው
ይሄንን ያመጣልን መማር ሲፈልግ ነው
ሀጢያት ሰርተናል አውቀንም ሳናውቀው
ተውበት ያላረገ ገሀነም እኮ ነው ነገ ሚጠብቀው
መፀፀት አለብን ነብስያን ተገፍቶ
አላህ መሀሪ ነው አይጎልበት ከቶ
ሀጢያታችን በዝቶ ጣራ እንኳ ቢነካ
ፈጣሪ ታጋሽ ነው በሀጢያታችን ፋንታ ሀጅር እስክንተካ
በዚ ቀን ካልቶበትን ምኑን ሰው ሆነው
ሀጅር መሰብሰቢያ የረመዳን ወር ነው
አንድ ሀጢያት ብሰራ አንዱ ነው ሚፃፈው
ጥሩ ግን ብሰራ በሺ ተባዝቶ ነው
ረመዳን እኮ የተውበት ግዜ ነው
አላህን አጥብቀን ምስጋና እንድንሰጠው
ረመዳን እኮ የአላህ ስጦታ ነው
ለኛማ ሚሻለው እያወደስነው እሱን ማስደሰት ነው
ረመዳንን በንፁ ልባችን ከፆምነው
አላህማ አዛኝ ነው እሱማ መሀሪ ነው
✍አሚር አደም
❦ ══•⊰❂ ጣፋጭ ግጥሞች ❂⊱•══ ❦
?አንዴ ብትሰጠኝ?
ቀምሼው አላውቅም
እያልኳት አትስጭኝ
ልብሱን ገለጥ አርጋ
መልኩን ብታሳየኝ
እኔው ሰፍ ብዬ
አልኳት ስጭኝ ስጭኝ
እርሷም ሳትሳሳ
አንድ ጊዜ ብትሰጠኝ
ሁሌም ስጭኝ አልኳት
በጣም ነው የጣመኝ
ስሙንም ስትነግረኝ
እንዳይጠፋኝ ብላ
ለካስ የማውቀው ነው
ደስታ ከረሚላ!!!
???
? እንቅልፍና ሴት ?
••••✍✍••••
በአንድ አልጋ ላይና
በአንዲት ሴት ላይ
ሶስት አይነት አንድነት
ህልም-ፍቅር-ህይወት
ከነዚህ መሀከል-ህልም የምንለው
ፈቺ የሚፈልግ አሳሪ የሌለው
የኔና ያንቺ ፍቅር ያልጋ ላይ ህይወት ነው
ፍቅሬ ገብቶሽ እንደው
ፍቅር እንደዚህ ነው።
ከራስ አስበልጦ ሌላ ሰውን መውደድ
ባንድ አለም ተከብሮ ባንዲት ሴት መዋረድ
ክብር ነው ትርጉሙ
በሴት ልጅ ተማርኮ ከዙፋን ላይ መውረድ።
ፍቅሬ ገብቶሽ እንደው
ህይወት እንደዚህ ነው
ተኝቶ መነሳት
የታወሰን መርሳት
ያሰሩትን መፍታት
ኖሮ ኖሮ መሞት።
ፍቅሬ ገብቶሽ እንደው
ሴትና እንቅልፍ ያው ነው
የትኛውም ፍጥረት ባልጋው ያንቀላፋል
ማንም ወንድ ነኝ ቢል በሴት ይሸነፋል።
@fonkabcha1
@fonkabcha1
ያገር ልጅ ህይወቱ ፣ ከ ጽሁፍ ሲጣቀስ
እንዴት ዝቅ ይባላል ፣ ከ ሽንት ቤቱ ጥቅስ?
"Work as a slave live as a king"
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
ስራው ማለት ኑሮው ፣ በሆነባት ሃገር
እንደባርያ ስራ ፣ እንደ ንጉሶች ኑር
ይለኛል ገራገር
.
.
ተረግጦ ተረግጦ
ተረግጦ ሲብሰው
እንደ ነገስታት ኑር ፣ ይለኛል የዋህ ሰው
.
.
የብሶቱን ጽዳጅ
ሊጸዳዳው መጥቶ ፣ ባለ ሽንትቤቱ
ዝቅ በል ይለኛል
ብቸኛ ነው መሰል ፣ ዝቅ ያለው ህይወቱ
.
.
ብቸኛ ነው መሰል ፣ መውረዴን ይመኛል
ከዚህ በላይ ዝቅጠት
ከዚህ በላይ ውርደት ፣ ከወዴት ይገኛል
ፅድድቱን ረስቶ
ሽንት ቤት በጻፈው ፣ ንጉሦ ነኝ ይለኛል
.
.
አላወቀም እንጂ...
ሳር ሳሩ እየታየ ፣ በተማሰ ቅጥር
ጎምበስ ብሎ ሰርቶ ፣ ቀና ማለት ቢጥር
ቁልቁል ነው ሚወረድ ፣ ዝቅ ባለ ቁጥር
.
.
ወፊቱ አለቀሰች ፣ ዜማ ወጥቷት ዕምባ
መወጣጫ ሲሆን ፣ ያጎንባሽ ሰው ጀርባ
ዝቅ አልኩኝ እያለ ፣ ሰው ገደል ሲገባ
.
.
ወፊቱ አለቀሰች ፣ እምባ ወጥቷት ዜማ
የለፍቶ አደር መዳፍ ፣ ቀን ተ ቀን ሲደማ
ማለዳ ማለዳ ፣ እሮሮ ስትሰማ
<ምንአረኩ> እያለ ፣
ሰው አምላኩን ሲያማ።
.
.
ወፊቱ በትዝብት ፣ እንዲ አለች አንድ ቀን
<ከፍ ብለን ስናይ ፣ እኛም ከሰው ልቀን
አይፍጠርህ እንጂ ፣ ከታችኛው መደብ
አንተም ስትረግጥ ነው ፣ ከላይ ምትመደብ>
.
.
አይፍጠር ነው መቼስ
[ ቶማስ ትግስቱ ]
////የተጠገነ ቃል\\
-------------------------------
የተሰበረ ልብ በምን ይጠገናል፣
ጊዜ ሽሮት እንኳን
ጠባሳውም ያማል፣
በታወሰ ቁጥር ህመም ያገረሻል፣
ስንት ነው ተመኑ
ዋጋ ወጥቶለታል፣
ያፈቀረን መግፋት
እንደው ስንት ያወጣል።
ከረፈደ ነቅተው የቦዘዙ አይኖች፣
በእርጅና የደከሙ የዛሉ ጉልበቶች።
ማስተዋል ሲያገኙ
ሲነቁ ከህልማቸው፣
እንደው ቢጠየቁ ቢሰማ ድምፃቸው፣
የገፉትን ማግኘት
ይሆን ወይ መልሳቸው።
እንጃ፣
ብቻ፣ ባላወኩት አለም በሃሳብ ተሰድጄ፣
የጎዳሽኝ አንቺን በሀሳብ አስረጅቼ።
ድንገት ባስብ ጊዜ፣
ስለሰበርሽው ልብ ፀፀቱ ሲገልሽ፣
ከሀሳብ መለስ ብዬ
ደብዳቤ ፃፍኩልሽ፣
እርሺኝና ኑሪ ሀዘን አይብዛብሽ፣
አለም አሰቃይታ ቁጭት አይግደልሽ፣
ሺህ ብታደሚኝም ይኸው ይቅር አልኩሽ፣
በሄድሽበት ሁሉ መልካሙ ይግጠምሽ፣
በእንባዬ አትሜ ይቅርታን ላኩልሽ፣
እውነት መልካሙ ይግጠምሽ።
ምንድን ናት
እናት ምንድን ናት ቃል አላት
ብቻ ግን ውድ ናት ልትፈታ ማችል ቅኔ ናት
ሴት እናት ስትሆን ሂወትም አይኖራት
የኔ ለኔ የሚባል ጥቂት ደስታም የላት
እና እናት ምንድን ናት
ቃል አላት ምን ገልጿት ምን ልንላት
ብቻ እናት ውድ ናት በየቦታው ያለች እንቁም ልዩም ናት
ገጣሚ አሚር አደም
ጥር 21/2015
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 6 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 month ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 weeks ago