قناة أبي أيمن علي بن عيسى

Description
We recommend to visit

للتواصل @Gggslbot
مرحبا بكم في قناة مسلسلات نتفليكس الاصلية✅
نقوم في نشر اكثر من مسلسل في اليوم
للاعلانات @PpFFBOT

قناتنا الاخرى للافلام? @Qaflam
لطلب المسلسلات✅ @netflix239bot

القناة الرسمية لمسلسل أبو العروسة الموسم الثالث علي تيليجرام?

- بوت تحميل من الأنستا ومن جميع مواقع التواصل الإجتماعي: ✅ .

- بوت التحميل من التيك توك: @EEEBOT

بوت التحميل من الأنستا: @xxzbot

- بوت التحميل من اليوتيوب: @EMEBOT

- ? ? .

- للتمويل: @NNEEN

1 year, 8 months ago

?የሪዝቅ ሰበቦች በአንድ ስንኝ ዉስጥ

#أسباب_الرزق في القرآن ... في بيت
.....
【أسباب رزقٍ جاء في القرآنِ ...... تـاءانِ حـاءٌ هـمزةٌ صـادانِ】
...
١-التوكل:«ومن يتوكل على الله فهو حسبه»
٢-التقوى:«ومن يتق الله يجعل له مخرجا و يرزقه من حيث لا يحتسب».
.
٣-الحركة :«وهزي إليك بجذع النخل تساقط عليك رطبا جنيا»
.
٤-الاستغفار : «فقلت استغفروا ربكم إنه كان غفارا يرسل السماء عليكم مدرارا ويمددكم بأموال وبنين ويجعل لكم جنات ويجعل لكم أنهارا».
.
٥-الصلاة: « وامر أهلك بالصلاة واصطبر عليها لا نسألك رزقا»
٦-الصدقة: «وما أنفقتم من شيء فهو يخلفه وهو خير الرازقين»
.....

?https://t.me/murselseid

1 year, 9 months ago
1 year, 9 months ago
2 years ago

እውን ፍጡር የሚያመልክ የለም?
~
ስለ ሺርክ ሲወራ በዚህ ዘመን ፍጡር የሚያመልክ የለም የሚሉ ሰዎች አሉ። የነዚህ ወገኖቻችን ችግር ወይ የሺርክን ምንነት አለመረዳት ነው። ወይ ደግሞ የዒባዳን ምንነት አለመለየት ነው።
1- የመጀመሪያውን በተመለከተ ሺርክ ማለት አምልኮትን ለፈጣሪም ለፍጡርም መስጠት ነው። አንዳንዶች ግን ሺርክ ማለት ሁለት ፈጣሪ አለ ብሎ ማመን ላይ የተገደበ ይመስላቸዋል። ከአላህ ውጭ ሌላ ፈጣሪ አለ ካላሉ ሺርክ እየፈፀሙ እንደሆነ አይገባቸውም። ነገር ግን መታወቅ ያለበት ከነብያችን ﷺ ጋር ሲፋጠጡ የነበሩትም አጋሪዎች ከአንድ በላይ ፈጣሪ አለ የሚሉ አልነበሩም። ይልቁንም የአላህን ፈጣሪነት፣ ረዛቂነት፣ ሲሳይ ሰጪነት፣ ሁሉን አስተናባሪነት ያምኑ ነበር። ይህንን የሚያስረግጡ በርካታ ቁርኣናዊ መረጃዎች አሉ። ሺርካቸው የነበረው አምልኮትን (ዒባዳን) ለፍጡር መስጠታቸው ነው። አላህን እንደሚገዙት ፍጡርን መገዛታቸው ነው። ስለዚህ አላህ ብቸኛ ፈጣሪና አስተናባሪ ነው ብሎ ማመን አስፈላጊ ቢሆንም ብቻውን በቂ አይደሉም።
2- ሁለተኛውን በተመለከተ የአምልኮትን (የዒባዳን) ምንነት የመለየት ችግር ነው። ብዙ ሰዎች ዒባዳ ማለት ሶላት፣ ፆም፣ ሐጅ ብቻ ይመስላቸዋል። ነገር ግን አምልኮታዊ እርድ፣ ስለት፣ ዱዓእ ፣ ወዘተ ዒባዳ ናቸው። ለምሳሌ ያክል ዱዓን እንውሰድ። ነብያችን ﷺ "ዱዓእ አምልኮት (ዒባዳ) ነው" ይላሉ። ስለዚህ አንድ ሰው አላህን አንደሚለምነው ሙታኖችን የሚለምን፣ የሚማፀን ከሆነ እያመለካቸው ነው ማለት ነው። ይሄ አምልኮትን ለፍጡር መስጠት በሰፊው ያለ ብዙዎች የወደቁበት ችግር ነው። የሙሐመድ አወልን መንዙማ እንደምሳሌ ልጥቀስ፦

"ቀልቤን ወደሳቸው አድርጌ ሰንዘር
አቤት ጮህኩባችሁ ጌቶቼ ዱስቱር።"

አላህ ደግሞ እንዲህ ይላል፡-
(وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّنْ يَدْعُو مِنْ دُونِ اللَّهِ مَنْ لَا يَسْتَجِيبُ لَهُ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ وَهُمْ عَنْ دُعَائِهِمْ غَافِلُونَ)
(ከአላህ ሌላ እስከ ቂያማ ቀን ድረስ መልስ የማይሰጠውን እንደሚጣራ ሰው የጠመመ ማነው? እነሱ ከመጠራታቸው ዘንጊዎች ናቸው።) [አሕቃፍ፡ 5]

"ተሙስጠፋ ይዤ እስተ አቡል በሸር
አንቢያ ሙርሰልም አንድ እንኳን ሳይቀር።"

አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَادْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا لَكُمْ إِنْ كُنْتُمْ صَادِقِينَ)
(እነዚያ ከሱ ሌላ የምትጠሯቸው የናንተው አምሳያ ባሪያዎች ናቸው፡፡ ጥሯቸው እስኪ ይመልሱላችሁ እውነተኞች ከሆናችሁ?) [አዕራፍ፡ 194]

"ደሞ አራተኛቸው ዐልዩ ሐይደር
ነበረ ለነቢ ማኖሪያ ሚስጥር
ዒልመል ገይብ ተሱ ይጠየቅ ነበር።"

ይሄ ፍጥጥ ያለ ውሸት ነው። እንዲያውም አላህ እንዲህ ይላል፡-
(قُلْ لَا يَعْلَمُ مَنْ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ الْغَيْبَ إِلَّا اللَّهُ ۚ وَمَا يَشْعُرُونَ أَيَّانَ يُبْعَثُونَ)
("በሰማያትም በምድርም ያለን የሩቅን ምስጢር አላህ እንጂ ማንም አያውቅም፡፡ መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም" በላቸው።) [ነምል፡ 65]

"በዘበን ያላችሁ ሳዳቶች አኽያር
ቀኝ አጄን ጨብጡኝ ወድቄ እንዳልቀር።"

አላህስ ምን ይላል?
(قُلِ ادْعُوا الَّذِينَ زَعَمْتُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ ۖ لَا يَمْلِكُونَ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ وَمَا لَهُمْ فِيهِمَا مِنْ شِرْكٍ وَمَا لَهُ مِنْهُمْ مِنْ ظَهِيرٍ * وَلَا تَنْفَعُ الشَّفَاعَةُ عِنْدَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ ۚ حَتَّىٰ إِذَا فُزِّعَ عَنْ قُلُوبِهِمْ قَالُوا مَاذَا قَالَ رَبُّكُمْ ۖ قَالُوا الْحَقَّ ۖ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ)
("እነዚያን ከአላህ ሌላ የምታስቧቸውን ጥሩ፡፡ በሰማያትም በምድርም ውስጥ የብናኝ ክብደት ያክል ምንንም አይችሉም፡፡ ለእነርሱም በነሱ ውስጥ ምንም ሽርክና የላቸውም፡፡ ከእነርሱም ለእርሱ ምንም አጋዥ የለውም" በላቸው፡፡) [ሰበእ: 22-23]

"ሺሊላ ጌቶቼ አርሂቡ ዱስቱር
መቼም አለናንተ ሁሉም አያምር
በናንተ የሸሸ ምነዜም አያፍር።"

አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(مَثَلُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِنْ دُونِ اللَّهِ أَوْلِيَاءَ كَمَثَلِ الْعَنْكَبُوتِ اتَّخَذَتْ بَيْتًا ۖ وَإِنَّ أَوْهَنَ الْبُيُوتِ لَبَيْتُ الْعَنْكَبُوتِ ۖ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ)
(የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች ሸረሪት ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ (አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር።)) [ዐንከቡት፡ 41]

"ጌቶቼ አትለፉኝ አደቤም ባያምር
አደበቢስ ቡልሀ እንደኔ ቢኖር
ባሪያ ሲባል ማጥፋት እለት ነው እድር
ለናንተ ይገባል ያጠፋን መማር
ቀልቤን ያዞረልኝ ወደናንተ በር
በናንተ የሸሸ ያገኛል ሹም ሽር።"

አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(لَهُ دَعْوَةُ الْحَقِّ ۖ وَالَّذِينَ يَدْعُونَ مِنْ دُونِهِ لَا يَسْتَجِيبُونَ لَهُمْ بِشَيْءٍ إِلَّا كَبَاسِطِ كَفَّيْهِ إِلَى الْمَاءِ لِيَبْلُغَ فَاهُ وَمَا هُوَ بِبَالِغِهِ ۚ وَمَا دُعَاءُ الْكَافِرِينَ إِلَّا فِي ضَلَالٍ)
(እውነተኛ ጥሪ ለሱ ነው፡፡ እነዚያም ከሱ ሌላ የሚጠሯቸው በምንም ነገር መልስ አይሰጧቸውም፤ ወደ አፉ ይደርስ ዘንድ (ከሩቅ ሆኖ) ወደ ውሃ መዳፎቹን እንደሚዘረጋ ሰው ምሳሌ እንጂ፡፡ ነገር ግን ወደ አፉ ደራሽ አይደለም፡፡ የከሃ - ዲዎችም ጥሪ ከንቱ እንጂ (ሌላ) አይደለም፡፡) [ረዕድ፡ 14]

"አህለል በይት ሁላ ተዳር እስተዳር
ሁሉም ባንድ ሁኖ እሙስጦፋ ጋር
ዛሬ ይድረሱልን ላገኘን ችጋር።"

አንዳቸውም አይደርሱልህም። ምክንያቱም አላህ እንዲህ ይላል፡-
(يَا أَيُّهَا النَّاسُ ضُرِبَ مَثَلٌ فَاسْتَمِعُوا لَهُ ۚ إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ لَنْ يَخْلُقُوا ذُبَابًا وَلَوِ اجْتَمَعُوا لَهُ ۖ وَإِنْ يَسْلُبْهُمُ الذُّبَابُ شَيْئًا لَا يَسْتَنْقِذُوهُ مِنْهُ ۚ ضَعُفَ الطَّالِبُ وَالْمَطْلُوبُ)
(እናንተ ሰዎች ሆይ! ምሳሌ ቀርቧልና አድምጡት፡፡ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው ዝንብ አይፈጥሩም፣ ለዚሁ አላማ ቢሰበሰቡ እንኳን፡፡ ዝንቡ የሆነን ነገር ቢነጥቃቸውም አያስጥሉትም፡፡ ከጃይም ተከጃይም ደካሞች ናቸው፡፡) [ሐጅ፡ 73]

2 years, 3 months ago
***?*** አስደሳች ዜና ለተፍሲር እውቀት ፈላጊዎች!

? አስደሳች ዜና ለተፍሲር እውቀት ፈላጊዎች!

? አዲስ የደርስ ማስታወቂያ

? የሚጀመረው ደርስ :-
تيسير الكريم الرحمن في تفسير كلام المنان

የኪታቡ አዘጋጅ :-
الشيخ العلامة عبد الرحمن بن ناصر السعدي -رحمه الله-

? ትምህርቱን የሚሰጡት :-
ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም -ሐፊዘሁላህ-

? ትምህርቱ የሚሰጥበት ቦታ:- ፉሪ (በፉሪ ሜዳ ፊት ለፊት ባለው ቅያስ ገባ ብሎ) አቡበክር አስሲዲቅ መስጂድ

? ትምህርት የሚሰጥበት ቀንና ሰዐት :- ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከረፋዱ 4:00 ጀምሮ እስከ 5:00

? ትምህርቱ ሚጀመረው :- ሰኞ ዙልሒጃህ 18,1445 ሂጅሪ (ሰኔ 17,2016 E.C)

-
ለሴቶች በቂ ቦታ አለ
በአካል ተገኝታችሁ መከታተል ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል እንዲሁም ሪከርዱም ይለቀቃል ኢንሻአሏህ።

የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam

We recommend to visit

للتواصل @Gggslbot
مرحبا بكم في قناة مسلسلات نتفليكس الاصلية✅
نقوم في نشر اكثر من مسلسل في اليوم
للاعلانات @PpFFBOT

قناتنا الاخرى للافلام? @Qaflam
لطلب المسلسلات✅ @netflix239bot

القناة الرسمية لمسلسل أبو العروسة الموسم الثالث علي تيليجرام?

- بوت تحميل من الأنستا ومن جميع مواقع التواصل الإجتماعي: ✅ .

- بوت التحميل من التيك توك: @EEEBOT

بوت التحميل من الأنستا: @xxzbot

- بوت التحميل من اليوتيوب: @EMEBOT

- ? ? .

- للتمويل: @NNEEN