A place to learn English easily.
Owner - @Samson_G
Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian
Last updated 2 weeks, 2 days ago
NGO, የመንግስት እና የግል ድርጅቶች የስራ ማስታወቂያ እና ነፃ የትምህርት እድሎችን ያገኛሉ ቤተሰበ ይሁኑ ሌሎችንም ይጋብዙ
ለማስታወቂያ @Human133 ላይ አናግሩን
We need promoters
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12
Last updated 4 months, 2 weeks ago
?ተዉጂሐት ሊል_ሙእሚናት?:
حكاية المرأة التي
خطبت زوجـــــــها مــن ربِّـــــــــها
!!
!!
كانت هناك امرأة تحب زوجــها من كل قلبها حبــاً كبيــراً
وكانت تخاف أن تدخل الجنة ولا تكون زوجته فى الجنة ..
كما كانت زوجته فى الدنيا !
هذه المرأة هى "أم الدرداء" زوجة " أبى الدرداء"
وهو من كبار الصحابة الذى لـُقبّ
بـ"حكيم هذه الأمة وسيد القراء بدمشق"
فإذا بـ"أم الدرداء" تقـوم و تتوجه إلى ربـــــــها ، وتقول :
) اللـــهم إن أبا الدرداء خطبنــى ، فتزوجنـــى فى الدنيــــــا
اللهم فأنا أخطبــــــه إليك فأسألك أن تزوجنيــــــه فى الجنــــــة ( ..
فقال لها "أبو الدرداء" :
} فإن أردتِ ذلك ، ومتُّ قبلكِ ؛ فلا تتزوجى بعدى {..
فمــات "أبو الدرداء"
وكانت " أم الدرداء" ذات حُسن وجَمال ؛ فأراد " معاوية"
أن يخطبها فقالت :
} لا والله لا أتزوج زوجاً فى الدنيا حتى أتزوج أبا الدرداء - إن شاء الله - فى الجنــة{..
هكذا يكون الحـــب الحقــيقى وهكذا يكون الوفـــــاء
(የዱኒያ) ባሏ (የነበረን በጀነት መልሶ እንድያጋባት) እጮኛን ከጌታዋ (የጠየቀችው) ሴት ታሪክ!
ባሏን በሙሉ ልቧ በጣም ትልቅ ውደታን የምትወድ ሴት ነበረች ፣ (ለባሏ )በዱኒያ ሚስት እንደሆነችው ሁሉ ጀነት ትገባና (ለባሏ) በጀነት ሚስቱ ሳትሆን እንዳትቀር ትፈራ ነበረ! ይህች ሴት " ኡሙ ደርዳእ" "የአባደርዳእ" ሚስት ነች ፣እርሱ(አባ ደርዳእ) የዚች ኡማ ጠቢብ የሚል ቅፅል ስም ያለው በድመሽቅ የቃሪኦች ዋና ፣ ከትልልቅ ሶሃባዎች(የነበረ) ነው፣ እርሷ "ኡሙ ደርዳእ " በቆመች ወደ ጌታዋ በተቅጣጨች ጊዜ እንድህ ትል ነበር:
(አላህ ሆይ! አባደርዳእኮ በዱኒያ አጭቶኝ አግብቶኝ ነበር፣ አላህ ሆይ! እኔ እርሱን ወደ አንተ(ከአንተ የምጠይቀው ለእኔ )እጮኛ (ይሆን ዘንድ) በጀነት እኔን እንድታጋባው እጠይቅኻለሁ )
(ኡሙ ደርዳእ አባደርዳእን በጀነት ባሏ እንድሆን እርሱን ማጣት እንደማትፈልግ ስትነግረው)
"አባደርዳእም" ለእርሷ እንድህ አላት:
ይህን (በጀነት መጋባታችንን ) ከፈለግሽና ከአንች በፊት ከሞትኩኝ ከእኔ በሇላ (ሌላ) እንዳታግቢ (አላት)።
"አባ ደርዳእም" ሞተ ።
" ኡሙ ደርዳእ" የውበት ባልተቤት (ቆንጆ) ነበረች ፣ " ሙዓውያ" ሊያጫት(ሊያገባት) ፈለገ (እርሷም እንድህ) አለች :
{በአላህ ይሁንብኝ አይሆንም በዱኒያ አላገባም አላህ ከፈቀደ በጀነት አባደርዳእን እስከማገባ ድረስ }
እንድህ ነው ትክክለኛ ውደታ/ ፍቅር ማለት ! እንድህ ነው (ቃልን) መሙላት ማለት! "
https://t.me/Tewjihat
©Tewjihat
Telegram
🌷ተዉጂሐት ሊል_ሙእሚናት🌷
ተዉጅሃት ሊልሙእሚናት ሙስሊም እህቶችን የሚመለከቱ ህግጋት የሚሰራጭበት ቻናል ነው Join እና ሸር ማርግውን አይርሱ***🌷*** Telegram***👇*** t.me/Tewjihat t.me/Sadatcom1 t.me/Menhaj\_Salafiya t.me/IbnuMuneworcom t.me/Muhammedsiragecom
قال معاذ الله?
?"በአላህ እጠበቃለሁ"!
? እህቴ ሆይ!
በቅድሚያ፤ ያለሽው በፈተናዎች ዘመን ስለሆነ የተጋረጠብሽን ለመወጣት ካንቺ ጥንቁቅነት፣ ቆራጥነትና በአላህ መመካት የመሳሰሉ ባህርያትን መላበስ እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን ልብ በይ።
ባለንበት ዘመን አንቺን ወደ መጥፎ ነገሮች የሚጎተጉቱ ወስዋሶች በርካታ ናቸው።
☞ በተለይም ነፍሲያ፣ የሰው ሰይጣናትና የጂን ሰይጣናት ተጠቃሾች ናቸው።
ነፍሲያ ማለት የየራሳችን ግላዊ ስሜት ሲሆን፤
የሰው ሰይጣናት ስንል ደግሞ እንደ እኛው ሰዎች የሆኑ፤ ግና በሩቅም በቅርብም ሆነው ወደ ክፉ ነገር የሚያነሳሱን፣ ወደ ስህተት የሚገፋፉንና ለወንጀል የሚያመቻቹን የጥፋት ጓዶች ናቸው።
ባህሪያቸው የሰይጣንን ባህሪ የተላበሰ በመሆኑ የሰው ሰይጣናት ይባላሉ።
የጂን ሰይጣናት ደግሞ በተፈጥሮአቸው ከማይታዩት ከጂኖች/አጋንንቶች የሚመደቡ ሲሆን፤ በቁንጮአቸው ኢብሊስና ዝርዮቹ የሚመሩ ናቸው። እነኝህ ሰዎችን በስውር የሚጎተጉቱና ለወንጀል የሚዳርጉ ክፉ ፍጡሮች ናቸው።
☞ የሰው ሰይጣናዊነት አንዱ ባንዱ ላይ በሚያደርገው ክፉ እምነትና ተግባር የሚገለፅ በመሆኑ በብዙ ነገሮች ውስጥ ይገባል።
ለምሳሌ ያክል በዘመኑ የመገናኛ አውታር በኢንተርኔት በሰው ሰይጣኖች ገፋፊነት ብዙ ፈሳዶች ሲተገበሩ ይታያል ይሰማልም።
ሙስሊሟን ሴት ለማጥቃት እና ወደ ብልግና ለመሳብ ከስክሪን ጀርባ እንዳሰፈሰፉ መሽቶ የሚነጋባቸው ወስላቶች እዚህ ጋር ተጠቃሽ ናቸው።
በተለያዩ ዘዴዎች ካንቺ ጋር ይፃፃፋሉ፣ ያወጋሉ። አንቺም ሂጃብሽ፣ ድብቅነትሽና ጥንቃቄሽ ትርጉም እንዲያጣ በሚያደርግ መልኩ በሱስ ትጠመጂና ወሬ ለጀመረ ሁሉ በርሽን ክፍት ታደርጊያለሽ።
የዚያኔ ቀድመው የተዘጋጁት መሰሪዎች የባጡን የቆጡን እየፈለፈሉልሽና እያስለፈለፉሽ ወደ ተንኮል መረባቸው ይከቱሻል። የትዳርም ይሁን ሌላ ወሬ ይዘው በምርቃና ያከንፉሻል፤ ላሰቡት ፀያፍ ምግባር ግብአት እስክትሆኚም በነገር ያዋኙሻል፤
ይህ ጉዳይ አንተን ወንድሜንም ይመለከተሃል ።
በእንደዚህ አይነቶቹ የሰው ሰይጣናት ተሸንግለህ እውነተኛ ማንነቷን በውል ከማታውቃት ሴት ጋር የቻት የወሬ ትጀምራለህ፤ ቀስ በቀስም ውሃ ውስጥ እንደገባ ጨው ትሟሟለህ።
ሀራምን የመራቅ ብቃትህ፣ ሃይልህና ትእግስትህ ሁሉ ይመናመናል።
እናስታውስ...❗
ነቢዩላህ ዩሱፍ (ዓለይሂሰላም) ባሪያ ሆነው ተሽጦ ነበር። እንደፈለገ በሚያዝዘውና በሚያደርገው ንጉስ ስር በቤተመንግስት ነዋሪም ነበር።
በወቅቱ ነቢዩ ዩሱፍ በንጉሱም ሆነ ንግስቲቱ የታዘዘውን ከመፈም ውጭ አማራጭ አልነበረውም።
አንድ ጊዜ በክፍሉ ውስጥ ብቻውን እያለ የንጉሱ ሚስት በጣም ተውባና ተቆነጃጅታ ዘው ብላ ገባች። በሮቹን ሁሉ ቆላለፈች። ለእርሱ ስትል ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀችም አበሰረችው። የምትፈልገውን እንዲያደርጋትም ሹክ አለችው።
ይህንን ታሪክ አላህ በቅዱስ ቃሉ እንዲህ ደ
ገለፀልን፦
{ وَرَاوَدَتْهُ الَّتِي هُوَ فِي بَيْتِهَا عَن نَّفْسِهِ وَغَلَّقَتِ الْأَبْوَابَ وَقَالَتْ هَيْتَ لَكَ ۚ قَالَ مَعَاذَ اللَّهِ ۖ إِنَّهُ رَبِّي أَحْسَنَ مَثْوَايَ ۖ إِنَّهُ لَا يُفْلِحُ الظَّالِمُون َ}
[يوسف : 23]
« ያቺም እርሱ በቤትዋ የነበረባት ሴት፣ ከነፍሱ አባበለችው፤ ደጃፎችንም ዘጋች፤ ላንተ ተዘጋጅቼልሀለሁና ቶሎ ና አለች፤ "በአላህ እጠበቃለሁ" እርሱ (አሳዳሪዬ የገዛኝ) ጌታዬ ኑሮዬንም ያሳመረልኝ ነውና (አልከዳውም)፤ እነሆ! በደለኞች አይድኑም፤ አላት።»
ዩሱፍ : 23
ነቢዩላሂ ዩሱፍ (ዓለይሂ ሰላም) ስሜቱን ከጫፍ የሚያደርሱ ነገሮች ቢያጋጥሙትም ራሱን አቅቦ፣ አሳዳሪ ንጉሱን ባለመክዳት፣ ፈጣሪ ጌታው አላህንም በመፍራት ይህን አጭር ምላሽ ሰጣት።
ምንም በንግስቲቷ ጥላ ስር ቢኖር፣ በሩን ቆላልፋበት ብታስገድደው፣ አማራጭ ማምለጫ ባይኖረውም ተስፋ አልቆረጠም፤ የጭንቅ ግዜ ደራሹ ወደሆነው አላህ ጥሪውን አቀረበ።
"قال معاذ الله"
«በአላህ እጠበቃለሁ አላት»
ዩሱፍ : 79•
በልቡ ውስጥ ያለና እርግጠኛ እምነቱ ነበርና ጌታውም አላህ ጠበቀው ፤ ከፈተናም አዳነው።
የዚህ አይነቱ ወደ ፀያፍ ተግባር የሚደረግ ጥሪ ዛሬም በኢንተርኔት የቻት መስኮቶች በተደጋጋሚ እየተለፈፈ ነው። ነገር ግን ከወንዱም ከሴቷም የነብዩ ዩሱፍን አይነት አቋምና ምላሽ ማን ይስጥ ❓
«በአላህ እጠበቃለሁ!» የሚል!
ሁሌም ከአጉል ስሜት፣ ከሰውና ከጂን ሰይጣናት ለመጠበቅ የአላህ ፍራቻና ዱዓእ ሊለየን አይገባም።
ውድ እህቴ በተለያዩ የመገናኛ መስመሮች ከሚደረጉብሽ ትንኮሳዎችና የተሳሳቱ ግብዣዎች ራስሽን ተከላከይ❗ማንነትሽን ጠብቂ! ክብርሽንም አታስደፍሪ! በአቋምሽ ላይም የፀናሽ ቆራጥ ሁኚ!
«በአላህ እጠበቃለሁ!» ማለት የሁልጊዜ ልማድሽ ይሁን!
አላህ ሆይ! እህቶቻችንን ከጥፋት ሁሉ ጠብቅልን! የሙስሊሙ ማህበረሰብ አለኝታና የቤተሰብ መሰረት ናቸውና ከሰውና ከጂን ሰይጣናት ሁሉ ሰውራቸው! ለትእዛዝህ ተገዢም አድርጋቸው!!
አሚን?
#ውዷ እህቴ ሆይ ይህን አንብበሽ ለሌሎች እህቶችሽ ተደራሽ አድርጊው!?
https://t.me/yeswnaehitochmena
Telegram
🌹የሱና እህቶች የለውጥ ሚና🌹
♡..አንቺ ሙስሊም እህቴ ሆይ! ከመገላለጥ ተጠንቀቂ {{በአላህ ፍቃድ}} ከፈተናዎች ጠባቂሽ የሆነውን ሂጃብሽን አጥብቀሽ ያዢ!❥... ***🍃*** ═══ ¤❁✿❁¤ ═══***🍃***
መጠቀም።
.
ለ. ማንም ይሁን ማን ከተቃራኒ ፆታ ጋር ግድ ካልሆነ በስተቀር መልእክት አለመለዋወጥ።
.
ሐ. መልእክቱን ስንለዋወጥ ከዋና ሰላምታ በስተቀር ወደ ዝርዝር ደህንነት ጥየቃ አለመግባት፤ ስምን አለማቆላመጥ እንዲሁም ቁም ነገሩ ላይ ብቻ ማተኮር። በሚሴጅ ለሚያወራን ሰው ውጭ ከሚታየው ባህሪያችን የተለየ አለማሳየት።
.
መ. ሰበብ እየፈጠሩ መልእክት ከመለዋወጥ መቆጠብ። እንዲሁም ያለ በቂ ምክንያት መልእክት እየተላከልን እንደሆነ ከጠረጠርን ቶሎ መልስ አልመስጠት፣ ችላ ማለት፣ ጥርጣሬው ካየለብን ደግሞ ከናካቴው መተው።
.
ማጠቃለያ
.
በFB መልካም ነገርን በመሻት እስከቆየን ድረስ የመልካምነትን ካባ የደረቡ የቀበሮ ባህታዊዎች በዙሪያችን እንዳሰፈሰፉ ልብ ልንል ይገባል። ከሁለቱም ፆታ አላማቸው ፈሳድ ሆኖ ሳለ ከላይ መልካም ነገር በማሳየት የሰዎችን ትኩረት በመሳብና ታዋቂነት በማትረፍ ለእኩይ ተግባራቸው የሚያመቻቹ አሉ።
.
እናም ራሳችንን ከነኝህና መሰሎቻቸው ተንኮል ለመታደግ ይቻለን ዘንድ ከላይ የተቀመጡትን ቅድመ ጥንቃቄዎች ብናደርግ እመክራለሁ።
.
ይህንንም አድርገን ግን ገፍቶ የሚመጣ አካል ካለ አንድም ቅድም እንዳልነው የቀበሮ ባህታዊ ነው ወይም ደግሞ በመጀመሪያ እንዳወሳነው ደመና ለመዝገን የሚጥር ሞኝ ነው። ከሁለቱም ጋር የምናሳልፈው ግዜ መጨረሻው ውድቀት መሆኑን አምነን ሁለቱንም በግዜ መሸኘት መልካም ነው እላለሁ።
.
Notice፦ በዚህ ፅሁፍ ላይ ተቃራኒ ፆታ ሲባል የተፈለገበት አጅነቢ የሆነውን ነው።
.
አላህ ከፈተና ይጠብቀን!
FB እና አጅነቢ
በሙሀመድ ኢብራሂም
(ረጅም ፅሁፍ ነው ግን ጠቃሚ ስለሆነ አያምልጣችሁ)
.
እንደ መግቢያ ...
ይህ ፅሁፍ በፌስቡክ አጠቃቀማችን ላይ አላስፈላጊ የተቃራኒ ፆታ ግንኙነትን (ቃሉ ሰፊ ነው) ለማስቀረት መውሰድ ያለብንን እርምጃ ለመጠቆም ያለመ ነው።
.
አላስፈላጊ የተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ለድንበር ያለፈ ወሬና ጨዋታ ብሎም ከዚህ ለከፋ ሐራም ተግባራት አጋልጦ መጨረሻውን ለከባዱ ወንጀል ይዳርጋል። ግለሰቡንም ለስነ-ልቦና ስብራትና የሞራል ድቀት ያበቃል።
.
በምሳሌ ለማስረዳት ... አንድ ለሸሪዓዊ ትእዛዛት እጁን የሰጠ ሰው ፌስቡክን ተጠቅሞ ዲኑን በመማር ላይ ሳለ ከሚያገኘው የተቃራኒ ፆታ ጋር አላስፈላጊ ግንኙነት ውስጥ ከገባ ቀስ በቀስ በሚከተለው ረብ የለሽ ወሬ ከዛም ተግባቦቱን ተከትሎ በሚፈጠረው መላመድ ተገፋፍቶ የማይደፈሩ የሚመስሉ ሐራም ተግባራትን ከመዳፈር አልፎ እስከ አስከፊው ነውር ድረስ ሊዘልቅ ይችላል።
.
ይህ ሁሉ ሲሆን ነፍስያ የሚሰጠው ሽፋን 'የትዳር አጋር ሊሆን ይችላል' የሚል ነው። ይሁንና ይህ ምክንያት ሐራም ሰርቶ አላህ ፊት ከመጠየቅ አያድንም።
.
ይህንን ፈተና ሰውየው በየትኛውም ደረጃ ላይ ያቋርጠው ኋላ ላይ የፈፀመው ስህተት ስለሚቆረቁረው ሞራሉ የተሰበረ እና ስነ-ልቦናውም የተጎዳ እንዲሆን ያደርገዋል። እናም ሰውየው በንፁህ ተውበት ተመልሶ ጠንካራ መንፈስ ካላጎለበተ በስተቀር በቀጣይ የትዳር ህይወቱም ሆነ በኢስላማዊ ስራዎች ላይ ባለው ተሳትፎ ውስጥ ተፅእኖ ሊያሳድርበት ይችላል።
.
ከዚህ ሁሉ ጣጣ ግን አንድ ሰው ራሱን እንዴት ከዚህ ፈተና መታደግ እንደሚችል ጠቃሚ ጥቆማዎች ልስጥ ... (እንኝህ ጥቆማዎች ምክረ ሐሳብ እንጂ የአድርግ አታድርግ መመሪያ አይደሉም)
.
1. ዓላማችንን እንቅረፅ!
.
ወደ ፌስቡክም ሆነ ሌሎች ማህበራዊ ሚድያዎች ስንቀላቀል ዓላማ ይኑረን። ዓላማችንም ሐራም ያልሆነ እና ከጨዋታና ዛዛታ ፍላጎት የጠራ ይሁን።
.
ዓላማን ማስተካከል እና ፍላጎትን ቁም-ነገር ላይ ማድረግ፤ ከዛ ባሻገርም ዲናዊ ዕውቀትን በመሻት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ዓላማን መቅረፅ ያስፈልጋል። ይህን ማድረግ ካልተቻለ ግን ራስን ከፌስቡክ ማግለል ከፈተና ለመጠበቅ የተሻለ አማራጭ ነው።
.
ሌላው መጠንቀቅ ያለብን ከሸሪዓዊ ዕውቀትን የመሻት ዓላማ ጋር አዳብሎ ትዳርን ከፌስቡክ መፈለግ አንድም ለዕውቀት ፍለጋ ስንነሳ ያነገብነውን ኒያ ሊያበላሽብን ሲችል በሌላ መልኩ የማይዘገን ጉምን እንድንመኝ የሚያደርግ ግልብነት ነው።
.
[እንደዚህ ፅሁፍ ፀሐፊ እምነት በሶሻል ሚድያ የሚደረግ የትዳር ፍለጋ ስኬታማነት የመነመነ፣ ለፈተና እና ሐራም የሚያጋልጥ እንዲሁም ለማታለልና ሽወዳ የሚዳርግ ስህተት ነው - ሌላ ግዜ በሰፊው እመጣበታለሁ ኢንሻ አላህ]
.
እናም እንዲህ ያለውን ህልመኝነት ትተን የምንፈልገውን ሸሪዓዊ ዕውቀት ጥርት ባለ ኒያ ዓላማችን ማድረግ ይገባናል። (ይህን ስል FBን ከወዳጅ ዘመድ መገናኛነት ወይም የስራ ጉዳይ አናውለው ለማለት እንዳልሆነ ልብ እንበል)
.
2. የከፈትነውን አካውንት እናስተውል!
.
በቅድሚያ ፌስቡክን ለመቀላቀል ስናስብ ስለአጠቃቀሙ እና መጠንቀቅ ስላለብን ነገር እንወቅ። ሌላው ደግሞ የምንጠቀምበትን አካውንት ከአንድ በላይ አናድረግ ወይም በአንድ እንብቃቃ። ከዛ በመቀጠል ...
.
ሀ. የምንጠቀምበትን አካውንት ስንከፍት በስልክ ቁጥራችን የምንከፍት ከሆነ ቁጥሩን እንዳይታይ ማድረግ አንርሳ፤ ይህ ካልሆነ ስልካችን ማንም እጅ ስለሚገባ ፈተናን በራችን ድረስ መጥራት ነው የሚሆነው።
.
ለ. ለአካውንቱ የምንሰጠው ስም ትክክለኛ ወይም ሰዎች ዘንድ የምንታወቅበት ይሁን። ይህ ሲሆን የአካውንቱ ባለቤት ቁም-ነገረኛ መሆኑን ያመለክታል። (ኩንያ የምንጨምርበት ከሆነ 'አቡ' ወይም 'ኡሙ' በሚል መልኩ መጠቀም ከፈተና አይነተኛ መጠበቂያ ነው)
.
ሐ. የምንጠቀመው ስም ትኩረት ሳቢ ከሆኑ መጠሪያዎች እንጠብቀው። ለምሳሌ ... ቆንጆ ... Love ... ሳቂታው ... ቀብራራው ... ከመሳሰሉ ራስን ከሚያጎሉ እና እይታ ውስጥ ከሚከቱ ስሞች መጠንቀቅ።
.
መ. የምንጠቀመውን ፕሮፋይል ፒክቸርም ይሁን ከቨር ፎቶ ልክ እንደስማችን ከትኩረት ሳቢነት እናፅዳው። የራስን ምስል ማስቀመጥ ከምንፈራው ፈተና ጋር እሳትና ጭድ በመሆኑ በፍፁም ማድረግ አይገባም።
.
ሠ. ስለራሳችን የሚገልፁ የፕሮፋይላችን ክፍሎችንም ከላይ ባሳለፍነው መልኩ ትኩረት ሳቢ እንዳይሆኑ ማድረግ። በምንወዳቸው መፅሐፍት፣ ቲቪ ሾው፣ ጥቅሶች የመሳሰሉ ፍላጎትን ማሳወቂያ ቦታዎች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ።
.
ረ. 'Intersted In' የሚመለውን ምርጫ መተው! ይህ ቦታ ፌስቡክን ለፆታዊ ፍላጎታቸው ማርኪያነት የሚቀላቀሉ ሰዎች ፍላጎታቸውን እንዲለዩበት የተቀመጠ ነው። (ባለማወቅ አንዳንዶች ተመሳሳይ ፆታቸውን ወይም ሁለቱንም ይጠቅሳሉ - ይህ ተቃራኒን ከመጥቀስ የባሰ ትርጉም አለው)
.
ሰ. 'Relationship Status' ላይ ትዳር እንደመሰረትን ለመግለፅ ካልሆነ በስተቀር ሌሎች አማራጮችን አለመጠቀም። ይህ በራሱ ሌላ ጥሪ ነውና!
.
ሸ. ፕሮፋይላችን ላይ የቤተሰብ አባላትን ስንጠቅስ እነርሱ በፎቶ እና መሰል ጉዳዮች ላይ የላላ አቋም ካላቸው የኛን ምስል ሊለቁ ስለሚችሉ ወይም የነርሱን በማየት ልቡ ላይ በሽታ ያለበት መጥፎ ግምት ውስጥ ሊገባ ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ።
.
ቀ. በመጨረሻም በዚህ ክፍል ከምናደርገው ጥንቃቄ አንዱ የትውልድ ዘመንን ግልፅ አለማድረግ ነው። ይህ ከሆነ መጥፎ ኒያ ያለው ሰው አይን ውስጥ አያስገባንም።
.
3. ጓደኝነትና መስተጋብር ...
.
ሀ. ፌስቡክ ላይ ጓደኛ እንዲሆኑን የምንፈቅድላቸውን ሰዎች ልንመርጥ ይገባል። መልካም ስብእና የሌላቸውን፣ ካፊሮችን እና ከሱና ጋር የማይገጥሙ አቋሞችን የሚያሰራጩ ሰዎች ለፈተና ቅርብ ናቸውና እነርሱን ከመጎዳኘት መቆጠብ ይኖርብናል። እንዲሁም ሀሰተኛ እንደሆኑ የምንጠረጥራቸውን አካውንቶች ከጓደኝነት ማቀብ።
.
ለ. ፌስቡክ ላይ ፍሬንድ ካደረግናቸው አካላት ጋር ሁሉ ትውውቅ ለመፍጠር አለመጣር። ራስን ለማሳወቅ አለመድከም።
.
ሐ. ፍሬንድ ካደረግናቸውም ይሁን ሌሎች የሚደረጉ ፓስቶችን ሁሉ ላይክ፣ ሼር ወይም ኮመንት ከማድረግ መቆጠብ። ይልቁን ጠቃሚ የሆኑትንና ከታማኝ ምንጭ የተገኙትን በአግባቡ መያዝ።
.
መ. ሌላው ምንም ፋይዳ ሊያገኝበት የማይችልበትን ፓስት ከማድረግ መታቀብ። ከምናውቃቸው ሰዎች ጋር ግላዊ ውይይቶችን በኮመንት ከማድረግ ይልቅ በውስጥ መስመር ማድረግ። ትኩረት ሊስቡ የሚችሉ ሌላውን ሊፈይዱ የማይችሉ ምልልሶችንም እዛው መጨረስ።
.
ሠ. ግለሰቦች ከሚለቁት ፎቶ፣ ግላዊ ፓስቶች የመሳሰሉ ቦታዎች ላይ ያለፋይዳ ኮመንት ከማድረግ መቆጠብ።
.
ረ. ዲናዊ ፓስቶችን በምናጋራበት ወቅት ወይም ኮመንት በምናደርግበት ወቅት ትኩረታችንን መልእክቱ ላይ ማድረግ። ግለሰቦችን ከእይታ ማውጣት። እኛም ይህን ስናደርግ ሰዎች በዚህ እይታ እንዲያዩት ማድረግ።
.
ሰ. ተሳትፎአችንን ተከትለው የሚመጡ አድናቆቶችን በተከፈተ ልብ አለመቀበል። አንድም ኒያችንን ሊያበላሽ ይችላል በሌላ ጎን ደግሞ በአድናቂዎች ላይ እንድናተኩር በር ይከፍታል።
.
ሸ. ጥያቄዎች ወይም ማብራሪያዎችን በተቻለ መጠን በኮመንት ለመጨረስ መሞከር። የኮመንት ምልልስ ላይ የተቃራኒ ፆታን ስም ከማቆላመጥ መቆጠብ፤ ጭፍን ከሆነ ድጋፍም ሆነ ግብዝ አለሁ ባይነት ራስን ማቀብ።
.
4. ሚሴጅ/ቻት!
.
ሀ. ከአላፊ አግዳሚ ወሬ ራስን ለመጠበቅ ቻትን 'Off' ማድረግ። አስፈላጊ ካልሆነ ሚሴንጀርም አለ
? قـ✑ـال الامـــام سفيــان الثــوري
رحمـہ اللـہ تعالــﮯ :
☜ وليڪن جليسك من يزهدك فـﮯ الدنيا ويرغبك فـﮯ الآخرة وإياك ومجالســة أهل الدنيا الذين يخوضــون فـﮯ حديث الدنيا، فإنهم يفسدون عليك دينك وقلبــك ....
?? سفيان الثوري / حلية الأولياء 【 ٨٢/٧ 】
ኢማሙ ሱፊያን አስሰውሪ አላህ ይዘንላቸውና እንድህ አሉ:
" አቀማማጭህ/ጓደኛህ ለዱኒያ(ድንበር የለሽ ፍቅር) ግድየለሽ የሚያደርግህ ለአኼራ (ደግሞ ) የሚያስከጅልህ/የሚያነሳሳህ ይሁን።
እነዚያን በዱኒያ ወሬ የሚሰምጡን የዱኒያ ባልተቤቶች አቀማማጮችን (ከመቀማመጥ ራቅ) አደራህን። እነርሱ በአንተ ላይ ድንህንም ቀልብህንም ያበላሻሉ…"
ሱፊያን አስሰውሪ/ሂልየቱል አውሊያእ [82/7]
https://t.me/Tewjihat
©?Tewjihat
Telegram
🌷ተዉጂሐት ሊል_ሙእሚናት🌷
ተዉጅሃት ሊልሙእሚናት ሙስሊም እህቶችን የሚመለከቱ ህግጋት የሚሰራጭበት ቻናል ነው Join እና ሸር ማርግውን አይርሱ***🌷*** Telegram***👇*** t.me/Tewjihat t.me/Sadatcom1 t.me/Menhaj\_Salafiya t.me/IbnuMuneworcom t.me/Muhammedsiragecom
? قـ✑ـال شيـخ الإســـلام ابن تيميــة
رحمــہ اللـہ تعالـــﮯ :
? وَحَســَدُ النِّسَــاءِ بَعْضِهِنَّ لِبَعْضِ ڪَثِيرٌ غَالِبٌ لَا سِيَّمَــا الْمُتَـــزَوِّجَاتُ بِــزَوْجِ وَاحــِدٍ فَإِنَّ الْمَرْأَةَ تَغَارُ عَلَى زَوْجِهــَا لِحَظِّهــَا مِنْــہُ فَإِنَّــہ بِسَبَبِ الْمُشَارَكَةِ يَفُوتُ بَعْضُ حَظِّهَا .
?? مجموع الفتاوى 【 ١٢٥/١٠ 】
ሸይኸል ኢስላም ኢብን ተይሚያ:·
【ሴቶች በሴቶች ላይ መቅናት በጣም ብዙ ነው። በተለይ አንድ ባል ስር ያሉ ሴቶች፣ ሴት (ሚስት) በባሏ ላይ ባላት እጣፈንታ(ድርሻ) ትቀናለች ምክኒያቱም አንድን ባል መጋራት አንዳንድ ድርሻዎቿን ሊያሳጣት ስለሚችል】 ይላሉ።
ምንጭ: · መጅሙዑል ፈታዋ (10/120)??
https://t.me/Tewjihat
© Tewjihat
" والمرأة ينبغي لها اذا خاطبت الاجانب أن تغلظ كلامها وتقويه ، ولا تلينه وتكسره ، فان ذلك أبعد من الريبة والطمع فيها ".
.
[] #ابن_القيم | #مفتاح_دار_السعادة ١ / ١١١ []
ኢብነል ቀይም አልጀውዚይ ረሂመሁሏሁ ተዓላ:·
《ሴት ልጅ አጅነቢይ(ባእድ ወይም ቅርብ ዘመዷ ያልሆነን) ወንድ ስታናግር ንግግሯን ከበድ እና ጠንከር ልታደርገው ይገባታል። ለስላሳ እና ሰበር ማድረግ የለባትም። ይህን ማድረጓ ከጥርጣሬ እና (በተቃራኒ ፆታ) በመጥፎ ከመከጀል ያርቃታል》ይላሉ።
ምንጭ ሚፍታሁ ዳሪ ሰዓዳህ 1/111
https://t.me.Tewjihat
©?Tewjihat
ደሽ ድን ያለው
ን የሱና አንበሳ የትዳር አጋርሽ ይሆን ዘንድ ፍቀጅ ምረጭ………
https://t.me/Tewjihat
©Tewjihat
Telegram
🌷ተዉጂሐት ሊል_ሙእሚናት🌷
ተዉጅሃት ሊልሙእሚናት ሙስሊም እህቶችን የሚመለከቱ ህግጋት የሚሰራጭበት ቻናል ነው Join እና ሸር ማርግውን አይርሱ***🌷*** Telegram***👇*** t.me/Tewjihat t.me/Sadatcom1 t.me/Menhaj\_Salafiya t.me/IbnuMuneworcom t.me/Muhammedsiragecom
?ሷሊሇ ሴትና በድን ላይ ያላት ኢስቲቃማ?
ሷሊሇ ሴት ማናት?
ኽፍል 4
ሷሊሇ ሴት የዱኒያንም ሆነ የአኼራን ስኬት ለመጎናፀፍ ድኗ በሚያዛት አውቃ በተግባር ላይ የምታውል እንቁ እንስት ናት።
ሷሊሇ ሴት ከድን የራቁ ሰዎችን ወዳጆቿ /ጓደኞቿ እንድሆኑ እንደማትፈቅደው ሁሉ ለድኑ ግደለሽ ተውሂድን ሱናን ወደሇላው ጥሎ በሽርክያትና ቢድዓ ፈጠራ የተጠመደን ወንድ የትዳር አጋሯ ይሆን ዘንድ በፍፁም አትፈቅድም።
ይህንንም የጌታዋን ቃል ታስታውሳለች :
( "ﻭﻟﻌﺒﺪ ﻣﺆﻣﻦ ﺧﻴﺮ ﻣﻦ ﻣﺸﺮﻙ ﻭﻟﻮ ﺃﻋﺠﺒﻜﻢ
አማኝ ወንድ ባሪያ ከአጋሪ ወንድ በላጭ ነው ፣ ይህ (አጋሪ በውበቱ ማማር) ቢያስድንቃችሁም እንኳን") የሚለውን
እንድሁም አላህ ዘንድ የበላጭነት መለኪያው ምን እንደሆነ በዚህ የጌታዋ ቃል ስለምታስታውስ:
( " ﺇﻥ ﺃﻛﺮﻣﻜﻢ ﻋﻨﺪ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﺗﻘﺎﻛﻢ
አላህ ዘንድ የተከበረው በላጫችሁ (አላህ ያዘዘውን ታዛዥ፣የከለከለውን ተከልካይ) ጥንቁቃችሁ ነው " )የሚለውን
እንድሁም የመልእክተኛውን (ሰለላህ ዐለይሂ ወሰለም)ን ይህን የሷሊህ ባል መገለጫ የተናገሩበትን ሀድስ አክብራ ተቀብላ ተግባር ላይ ታውላለች:
"ﺇﺫﺍ ﺟﺎﺀﻛﻢ ﻣﻦ ﺗﺮﺿﻮﻥ ﺩﻳﻨﻪ ﻭﺧﻠﻘﻪ ﻓﺄﻧﻜﺤﻮﻩ ، ﺇﻻ ﺗﻔﻌﻠﻮﺍ ﺗﻜﻦ ﻓﺘﻨﺔ ﻓﻲ ﺍﻷﺭﺽ ﻭﻓﺴﺎﺩ ﻋﺮﻳﺾ ) ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺘﺮﻣﺬﻱ 866 ﻭﺻﺤﺤﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ﻓﻲ ﺻﺤﻴﺢ ﺳﻨﻦ ﺍﻟﺘﺮﻣﺬﻱ 1084 .
ድኑንና ፀባዩን የምትወዱለት (አማኝ ወንድ ) መጥቷችሁ (ሴት ልጃችሁን ከጠየቀ) አጋቡት፣
ይህን ካልፈፀማችሁ (አንሰጥም) ካላችሁ በመሬት ላይ ፈተና ትልቅ ብልሽት እንደምትሆን እወቁ !"
ይህ ነው የሷሊሇ እንስት የትዳር አጋሯ ይሆን ዘንድ መምረጫ መስፈርቷ ። ከሁሉም ፊት ድንን የምታስቀድም ። በድኑ ላይ ጀግና የሆነ በተውሂዱ በመንሃጁ ሱናንን በመከተል ቀጥ ያለውን ፣ ሶላቱን በመጠበቅ ጥንቁቅ የሆነ ከጀማዓ በመቦዘን ወደ ሇላ የማይለውን፣ በጥሩ ስነ ምግባሩ የተመሰገነውን መልካም ባል ነው አጋሯ ይሆን ዘንድ የምትፈቅደው፣ የልጆቿ አባት ይሆን ዘንድ የምትፈቅደው። አላህ ፈቅዶት ከድኑ በተጨማሪ ሌሎች ፀጋዎች ከተገኙላት ማሻአላህ ካልሆነ ግን ሃብትና ውበት አለው ብላ ለድኑ ግደለሽ ሁለመናው ሱና ያልሸተተው ዋልጌ ወሰላታ በሃብቱና ውበቱ ተሸንግላ ገብታ ለቅኝ ግዛት ባርነት (በድን መመሪያ የማይኖሩበት) ሂዎትን መኖርን በፍፁም አትፈቅድም።
ይህች ጠንካራ ሷሊህ ሴት በሁለ ነገሯ መንፈሰ ጠንካራ በቀዷና ቀደር ጠንካራ እምነት ያላት በጌታዋ ላይ ያላት ተወኩል ዝንፍ የማይል የሆነች አላህ ሷሊህን ባል ወፍቋት የሚጣፍጥ ሂዎትን እያጣጣሙ ቆይተው የአላህ ቀደር ሆኖ ሷሊሁ ባሏ ወደ አኼራ ቢቀደም። በደረሰባት ሙሲባ ተስፋ ቆርጣ በድኗ የሇሊት አፈግፍጋ ፈትልን ፈትላ መልሳ እንደምትተረትረው ከንቱ ለፊ ሴት አይደለችም ። ይልቁንም በደረሰባት ሙሲባ ለጌታዋ ስትል ታግሳ አመስግናው የእርሱን እዝነት ከጅላ በድኗ ላይ ቀጥ የምትል ባሏ ትቷቸው የሄዳቸውን ልጆቹን በኢስላማዊው ተርቢያ ላይ ቀርፃ የምታሳድግና በአላህ ፍቃድ ለድኑ አገልጋይ ለእናትና አባታቸው ዱዓ የሚያደርጉን ሷሊህ ጅግና ጀግና ልጆችን የምታፈራ የምታበቃ እንቁ ጀግና እንስት ናት።
አንችስ የትዳር አጋርሽን ስትመርጭ ቅደመ መስፈርትሽ ሀብትና ውበት የሆነው ሙስሊሟ እህት! በተለይ ወደ ድን ተጠግተሽ በሱና ላይ ጠካራ መስለሽ የምትታይው ነገር ግን የትዳር አጋርሽን የመምረጥ ጊዜ ወኔሽ ተልፈስፍሶ አይንሽ ወዳ ወድህ እያለ የምታማትሪው፣ ሃብት ያለው ውበት ያለው እያልሽ ! ግንኮ ምነው ሀብትና ውበትን የሚያሳምራቸው ዋናው መሰረት ላይ ለመካብ በፈለግሻቸው ከታላቁ የድን መሰረት ላይ ለመገንባት በሞከርሻቸው ባልከፋ ነበር። ነገሩ ግን የተገላቢጦሽ ሆኖብሽ የወደፊት መዘዙን ቆም ብሎ ማሰብ አቅቶሽ የጊዚያዊ ሸህዋ ስሜት ጋርዶሽ ሀብትና ውበት ብቻ ስላለው ብቻ አግብተሽው ባሰብሽው መንገድ ሁሉን በእጅሽ ሁሉን በደጅሽ የምታደርጊው መስሎ ታይቶሽ ከሆነ በጣሙን ተሳስተሻል።
እስኪ የአንችን አስተሳሰብ አስባ ወይም የዱኒያ ባሪያ በሆኑ ቤተሰብ ተገዳ ሀብት ስላለው ብቻ ለድኑ ግደለሽ ለዋጅባቶች ዝንጉ፣ የሱና ኑሮች /ብርሃኖች ከላይቱ ላይ የተገፈፉ ሀሳቡና ጭንቀቱ ጧት ማታ በዱኒያ የተጠመደ ዱኒያን የት ገባሽ የት ወጣሽ ብሎ እያሳደደ ምንም እንኳ በዱኒያ ቁሳቁስ ቤቱን ያጨናነቀ ቢሆንም ነገር ግን በቤቱ የአላህ ቃል የማይሰማበት፣ የነብዩ(ሰለላህ ዐለይሂ ወሰለም ሀድስ የማይነገርበት) ፣አዝካሮች የማይደረግበት ፣አምፖል ብቻ እንጅ እውነተኛው ብርሃን የሌለበት ቤት ፣ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የሚያኖራትን ድን የለሽ የዱኒያ ባሪያ አግብታ ገንዘብ ስላለው ብቻ ያለ ርህራሄ ረግጦ የሚይዛትና ሃብቱን ላለማጣትና የወለደቻቸውን ልጆች ሂወት ምስቅልቅልነት በመፍራት ትክክለኛ ድናዊ ምሪት ያለበትን ሂወት ተነፍጋ በጭንቀትና ትካዜ የምትኖር መላቀቅ አቅቷት እርሷንም የዱኒያ ባሪያ ካደረጋት የትዳር አጋር ዘንድ እውነተኛውን የልብ ደስታ አገኘሁ ብላ ያወራችሽ ታውቂያለሽ ? በፍፁም ! በእርግጥ ቅል ግጣሙን አያጣም እንድሉ ምን አልባት እርሷም ደዩስ እርሱም ደዩሶች ለድን ግደለሾች ሆነው የሚገናኙ ለጊዜው በዱኒያዊ ማቴሪያል ጅስማቸው ወፍሮ ጥርሳቸው የሳቁ የመሰሉ ግን ቀልባቸው በኢማን ድርቅ የተመታች ምላሳቸው አላህን ከመዝከር የታሰረች እይታቸው በሃራም ነገሮች የፈዘዘች ጆሮቸው በዛዛታና ክልክል ድምፆች የደነቆረች …… እውነተኛውን የልብ ደስታ አጥተውት የሚሰቃዩን ታይ ይሆናል ግን እንደት ተብሎ በጊዘያዊ የዱኒያ ማቴሪያል ጠፊ ብሊጭታዎች የልብ ደስታ ይገኛል።
ስለዚህ እህቴ የትዳር አጋርሽን ስትመርጭ ሇላ ከመሟቀቅ አስቀድሞ ለመጠንቀቅ ሰበቡን አድርሽ ከምንም በፊት ቅድሚያ ለድኑ ምረጭ! አላህ ፈቅዶት ከድኑ በተጨማሪ ሌሎች መልካም ፀጋዎች ከተገኙ ማሻአላህ ይበልጥ አማረ። ካልሆነ ግን ድን ያለው ድሃና ከድን የተራቆተ ሃብታም ቢመጡልሽ ድን ያለውን ምረጭ። ለታላቁ የሰለፍ ዐሊም ሀሰነልበስሪ ተጠይቀው እንደመለሱት" ሴት ልጅ ነበረችኝ ልትታጭ ነበር ለማን ልዳራት ብሎ" ጠያቂው ሲጠይቃቸው እርሳቸውም እንድህ አሉት " አላህን ለሚፈራው ዳራት ከወደዳት ይንከባከባታል ያከብራታል፣ ከጠላት ደግሞ አይበድላትም" አሉት ።
ይህ ነው እውነታው ድን ያለው አይበድልሽ ሁሉን ነገር ለአላህ ሲል ይታገስሻል ፣ አልሆን ብሎ መለየት ካሰፈለገ በሰላም ያለበደል ወደ ቤተሰቦችሽ ይመልስሻል።
እህቴ እዚህ ላይ የማስታውስሽን እንድታሰምሪልኝ የምፈልገው ሴት እንደ መሆንሽ መጠን የትዳር አጋርሽን ስትመርጭ አንች ለጊዜው ያለሽበትን ጥንካሬ አይተሽ አይንሽ ያረፈበትን ድን የለሽን ተውሂድ የለሽ ከሱና ያፈነገጠን ጫት ቃሚ ሱሰኛ ወንድ አግብቼ ሇላ በምፈልገው አሽከረክረዋለሁ ብለሽ ለማግባት አስበሽ የተነሳሽ ከወድሁ ተጠንቀቂው ሇላ አንችኑ አሽከርክሮ ለጫት ቂምሃው ቡና አፍሊ ካዳም አድርጎ እንዳያስቀርሽ።
ይህ የእቀይራታለሁ እቀይረዋለሁ የሚባል ቀመር ብዙ ጊዜ የታሰበው እንደታሰበው ሆኖ ሳይገኝ ሲቀርና ከባድ ዋጋ እያሰከተለ ሲገኝ መመልከቱ አድስ አይደለም ከሌሎች መማር ተገቢ ነው። ምክንያቱ ሂድያተ ተውፊቅ/የመገጠም ቅናቻ አላህ ብቻ ስለሆነ የሚሰጠው። በተለይ ሴት እህት ጠንካራ ነኝ ብላ ብታሰብም ወንድ ላይ ተፅኖ አድርጋ ከመጥፎ የመመለስ ሰበቧ አቅሟ አናሳ ነው ስለዚህ ጨለምተኛ ሂዎት ውስጥ ገብቶ ከመሰቃየት በፊት ከወድሁ ጥንቃቄ ወስ
A place to learn English easily.
Owner - @Samson_G
Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian
Last updated 2 weeks, 2 days ago
NGO, የመንግስት እና የግል ድርጅቶች የስራ ማስታወቂያ እና ነፃ የትምህርት እድሎችን ያገኛሉ ቤተሰበ ይሁኑ ሌሎችንም ይጋብዙ
ለማስታወቂያ @Human133 ላይ አናግሩን
We need promoters
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12
Last updated 4 months, 2 weeks ago