The official Telegram on Telegram. Much recursion. Very Telegram. Wow.
Last updated 1 month, 2 weeks ago
🌐 https://ipapkorn.github.io
Stay connected with the latest iPapkorn Bots and News 🗞️
Bots: https://t.me/iPapkornBots/2
Last updated 2 months, 1 week ago
Breaking News | Observing world events unfold in the grand theater of our time.
Last updated 3 weeks, 3 days ago
“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)
ካለኝ ከ30 በላይ መጽሐፍት የመጻፍ ልምድ በመነሳት የመጽሐፍን አጻጻፍ ክህሎት የማዳበርን መንገድ እንዳሰለጥናቸው የሚጠይቁኝ ሰዎች በመበራከታቸው ምክንያት አጠር ያለች ስልጠናን አዘጋጅቻለሁ፡፡
• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)
• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡
• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ
ስልጠናው ከሚዳስሳቸው ዋና ዋና ርእሶች መካከል ጥቂቶቹ:-
የሕትመት አስፈላጊነት ጠቅላላ መረጃዎች
የጽሑፍ ጥቅሞች
የተለያዩ የግንኙነት (communication) አይነቶች ትርጉም (ጽሑፍን ጨምሮ)
ለምን፣ ለማን፣ ምን መጻፍ ፈለኩ?
የጽሑፍ አይነቶች
የመጽሐፉ ንድፍና ፍሰት
ከጽሑፍ ጅማሬ እስከማሳተም ያሉ ሂደቶች
Dr. Eyob Mamo
የልዩነቴ ዋጋ!
ልዩ ሰው መሆኔ ሁለት አይነት ዋጋን ያስከፍለኛል፡፡ ከሁለቱ አንዱን የመምረጥ መብቱ ግን አለኝ፡፡
አንደኛው ዋጋ፣ ፈጣሪ የሰጠኝን እኔነቴንና ራሴን በመሆኔና እንዲሁም የማምንበትን እውነት በመኖሬ ምክንያት ያንን የማይቀበሉ ሰዎችን ሲለዩኝና እንደእነሱ ስላልሆንኩኝ ሲቃወሙኝ የምከፍው ዋጋ ነው፡፡ ይህ ዋጋ ሰዎችን የማጣት ዋጋ ነው፡፡
ሌላኛው ደግሞ ልዩነቴን ላልተቀበሉ ሰዎቸ ስል ራሴን ትቼ እንደሌላው ሰው ለመኖር በመሞከሬ የምከፍለው ዋጋ ነው፡፡ ይህ ዋጋ ራስን የማጣት ዋጋ ነው፡፡
ለሰዎች ብሎ ማንነትን ትቶ መሄድ እጅግ የከፋ ዋጋ ያስከፍላ፡፡ ራስን ሆኖ በመኖር ግን ምንም እንኳን ሰዎች ባጣቸውና ሰዎች ቢቃወሙኝ ራሴንና ዓላማዬን አገኛለሁ፡፡ ምንም እኳን ከእነሱ ጋር ባልስማማም፣ ከራሴ ጋር ግን እስማማለሁ፡፡
የብዙ ሰዎች ማሕበራዊ ችግርና ቀውስ ያለው እዚህ ላይ ነው፤ ሌላውን ሰው ላለማጣት ሲሉ ራሳቸውን ማጣታቸው!
እንግዲህ ምረጡ! ለሰው ብላችሁ ማንነታችሁን ትታችሁ በመሄድ ሰዎችን አግኝታችሁ በሂደቱ ራሳችሁን ማጣት ይሻላችኋል ወይስ ማንነታችሁን ኖራችሁ በሂደቱ አንዳንድ ሰዎችን አጥታችሁ ራሳችሁን ብታገኙ?
ሰዎችን ላለማጣት ብሎ ራስን የማጣት ሁኔታ . . .
ሰዎችን ሁሉ አስደሳች ለመሆን ከመፈለግ ይመጣል
ውጥረት ወይም አለመግባባት እንዳይከሰት ከመታገል ዝንባሌ ይመጣል
ለሰዎች የቀይ መስመር የማስመር አቅም ከማጣት ወይም ብልሃቱን ካለማወቅ ይመጣል
የራስ ዓላማ እና አቋም ካመኖር ይመጣል
ለመደምደም ያህል፡- ራስንና ያመኑበትን መኖር፣ አላስፈላጊ ሰዎችን ከሕይወታችሁ የማጥራት ከፍተኛ አቅም እንዳለው በመገንዘብ ይህንን ከባድ፣ ነገር ግን አስገራሚ ጉዞ አሁኑኑ እድትጀምሩ ላነሳሳችሁ፡፡
የልዩነቴ ዋጋ!
ከልዩነት ባሻገር!
ልዩነቱ የዘር፣ የቋንቋ፣ የመልክ፣ የቁመናም ሆነ የእምነት . . . ከእናንተ ለየት የሚለው ሰው በአካባቢያችሁ ሲሰራም ሆነ ሲኖር፣ ለየት ያለ ሰው በመሆኑ ምክንያት ከእናንተ ምንም አይነት ጥቃት፣ በደልና መገለል እንደማይደርስበት እንዲሰማው የማድረግ ሃላፊነት እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ፡፡ ይህንን ሃላፊነት መወጣት የትክክለኛ ስብእና ምልክቱ ነው፡፡
የእኛ ዘር፣ ቋንቋ፣ መልክ፣ ቁመና እና እምነት ያለው እኛን መሰል ሰው የሚጠቃበት፣ የሚበደልበትና የሚገለልበት አካባቢ እንዳለ አትዘንጉ፡፡ እኛ እዚህ በሌላው ላይ የምናደርገውን ሌሎች እዚያ በእኛ እና እኛን በመሰሉት ላይ ያደርጉታል፡፡ ዑደቱ ይኸው ነው፡፡
የጨዋነት ሁሉ ጨዋነት ከእኛ ለየት ያሉትን የመቻልና የመቀበል ጨዋነት ነው!
መልካም ቀን!
አድናቂያችሁ ነኝ!
• ሌላ አማራጭ መከተል ስትችሉ የምትወዷቸውን ቤተሰቦቻችሁን መርዳት ስላለባችሁ ብቻ የማትፈልጉትን ስራ ለምትሰሩ፣
• ትዳር ይዛችሁ የግል ሕይወታችሁን መኖር ስትችሉ እናንተ ከሄዳችሁ ደጋፊ ለሌላቸው ሰዎች ስትሉ እቅዳችሁን ይቆይልኝ ላላችሁ፣
• ሌላ ስፍራ ሄዳችሁ መኖር ስትችሉ የእናንተ በአካባቢው መገኘት ለሕልውናቸው ወሳኝ ለሆነላቸው ሰዎች ስትሉ እግራችሁን ለሰበሰባችሁ፣
• ሌላ ሕይወት መጀመር ስትችሉ ለልጆችሁ ስትሉ ለጊዜውም ቢሆን የብቸኝነትን ኑሮ ይዛችሁ ለምትታገሉ ብቸኛ ወላጆች (Single Parents)፣
• ለተደረገባችሁ ክፉ ነገር አጸፋ ብትመልሱ ለብዙ አመታት የተገነባ ነገር እንዳይፈርስ በማለት ብዙ ነገር በትእግስትና በዝምታ ለተሸከማችሁ፣
ለእናንተና መሰሎቻችሁ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት አለኝ!
ፈጣሪ ያግዛችሁ! ይካሳችሁ! ለሌላው ብላችሁ ለእናንተ የሚበጀውን በተዋችሁት ሁሉ በብዙ እጥፍ ይስጣችሁ!
ሁሌም አድናቂያችሁ ነኝ!
እንኳን በሕይወት ነቃችሁ!
በሰላም ስላደራችሁ ደስ ይበላችሁ!
በዓለም ላይ በቀን ወደ አንድ መቶ ሺህ (100 ሺህ) አካባቢ አይሮፕላኖች እየተነሱ በሰላም ያሰቡበት በመድረስ ያርፋሉ፡፡ ከእነዚህ በረራዎች መካከል ግን የአንዱም እንኳን በሰላም መግባት በዜናዎች ላይ ሲነገር አንሰማም፡፡ ሆኖም፣ አንድ በረራ ላይ አደጋ ከደረሰ ግን ትኩረት ይስባል፣ ዜናውን ይሞላዋል፣ ወሬው ይሸጣል፡፡
የአንድ ጤናማ ሰው ልብም ቢሆን በቀን ወደ አንድ መቶ ሺህ (100 ሺህ) አካባቢ ይመታል፡፡ ይህንን ያህል ጠንክሮ የሚሰራው አካላችን ግን በቀን ውስጥ ትዝም አይለን፡፡ የምናስታውሰው መምታት ለማቆም ሲዳዳውና የምቱ ድግግሞሽ ሲለይብን ነው፡፡ ለምን? መልካሙ ነገር ተለምዷል፡፡ የምስራች የሆነው ነገር ትዝም አይለን፡፡
ዛሬ መልካም መልካሙን ላስታውሳችሁ፡፡ ዛሬ የምስራቹ ትዝ ይበላችሁ፡፡ በሰላም የመንቃታችሁ ጉዳይ፣ በሌሎች ላይ የደረሰ እናንተ ላይ ያለመድረሱ ጉዳይ፣ የደረሰባችሁ ነገር ከዚህ የከፋ ያለመሆኑ ጉዳይ . . . ትዝ ይበላችሁ፡፡
ከደረሰብን ክፉ ነገር የሆነልን መልካም ነገር ይበዛልና ደስ ይበላችሁ፡፡
ፈጣሪን አመስግኑ! ቤተሰቦቻችሁን፣ ጓደኞቻችሁንና በሕይወታችሁ ላይ መልካም ተጽእኖ ያደረጉ ሰዎችን አድንቁ!
መልካም ቀን!
ሁለት የደስታ እውነታዎች
ለራሳችሁ ደስተኛነት ሃላፊነቱን መውሰድ ያለባችሁ ራሳችሁ መሆናችሁን ለአፍታም አትዘንጉ፡፡
ሰዎች ደስተኛ እንዲያደርጓችሁ በጠበቃችሁ ቁጥር እንዳዘናችሁና እንደተጎዳችሁ ትኖራላችሁ፡፡
በዚያ ምትክ፣ ሰዎች ደስ የሚያሰኛችሁን ሲያደርጉላችሁ አመስግኑ፣ የጠበቃችሁትን ካላገኛች ግን ከራሳችሁ ጋር በደስተኛነት መኖርል ልመዱ፡፡
በሌላ አገላለጸ፣ ከሰዎች ውጪ ደስተኛ መሆንን ተለማመዱ!
ሰዎች ያደረጉትንና ያላደረጉትን ከመቁጠር ይልቅ ፈጣሪ ያደረገላችሁን እያሰባችሁ በደስተኛነት መኖር ልመዱ!
በተመሳሳይ ሁኔታ ለሌሎች ሰዎች ደስተኛነት እናንተ ሃላፊነትን አትውሰዱ፡፡
ሰዎችን ደስተኛ ለማድረግ በታገላችሁ ቁጥር ከማንነታችሁ፣ ከዓላማችሁና ራሳችሁን ሆናችሁ ከመኖር እየራቃችሁ ትሄዳላችሁ፡፡
በዚያ ምትክ፣ ለሰዎች መልካም ነገር አድርጉ፣ ደስተኛ የመሆንንና ያለመሆንን ምርጫ ግን ለእነሱ መተውን ተለማመዱ፡፡
በሌላ አገላለጸ፣ ከሰዎች ደስተኛነት ውጪ ሙሉ ሕይወት መኖርን ተለማመዱ!
ሰዎች በእናንተ የመደሰታቸውንና ያለመደሰታቸውን ሁኔታ ከመቁጠር ይልቅ ለሰዎቹ ማድረግ የቻላችሁትን ነገር ለማድረግ ፈጣሪ ስለረዳችሁ እያሰባችሁ በደስተኛነት መኖር ልመዱ!
The official Telegram on Telegram. Much recursion. Very Telegram. Wow.
Last updated 1 month, 2 weeks ago
🌐 https://ipapkorn.github.io
Stay connected with the latest iPapkorn Bots and News 🗞️
Bots: https://t.me/iPapkornBots/2
Last updated 2 months, 1 week ago
Breaking News | Observing world events unfold in the grand theater of our time.
Last updated 3 weeks, 3 days ago