ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 10 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 6 days, 14 hours ago
BoA Social media links
https://www.facebook.com/BoAeth
https://www.instagram.com/abyssinia_bank
https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot
Last updated 3 weeks, 1 day ago
ብርዕ- በደም ዕንባ!
(ሙሉጌታ ተስፋዬ- አያ ሙሌ)
በኔው ‘ኔ ጥራና
በኔው ኔ’ ብራና
ባዕሜ ቀሰም ብርዕ – በህይወት ማቅለሚያው
ጠርቤ ስለቁጥ
የኑሮን ሽቁጥቁጥ
የራሴ ጉልቻ…አንገቴ አለ ዘምበል
የደም ወዜ ጠለል…እንባዬ አለ ከምበል
በሞት ሞት ጣረሞት…በልቤ ልብ በል!
ስጋት እንደ ውጋት
ነፍሴን ሲሰንጋት
በቅኔ እንቆቅልሽ…ቁልቁል ተቆልፌ
በእምነት…እምም እመ-እዝነት
በህልም ዓለም ሽምጥ…ግልቢያ ተሰልፌ
ለሥጋ ታርቄ -ለገላ መርቄ
እርቃኔን ወጥቼ-ግብኔን አስጥቼ
የጎኔን ጨረስሁት ሆዴን ስሸነግል
ለነገ ራሴ ስንቅ – ለቋንጣዬ አገልግል
ካምና ከታችአምናው
የጉልበት የጤናው
ቢታይ ሁለንተናው- ሁሉ ሁለመናው
የልቤ ልብ በል – ለልቤ ሲጠናው
ብቻ ላይኔ ብቻ- ላይኔ ለብረቱ- ላይኔ ብቻ ቀናው!
ለታይታ ለዝናው
በሰው ፊት በሸንጎ ለወግ ማ’ረግ ዝናው!
አዎ! በኔው ‘ኔ ጥራና
በኔው ኔ’ ብራና
በብርዔ ስከቁጥ-የኑሮን ሽቁጥቁጥ
ደም እንባ- ደም እንባ- እንበለ እንባ ደም
ሕይወት እንጉርጉሮ- በአታሞ አይታደም
(ለሚንቁኝ ለማያውቁኝ
29/07/1984
(የባለቅኔ ምህላ ገጽ 1)
ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ለማንኛውም አስተያየት እንዲሁም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል [email protected]
ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!
Telegram
ባይራ |Bayra
ዲጂታል መጽሔት (Digital Magazine) ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/ ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital ለማንኛውም አስተያየት ኢ-ሜይል [email protected]
እንኳን ደስ አለን።
የወርቅ ሜዳልያ በማራቶን።
ፓሪስ ኦሎምፒክ 2024
ከአዲስ የኦሎምፒክ ማራቶን ክብረወሰን ጋር!
በታምራት ቶላ!!!
ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!
ሰላም ውድ የባይራ ዲጂታል መጽሔት ቤተሰቦች
እስካሁን ድረስ በሰባት እትሞች ወደ እናንተ ያደረስናቸውን ጽሑፎች በሙሉ ከድረ ገጻችን ላይ ስለጫንናቸው ድረ ገጻችንን እየጎበኛችሁ ማንበብ እንደምትችሉ ስናሳውቅ ደስ እያለን ነው፡፡
ለሌሎችም ይደርስ ዘንድ በቅንነት ስለምታጋሩልን አከባሪያችሁ ነን፡፡
ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ለማንኛውም አስተያየት እንዲሁም ጽሑፍ ለመላክ
ኢ-ሜይል [email protected]
ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!
እነሆ
ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ባይራ ቅጽ 1 ቁጥር 7
•telegram- t.me/Bayradigital
•Website- bayradigital.com
•Facebook - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
•Twitter- x.com/BayraDigital
•ለማንኛውም አስተያየት: [email protected]
ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!
ስነ ምግባር የራቀው የስነ ጽሑፉችን ቀጠና
ሲራክ ወንድሙ
የዓለም ሁለንተናዊ የኑረት መስተጋብር ጥበብ በነካው መዳፍ ቢዳሰስ የተሻለ ነው ከሚሉት ወገን ነኝ። ጥንት የሰው ልጅ ራሱን በልቦና ሀዲዱ ላይ እስካወቀበት ጊዜ ድረስ በመሰልቸት የተቃኘውን የኑረት ቀለም ጥበብ በመሰሉ ወልጣቀኞች ኩሎ ተግ ማለት የጀመረው እሳትን ካገኘበት ... ፣ ረጅም እንጨት ጠርቦ መሬት ከቆፈረበት በዚያ ከድንጋይ ዘመን መለስ ነው።
የቤቱን ጎጆ ሲያቀና ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ ለነፍሱ እሴት እፎይታ በሚሰጠው ወሰን ይበለጥ ነበር። በተለይ ባደግሁበት የገጠር ከባቢ የቤቶቻቸውን ግድግዳ በነጭ የኖራ ቀለም ቀብተው የሚያምር የግድግዳ ስዕል፣ ጥቅስና መሰል ምልክቶችን በፊት ለፊቱ ላይ በሚያስውቡ ጥበበኛ እጆች በዝቶ ይጎላ ነበር። ከጎጆ ቤታቸው ከፈፍ ላይም ልክ እንደ ቤተስኪያን ጉልላት የተለያዩ ከጥቅም ውጭ የሆኑ መገልገያዎችን ማስቀመጥ ሌላ የውበት መቸርን ቀለም ይጎዘጉዙበት ነበር። ከጉበኑ ከባቢ ታዛው ላይ የሚሰራው ና በየወቅቱ በስስ እበት የሚለቀለቀው መልኛ መደብ - አባወራው አመሻሹን ተቀምጦበት ውጭ ውጪውን የሚታዘብበት ዓለምን የማያ መድረኩ ነች። ይህን የደቡብ የስነ ውበት ጠልሰማዊ ፍሰት እኔ ከኖርኩበት ዳርቻ ጋር አገናኘሁት እንጂ በሁሉም ከባቢ ይሄን የመሰለ የአኗኗር ጥበባዊ ክዋኔ ያረፈበት ውበታዊ ግዝፈት እንዳለ አለፍ ገደም ስል ያስተዋልሁት ነው።
ጥበብን እንደቅንጦት ከማይመለከቱት ወገን ነኝ። ጥበብ የአንድን ነገር መነሻ ና መድረሻ እይታው ውበታዊ እውቀታዊ በሆነ መንገድ ለማሳየት የምንጠቀምበት መስመር ሲሆን፤ ቅንጦት ግን ለስሜታዊ ግለት ብቻ በመሸነፍ እጃችን ላይ ያለውን አዱኛ የምንከትበት እመቀ መቃት ነው።
ካለ ጥበብ የነቃ ጎጆ በራድ ነው። የአንድን ቁስ አካልም ይሁን ሌላ ነገር ካለ ጥበብ መስራት የሚቻል ሲሆን ጥበብን አልብሶ ማበጀት ደግሞ ሩቅ እንዲሻገር ያደርገዋል። የሚለው ነጥብ ደግሞ የማያሻማ እውነታ መሆኑን እገነዘባለሁ።
የሰለጠነ ሰው ደጅ እያንዳንዱ እርምጃ የጥበብ ሸማን ይለብሳል። የውበት ቅኔን ይደርሳል። በዘፈቀደ ተሂዶ - በዘበት መመለስ እርም ነው። ትንሽም ቢሆን የጥበብ እጅ መንሻ ያልታከለበት ማንኛውም ነገር አድሮ ከመሻገት አይጎድልም።
በሰው መሻት ውስጥ ስፍር የሌለው ደካ ነው። እውነት የተራራን ያህል የገዘፈ የአለትን ያህል የጠነከረ የፍለጋ ዳርቻ ነው።
ሰው እውነቱን ፍለጋ ሲወጣ መባከን እንዳይስበው፣ የድል ስምረት እንዳይከዳው፣ ከጉዘቱ ጋር የሚያስፈልጉትን ሰንሰለቶች ጤነኝነታቸውን እየመጠነ ዘለበቱን በመልክ በመልክ ያበጀዋል። ያደረጀዋል። የማጣት ፀሀይ እንዳትወጣበት የጥበብ ጀምበሩን ይዋጅበታል። ችክ ያለ ነገር ሁሌም ቢሆን ለቅርብ ምክነት ተጠቂ ነው።
ይህ ከላይ ያነሳነው ሟቹ መንገደኛው ሰው ለመንገድ ስምረትና ህብረት በዘገነው እፍኝ ዳር የሚነሰንሰው ብዙ ነገር አለው።
(ከባይራ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ አንድ ቁጥር 7 የተቀነጨበ)
ሙሉውን ለማንበብ የቴሌግራም ገጻችንን ይቀላቀሉ፡፡
https://t.me/Bayradigital
በሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችም ያገኙናል፡፡ ቤተሰብ ይሁኑ፡፡
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ለማንኛውም አስተያየት
ኢ-ሜይል [email protected]
ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!
Telegram
ባይራ |Bayra
ዲጂታል መጽሔት (Digital Magazine) ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/ ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital ለማንኛውም አስተያየት ኢ-ሜይል [email protected]
ሰቆቃዎ ጴጥሮስ
...... ...... ........ .......
አዬ ምነው እመብርሀን
ኢትዮጵያን ጨከንሽባት
ምነው ቀኝሽን እረሳሻት
እስከመቼ ድረስ እንዲህ መቀነትሽን ታጠብቂባት
ልቦናሽን ታዞሪባት
ፈተናዋን ሰቀቀኗን ጣሯን ይበቃል ሳትያት
አላንቺ እኮ ማንም የላት
አውሮፓ እንደሁ ትናጋዋን በፋሺስታዊ ነቀርሳ
ታርሳ ተምሳ በስብሳ
ምድራዊ እባጭ ጫንቃዋን እንደ ኮረብታ ተጭኗት
ቀና ብላ እውነት እንዳታይ አንገቷን ቁልቁል ጠምዝዟት
ነፍሷን ድጦ ያስበረከካት ስልጡን ብኩን መፃጉዕ ናት
እና ፈርቼ እንዳልባክን ሲርቀኝ የሀይልሽ ውጋጋን
አንቺ ካጠገቤ አትራቂ በርታ በይኝ እመብርሀን
ቃልኪዳኔን እንዳልረሳት እንዳልዘነጋት ኢትዮጵያን
አዎን ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ
እማማ ኢትዮጵያን መንፈሴ ተፈትቶ እንዳይክዳት ሰጋሁ
አዋጅ የምስራች ብዬ የትብት ምግቤን ገድፌ
ከእናቴ ማህፀን አልፌ በኢትዮጵያ ማህፀን አርፌ
ካፈሯ አጥንቴን ቀፍፌ ደሜን ከደሟ አጠንፍፌ
ከወዟ ወዜን ቀፍፌ
በህፃን እግሬ ድኬባት በህልም አክናፌ ከንፌ
እረኝነቴን በሰብሏ በምድሯ ላብ አሳልፌ
ከጫጩት እና ከጥጃ ከግልገል ጋር ተቃቅፌ
በጋው የረኛ አደባባይ ክረምት እንደ ወዙ ፍሳሽ
በገጠር የደመና ዳስ በገደል የሸለቆ አዳራሽ
ከቆቅና ከሚዳቋ ከጅግራ ጠረን ስተሻሽ
በወንዝ አፋፍ ሐረግ ዝላይ መወርወር መንጠልጠል ጢሎሽ
ከፍልፈል ጋር እሩጫ ስገጥም ከቀበሮ ድብብቆሽ
ከራዳ ጫፍ ሳር ለግት ላሜ ትንሽ ግጦሽ
ለጥጃዬ የሌት ግርዶሽ
ለጥማድ በሬዎቼ እራት ለማታቸው ጥቂት ድርቆሽ
ለግልገሌ ከአውሬ ከለል እማሳው ስር ጎጆ መትከል
ለፀሐይ የሾላ ጠለል ለዝናብ የገሳ ጠለል
ውሎ የንብ ቀፎ ማሰስ ያበባ እምቡጥ ሲፈነዳ
የግጦሽ ሳር ሲለመልም ሲሰማሩ ሰደድ ሜዳ
አዝመራው ጣል ከምበል ሲል ከብቱ ለሆራ ሲነዳ
ፈረስ ግልቢያ ስሸመጥጥ ከወፎች ዜማ ስቀዳ
ልቤ በንፋስ ተንሳፎ በዋሽንት ዋይታ ሲከዳ
ያቺን ነው ኢትዮጵያ የምላት
እመብርሀን ምነው እረሳሻት
ያቺን የልጅነት ምስራች የህፃንነት ብስራት
የሳቅ የፍንደቃ ዘመን የምኞት የተስፋ ብፅዓት
ያቺን የልጅነት እናት
አዛኝቱ እንዴት ብለሽ ጥርሶችሽን ትነክሺባት
ስሜን በስምሽ ሰይሜ ባገልግሎትሽ ስዋትት
ከዜማ ቤት ቅኔ ቤት ከድጓ ቤት መጻህፍት
ካንቺ ተቆራኝታ እድሌ ካንቺ ተቆራኝታ ነፍሴ
ከቀፈፋ ደጀ ሰላም ከቤተልሄም ቅዳሴ
አኮ... ቀዶ.. ቀፍፎ .... ዳባ ለብሶ
ቅኔ ዘርፎ .....ግስ ገሶ
መቅደስ አጥኖ ማሕሌት ቆሞ
በልብሰ ተክሕኖ አጊጦ በብር አክሊል ተሸልሞ
እመብርሀን ያንቺ ፅላት ነፍሴ ላይ በሳት ታትሞ
የመናኒው የአባ ተድላ ርድ ሆኜ አብሮኝ ታድሞ
ሕይወቴ እምነትሽን ፀንሶ
ስጋ ፈቃዴ ተድሶ
ለሕንፃሽ መዲና ቆሞ ለክብርሽ ድባብ ምሰሶ
ስሜን በስምሽ ሰይሜ ሆነሽኝ የእምነቴ ፋኖስ
ለዋዜማሽ ግሸን ማርያም ለክብርሽ ደብረ ሊባኖስ
ስሮጥ በወንበሩ አኖርሽኝ በአንበሳው በቅዱስ ማርቆስ
ታዲያን ዛሬ ኢትየጵያ ስትወድቅ ከምትሰጪኝ ለፍርሃት ጦስ
ምነው በእረኝነት እድሜ አይኔን በጓጎጣት የሎስ
የጋኔል ጥምብ አንሳ ከንፎ ወርዶ በጨለማ በርኖስ
እባክሽ እመብርሀን ይብቃሽ እባክሽ ስለ ፍቅሩ ወልዳ
ፅናት ስጪኝ እንድካፈል የእናቴን የኢትዮጵያን ፍዳ
ከነከሳት መርዝ እንድቀምስ ከነደደችበት እቶን
የእሷን ሞት እኔ እንድሞታት ገላዋ ገላዬ እንዲሆን
አዎን ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
ህፃን ሆኜ የርግብ ጫጩት
አንዳንዴ ራብ ሲያዳክማት
ችጋር ከጎጆዋ ገፍቶ እዛፉ ግርጌ ሲጥላት
እናቷ በርራ ደርሳላት
በአክናፏ ሙቀት ታቅፋት
እፍ እያለች ግንባሯ ላይ ሕይወት ስተነፍስባት
ወዲያው ነፍስ ትዘራለች
ችር.... ብር.... ትር.... እያለች
እባክሽ አንቺማ አትራቂብኝ እመብርሀን እናቴ
ትንፋሽሽን እፍ በይብኝ
ፅናትሽን እፍ በይብኝ
ወይም ይቺን የሞት ፅዋ ጥላ ነፍሴን ካፈናት
እንዳልጠጣት አሳልፌያት
መራራ ክንፏና ገንጥለሽ ቀጠሮ ቃሏን ግደፊያት
አለዚያም ፅናትሽን ስጪኝ ልጠጣው ኪዳነ ውሉን
የኔ ፍቃድ እምነትሽ ነው ያንቺ ፍቃድ ብቻ ይሁን
እንደ ጳውሎስ እንድፀና በፍርሃት እንዳልታሰር
በውስጤ ከሚታገለኝ በስጋ አውሬ እንዳልታወር
በየለቱ ሞት እንዳልሰልፍ የኪዳኔ ቃል እንዳይነጥፍ
ቃልሽ በህሊናዬ ዲብ ኃይልሽ በህዋሴ ይረፍ
ፍርሃት ቢያረብብኝም አንቺ ካለሽኝ አልሰጋም
ኩርትም ብዬ እችልበት እሸሸግበት አይጠፋም
የግማደ መስቀሌን ጉጥ እታገስበት አላጣም
አለዚያማ ብቻዬን ነኝ ኢትዮጵያም ያላንቺ የላት
አንቺ አፅኚኝ እንድፀናላት
አስርጪብኝ የምነት ቀንጃ
ለስጋቴ አጣማጅ አቻ ለጭንቀቴ መቀነቻ
አዎን ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ።
ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን (1961 ዓ.ም)
ውድ የባይራ አንባቢያን
በዚህኛው እትም የመግቢያ ገጽ ላይ "ስነምግባር የራቀው ስነ ጽሑፋችን" የተሰኘው ጽሑፍ የጽሑፉ ባለቤት ስም በቴክኒክ ስህተት ምክንያት በሌላ አምደኛችን ስም የወጣ በመሆኑ ይቅርታ እየጠየቅን "ሲራክ ወንድሙ" ተብሎ እንዲነበብልን ስንል እንጠይቃለን።
እናመሰግናለን!
ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!
እነሆ
ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ባይራ ቅጽ 1 ቁጥር 7
ቴሌግራም- https://t.me/Bayradigital
ድረገጽ (Website)- https://bayradigital.com/
ፌስቡክ (Facebook) - ባይራ ዲጂታል መጽሔት
ትዊተር (Twitter) - https://x.com/BayraDigital
ለማንኛውም አስተያየት
ኢ-ሜይል [email protected]
ኑኒ ባይራክ!
ታላላቆች ነን!
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 10 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 6 days, 14 hours ago
BoA Social media links
https://www.facebook.com/BoAeth
https://www.instagram.com/abyssinia_bank
https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot
Last updated 3 weeks, 1 day ago