Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад
በረቢዑል አወል ወር በረሱለላህ ዙሪያ የነበሩ ሴት ሰሐቢያቶችን ታሪክ በተከታታይ ወደ እናንተ ሳደርስ የቆየሁትን በቡክሌት መልክ አዘጋጅቼዋለሁ! 💚
ለመልካም አስተያየታችሁ በጣም አመሰግናለሁ!...መልካም ንባብ!
ኸሚስ ነው በዱዓችሁ 🥰💚
የረሱሉﷺ የመጨረሻ የህይወት ዘመናቸው ላይ ሙሰይለማ አል ከዛብ የሚባል እኔም ከአላህ የተላኩኝ ነብይ ነኝ የሚል ውሸታም ሰው መጣ። ከዛም የድፈረቱ ድፍረት ለሸፊዒ በመልዕክተኞቹ አማካኝነት ደብዳቤ ይልካል። ደብዳቤው ላይም እርሳቸውም እርሱም የአላህ ነብዮች ስለሆኑ ተልዕኳቸውን ብሎም የሚያስተዳድሩትን መሬት መከፋፈል እንዳለባቸው ይገልጻል።
ሸፊዒﷺ ደብዳቤው እንደተነበበላቸው ሙሰይለማ ወደላካቸው ሰዎች ዞሩና “እናንተም እሱ በሚለው ታምናላችሁ?” ብለው ጠየቁ። እነርሱም እንደሚያምኑ ነገሯቸው። ለአለማት እዝነት የተላኩት ነብይምﷺ፡ “ወላሂ! ከአንድ ቦታ መልዕክት ለማድረስ የተላከ አምባሳደር መጉዳት ባይከለከል ኖሮ ከእጄ አታመልጡም ነበር።” አሏቸው። ለሙሰይለማ'ም ምላሻቸውን ላኩ። እንዲህም አሉ፡
«بسم الله الرحمن الرحيم : من محمد رسول الله إلى مسيلمة الكذاب : سلام على من اتبع الهدى ، أما بعد فإن الأرض لله يورثها من يشاء من عباده والعاقبة للمتقين» ✨️♥️
«በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ አዛኝ በሆነው፤ ከሙሐመድ ረሱለላህﷺ ለሙሰይለመቱል ከዛብ: ሰላም ለእነዚያ በቀጥተኛው መንገድ ላሉት ይሁን፤ እንግዲያውስ አንተ ለመከፋፈል የምታስበው መሬት ባለቤትነቱ የአላህ ነው። ድልም አላህን ፈሪ ለሆኑት ባሮቹ የተሰጠ ነው።» የሚል ውብ ምላሽን መለሱ።
ይህንን ምላሻቸውን እንዲያደርስ በዋነኝነት የላኩት አምባሳደራቸው የኑሰይባ ቢንት ከዓብ ልጅ የነበረው ሐቢብ ኢብን ዘይድ ነበር። ከእርሱ ጋርም ሌላ አንድ ባልደረባቸውን አስከትለው ልከው ነበር። ልጇ ሐቢብ ደብዳቤውን አንብቦ እንደጨረሰ ሙሰይለማ "መልዕክተኛው የአላህ ነብይ እንደሆኑ ትመሰክራለህ?" ብሎ ጠየቀው። "አዎ!" አለ። እኔ የአላህ ነብይ እንደሆንኩ'ስ አለው። ሐቢብ: "የምትለው አይሰማኝም።" አለ ጥያቄው ምን ያህል አሳፋሪ እንደሆነ እንዲረዳ! ሙሰይለማ ሁለተኛ ጊዜ ደግሞ ጠየቀው፤ መልሱ ተመሳሳይ ነበር። ሶስተኛ ጊዜ እያስፈራራው ጠየቀው፤ ሐቢብ'ም የነቢየላህን መልዕክተኝነት በልበ ሙሉነት ምንም ሳይፈራ መለሰ። ♥️
ከዚያም ይህ ጨቃኝ ሰው ሐቢብን በህይወት እንዳለ ህዝቦቹ ፊትለፊት ሰቅሎ እያንዳንዱን አካሉን በአሰቃቂ ሁኔታ መቁረጥ ጀመረ፤ የሸፊዒﷺ አፍቃሪ፤ የኡሙ አማራህ ልጅ ሐቢብ ግን እርሳቸውን የኡሁድ ወቅት እንደተከላከለው ሁሉ ለእርሳቸው ሲል ሰውነቱን ፊዳ አደረገ፤ "የአላህ መልዕክተኛ ነብይ እንደሆኑ እመሰክራለሁ።" የሚለው ከምላሱ ሳይጠፋ መስዋዕት ሆነ።
እናቱ ኡሙ አማራህ ዜናው ሲደርሳት የኡሁዷ ፈርጥ እንዲህ የሚል ድንቅ ንግግር ተናገረች:
"ልጄን ለዚህ ሰዓት አዘጋጅቼው ነበር። ምንዳውንም የምጠይቀው አላህ'ን ነው። ልጄ ሐቢብ ልጅ እያለ እርሳቸውን በነፍሱ ለመጠበቅ የአቀባ ስምምነት ላይ ቃል ከገባላቸው ነበር፤ ትልቅ ከሆነ በኃላ ደግሞ ቃል የገባላቸውን በተግባር አሳያቸው።" በማለት ትናገራለች ሱብሓነላህ!
የሰሐቦች መሐባ ግን እንዴት ያለ ነበር? ነፍሳቸውን ለሐቢበላህﷺ ፊዳ ማድረግን ማዕረጋቸው አድርገው ለአለም አበሩ። ♥️
አላሁመ ሰሊ ወሰሊም ወባሪክ አላ ሰይዲና ሙሐመድ ﷺ
ኡሙ ሱለይምም ልጇን በማጣቷ ብትሰበርም ለባሏ እንዴት መንገር እንዳለባት ግር አላት። ከዛም ጥሩ ምግብ ሰርታ፤ ቆንጆ ልብስ ለብሳ ጠበቀችው። ባሏ መጣ ከዛም አብረው ተመገቡ፤ ምንም መናገር ከበዳት፤ ጠዋት ላይም እንዲሁ ስትጨነቅ ቆየችና እንዲህ አለችው: "ያ አባ ጠልሓ! አንድ ሰው የሆነን አማና ሰጥቶህ ከቆይታ በኃላ አንድ ቀን መጥቶ አማናውን መመለስ ቢኖርብህ ምን ታደርጋለህ?" ብላ ጠየቀችው። "በምስጋና እመልሳለሁ።" አለ!..እርሷም ሀዘን በተሞላው ድምፅ: "ያ አባ ጠልሓ! ልጅህን(አማናህን) አላህ ወስዶታል።" አለች። ማታውኑ የልጁ ሞት ስላልተነገረው ከሀዘኑ ጋር ተጨምሮ ከባድ ስሜት ውስጥ ከተተው። እጅጉኑ ተሰበረ! ወደ ሸፊዒም በዚህ ስሜት ሄደ።
ረሱሉ ﷺ ከሩቁ አይተውት ፈገግ አሉና ሲቀርባቸው: "ያ አባ ጠልሓ! ምሽቱን ያሳለፋችሁበትን ጉዳይ አላህ ይባርከው።" አሉት! ... ኡሙ ሱለይም ልጇን ባጣችበት በተመሳሳይ ምሽት አርግዛ ኖሯል። አብዱላህ ብለው የሰየሙትን ወንድ ልጅ ልጃቸው ኡመይርን ባጡበት በአመቱ ተሸለሙ። ልጃቸው አብደላህም በኃላ ላይ 7 ሐፊዘል ቁርኣን የሆኑ ወንድ ልጆችን አላህ ይሰጠዋል። የአላህ ስራ እኮ 🥰
ረሱለላህﷺ በአንድ ወቅት በህልማቸው ያዩትን እንዲህ በማለት ይገልፃሉ: "በህልሜ ጀነት ገብቼ ተመለከትኩኝ። ወዲያውም ሩመይሳን አስታወስኩኝ፥ ዐይኔ ላይ'ም እሷ መጣች። የእግር ኮቴ ስሰማም ጂብሪልን ጠየቅኩት። እርሱም ቢላል ነው አለኝ። ከዛም ግዙፍ ቤተመንግስት ተመለከትኩኝ። እሱ ደግሞ የኡመር ኢብነል ኸጣብ ነው አለኝ።" በማለት ያዩትን ህልም ይናገራሉ። ሱብሓነላህ 🥰፤ ምን አይነት ድንቅ ሴት ብትሆን ነው?
ይህች ታላቅ የአንሷር ሴት'ም ከ28 አመት የሒጅራ ጉዞ በኃላ የምትወዳቸውን፤ የምትሳሳላቸውን ነብይ ተቀላቀለች። አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላት። رضي الله عنها 💚
የአላህ ሰላትና ሰላም በውዱ መልዕክተኛﷺ ላይ ይውረድ!
ዛሬ የረቢዓል አወል ማገደጃ እንደመሆኑ ከረቢዕ አንድ ጀምሬ ወደ እናንተ ሳደርስ የቆየሁትን የውድ ሰሐቢያቶችን ታሪክ በእዚህ እቋጫለሁ። በጊዜ እጥረት ምክንያት አዘጋጅቼያቸው ያልፖሰትኳቸው የአምስት ሰሐቢያቶችን ታሪክ ጨምሬ በቡክሌት መልክ አዘጋጅቼ በአላህ ፍቃድ ሰሞኑን ወደ እናንተ የማደርስ ይሆናል! ...አላህ ያስጠቅመን! በጀነቱም ከሁሉም ጋር ያጎራብተን! ለመልካም አስተያየታችሁ አመሰግናለሁ 🥰♥️
#በመልዕክተኛውﷺ_ዙሪያ_የነበሩ_ሴቶች... ፪፰
#ሩመይሳ_ቢንት_ሚልሃን
«የምርጥ መሕር ባለቤት» ✨💚
የአንሷሯ ኡሙ አይመን ነች ይሏታል። መዲና ውስጥ የሚገኙ የአብዱልሙጠሊብ ዘመዶች ጎሳ ማለትም የበኑ ነጃር ሰው ነች። ኢማም ነወዊ እርሷን እና እህቷ ኡሙ ሐራም'ን እንደ እርሳቸው አክስት እንደሚቆጠሩ ይገልፃሉ። እርሳቸውን ከእይታዋ ማጣት የማትፈልገው፤ የረሱለላህﷺ አፍቃሪ ብሎም የአነስ ኢብን ማሊክ እናት ሩመይሳ ቢንት ሚልሃን በተለምዶ መጠሪያዋ ኡሙ ሱለይም رضي الله عنها 💚
ሩመይሳ የስሪብ ላይ በውበቷ፤ ነገሮች ላይ ባላት እርግጠኝነት፤ በግጥም ችሎታዋ ትታወቅ ነበር። የስሪብ ላይ ትልቅ ቦታ የነበራት ሰው ነበረች። ባሏ ማሊክ ኢብን ነድር'ም መዲና ላይ እጅግ ሀብታም ከሚባሉ ነጋዴዎች ነበር። ከእርሱም ሁለት ወንድ ልጆችን አገኘች። አነስ ኢብን ማሊክ እና አል በራ ኢብን ማሊክ!
ረሱለላህﷺ ወደ መዲና ከመምጣታቸው በፊት ወደ ከተማዋ እንደ አምባሳደር የላኩት ሙስዓብ ኢብኑ ዑመይርን ነበር። መጀመሪያ ገብቶ ያደረገው የዳዕዋ ስብስብ ውስጥ ኡሙ ሱለይም ነበረች። የእስልምናን መልዕክት እንደሰማች ወዲያውኑ ሰለመች። ኡለሞች እንደውም የመጀመሪያዋ እስልምናን የተቀበለችው አንሷሪ ሴት ኡሙ ሱለይም ናት ይላሉ። ባሏ ከሄደበት ንግዱ ሲመለስ ኡሙ ሱለይም አምልኮዋን እየፈፀመች ተመለከታት። በድርጊቷ ተበሳጭቶ: "ይህንን የሞኝ ሐይማኖት ተቀላቀልሽ?" አላት። እርሷ ደግሞ: "አይ አመንኩኝ።" ብላ መለሰች። ይበልጥ መልሷ አናዶት ይጮህባት ጀመር። እሷ ግን ገና ልጅ የሆነውን አነስን "ላኢላሃ ኢለላህ መሐመዱን ረሱሉላህﷺ" ታስብላለች። ከባሏ ጋር ብትጋጭም ግን ወደ ፍቺ አልሄዱም ነበር! በዚህ መሐል
ባሏ ለንግድ ወደ ሻም እንደሄደ ይሞታል።
እርሱ ከሞተ ከቆይታ በኃላ የስሪብ ላይ በሐብቱ እና በመልካም ስነምግባሩ የሚታወቀው አቡ ጦልሓ ለትዳር ይጠይቃታል። ኡሙ ሱለይም'ም: "ያ አባ ጠልሓ! አንተ ጥያቄ የሚመለስብህ ሰው አይደለህም። ግን እኔ ሙስሊም ነኝ፤ አንተ ደግሞ ሙሽሪክ ነህ። ይህ ኒካህ ደግሞ የተፈቀደ አይደለም።" ብላ መለሰች። አቡ ጦልሓ ግን ምላሿ ሊሰጣት ያሰበው ገንዘብ ስላነሳት ስለመሰለው "የበለጠ ወርቅ እና ብር ስለፈለግሽ እንጂ እኔን እምቢ ለማለት እንዳልፈለግሽ አውቃለሁ።" አላት! ይህች ድንቅ ሴትም:
«بل إني أشهدك يا أبا طلحة وأشهد الله ورسوله أنك إن أسلمت رضيت بك زوجاً من غير ذهب ولا فضة، وجعلت إسلامك لي مهراً
«ባይሆን ያ አባ ጠልሓ! እኔ በአላህ እመሰክራለሁ፤ አንተም በአላህና መልዕክተኛውﷺ እንድትመሰክር እጠራሃለሁ። አንተ ካልከው ወርቅ'ም ሆነ ብር ሙስሊም ሆነህ ዘውጄ ብትሆን የምወድ ነኝ። መሕሬም እስልምናህ ነው።» በማለት መለሰችለት! ...አላህ አላህ 🥰
አቡ ጦልሃ ለተወሰኑ ጊዜዎች ሊያስብበት ቆየ። እናም አንድ ቀን ጣዖቱን ሲያመልክ አገኘችውና አዕምሮው ጥያቄ እንዲፈጥር: "ያ አባ ጠልሓ! ጣዖትህ እሳት ውስጥ ቢወረወር ምን ይሆናል?" አለችው እርሱም "ይቃጠላል" አላት! ኡሙ ሱለይም'ም: "እና የሚቃጠል አምላክ ነው የምታመልኩት?" አለችው። አቡ ጠልሓ ንግግሯ ዐይኑን እንዲከፍት አደረገው። ወዲያውም ወደ እርሷ በመምጣት የእርሱ እስልምና መህሯ ሆኖ በትዳር ተጣመሩ። ኡሙ ሱለይምም በሰዓቱ 10 አመት የነበረውን ልጇ አነስን ነበር ወሊይ ሆኖ ኒካህ እንዲያስራት ያደረገችው። 😊
ሰሐቢዩ ሰውባን'ም: "ልክ እንደ ኡሙ ሱለይም መህር የተሻለ መህር አናውቅም" በማለት ይመሰክራል። ኡሙ ሱለይም ከረሱለላህﷺ ጋር የተደረገው የሁለተኛው የአቀባ ስምምነት ላይ ከልጇ አነስ ጋር ሆና ወደ እርሳቸው ሄዳ ቃል ከገባችላቸው ድንቅ ሴት ነበረች። ከ73 አንሷሪዎች እርሷና ኑሰይባ ቢንት ከዓብ ብቻ ነበሩ ሴቶች 🥰... ኡሙ ሱለይም ግን ቃል መግባቷ ብቻ አልበቃትም፤ ለእስልምና እና ለመልዕክተኛውﷺ ያላትን ነገር ሁሉ መስጠት ፈለገች። ለእናት ትልቁ ሐብቷ ልጇ ነውና ውድ ልጇ አነስን ይዛ ወደ ሸፊዒﷺ ሄደችና "ያ ረሱለላህ! ልጄ አነስ እርሶን እንዲያገለግል ይፍቀዱለት። ዱዓም አድርጉለት።" ከዛም ሸፊዒﷺ ጥያቄዋን ተቀበሉና: "ያ አላህ! በሐብት፤ በመልካም ልጆች እንዲሁም አንተ ጋር ባለው መልካም ነገር ሁሉ ባርከው።" ብለው ለአስር አመቱ አነስ ዱዓ አደረጉለት። አነስ ይህንን ክስተት ሲያስታውስ ያለቅስ ነበር ይላሉ 🥹💚
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ መዲና ከመጡ በኃላ ኡሙ ሱለይም ለሳቸው መህረም ስለሆነች ቤትዋ መሄድን ያዘወትሩ ነበር። ልጇ አነስ: "ረሱለላህ ﷺ መዲና ውስጥ እንደ ኡሙ ሱለይም ቤት በብዛት የሚመላለሱበት ቤት አልነበረም።" በማለት ይናገራል።
ቤቷ በመሄድ የኡሙ ሱለይም ሙሰላ (የመስገጃ ስፍራ) ላይ ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር። ለእሷና ለቤተሰቦቿም በብዛት ዱዓ ያደርጉ ነበር። የነበራቸው ትስስር እጅግ ውብ ነበር። ኡሙ ሱለይም እኮ ረሱለላህ ﷺ ሲራቡ እንኳን በድምፃቸው አወጣጥ ምንም አለመመገባቸውን ተረድታ በአነስ በኩል ያላትን ነገር ትልክላቸው ነበር። ያ አላህህ
አንድ ቀን ባሏ አቡ ጦልሓ ወደ እርሷ መጣና የረሱሉ ድካምና ረኸብ በድምፃቸው እንደታወቃቸው ነገራት። አፍቃሪያቸው ኡሙ ሱለይም'ም ወዲያው ቤቷ ውስጥ የነበረውን ዳቦ በጨርቅ ጠቅልላ ለረሱሊﷺ እንዲያደርስ ለአነስ ሰጠችው። አነስ ወደ እርሳቸው ሲመጣ ከአህሉ ሱፋዎች ጋር ተቀምጠው ነበር። ውዱ ኻዲማቸውን አዩትና: "ያ አነስ! አቡ ጦልሓ ልኮህ ነው የመጣኸው?" ብለው ጠየቁት። አነስ አዎ አለ። "ከምግብ ጋር?" አሉ። አነስ አሁንም አዎ አለ። ሸፊዒም ብድግ ብለው 80 የሚጠጉ አህሉ ሱፋዎችንም "ተነሱ ወደ አቡ ጦልሓ ቤት እንሂድ" ብለው ጉዟቸውን ጀመሩ።
ለረሱለላህﷺ ብቻ የሚበቃ ዳቦ ይዞ የሄደው አነስ መልዕክቱን በትክክል እንዳላደረሰ ስለገባው በፍጥነት ወደ እናቱ ጋር ሄዶ የተፈጠረውን አወጋት። ኡሙ ሱለይምም: "ረሱለላህ ﷺ እንዲህ ያደረጉበትን ምክንያት ያውቁታል።" አለች በሙሉ እምነት 🥰.. ሸፊዒ ወደ ቤቷ መጥተው: "ያ ኡሙ ሰለይም! ቤት ውስጥ ምን አለ?" አሉ። እርሷም ለአነስ የሰጠችውን ዳቦ ሰጠቻቸው። ቅቤ ካለ ጠየቁ፤ እርሷም ያለውን ይዛላቸው መጣች። ከዛም ማሰሮ ውስጥ አደረጉትና ረጅም ሰዓት ዱዓ አደረጉ! አነስንም 10 ሰዎችን እንዲጠራ ነገሩት። ሁሉም ገብተው ከዳቦው በሉ። ሰማኒያዎቹም በተራ ተራ እየገቡ ለረሱለላህ በተሰጠው ሙዕጂዛ ያገኙትን በረከት ተቋደሱ። 🥰... አነስ: "ለሁለት ወሮች ከማሰሮው ውስጥ ያልተቋረጠ ምግብ እያገኘን ነበር።" ይላል!
የኡሙ ሱለይም ውዴታ ይለያል። በአንድ ወቅት ረሱለላህ ﷺ በጣም ሞቃታማ የነበረበት ቀን ላይ አረፍ ሊሉ ወደ ቤቷ ጎራ ይላሉ። ኡሙ ሱለይም'ም ላባቸውን በጨርቅ እያደረቀች ሽቶዋ ውስጥ ስትጨምር ሐቢበላህ ﷺ ግራ በመጋባት ይጠይቋታል! እስዋ'ም: "ከእርሶ ከሚወጣው ኒዕማ በረካውን እየወሰድኩ ነው ያ ረሱለላህ ﷺ!" ትላቸው ነበር። ያ ኡሙ ሱለይም! 🥹
አቡ ጦልሓ ኡሙ ሱለይምን ካገባ በኃላ አባ ኡመይር የሚባል ወንድ ልጅ አግኝተው ነበር። ትንሽዬ ወፍ በማሳደግና አብሮት በመጫወት ይታወቅ ነበር! ሸፊዒﷺ እርሱን ባገኙት ቁጥር ስለ ወፉ ይጠይቁት ነበር፤ አንድ ቀን ወፉ ሞታበት ሲያለቅስ አገኙትና አብረውት ተቀምጠው አፅናኑት። ያ ረሱለላህ 🥹... አቡ ጦልሓ ከብቸኛ ልጁ ጋር ልዩ ውዴታ ነበረው እና በልጅነቱ ድንገት በከፍተኛ የሰውነት ሙቀት ወደ አኺራ ተሸጋገረ።
አንድ ቀን ረሱለላህﷺ ጁወይሪያህ ጋር ነበሩና በጠዋቱ ፈጅር ለመስገድ ወደ መስጂዳቸው ሲገቡ እርሷ ደግሞ መስገጃዋ ላይ ዚክር በማድረግ ላይ ነበረች። ሐቢበላህﷺ ፈጅር ሰግደው፤ አንዳንድ ጉዳዬችን ጨርሰው ተመልሰው እርሷ ጋር ሲመጡ አሁንም ዚክር እያደረገች አገኟት። ሐቢበላህምﷺ ተገርመው: "እስካሁን እዚሁ ቦታ ላይ ነበርሽ?" አሏት። አዎ አለቻቸው። ከዛም እንዲህ አሉ: "ያ ጁወይሪያህ!እስካሁን ስትያቸው ከነበሩት ቃላቶች በሚዛን የከበዱ አራት ቃላቶችን እንደ ስጦታ እሰጥሻለሁ።" አሏት። እነርሱም
سبحان الله وبحمده،
عدد خلقه، ورضا نفسه،
وزنة عرشه، ومداد كلماته.
እነዚህን ውዳሴዎች በቀኗ ውስጥ ሶስት ሶስት ጊዜ እንድትል መከሯት። እኛም በቀን ውስጥ ይህንን ዚክር ሳንል መዋል የለብንም ኢንሻአላህ 💚
ረሱለላህﷺ ካለፉ በኃላ ልክ እንደ አብዘኸኞቹ ሚስቶቻቸው አምልኮዋ ላይ ትኩረት አድርጋ እንደነበር የፊትናው ሰዓትም እራሷን አግልላ እንደነበር እናገኛለን። መዲና ሒጅራ ካደረጉ ከ56 አመት በኃላ የህዝቦቿ በረከት የነበረችው፤ ህይወቷ አላህን በማጥራት ያሳለፈችው ጁወይሪያህ ረሱለላህንﷺ ተቀላቀለች። አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላት። رضي الله عنها 💚
#በመልዕክተኛውﷺ_ዙሪያ_የነበሩ_ሴቶች... ፪፯
#ጁወይሪያ_ቢንት_አልሃሪስ
«ለህዝቦቿ በረከት የሆነች ሴት» ✨💚
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ትዳሮች ብዙ ሒክማን ያዘሉ ናቸው። ከሐያል ጎሳዎች እና ህዝቦች ጋር ትስስር ለመፍጠር ያገቧቸው ሴቶች ነበሩ። ከእነርሱም ውስጥ አንዷ የበኒል ሙስጠሊቅ መሪ የነበረው የአል ሃሪሳ ኢብን ዲራር ልጅ በራህ ቢንት አል ሃሪሳ ወይንም በኃላ ረሱሊﷺ ስሟን በቀየሩላት ስም የምትታወቀው ጁወይሪያ ቢንት አል ሃሪስ ኢብን ዲራር ✨💚
በኒል ሙስጠሊቅ በመካ እና መዲና መካከል የሚገኙ ህዝቦች ሲሆኑ መካ ላይ የሚገኘው የበኑ ኹዛዋ አካል ናቸው። ሙረይሲዕ በመባል የሚጠራ አካባቢ ላይ ሰፍረዋል። ከቁረይሾች ጋር ያላቸው ትስስር ጠንካራ ነበር። አል መናት የሚባለው ጣዖትም የሚገኘው እነርሱ ጋር ነበር። ሙስሊሞች ወደ መዲና ሒጅራ ካደረጉ በኃላ ወደ መካ የሚገቡ ቅፍለቶችን እየወሰዱ ስለነበር በኒል ሙስጠሊቅ ከመካ የሚያገኙት የንግድ ጥቅም ክፍተት እየፈጠረ በመሆኑ ሙስሊሞችን ማጥቃት ላይ ከቁረይሾች ጎን ሆኑ። የኡሁድ ዘመቻ ላይም እገዛ አድርገውላቸው ነበር።
ከኡሁድ በኃላ ግን ቁረይሾች በኒል ሙስጠሊቅ እነሱን ያጠቃሉ ብለው ስለማይጠበቁ ረሱለላህንﷺ በድብቅ እንዲያጠቁ ይመክሯቸዋል። ዘመቻ ለመክፈትም በሚስጥር ማቀድ ጀመሩ! ወደ መዲና ሒጅራ ካደረጉ ከአምስት አመት በኃላ ነበር። የአላህ መልዕክተኛምﷺ ስለዚህ ጉዳይ ሰሙ። ዜናው እንደደረሳቸው ያደረጉት ግን እውነት ይሁን አይሁን የሚለውን ማጣራት ነበር። ከዛም በሒጅራው ጉዟቸው ላይ ያገኙት፤ የመዲና ጥግ ላይ የሚኖረውን የገጠር ሰው ቡረይዳ ኢብነል ሁሰይብ'ን ጠሩና ተልዕኮ ሰጡት።
"በኒል ሙስጠሊቆች ጋር ሄደህ፤ እነርሱን መስለህ ባቀዱት ዘመቻ ላይ መካፈል እንድምትፈልግ ንገራቸው።" አሉት! ቡረይዳ የሚታወቅ ሰው ስላልነበር በኒል ሙስጠሊቆች ጋር ሄዶ እርሳቸው እንዳሉት ሲጠይቅ አንዳቸውም አልተጠራጠሩም ነበር። ምን እንዳቀዱ አረጋግጦ ወደ ሸፊዑና ተመልሶ ዜናው እውን እንደሆነ ነገራቸው። የአላህ መልዕክተኛምﷺ ባልደረቦቻቸውን ይዘው ወደ ሙረይሲዕ መትመም ጀመሩ
ሒቡ ረሱሊላህﷺ የሆነውን ተወዳጃቸውን ዘይድ በቦታቸው ተክተው መዲና እንዲቆይ አደረጉ፤ ሰይዲና አባበክር የሙሐጂሮችን ባንዲራ፤ ሰዒድ ኢብን ዑባዳ ደግሞ የአንሷሮችን ባንዲራ እንዲይዙ አደረጉ። በዚህ ዘመቻ ወቅት ሌላ ጊዜ ዘመቻዎች ላይ ላለመሳተፍ የሚሸሹት ሙናፊቆች አብረዋቸው ለመውጣት እጅግ ፈለጉ። ምክንያቱም ዘመቻው ለረሱለላህ እና ባልደረቦቻቸው ቀላል እንደሚሆን ስለሚያውቁ በጦርነቱ ላይ ያለውን ምርኮ ለማግኘት አስበው አብረዋቸው ወጡ።
እንደደረሱም ቀስተኞቻቸው የጎሳውን መንደር እንዲከቡ ካደረጉ በኃላ ድንገት ባላሰቡበት ሁኔታ ቀስት መወርወር ጀመሩ። አብዘኸኞቹም እጅ ሰጡ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ጠፉ(ከጠፉት መካከል መሪያቸው የነበረው የጁወይሪያ አባት ነበር።)... ከዛም ምርኮዎችን መሰብሰብ ላይ አንሷሮችና ሙሐጂሮች ሲተጋገዙ ማየት ዐይኑን ያቀላው ሙና*ፊቁ አብደላህ ኢብን ኡበይ ኢብን ሰሉል በመካከላቸው መርዝ ለመርጨት ወደ አንሳሮቹ ሄዶ: "ውሻህን አደልብ(አብላ፤ አወፍር)፤ በኃላ ላይ ይበላሃል።" አለ.. "ሙሐጂሮች ሀገራቹ ላይ መጥተው እንዴት የበላያቹ እንደሆኑ ተመልከቱ!" በማለት ክፍተት ለመፍጠር ይሞክር ጀመር። ዓላማው ረሱሉﷺ ወደ መዲና ሲመለሱ እርሳቸውን አስወግዶ እርሱ መሪ የመሆን ነበር።
አላህም የአብደላህ ኢብን ሰሉል'ን መርዛማ እቅድ ለረሱለላህﷺ በቁርዓን አሳወቃቸው፤ ሰሐቦችም አወቁ። በዚህም ምክንያት የእርሱ እቅድ ከሸፈ። ከበኒ ሙስጠሊቅ የተማረኩ 100 ቤተሰቦች፤ ከእነርሱም ውስጥ አንዷ ጁወይሪያህ ትገኝበታለች። 2000 ግመሎች እና 600 ፍየሎችን ጭምር ይዘው ወደ መዲና መጡ!
ጁወይሪያህ: "ረሱለላህﷺ ወደ እኛ ከመምጣታቸው በፊት ለህዝቦቼ በህልሜ ጨረቃ ሙረይሲዕ ላይ ደምቆ እንደተመለከትኩኝ ተናግሬ ነበር።" ትላለች። መዲና ከገባች በኃላ እሷን ይዟት የነበረው ሰሐቢዪ ሷቢት ኢብን ቀይስ ነበር። በጦር*ነት ምክንያት የተማረኩ ሰዎች ነፃ የሚሆኑበት የአል-ሙካተባ ህግ አለና በ7 ግራም ብር እንዲለቃት ጠየቀችው። እርሱም ተስማማ!
ከዛ በኃላ ያለውን ክስተት በሰዓቱ የሀሰት ወሬው የተጀመረባት እናታችን አዒሻ እንዲህ በማለት ትናገራለች። "በኒል ሙስጠሊቅ የተሸነፈ ጊዜ፤ ይህች ውብ እና ግርማ ሞገስ ያላት ሴት ከእስር እራሷን ለማስለቀቅ ሐቢበላህን ﷺ ለመጠየቅ ወደ ቤታችን መጣች። በሩን አንኳኩታ እንደተመለከትኳት አልወደድኳትም።" ትላለች 😅... የእናታችን አዒሻ ቅናት እንደምናውቀው ነው! ወደ ረሱሉም ﷺ መጥታ: "ያ ረሱለላህ! ጁወይሪያህ እባላለሁ የበኒል ሙስጠሊቅ መሪ ልጅ ነኝ። ወደ እርሶ የመጣሁት ማስለቀቂያ ገንዘቡን እንድትከፍሉልኝ ነው።" አለቻቸው። ድፍረቷ አይገርምም? 😅
ሸፊዒ'ም: "አንቺ ካልሽው የበለጠ ቢሆንስ?" አሉ። "ከፈለግሽ ገንዘቡን ከፍዬልሽ ነፃ ትሆኛለሽ፤ ወይንም አንቺን ላገባሽ እችላለሁ።" አሏት። እርሷም ውዱ ነብይንﷺ ማግባት መረጠች 🥰...ይህ ዜና መዲና ላይ ሲንሰራፋ የመሪያቸው ልጅ ውዱ መልዕክተኛውን አግብታ የበኒል ሙስጠሊቅ የተያዙ ቤተሰቦችን በእስር ማቆየት ስላልተዋጠላቸው ሁሉም የያዟቸውን ሰዎች ለቀቁ። ገንዘቦቻቸውንም መለሱላቸው። በዚህም ምክንያት እናታችን አዒሻ ስለ ጁወይሪያህ:
فما أعلمُ امرأةً أعظمَ بركةً منها على قومِها
"እንደ ጁወይሪያህ ለህዝቦቿ ትልቅ በረከት የሆነች ሴት አላውቅም።" በማለት ትመሰክራለች 💚... የበኒል ሙስጠሊቅ ህዝቦችም በሙስሊሞች እዝነት ተማረኩ፤ ሰላም'ም ፈጠሩ። በዚህ መሐል ከገዝዋው የጠፋው አባቷ አል ሃሪስ በድብቅ ያስቀመጣቸውን ሐብቶችን ይዞ ልጁን ለማስለቀቅ ወደ መዲና ጉዞውን ይጀምራል። 😊
ልጁ ታላቁን ሰው እንዳገባችም አላወቀም። በመንገዱ ላይም ዋዲል-ዐቂቅ የሚባል ሸለቆ ውስጥ ገባ እና ከያዛቸው ውስጥ ሁለት ግመሎች ማረኩት እና ተመልሰው ሊወስዱት እዚህ ዋሻ ውስጥ ደብቋቸው ወደ መዲና ጉዞውን ቀጠለ። ወደ እርሳቸው ገብቶም ያመጣቸውን ገንዘቦች ለልጁ ማስለቀቂያ እንዲሆን ጠየቀ። ረሱለላህ ﷺ ፈገግ አሉና: "ዋዲል-ዐቂቅ ዋሻ ውስጥ የደበቅካቸው ሁለቱ ግመሎች'ስ?" አሉት። አባቷም ወዲያው ሸሐዳ ያዙ። ልጃቸውን እንዳገቡ ሲያውቁም እጅጉኑ ተደሰቱ። 💚
ጁወይሪያህ ረሱለላህንﷺ ካገባች በኃላ ከእስልምና በፊት በሐብት ተከባ፤ እንደ ልዕልት የምትታይበትን ህይወት ትታ ዙሕድን መረጠች። የረሱሉ ሚስቶች እርሳቸውን ካገቡ በኃላ ህይወታቸውም ሐብታቸውም አምልኳቸው ይሆናል ሱብሃነላህ! ... በፆም፤ በሰደቃ ጠንካራ ነበረች። የምትታወቀው እና የምትለየው ግን በዚክሯ ነበር ይላሉ። ቀኑን ሙሉ አላህን እየዘከረች ትውል ነበር። እንደውም አንዳንድ ሙፈሲሮች አላህ ቁርዓኑ ላይ: "አዝ-ዟኪሪነ ከሲራ ወዟኪራት" ያሉት እንደ ረሱለላህና ﷺ እንደ ጁወይሪያህ ለማለት ነው ብለው ምሳሌ ያስቀምጣሉ። 😊💚
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад