Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 8 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 3 weeks, 1 day ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ማጎንበስ መሸነፍ ወይንም መውደቅ አይደለም!
አዎ አንዳንድ ጊዜ በሕይወታችን ጎንበስ ካላልን ሰብሮን የሚያልፍ ከባድ ነፋስ አለ:: ዝቅ ካላልን ጎድቶ የሚያልፉ እልፍ ፈተናዎች!
እውነቴን ነው ከፍ ለማለትም ጊዜ አለው፣ ጎንበስ ለማለትም ጊዜ አለው፣ ለጨለማም ጊዜ አለው፣ ለብርሃንም ጊዜ አለው፣ ብቻ ለሁሉም ጊዜ አለው። ይህ እውነት ነው!
አዎ...
ለጊዜው ጎንበስ፣ በጊዜው ቀና:
ለጊዜው ዝቅ፣ በጊዜው ከፍ! ማለት ሞኝነት ወይም አላዋቂነት ሳይሆን ብልህነት ነውና በሕይወታችን እንለማመደው።
ለጊዜው ያጎነበሰ፣ በጊዜው ቀና ማለቱ አይቀርምና አይዞን ተስፋ አንቁረጥ፣ እንቀጥል!
ከእናንተ በርትቼ እንኳን አይደለም...ግን በቃ እኔን ያበረታኝ ያበርታችሁ፣...ለእኔ ተስፋ የሆነኝ ተስፋ ይሁናችሁ...የረዳኝ እርሱ ይርዳችሁ!
አዎ በርግጥም ማጎንበስ መሰበር አይደለም፣ መሸነፍም አይደለም፣ ከመኖር ጥበቦች አንዱ እንጂ!
መልካም ሰንበት🙏
©Amanuel T.
@AmanAsham
ሰሎሞን
'ዝም ለማለት ጊዜ አለው: ለመናገርም ጊዜ አለው' አለ።
ዝምታን ያስቀድመው በዝምታችን ወቅት የመናገርን ጥበብ ስለምንማር ነው።
#ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ(Known Theologian and Philosopher)
@AmanAsham
የንጋቱን ሰማይ ለማየት የበቃ፣
ተመስገን ይለዋል ከእንቅልፉ ስነቃ፡፡
#ተመስገን🙏
(ሰናይ ቀን...)
-ዶክተር በሃያዎችሁ እድሜ ላይ ያለ ወጣት ምን ሊገድለው ይችላል?
"እምም..ድንገተኛ አደጋ፣ ካንሰር?"
-ተሳስተሃል ዶክተር በደስታ ማጣት፣ በተስፋ መቁረጥ፣ በድብርት ከመጠን በላይ በመጠጣት እና ህልሞችሁ ሲወድሙ ማየቱ ነው የሚገድለው!
ጆርጅ አርዌል
@AmanAsham
ማጨስ አቆመ፤ አስካሪ መጠጥ መጠጣት አቆመ።
ከብዙ ሴቶች ጋር አጉል ነገር ማውራት አቆመ። ከጓደኞቹ ጋር የሆነ አላስፈላጊ ቦታ መሄድ አቆመ።
ሁሉንም አላስፈላጊ ነገሮችን አቁሟል ምክንያቱም..
ራሱን ወደ ተሻለ ስሪት መቀየር ጀመረ፤ ትዕቢቱን ዝቅ ማድረግ ጀመረ፤ መስማት እና መማር ጀመረ፤ ተገቢውን እና አስፈላጊውን ነገር ይከተል ጀመር።
ምክንያቱም እምነቱን ጠንቅቆ ተረዳ። ወደ ፈጣሪውም ቀና አለ። እርሱም አላሳፈረውም፣ በፈንታው መንፈሱን በደስታ ሞላው።
ማድረግ ቢፈልግ ያደርገው ነበር። ፍላጎት ካለ መንገድም አለ። ስለዚህ ሰውን እንዲቀየር አታስገድዱት እውነተኛ ሰው በፈቃዱ በጊዜው ይቀየራልና።
©Imagination Officially and With minor modifications by Aman.
ይህንን ያልሰሙ ጆሮች፣ ይህንን ያላዩ ዓይኖች የተባረኩ ናቸው።
ከአንዳንድ መስማቶች ይልቅ አለመስማት ይሻላል፣ ከአንዳንድ እይታዎች አለማየት እጅግ ይልቃል፣
በጠቅላላው ከአንዳንድ ዕውቀቶች ይልቅ አለማወቅ ይሻላል።
ይህ በእኛ ሀገር ከተደፈጸሙ ነውሮች አንዱ ነው፣ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች አይደል እንደ የተባለው???
እሺ እኛስ በስራችን ነው፣ ምንም የማያውቁ ህጻናትስ ምን አጠፉ? አዬ ኢትዮጵያ፣ አዬ ሰው💔💔💔
ሲምቦ ብርሃኑ💔 ትባላለች የ8 አመት ታዳጊ ስትሆን ነዋሪነቷ በምዕራብ ሸዋ ሜታ ወልቂጤ ወረዳ ነው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ከተፈፀመባት በኋላ ህይወቷ ሲያልፍ አስክሬኗን ሰቅለው ሄዷል።
እንግዲህ ምንም ማለት ባልችል፣ አሁንም እጃችንን ወደ ላይ መዘርጋታችን አናቁም፣ አምላክ ሆይ ታረቀን፣ ጌታ ሆይ በቃችሁ በለን!!!
ከንቱ💔💔💔
©Amanuel T.
@AmanAsham
አስታውስ ለውጥ ፈልገህ ነበርክ...ህይወት ስትፈትንህ አይግረምህ!
!!
@AmanAsham
የሆነ ሰውዬ አንድ አዋቂ ሽማግሌን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦“ወንዶች ያለቅሳሉ እንዴ?”
ጠቢቡም አባት፦አዎ ወንዶች ያለቅሳሉ።
ሰውየውም“ወንዶች መቼ ነው የሚያለቅሱት?”
ጥበበኛውም አባት እንዲህ ሲሉ መለሱ፦
ወንዶች እናቶቻቸው ሲሞቱባቸው ያለቅሳሉ፤
ወንዶች ወላጆቻቸውን ሲያጡ ያለቅሳሉ፤
አንድ ወንድ ልጁ ሲታመም ያለቅሳል፤
ወንዶች ሴት ልጆቻቸው ሲያገቡ ያለቅሳሉ፤ ወንዶች ለልጆቻቸው ትግል ወይም እድገት አንድ ቃል ሳይናገሩ ያለቅሳሉ።
ወንዶች ለልጆቻቸው የሚያስፈልጋቸውን ነገር ማቅረብ ሲያቅታቸው ያለቅሳሉ፤
ወንዶች ከቤታቸው አንድ ሰው ሲጠፋ ወይም የሚወዱት ሰው ሲለያቸው ያለቅሳሉ!፤
ወንዶች ያለቅሳሉ ግን ወደ ጨለማ ከዝናብ በታች በትራሳቸው ላይ ዝቅ ብለው ያነባሉ።
ልጄ ሆይ የወንድን እንባ ጉንጭ ላይ ወይም ከአይን ሲወጣ አትመልከት። እሱን ሁሉም ያየዋል። ይልቅስ ከልብ ወጥቶ ልብ ላይ ይቀመጣል።
በመጨረሻም በተገለጠ ጊዜ በመልካቸው ላይ፣ በፊት መሸብሸብ፣ በነጭ ፀጉራቸው እና በእጅ መንቀጥቀጥ ይገልጹታል። ወንዶች እንዲህ ነው የሚያለቅሱት!።
አዎን ወንዶች ያለቅሳሉ፣ ግን ስያለቅሱ ብዙ ጊዜ እንባቸውን በጉንጭ ላንመለከት እንችላለን!
ወንዶች ያለቅሳሉ እንዴ አባቴ💔?
―በትምህርት ቤት ደካማ ተሳትፎ የነበረው አንድ ልጅ ወደ እናቱ መቃብር ሄዶ፡- መች ነው እኔ ጋር የምትመጪው? መምህሩ በተማሪዎቹ ፊት ሁሌ እየመታኝ እንዲህ ይለኛል፦ “እናትህ ግድ የለሽ ናት ስለ አንተ ደንታ የላትም!”
💔
ካነበብኳቸው ውስጥ በጣም ከረበሹኝ እና ልቤን ከነኩኝ መካከል👆
#2
ካነበብኳቸው ውስጥ በጣም ከረበሹኝ እና ልቤን ከነኩኝ መካከል:-
#1
―ዶክተሩ፡- የስኳር በሽታው ጸንቶብሻል ሌላኛውን እጅሽን ለመቁረጥ እንገደዳለን..
እሷም እንዲህ አለችው፦ “ አንድ ሳምንት መጠበቅ እንችላለን። ልጄ ጉዞ ሊያደርግ ነው። እና በአውሮፕላኑ ውስጥ ሲገባ ለመጨረሻ ግዜ እጄን ማወዛወዝ እፈልጋለሁ!”
💔
Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 8 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 3 weeks, 1 day ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 months, 2 weeks ago