Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 8 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 3 weeks, 1 day ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 months, 2 weeks ago
Сотрудничество 🙏
የጅማ ዩኒቨርስቲ አርክቴክቸር አሶሴሽን ያዘጋጀውን ውድርድር እናሸንፍ ዘንዳ ከስር ባለው የቻናል ማስፈንጠሪያ እየገባቹ Code 6 (🐝) በመምረጥ ቀና ትብብራቹን ትለግሱን ዘንዳ በአክብሮት እንጠይቃለን 😒
የተኩስ አቁሙ በጋዛ በታወጀበት እለት ጋዛዊያኑ አንድ ወጣትን ሲሸከሙ የሚያሳይ ቪድዮ አይቼ ነበር።ስለዚህ ሰው ሳጣራ የሚከተለውን አገኘሁ....
ዶክተር ሙሐመድ ጧሂር አል-ሙሰዊይ በእንግሊዝ ለንደን የሚኖር ትውልደ ዒራቃዊ የአጥንት ቀዶ-ጥገና ዶክተር ነው።
ሙሐመድ ከስምንት ወር በፊት ነበር ከእንግሊዝ በጎ ፍቃደኛ ዶክተሮች ጋር ወደ ጋዛ የመጣው።በጋዛም ለ3 ሳምንታት ያለ እረፍት ሲያገለግል ከቆየ በኃላ ጊዜው ስላበቃ ወደ ለንደን ይመለሳል።ወደ ለንደን ለመመለስ ሲነሳ በቁድስ ከተማ ላገኘው ጋዜጠኛ በእምባ ተሞልቶ:-
"እዚህ ኢማን አለ።እዚህ ፅናት አለ።ይህን ህዝብ አልተውም በቅርቡ እመለሳለሁ።ጋዛ ተመልሼ ብሰዋ እንኳን ምንም አይደለም።ይህ ከኔም ከእናቴም ሆነ ከጓደኞቼ ስሜት ከፍ ያለ ነገር ነው።" ብሎ ነበር።
ሙሐመድ በለንደን በርሱና ወንድሞቹ የሚጣሩ በእድሜ የገፉ እናት አሉት።ነገር ግን በጋዛ ያየው ሁኔታ እረፍት ሊሰጠው አልቻለም።
እንዳለውም ሁለት ሳምንት ሳይቆይ ተመለሰ።ይህ ጊዜ የጋዛ ሆስፒታሎች ሳይቀር በከባባድ ጥቃቶች የደረሰባቸው ሰዓት ነበር።
በጋዛ ቆይታውም እረፍት በሌለው ተከታታይ የስራ ቀናት ከ300 በላይ ከባባድ የቀዶ ጥገና ስራዎችን ሰርቷል።ከሁሉም መነጋገሪያ የነበረውም መርየም ሰባሕ ለተባለችው ህፃን የሰራው ተከላ ነው።የ9 ዐመቷ መርየም በፅዮናዊያኑ የአየር ጥቃት አደጋ ደርሶባት ዶ/ር ሙሐመድ ወደ ሚሰራበት ሹሀዳኡል-አቅሷ ሆስፒታል ስትደርስ እጇ ሙሉ ለሙሉ ተቆርጦ ነበር።ሙሐመድም ለአባቷ የተቆረጠውን እጅ ክፍል እንዲያመጣ ይነግራል።አባትም ወደ ቤቱ ተመልሶ ከፍርስራሾች መሃል የተቆረጠውን የእጇን ክፍል ፈልጎ ያመጣል።አምስት ሰዓታትን ከፈጀ የቀዶ ጥገና ስራም በኃላ ስራው የተሳካ ሆኗል።
ሙሐመድ በዚህ የከፋ ጦርነት ከጋዛዊያኑ ጋር ለአምስት ወራት አሳልፏል።ከሰሜን ጋዛ እስከ ደቡብ ጋዛ በቆየበት 5 ወራትም ውስጥ ፀጉሩን ሽበት ወሮት፤20 ኪሎን ቀንሶ ከለቅሷቸው ጋር አልቅሶ፤ህይወትን ዳግም እየወራ አሳልፏል።ቤተሰቦቹ በተደጋጋሚ እንዲመለስ ቢወተውቱትም እዚሁ እሰዋለሁ እንጂ አልመለስም ያለው ሙሐመድ በጋዛ ሳለ ነው የተኩስ አቁሙ የተፈረመው።ለዚህም ነው ጋዛዊያኑ ይህን ወጣት በጀርባቸው ተሸክመው ክብራቸውን የገለፁት።ሰው መሳይ መልዓክቶች አሏህ ይውደድላቸው🤲
©Ber Hum
የፓርላማ አባሉ የተከበሩ ዶ/ር አብዱሰመድ በሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አካታችነት ዙሪያ የሚነሱ ቅሬታዎችን ያማከለ ጥያቄ አቀረቡ
- ሀሩን ሚዲያ፣ ሕዳር 10/2017
የፖርላማ አባል የሆኑት ዶ/ር አብዱሰመድ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሕዝበ ሙስሊሙን ጥያቄዎችን በተገቢው ሁኔታ ለማስተናገድ ፍላጎት የለውም ተብሎ ለሚቀርበው ቅሬታ የኮሚሽኑ ምላሽ ምንድነው?ሲሉ ለፖርላማ ጥያቄ አቀረቡ!
የሀገራዊ ምክር ኮሚሽን ባለፉት ሶስት ወራት ያከናወናቸውን ተግባራት በዛሬው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል። ምክር ቤቱ ሪፖርቱን ከሰማ በኋላ ከምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎች ለኮሚሽኑ ተነስተዋል።
ጥያቄ ካቀረቡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መካከል የተከበሩ አብዱሰመድ (ዶ/ር) የሕዝበ ሙስሊሙን ጥያቄዎችን በተገቢው ሁኔታ ለማስተናገድ ፍላጎት የለውም ተብሎ ለሚቀርበው ቅሬታ የኮሚሽኑ ምላሽ ምንድነው? ሲሉ ጠይቀዋል።
ዶ/ር አብዱሰመድ በጥያቄያቸው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሸን ስኬት የሚወሰነው ከአደረጃጀት እስከ አካሄድ፣ ከተሳትፎ እስከ አጀንዳ አሰባሰብ፥ ከምክክር ሂደቱ እስከ የምክክሩ መቋጫ ስርዓቱ ላይ ባለ የአሳታፊነትና የፍትሃዊነት ደረጃ ጭምር ነው። በዚህ ረገድ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትና ሙስሊም ማህበራዊ አንቂዎች ከኮሚሽነሮች እስከ አማካሪዎቹ መረጣ፣ ከወረደ እስከ ዞን፣ ብሎም እስከ ክልል አቀፍ ደረጃ የሕዝበ ሙስሊሙ በበቂ መጠን ያለመወከል ጥያቄና ቅሬታ ሲነሳ ነበር።
በተለይም ጠቅላይ ምክር ቤቱ ሕዝበ ሙስሊሙን ባለው ቁጥር ልክ በተገቢው መልኩ ለማሳተፍ የቁርጠኝነት ችግር እንዳለ መጥቀሱን ያነሱት ዶ/ር አብዱሰመድ። በሁሉም የሕብረተሰብ ክፍልን የወከሉ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ነጋዴዎች፣ መምህራን፣ ሲቪክ ማህበራት፣ እድር፣ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ ተፈናቃይ፣ የተገለሉ የህብረተሰቡ ክፍሎች ወዘተ በሁሉም ተሳታፊዎች ላይ እኩል የሃይማኖት ስብጥርንና ኮታን መጠበቅ በሁሉም ማዕቀፍ መሆን ሲገባ ይህ አለመሆኑ በሁሉም ደረጃ የሕዝበ ሙስሊሙ ተሳታፊነት ጥቂት አድርጎታል ብለዋል።
በሌላ በኩል በሃይማኖት ማዕቀፍ ራሱ በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኩል ይወከሉ መባሉ ራሱ ቅሬታ ፈጥሯል ሲሉ አንስተዋል። ለዚህ ምክንያትም በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሙስሊሞች ተሳትፎ በቁጥራቸው ልክ ሳይሆን ሰባት ለአንድ መሆኑ ነው። በመሆኑም የሙስሊሙ የዘመናት ችግሮችና አጀንዳዎች መፍትሄ እንዲያገኙ በቁጥሩ ልክ ተሳትፎ ከሌለ አጅንዳዎቹ በተገቢው ሁኔታ አይስተናገዱም ሲሉ ሀሳባቸውን አንስተዋል።
መጅሊስ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖረው በሚል በሀገራዊ ምክከር ሂደት ላይ ኮሚቴ አዋቅሮ አጀንዳዎቹን ለይቶ ለኮሚሽኑ ማስገባቱ ጠቅሰው ሆኖም በሕዝበ ሙስሊሙ ተሳትፎ ላይ አሁንም ድረስ በመጅሊስ ጭምር ቅሬታ እንዳለ አንስተዋል።
እናንተም ከመጅሊስ አመራሮች ጋር በዚህ ቅሬታ ላይ ስብሰባ ማድረጋችሁን አውቃለሁ ያሉት ዶ/ር አብዱሰመድ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በዚህ ረገድ የሕዝበ ሙስሊሙን ጥያቄዎች በተገቢው ሁኔታ ለማስተናገድ ፍላጎት የለውም ተብሎ ለሚቀርበው ቅሬታ የኮሚሽኑ ምላሽ ምንድነው? በቀጣይም ኮሚሽኑ በተጫባጭ ለመውሰድ ያሰበው የሚታይ የእርምርት እርምጃ ምንድናቸው?ሲሉ ጠይቀዋል።
- የኮሚሽኑን ምላሽ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።
© ሀሩን ሚዲያ
በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ተስፋን ማጎንቆል
"አንዳንድ ጊዜ አንድ ነገር ሲከሰት መከሰት አልነበረበትም ብለን እንጨረጨር ይሆናል። በፍጹም መሆን የለበትም ብለን እናስባለን። ለምሳሌ የምንወደው ሰው ሲሞት፣ ሥራ ስናጣ፣ ጓደኛችን ሲሸፍጥብን ወይም ማንኛውንም ዓይነት ሽንፈት ሲያጋጥመን በጭራሽ መሆን አልነበረበትም ብለን እንተከተካለን። በቃ ሁሉም ነገር አበቃ፣ ዋጋ የለኝም ብለን ልናስብም እንችላለን።
ነቃ በል እንቶኔ። የምን መፍረክረክ ነው። ታላቅነት የሚገኘው ሁሉም ነገር ሲስተካከል ሳይሆን ሕይወት ምዝልግ አድርጎ ሲቆነጥጥህ፣ ከእግር ጥፍር እስከ ራስ ፀጉርህ ሲፈትሽህ፣ መንገድህ ሲሰናከል፣ ስትከፋ፣ ሀዘን ሲያሸንፍህ ነው።
በተራራ አናት ላይ መሆን ምን ያህል አስደናቂ እንደሆነ ሊረዳ የሚችለው በሸለቆው ጥልቅ ክፍል ውስጥ ማለፍ የቻለ ብቻ ነው።"
አንቶኒ ሆፕኪንስ
©
ለጠዋቶ ስንቅ ይሆኖት ዘንድ
ራሶትን አያታሉ
ሰበብ አስባብ አትደርድር:: ከወደቅክ ወድቀሃል:: ከተሸነፍክ ተሸንፈሃል:: ለውድቀትህ እና ለሽንፈትህ መሸፋፈኛ የሚሆንን ሌላ አካል ከመፈለግ ይልቅ እውነታውን ተቀብለህ ከውድቀትህ ተነስ:: ከሽንፈትህ አገግም:: ብቸኛው ጤናማ መንገድ ይህ ብቻ ነው::
©
የ12ኛ ክፍል ውጤት‼️
<<?ዘንድሮ 1,363 ትምህርት ቤቶች ምንም አይነት ተማሪ አላሳለፉም።
?የ12ኛ ክፍል ተማሪ በማሳለፍ አዲስ አበባ ቀዳሚ ነው።
?ዘንድሮ ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑት ተማሪዎች 36,409 ተማሪዎች ናቸው ያለፉት
?በሌላ በኩል ፤ በኦላይን ከተፈተኑ ተማሪዎች 26.6 በመቶ የሚሆኑት አልፈዋል።
?ሬሜዲያል ዘንድሮም ይኖራል።አምና ሰጥተናል። ዘንድሮ ከዓምናው የቀነሰ ቁጥር እንወስዳለን። የሬሜዲያል ፕሮግራም በሂደት እየቀነሰ ይሄዳል::
? የፈተናው ውጤት ለሊት 6 :00 ሰዓት ላይ ይፋ ይደረጋል
?ዘንድሮ ሁሉም ክልሎች አምና ካሳለፉት ተማሪ በላይ አሳልፈዋል "
?" በፐርሰንቴጅም በአክቹዋል ቁጥርም ካለፈው የተሻለ ነው "
?ከአክቹዋል ቁጥር ያነሰው አንድ ክልል ነው እሱም የአማራ ክልል ነው።ክልሉ ያነሰው ደግሞ የተፈተኑት ተማሪዎች ቁጥር ከግማሽ በታች ስለነበር ነው።ክልሉ ፈተና ካስፈተናቸው ውስጥ ግን 6.6 በመቶ ተማሪዎች አልፈዋል።አምና ከተመዘገበው 4.1 በመቶ ዘንድሮ በልጧል።
?በአጠቃላይ እንደሀገር ከፍተኛ ውጤት ከ500 በላይ ያመጡ ተማሪዎች ባለፈው አመት 273 የነበሩ በአሁኑ 1220 ከ500 በላይ ያመጡ ተማሪዎች ናቸው ።
?በአጠቃላይ 5.4 በመቶ ፈተናውን አልፈዋል ይህም ማለት 36 ሺ 4 መቶ ተማሪዎች አልፈዋል ።
ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡት ሴቶች ናቸው::
?በተፈጥሮ ሳይንስ ካቴድራል ትምህርት ቤት 575/600
?በማህበራዊ ሳይንስ ኢትዮ ፓረንትስ 538/600
አንድ ተማሪ አላሳለፉት:-
?አዲስ አበባ 4 ትምህርት ቤቶች
?አፋር 33 ትምህርት ቤቶች
? ቤንሻንጉል 36
? አማራ 56
? ኦሮሚያ 553
? ሶማሊያ 156
? ትግራይ 52
በሀረሪ ክልል የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሁሉም አሳልፈዋል። ይህ ማለት ሁሉም ተማሪዎችን አይደለም።
?በትግራይ ክልል ቀላሚኖ ትምህርት ቤት በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከተመዘገበው ሁሉ ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል ::675/700
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
t.me/bilalofficiall
الحمد للَّه علىٰ أصغر النعم ، والحمد للَّه علىٰ أكبر النعم ، والحمد للَّه علىٰ كلِّ النعم ، الحمد للَّه حبَّاً وشكراً ، والحمد للَّه يوماً وعمراً ، والحمد للَّه في السرَّاء والضرَّاء ، والحمد للَّه دائماً وأبداً
اللهُمَّ لا تجعل نعيمك يشغلنا عن حمدك ، ولا تجعل بلاءك يشغلنا عن استغفارك ، اللهُمَّ لك الحمد حتَّىٰ ترضىٰ ، ولك الحمد إذا رضيت ، ولك الحمد بعد الرضا ، ولك الحمد علىٰ كلِّ حال.
" وَمَنْ يَعْمَلْ سُوءًا أَوْ يَظْلِمْ نَفْسَهُ ثُمَّ
يَسْتَغْفِرِ اللَّهَ يَجِدِ اللَّهَ غَفُورًا رَحِيمًا "
- استغفِرُ اللهَ وأتوبُ إليه .
Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 8 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 3 weeks, 1 day ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 months, 2 weeks ago