TIKVAH-MAGAZINE

Description
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 4 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 6 days, 5 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 10 hours ago

11 hours ago
ለልጆቻችን ምን እንመግብ ?

ለልጆቻችን ምን እንመግብ ?

በሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ ዩኒሴፍ ዘገባ 38.6% ከ5 አመት በታች ያሉ ልጆች የቀነጨሩ ሲሆኑ 21% የሚሆኑ 5 አመት በታች ያሉ ልጆች ከሚጠበቅባቸዉ ክብደት በታች ያሉ ሲሆን ከ15-49 ያሉ ሴቶች በምግብ እጥረት የተጎዱ ናቸው።

ስለተመጣጠነ ምግብ ማውራት ብዙ ሰው ቅንጦት ይመስለዋል፤ ነገር ግን ቅንጦት ሳይሆን እጅግ በጣም ትኩረት ሊደረግበት የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።

ምክኒያቱም የምግብ ጉዳይ ከጽንስ ጅምሮ እስከ 2 አመት ለልጆች የምናበላዉ እስከ ህይወት ፍጻሜያቸዉ ድረስ ተጽኖ ስለሚያመጣ ትኩረት ልናደርግ ይገባል። 

ለልጆች መመገብ ካለብን ውስጥ፦

1፡ ጥሩ ቅባት (smart fat)

ህጻናት ትክክለኛ ቅባት/ fat /ያስፈልጋቸዋል። ይህ ማለት ዝቅተኛ ቅባት ሳይሆን ምርጥ ቅባት ያለዉ ምግብ ያስፈልጋቸዋል ማለት ነው።

-:ለህጻናት ጥሩ ቅባት ምንጭ ከሆኑ ምግቦች መካከል የባህር ምግብ(salmon)፣ ተልባ(flax oil)፣ አቮካዶ ፣ የአትክልት ዘይት ፣ ለውዝ (አላርጂክ ሊያስከትል ስለሚችል ከ2 አመት በኋላ)

- ለህጻናት ጥሩ ያልሆኑ ቅባቶች፡ ዘይት የበዛባቸውና የተጠበሱ ምግቦች፣ ብስኩት (crackers)

2: ጤናማ ስኳር (Best Carbs)

ህጻናት በተፈጥሮአቸዉ ስኳርና ጣፋጭ ነገሮችን ይወዳሉ፣ ሰዉነታቸዉም ይፈልጋል። ስኳር የሰዉነታቸዉ ዋናዉ ነዳጅ እና ሀይል ሰጪ ነዉ።

ጤናማ ስኳር የያዙ ምግቦች፦

አፕል ፣ ሙዝና ፍራፍሬ ፣ የጡት ወተት ፣ የወተት ተዋዖዎች (በተለይ ባዶ እርጎ) ፣ ትኩስ ፍራፍሬ፣ ፓስታ፣ ድንች ፣ አኩሪ አተር። ስኳር ድንች ፣ አትክልት እና አዝእርቶች።

3፡ ፕሮቲን 

ፕሮቲን ገንቢ ምግብ በመባል ይታወቃል። ፕሮቲን ለእድገት፣ ለሰዉነትን ግንባታ ትልቁ ድርሻ ይወስዳል።

በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦች፦

የባህር ምግብ ፣ የወተት ተዋዕዖ (እርጎ፣ቺዝ እና ወተት) ፣ ጥራጥሬ (አኩሪ አተር፣ ምስር፣ ቦሎቄ)፣ ስጋና የዶሮ ስጋ፣ እንቁላል የለዉዝ ቅቤ ፣ያልተፈተጉ እህሎች (ስንዴ፣ ሩዝ፣ አጃ፣ በቆሎ እና ማሽላ)

4፡ በፋይበር የበለጸጉ ምግቦችን ማዘውተር

ፋይበር/ቃጫ/ የምንለዉ የማይፈጨው የአትክልት እና የፍራፍሬ አካል ነው። በተፈጥሮ አንሸራታችነት ባህሪ ስላለዉ ከሰውነታችን አላስፈላጊ የሆኑ ቆሻሻዎችን  ለማሶገድ ይረዳል። ለህጻናት በፋይበር የበለጸገ ምግብ ሰገራቸዉ እንዲለሰልስና አላስፈላጊ ቆሻሻ ቶሎ እንዲወገድ ከመርዳቱም ባሻገር ድርቀትን ይከላከላል።

በፋይበር የበለጸጉ ምግቦች፦

አትክልት( ድንች ከነልጣጩ)፤ ያልተፈተጉ እህል፤ ቡኒ ሩዝ፤ ቦለቄ የመሳሰሉት፤ ካልተፈተገ እህል የተዘጋጀ ፓስታ፣ መኮረኒ፣ አጃ፣ ጥራጥሬ።

5፡ ቪታሚን

ከሶስቱ ዋና የምግብ ክፍሎች ( ቅባት፣ ፕሮቲን፣ ሃይል ሰጪ ምግቦች) በተጨማሪ ቪታሚን ለህጻናት እድገት ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርጋል። እንደ ዋና ምግቦች( Macro nutrients) እኚህ ቪታሚንና ሚኒራለስ (micro nutrients) በቀጥታ ለሰዉነታችን ሃይል አይሰጡንም። ነገር ግን ለህጻናት የበሉት ምግብ በአግባቡ እንዲጠቅማቸውና የሰውነት ክፍላቸው በአግባቡ እንዲሰራ ያደርጋል።

ሰውነታችን እነዚህን ንጥረነገሮች ካላገኘ በአግባቡ መስራት አይችልም። ሰውነታችን 13 ቪታሚኖች ያስፈልጉታል። ቪታሚን A, C, D, E, K, እና  8 የ B ቤተሰቦች ማለትም thiamine, niacin riboflavin, pantothenic acid, biotin, folacin, B6 and B12.

6: ሚኒራልስ

እንደ ቪታሚንስ ሚኒራልስ (micro nutrients) የሚካተት ሲሆን ለህጻናት እድገት አስፈላጊ ንጥረነገር ነው። ሚኒራል የምንላቸው ካልሽየም፣ ፎስፈረስ፣ ማግኒዝየም እነዚህ ሶስቱ ጠንካራ አጥንትን ለመገንባት ይጠቅማሉ።

አይረን እና ኩፐር (copper) ደምን ይገነባሉ። ዚንክ( zinc) በሽታ የመከላከል አቅምን ይገነባል፣ሶዲየምና ፖታሺየም( sodium and potassium) ኤሌክትሮ ላይት የምንለዉ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የውሃ መጠን ይቆጣጠራል።

7፡ የአይረን መጠንን መጨመር

እያንዳንዱ የሰውነታችን ክፍል( organs) በአግባቡ እንዲሰራ ብረት በጣም አስፈላጊ ንጥረነገር  ነው። ዋናው ስራውም ሂሞግሎቢንን (hemoglobin) መገንባት እና በቀይ የደም ሴል ውስጥ ያለውን ኦክስጅን የሚሸከም ነው።

አንድ ህጻን ልጅ ከ9_10 ወራት ውስጥ ሂሞግሎቢኑ መለካት አለበት፣ ይህም የሚሆንበት ምክኒያት ህጻኑ የደም ማነስ እጥረት ይኑርበት አይኑርበት ለማጣራት ነው።

በአይረን የበለጸጉ ምግቦች፦

የጡት ወተት፣ በብረት የበለጸጉ የህጻናት ወተቶች፣ የቲማቲም ጁስ፣ምስር፣ አኩሪ አተር፣አሳ፣ የዶሮ ስጋ፤ ቦለቄ እና የመሳሰሉት።

[ @BikuZega ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የቀረበ ]

@TikvahethMagazine

16 hours ago
መምህራንን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ላይ ያላቸውን …

መምህራንን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ላይ ያላቸውን እውቀት እንዲያሳድጉ የቀረበው ስልጠና

የሰውሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማበልጸግ የሚታወቀው OpenAI ከኮመን ሴንስ ሚዲያ ጋር በመሆን መምህራን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ጄኔሬቲቭ AI እና ChatGPT ላይ መሰረታዊ እና ሥነ-ምግባራዊ እንድምታዎችን የሚማሩበት ሞጁል አዘጋጅቷል።

ይህ ስልጠናም መምህራን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም የትምህርት ዕቅዶችን እና ለተማሪዎች ተጨማሪ አጋዥ ትምህርቶችን እንዲሰጡ የሚያስችላቸዋል ሲል ነው የገለጸው።

በዚህም ከኬጂ እስከ -12ኛ ክፍል የሚያስተምሩ መምህራን የኩባንያውን AI chatbot በመጠቀም እንዴት በክፍል ውስጥ መጠቀም እንደሚችሉ የሚያግዙ የኦንላይን የትምህርቶች ተዘጋጅተውላቸዋል።

AI በቅድመ መደበኛ እንዲሁም በመደበኛ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ተግባራዊ የሚድረጉ ሂደት ገና በጅምር ላይ ያለ ቢመስልም OpenAI ጨምሮ ሌሎች ኩባንያዎች እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ናቸው።

ምንም እንኳን መምህራን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን መጠቀማቸው እየጨመረ ቢሆንም በአብዛኛዎቹ አስተማሪዎች ዘንድ ቴክኖሎጂውን በመማሪያ ክፍል ውስጥ እንዲተገበር መታሰቡን አልወደዱትም።

ኮመን ሴንስ ሚዲያ በቅርብ ጊዜ በታዳጊ ወጣቶች ላን በሰራው አንድ የዳሰሳ ጥናት እንደሚያሳየው 70 በመቶዎቹ የቤት ሥራቸውን ለማገዝ ወይም አሰልቺ የሚሏቸውን ሂደቶች ላለመከተል Generative AI ይጠቀማሉ። ነገር ግን ከዚህ ውስጥ አንድ ሶስተኛው ብቻ ናቸው ይህን ቴክኖሎጂ እየተጠቀሙ መሆናቸውን ለወላጆቻቸው ያሳወቁት።

@TikvahethMagazine

16 hours ago
***😍***For ladies and gentlemen ***😍***

😍For ladies and gentlemen 😍
- ብራንድ የሴት ቦርሳዎች👜
- ኦርጅናል ሰአቶች ⌚️
-ቀሚሶች 💃
- Orginal duty free prefumes
-አድራሻ ቦሌ መድሀንያለም ሞል
-free delivery 🚚
ሱቃችንን ለመጎብኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇
https://t.me/+NuL9kONj3Mw1YzM0
https://t.me/+NuL9kONj3Mw1YzM0
https://t.me/+NuL9kONj3Mw1YzM0

1 week ago
TIKVAH-MAGAZINE
1 week ago
TIKVAH-MAGAZINE
1 week ago
[#DireDawa](?q=%23DireDawa)

#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ3 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ መኪኖችን በትራንስፖርት ዘርፍ ለማሰማራት የሚያስችል ስምምነት ከተማ አስተዳደሩ ከስዊፍት ቴክኖሎጂ እና ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ጋር ተፈራርሟል።

የስዊፍት ቴክኖሎጂ ተወካይ አቶ ብሩክ አሸብር  በሚቀጥሉት ሶስት አመታት የባጃጅ ተሽከርካሪዎችን በኤሌትሪክ መኪኖች ለመተካት  መታቀዱን ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለትም 21 የኤሌትሪክ መኪኖች መመረቃቸውን የገለጹት አቶ ብሩክ፥ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እነዚህን ዘመናዊ የኤሌትሪክ የትራንስፖርት መኪኖች በፍጥነት ስራ ለማስጀመር የብድር ምችችት እንደሚያደርግም አስታውቀዋል።

ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖቹ ወደ ስራ በሚገቡበት ወቅት የሀይል አቅርቦት ችግር እንዳይከሰት በተለያዩ ቦታዎች ቻርች ማድረጊያ ጣቢያዎች እንደሚዘጋጁም ተገልጿል።

@tikvahethmagazine

2 weeks ago
TIKVAH-MAGAZINE
2 weeks ago
TIKVAH-MAGAZINE
2 weeks ago
*" 17 በሽታ አምጪ ተህዋሲያን አዲስ …

" 17 በሽታ አምጪ ተህዋሲያን አዲስ ክትባት ሊፈለግላቸው እንደሚገባ በጥናት ለይቻው " - የዓለም ጤና ድርጅት

በአለም አቀፍ ደረጃ 17 ባክቴሪያ፣ ቫይረሶች እና  አዘውትረው በሽታን የሚያስከትሉ ጥገኛ ተህዋሲያን አዲስ ክትባት ሊፈለግላቸው እንደሚገባ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ባካሄደው አዲስ ጥናት ለይቷል።

ጥናቱ የተካሄደው በአህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ የጤና ሁኔታዎች ላይ በመመርኮዝ ነው። በዚህም ይህ እርምጃ ሥር የሰደደ በሽታ አምጪ ተህዋሲያንን ስልታዊ በሆነ መንገድ ለመከላከል የሚያስችል ነው ተብሏል።

ጥናቱ በአለም አቀፍ ደረጃ በአመት ወደ 2.5 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን በሞት የሚነጥቁትን  የኤች አይቪን፣ ወባን እና ሳንባ ነቀርሳን ጨምሮ ሌሎች ተዋህሲያን ለክትባት ምርምር እና ማልማት ቅድሚያ እንዲሰጣቸው አመልክቷል።

በዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገራት ከባድ ኢንፌክሽኖችን የሚያስከትለው እና እስከ 280ሺ የሚገድለው እንደ ግሩፕ A ስትሬፕቶኮከስ ለመሳሰሉት በሽታ አምጪ ተህዋሲያንም ቅድሚያ እንዲሰጥ ጥናቱ ለይቷል።

የክትባት ምርምር የሚያስፈልጋቸው በሽታ አምጪ ተህዋሲያን፦ ግሩፕ A streptococcus፤ ሄፓታይተስ ሲ ቫይረስ፤ ኤችአይቪ-1 Klebsiella pneumoniae ናቸው።

ክትባቶቻቸው የበለጠ እንዲበለፅጉ ከሚጠበቅባቸው መካከል ደግሞ ሳይቲሜጋሎ ቫይረስ፤ የኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ፤ ኖሮቫይረስ፤ ፕላዝሞዲየም ፋልሲፓረም ይገኙበታል።

ይህ ጥናት በአሁኑ ጊዜ የአለማቀፉን ማህበረሰብ በእጅጉ የሚጎዱ በሽታዎችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሱ ብቻ ሳይሆን ታካሚዎች በጤና ተቋም ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን ከፍተኛ የህክምና ወጪዎችን የሚቀንሱ ክትባቶችን ለማበልፀግ እንደሚረዳ ተነግሯል።

የዓለም ጤና ድርጅት ይህንን ትናት የሰራው ዓለም የአለምቀፍ እና አህጉራዊ ኤክስፐርቶች የሚሰጡትን ግምገማ መሰረት በማድረግ ሲሆን፤ በዚህ ግምገማ መሰረትም 17 በሽታ አምጪ ተዋህሲያንን አዳዲስ ክትባት እንዲሚያስፈልጋቸው መለየቱ ነው የተነገረው።

@tikvahethmagazine

2 weeks, 6 days ago

ምሽት 3:55 ላይ አዋሽ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር ከነዋሪዎች የመጡት መልዕክቶች ያስረዳሉ።

" የዛሬውስ ያስፈራ ነበር ፤ ... በጣም ነው ያስደነገጠን ፤ ከባለፉት አንጻር ዛሬ በጣም ነው የተሰማው " የሚሉ መልዕክቶች በውስጥ የመጡ ናቸው።

ንዝረቱ አዲስ አበባም ነበር።

@tikvahethiopia

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 4 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 6 days, 5 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 10 hours ago