Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

Description
FDRE, Ministry of Labor and Skills
We recommend to visit

The official Telegram on Telegram. Much recursion. Very Telegram. Wow.

Last updated 2 days, 1 hour ago

Stay connected with the latest iPapkorn Bots and News 🗞️

Bots: https://t.me/iPapkornBots/2

Last updated 4 months ago

Breaking News | Observing world events unfold in the grand theater of our time.

Last updated 3 days, 13 hours ago

1 week, 2 days ago
ሁሉንም በእኩል የሚያገለግል ገለልተኛ እና ዘመን …

ሁሉንም በእኩል የሚያገለግል ገለልተኛ እና ዘመን ተሻጋሪ የሆነ ሲቪል ሰርቪስ ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡

ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

ሀገራዊ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ላይ ያተኮረ ውይይት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪያ ካሚል እንደገለጹት ሁሉንም በእኩል የሚያገለግል ገለልተኛ እና ዘመን ተሻጋሪ የሆነ ሲቪል ሰርቪስ ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

አክለውም መንግስት ከስርዓት ጋር የማይለዋወጥ ሲቪል ሰርቪሱ ለመገንባት በቁርጠኛነት እየሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

ሀገራዊ የሪፎርም አቅጣጫውን ተከትሎ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከላይ እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥ ውጤታማና ጠንካራ የሆነ የሲቪል ሰርስ መዋቅር ለመገንባት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ሚያዝያ 14/2016 ዓ.ም
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official

1 week, 5 days ago
የምንገኝበት ምዕራፍ የእሳቤና የአሰራር ለውጥ ይፈልጋል፡፡

የምንገኝበት ምዕራፍ የእሳቤና የአሰራር ለውጥ ይፈልጋል፡፡

ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚንስትር

በዘርፉ የፐብሊክ ኢንተርፕረነርሺፕ እና ኢኖቬሽን ስነ-ምህዳር መገንባት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ለዘርፉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች እየተሰጠ ነው።

በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የዘርፉ አዲስ እሳቤ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡

ክብርት ሚኒስትር በመድረኩ ላይ እንደጠቀሱት፣ እስካሁን የመጣንበት መንገድና የለመድናቸው አሰራሮች ወደ ምንፈልገው ከፍታ ስለማያደርሱን አሁን የምንገኝበት ምዕራፍ የእሳቤና የአሰራር ለውጥ ይፈልጋል፡፡

የፐብሊክ ኢንተርፕረነርሺፕና ኢኖቨየሽን ስልጠና ደግሞ የዘርፉ ግቦች ለማሳካት እንደለውጥ መሳሪያ ይወሰዳል ብለዋል።

ስልጠናው ፐብሊክ ኢንተርፕሩነርሺፕ እና ኢኖቬሽን ምህዳር ግንባታ ላይ አተኩሮ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆይ ይሆናል።

ሚያዝያ 11/2016 ዓ.ም
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official

1 week, 6 days ago
Ministry of Labor and Skills - …
1 week, 6 days ago
Ministry of Labor and Skills - …
1 week, 6 days ago
Ministry of Labor and Skills - …
2 weeks, 4 days ago

"ዛሬ ያስጀመርነው የጎዳና ላይ የዶሮ ጥብስ ቢዝነስ ከሥራ ዕድል ፈጠራ ባለፈ ከሌማት ትሩፋት መርሃ ግብሩ ጋር በቀጥታ የሚተሳሰርና ሁሉም ዜጋ የዶሮ ሥጋን በቀላሉ ማግኘት የሚችልበትን ዕድል የሚፈጥር ነው።"

ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሀዋሳ ከተማ ሁለተኛውን የጎዳና ላይ የዶሮ ጥብስ ቢዝነስን በይፋ አስጀምሯል፡፡

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ መንግስት ለሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት ለዜጎች ምቹ፣ አስተማማኝና ዘላቂ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ሰፊ ርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከዚህ በፊት ከዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በአዳማ ከተማ የመጀመሪያውን የጎዳና ላይ የዶሮ ጥብስ ቢዝነስ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡

ይህም ከሥራ ዕድል ፈጠራ ባሻገር መንግስት በሥራ ባህል እና በስነ ምግብ የበለጸገ ትውልድ ለመገንባት በሚያደርገው ሁሉን አቀፍ ጥረት ውስጥ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ከግምት ውስጥ በማስገባት ሥራውን ወደ ሌሎች ከተሞች ለማስፋት ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

ዛሬ ያስጀመርነው የጎዳና ላይ የዶሮ ጥብስ ቢዝነስ ከሥራ ዕድል ፈጠራ ባለፈ ከሌማት ትሩፋት መርሃ ግብሩ ጋር በቀጥታ የሚተሳሰርና ሁሉም ዜጋ የዶሮ ሥጋን በቀላሉ ማግኘት የሚችልበትን ዕድል የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡

እሴት ሰንሰለትን መሰረት ባደረገው የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅጣጫችን መሰረት ሥራው በዶሮ እርባታ፣ በዶሮ መኖና ሥጋ አቅርቦት እንዲሁም በዶሮ ጤና አጠባበቅ ጋር ተያይዞ ሊፈጥር የሚችለው የሥራ ዕድል በጣም ከፍተኛ እንደሆነ ነው ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የጠቆሙት፡፡

ስለሆነም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የጎዳና ላይ የዶሮ ጥብስ ቢዝነሱን ፍላጎቱ ወዳለበት አካባቢ ለማስፋት፣ የገበያ ትስስር ለመፍጠር እና በዘርፉ በርካታ የሥራ ዕድል ለመፍጠር፤ በሂደቱም የዜጎቸን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

በእለቱ የጎዳና ላይ የዶሮ ጥብስ ቢዝነስ ከማስጀመር ባለፈ በሀዋሳ ከተማ በመናኸሪያ ክፍለ-ከተማ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ እድሳት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገ ሲሆን በከተማው ውጤታማ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች ተጎብኝተዋል፡፡

ሚያዝያ 5/2016 ዓ.ም
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official

Facebook

Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

2 months, 1 week ago

የማኅበረሰብ-አቀፍ ውይይት ለሥራ ባህል እድገትና ምርታማነት! በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ የሚገኘው የአመቻችነት የአመቻቾች ስልጠና እንደቀጠለ ይገኛል።

ስልጠናው በሀገራችን ከፍተኛ ጉድለት የሚታይበትን የሥራ ባህል ለማሳደግ፣ ምርታማነት ለማረጋገጥ፣  የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት እና  በየአካባቢው የሚገኙ መልካም ዕድሎችን ለመመልከት እና የሥራ ትጋት ለመጨመር የሚያስችል ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ስልጠናው የየአካባቢው ጸጋዎች ከመለየት ባሻገር አውጥቶ የመጠቀም እና ለማህበረሰብ ለውጥ ለማዋል አይን የሚገልጥ መሆኑንም ተመላክቷል።

የካቲት 12/2016 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ቲውተር፡- https://twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር

Facebook

Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

2 months, 1 week ago

"የማኅበረሰብ-አቀፍ ውይይት ለሥራ ባህል እድገትና ምርታማነት!”

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ምርታማነት ማረጋገጥ የሚያስችል የማህበረሰብ አቀፍ ውይይት ለማስጀመር በአመቻችነት የሚሳተፉ የአሰልጣኞች ሥልጠና ሁለተኛ ዙር መድረክ በሲዳማ እና  በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

የጅግጅጋውን መድረክ በንግግር ያስጀመሩት የሱማሌ ክልል ብልጸግና ጽ/ቤት ኃላፊ ኢንጅነር መሀመድ ሻሌ  እንደገለጹት፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የጀመረው በሥራ ባህል ላይ የሚደረገው ማህበረሰብ አቀፍ ውይይት ለዘመናት ተሸክመነው የቆየውን ድህነትና ኋላቀርነት ማራገፍ የሚስችል አዲስ መንገድ ነው ብለዋል።

የሀዋሳውን መድረክ በንግግር የከፈቱት በሲዳማ  ብሔራዊ ክልላዊ  መንግስት የሥራ ክህሎትና  ኢንተርፕራይዝ  ልማት ምክትል ኃላፊ እና የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ገቢሳ በበኩላቸው፣ የማህበረሰብ አቀፍ የምርታማነት ውይይት በትኩረት መተግበር ከተቻለ የሥራ ባህል በመቀየር በኩል ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል።

መድረኩ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ከኦሮሚያ፣ ከድሬዳዋ ከሀረሪ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ኢትዮጽያ፣  እና ከሱማሌ ክልሎች የተወጣጡ አንድ ሺህ የሚጠጉ ሰልጣኞች እየተሳተፉበት ይገኛል።

የካቲት 11/2016 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ቲውተር፡- https://twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር

Facebook

Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

2 months, 2 weeks ago

"ፕሮግራሙ ወጣቶች በተጨባጭ የሥራ ልምድ ብቁና ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል ክህሎትን የሚያላብሳቸው ነው፡፡"

ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም የመጀመሪያው ዙር ማጠቃለያ እና የሁለተኛ ዙር ምዕራፍ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በድሬደዋ ከተማ ተከናውኗል።

በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለፁት፤ መንግስት የሥራ አጥነት ምጣኔን ለመቀነስ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርም የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራው ክህሎት መር እንዲሆን አቅጣጫ አስቀምጦ በዘርፉ ሰፊ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህም ሚኒስቴር መ/ቤቱ በመደበኛ የሥራ ዕድል ፈጠራ ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጓዳኝ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር "ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም" ተግባራዊ በማድረግ ትምህርታቸውን በተለያየ ምክንያት ያቋረጡ ወጣቶችን ተጠቃሚ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ይህ ፕሮግራም ወጣቶች በሥራ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን አቅም ከመገንባት አንፃር በርካታ ልምድና ተሞክሮዎች የተገኘበት ነው፡፡

ፕሮግራሙ ወጣቶች በተጨባጭ የሥራ ልምድ ብቁና ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችል ክህሎትን የሚያላብሳቸው ነው ብለዋል።

ለፕሮግራሙ ስኬት አበርክቶ ለነበራቸው የዘርፉ አመራሮች፣ ባለድርሻ አካላትና ባለሙያዎች ምስጋና ያቀረቡት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በፕሮግራሙ አንደኛ ዙር ትግበራ የተገኙ ተሞክሮዎችን ቀምሮ በሁለተኛው ዙር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መረባረብ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የድሬዳዋ ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁዋር በበኩላቸው፣ መርሃ ግብሩን በጋራ እውን ላደረጉት ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ለዓለም ባንክ ምስጋና አቅርበው በከተማ የጀመረው መርሃ ግብር ወደ ገጠር አካባቢም እንዲሰፋ ጠይቀዋል።

የድረዳዋ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በመድረኩ ላይ እንደገለፁት፤ ብቃት የሥራ ላይ ልምምድ ከተሳተፉት ወጣቶች መካከል 96 በመቶ የሚሆኑትን ቋሚ የስራ ዕድል ባለቤት ማድረግ ተችሏሏ።

ከዚህ ባለፈም ለሁለተኛ ዙር ትግበራ መሰረት የጣለ፣ የመንግስት እና የግሉን ዘርፍ አጋርነት ያጎለበተ እና የሥራ ላይ ልምምድ ባህል እንዲዳብር ያስቻለ ስኬታማ ፕሮግራም ነው ብለዋል።

የካቲት 09/2016 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ቲውተር፡- https://twitter.com/Jobs_ሚኒስቴ

Facebook

Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

2 months, 2 weeks ago

በጋርመንት እና ቴክስታይል በምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ የሚገኘው ሀዋሳ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ካከናወናቸው የሪፎርም ሥራዎች  የማሰልጠኛ ተቋማት አካባቢያዊ ጸጋቸውን (zoning and differentiation)  መነሻ ያደረገ ስልጠና እንዲሰጡ  እና በዘርፉ ደግሞ የልህቀት ማዕከል ሆነው እንዲያገለግሉ ማድረግ ይገኝበታል፡፡

ይህንን የሪፎርም አጀንዳ ተቀብሎ በፍጥነት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከገቡ የፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጆች መካከል የሀዋሳ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ በቀዳሚነት ይጠቃሳል፡፡

የኮሌጁ ዲን አቶ መልካሙ  በራሳ እንደሚናገሩት አካባቢያዊ ጸጋ (zoning and differentiation)  መነሻ በማድረግ ማሰልጠኛ ተቋሙ ቀደም ሲል ስልጠና ይሰጥባቸው የነበሩ 33 የትምህርት መስኮች/ዶፓርትመንቶች በመቀነስ ወደ 22 ዝቅ አድርጎ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

አንደ ዲኑ ገለጻ ኮሌጁ እንደ ሀገርም እንደ ምስራቅ አፍሪካ በጋርመንት እና ቴክስታይል የልህቀት ማዕከል ሆኖ እየሰራ የሚገኘ ሲሆን በተመሳሳይ በአውቶሞቲቭ እና በቱሪዝምም የልህቀት ማዕከል ለመሆን ሰፊ ርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡

ኮሌጁ በዘንድሮ ዓመት አዳዲስ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ባቀደው መሰረት 2500 ሰልጣኞችን ተቀብሎ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

በአሁን ወቅት ኮሌጁ አዳዲስ የተቀበላቸውን አሰልጣኞችን ጨምሮ በቀን፣  በማታ እና በቅዳሜ እና እሁድ መረሃ ግብር ከ4ሺህ በላይ ሰልጣኞችን ተቀብሎ በማሰልጠን ላይ ይገኛል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት ደግሞ በአጫጭር ገበያ ተኮር ስልጠና ከ6ሺህ በላይ ሰልጣኖችን አሰልጥኗል፡፡

የካቲት 06/2016 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ቲውተር፡- https://twitter.com/Jobs_ሚኒስቴርj

Facebook

Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

We recommend to visit

The official Telegram on Telegram. Much recursion. Very Telegram. Wow.

Last updated 2 days, 1 hour ago

Stay connected with the latest iPapkorn Bots and News 🗞️

Bots: https://t.me/iPapkornBots/2

Last updated 4 months ago

Breaking News | Observing world events unfold in the grand theater of our time.

Last updated 3 days, 13 hours ago