Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад
እኔ ለአለም የማበራ ድንቅ ፀ-ሀ-ይ ነኝ !
ደውዬልሽ ነበር
ደህንነቴን ሳላውቅ" ደህና ነሽ" ወይ ልልሽ
ደውዬልሽ ነበር
ከምንጩ ታምሜ "ጤና ነሽ" ወይ ልልሽ
ደውዬልሽ ነበር
ቃላቶች አግኝቼ "ናፍቀሽኛል" ልልሽ።
ግን ስልኩን አንስተሽ ሀሎ ስትይ ያኔ
አንደበቴ ይዘጋል ቃል የለኝም ወኔ
ቆይ ግን ልክፍት ነው ፍቅር ይሉት ቅኔ?
ሰከርኩኝ ጠጥቼ
ነቃሁኝ ተኝቼ
አትሳቂብኝ እንጂ
እመኛለሁ እንጂ አላውቅም አግኘቼ።
ግን
ጠጥቼም ብሰክር ተኝቼም ብነቃ
በሳትኩት ሚዛኔ የለኝም ጠበቃ።
ብገደል ብገድል ድምብርብሬ ጠፍቶ
በሞቅታ ስሜት ስሜ እንኳ ገርጥቶ።
ብታይኝም ቅሉ
መንገዳገዴ ነው የለየኝ ከሁሉ።
ደግሞ ስቅ ባለኝ ቁጥር
አንቺ እንዳስታወሺኝ መሆኑን አውቄ
አልፈዋለው ስቄ
አትሳቂብኝ እንጂ ትዝ እንደማልልሽ አውቃለሁ ጠንቅቄ።
እውነተኛ ፍቅረኛ ከፈለክ እውነተኛ አፍቃሪ ሁን ! ምን ማለት ነው ከእኛ የሚፈለገው መልካም ሰው አፍቃሪ ሰው እንድናገኝ በመልካም እሳቤ ማመላለስ ነው ። ምን አይነት ግንኙነት ትፈልጊያለሽ ? ከምን አይነት ሰው ጋር ? ምን አይነት ባህሪ ያለው መልኩ አስተሳሰብ እነዚህን ጥያቄዎች ለራስሽ እየጠየቅሽ የምትፈልጊውን አይነት ግንኙነት ማሰብ ነው የሚጠበቅብሽ። ከዛም የስበት ሀይል ያሰብሽውን የፍቅር ህይወት የሚያኖርሽ ትክክለኛ ሰው በትክክለኛው ጊዜ ወደ አንቺ ያቀርብልሻል። ያን ያህል ቀላል ነው ።
ግን ብዙዎቻችን ይህ የግንኙነት ሚስጥር ስላልገባን የምንፈልገውን አይነት የፍቅር ህይወት ከማሰብ ይልቅ ፍቅር እኮ የለም፣ ታማኝ ሰው ጠፋ ፣ ሳፈቅር ብጎዳስ በሚሉ እና በመሳሰሉት ተራ አስተሳሰቦች መጥፎ አስተሳሰብ እየረጨን መጥፎ የፍቅር ህይወት እንኖራለን ። ስለዚህ መልካም የፍቅር ሰው እንዲሰጥሽ ስለ ፍቅር መልካም አስቢ ።
አንቺ የንጋት ፀሐይ በማለዳ ሳይሽ፣
ደስታን ምታለብሽኝ ምን ይሆን ሚስጥርሽ ?
ተነስተሀል ? ወይስ ተረስተሀል ?
ተነስ ለረሱህ አለው በላቸው ! የለም ብለው ለተውህ ከስሟል ብለው ለረገጡህ መኖርህን እየኖርክ አለመክሰምህን እያበራህ መስክርላቸው።
ቅድሚያ ግን በህይወት መኖርህን ለራስህ አሳየው! እየተነፈስኩ ነው ፣ተኝቼ ኝ የተነሳው ነው ፣ ውዬ እየገባው ነው ስለዚህ እየኖርኩ ነው አትበል ። ይሄንን ተግባር እኮ እንሰሳቱም ያደርጉታል የትኛውም ተራ ሰው ቆሞ ይሄዳል ነፋሳትም ነገሮችን ሳይመርጡ ለሚፈልጋቸው ይሰጣሉ። ታዲያ መኖር ምንድን ነው??? ካልከኝ ይህውልህ :-
መኖር በሆነ ቦታ በሆነ ጊዜ እና በሆነ ሁኔታ ውስጥ መቆየት ነው ። በዚህ ቆይታ ውስጥ ተአምራትን መፍጠር የሚችሉ ብቻ ናቸው እየኖሩ ነው ተብሎ በእርግጠኝነት መናገር የሚቻልላቸው። በዚህ የህይወት ቆይታ ድንቅ ነገሮችን ካልሰራህ መቃብር ውስጥ ካለ በድን አትሻልም ። ስለዚህ ተነስ! ከሙት እንደምትሻል ኖረህ አሳያቸው። ቁጭ ብሎ በሀሳብ ሰርቶ መውደቅ መኖር አይደለም ተነስተህ አድርገው ሞክር እና ውደቅ ድጋሚ በወደክበት መንገድ ብትሞክር አትሸወድም ምክንያቱም ወድቀህ ተምረሀል።
አቅምህን ተረዳ ፈጣሪ እድሜህን በሙሉ ተጠቅመህበት የማትጨርሰው አቅም እና ሀይል ሰጥቶሀል ። እባክህ ማድረግ እየቻልክ አትስነፍ! መከበር እየቻልክ አትዋረድ ! አሸናፊነት፣ ስኬት፣ ሀብት ፣ ዝና እና ክብር የተጋድሎ፣ የፅናት እና የአመለካከት አድማስ የፈጠራቸው ክስተቶች እንጂ የፀጋ ስጦታዎች አይደሉም ። ቢሆኑማ ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ በፃፈልን ነበር። ወዳጄ ተፈጥሮ አያዳላም! አምላክ አለማችንን የሞሉትን የሰው ዘሮች በሙሉ በእጁ አልፈጠረም ። በአንድ ሰው በአንድ አዳም ምክንያት እንጂ ። እያማረርክ ከሆነ በራስህ እፈር!
እችላለው ብለህ ተነስ ! ቀንህን በምስጋና ጀምር ! የመጣህበት የመኖር መረሐ ግብር (program) ነው ዛሬ ላይ ያለህን ማንነት ያሳየህ። አግባብ ካልሆነ ቀይረው እንቅልፋሙን program ከማንም ቀድሞ በሚነሳ ሌላ program ቀይረው ። ስነፉን ፣ አልችልም የሚለውን ፣ ሰው ምን ይለኛል የሚለውን የአስተሳሰብ program በተቃራኒው ድንቅ አመለካከቶች ቀይራቸው። ታዲያ በአንዴ መለወጥን ተጠየፍ. ቶሎ የበሰለ ፍሬ ቶሎ ይበላሻል። በሂደት እራስህን አንፀው ምክንያቱም ህይወት ሂደት ናት እና።
ይህውልህ እንግዲህ የአሸናፊነት ሚስጢር !
ምን መሰለሽ አለም
ተይ ያንቺ እንዳልመስልሽ ከመክኖሽ ብገኝም።
ምን መሰለሽ መሬት
ስጋዬ በአፈርሽ ተዋቅሮ ቢሰራ፣
ስኖርም ብሰክን ከፍሬሽ ብጋራ።
ስጋዬ እምብርትሽ ውስጥ ይመለሳል እንጂ፣
እኔ ያንቺ አይደለው አቅልሽን አትፍጂ።
ግን እኔ ያንቺ ነኝ
የመኖሬ ህላይ በአንቺ ተወስኖ፣
ብትኖሪልኝ ኑሬ ባጣሽ ዕድሜ ባክኖ።
ለመኖር ተስዬሽ
በሞቴ ብዘክርሽ፣
ሁልጊዜ ላንቺ ነኝ እናቴ ልንገርሽ።
አንቺ ቂል አለም ለምንድነው በጨለማ የምታኪው ?
@yene_eyta
ዝናብ የነብርን ቆዳ ያበሰብሰዋል እንጂ ቀለሙን አያስለቅቀውም ።
እግዚአብሔርን እያናገሩ ሴትን ከማሰብ ሴትን እያናገሩ እግዚአብሔርን ማሰብ ይሻላል።
@yene_eyta
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад