Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 5 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 15 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 week, 5 days ago
« ስርዓተ አልባነት፣ ድንቁርና፣ አደብ የሌላቸውን ነገሮች ማድረግ ቀላል ነገሮች አይደሉም። ሀያዕን የሚያህል ውበት፣ ህሊናን የሚያህል ፍትህ፣ መተናነስን የሚያህል ክብር መስወዓት ማድረግን ይጠይቃል! ምናልባት አንዳንድ ሰዎች ስርዓት አልባ ያልሆንነው የመልካም ስነ ምግባርን አስፈላጊነት ስለተረዳን ብቻ ሳይሆን እነዚህን ውድ ነገሮች ለመሰዋት አቅም እስክናገኝ ይሆናል። ነገራቶችን ሩቅ አሻግራችሁ በጥልቀት ለመረዳት ሞክሩ። ያላችሁ በሚመስላችሁ መልካም ስነ ምግባርም አትታለሉ። »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13
" ማስጠንቀቅያ ለባለቤቴ " 16
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
ይድረስ ለውዷ፣ ለማላውቃት ለወደፊቷ ባለቤቴ! እንዴት ነሽልኝ? ( ስለ ደህንነትሽ ስለጠየቅኩ ግር እንዳይልሽ ወጉ እንዳይቀርብሽ ነው።) እኔ ምልሽ እትዬዪት
የሆነ ሌላ ማስጠንቀቅያ ልፅፍ ነበር። ነገር ግን በሰርግ ካልሆነ አላገባም እንዳልሽ መረጃው ደረሰኝና ያሰብኩትን ተውኩት።
ቆይ ምን አስበሽ ነው? እኔ ሰርግ እንደማልወድ አታውቂም? አስበሽዋል በዚህ ቅጥነቴ ሱፍ ለብሼ ስታይ? ደግሞ ለሰርግ ለምንድን ነው ሱፍ የምለብሰው? ( ቢጃማ ብለብስ ቅር ይልሻል? ያው……ኧረ አጓጉል ነገር አታስቢ! ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም ያህል ነው!)
በእርግጥ እኔን የመሰለ ሰው ስታገቢ ደስታሽን ለሁሉም ለማሳየት እንደሆነ አልጠፋኝም። ግን እረፊያ! እኔ ደግሞ ይኸው አቃጣዬን እዩልኝ ማለት አልፈልግም! (ኧረ በፍቅር ነው አትንጨርጨሪ!)
ስሚኝማ ያው በሆነ ያህል ግርግር አይመችሽም። እኔን ማግኘትሽ እንጂ ሰርጉ ቢቀርም የምትከፊ አይደለሽም። ግን ደግሞ አንቺ አጋሰስ መዓት ሰርግ ይሄኔ እየሄድሽ ይሆናል። ለቤተሰብም ብለሽም ይሆናል።
እና ሰርግ መሰረጋችን የማይቀር ከሆነ ለምን በሰርጋችን ቀን ብዙ ሰው እንዳይመጣ እንዴት ማድረግ እንችላለን የሚለውን አሰብኩ! (አንቺ እንደሆነ አታስቢ እኔ እያለሁልሽ!)
አንቺም በኋላ ላይ አቋምሽን ቀይረሽ ሙልጭልጭ እንዳትዪ ስለሰጋሁና በሰርግ ጉዳይ አቋምሽ ሊከብድ ስለሚችል የሰርጋችንን ቀን የምወስነው እኔ እሆናለሁ።( አታጉረምርሚ ለሁለታችንም አስቤ ነው!)
እንግዲህ ሰርጉ አይቀርም ብለሽ ካልሽ ከእነዚህ ከምዘረዝርልሽ ቀናቶች ውስጥ አንዱን ምረጪ። ያው መቼስ እኔ ላንቺ የማልሆነው የለም።
1ኛ) የኢድ ቀን ልክ ሰላት ተሰግዶ እንዳለቀ!(ማብራራት አያስፈልግም!)
2ኛ) ረመዳን ላይ ከኢሻ በፊት! ( ይሄ ህዝብ ተራውሂ ይሰግዳል ወይስ ለእኛ ሰርግ ይመጣል? አስበሽዋል ይሄ ህዝብ እኔን ለመበቀል ተራውሂ ትቶ ወደ ሰርጋችን ሲመጣ። ጀመዓው የቀነሰባቸው የመሰጂድ ኢማሞች እባካችሁ ከተራውሂ በፊት ሰርግ አትጥሩ! ልጆቻችሁን አርሙ ብለው ዳዕዋ ሲያደርጉ። ያው እኔና አንቺ መቼስ እዛው መስጂድ ሆነን ነው የምንሰማው ዳዕዋውን! ምን ሰርጉን እንጥራ እንጂ ተራውሂውን እንደሆነ አንተወው! እንደውም ሰላት ጥለው ወደ ሰርጋችን የሄዱት ሲያጡን በዛውም የሰርግን አላስፈላጊነትና የሰላትን በላጭነት ያውቃሉ! እኔኮ አላስብ! )
3ኛ) ረመዳን 27ኛው ለሊት ላይ! ( እስቲ ሰው ለይሉን በኢባዳ ያሳልፋል ወይስ የእኛን ሰርግ ይመጣል? እሱን እናያለን! አንቺ ግን ወጥሪ በዱዓ! )
4ኛ) ሰላማዊ ሰልፍ የሚጠራበትና ረብሻ አለ ተብሎ የሚሰጋበት ቀን! ( ካልሰረጋችሁ ብሎ ሲያስጨንቀን የነበረና ሰርጋችንን የናፈቀ እስቲ ሳይፈራ ይመጣ እንደሆነ እናያለን!)
5ኛ) ከጁመዓ ሰላት በፊት! ( ይሄ ቀን ያሰጋል በርግጥ ሰርጉን ልሂድና ዝሁር እሰግዳለሁ እንዳይሉ ብቻ!)
6ኛ) ምርጫ የሚመረጥበት ቀን! (ብዙ ሰዉ ከጌታው የበለጠ መንግስትን ይፈራ የለ! መንግስትን የራስህ ጉዳይ ብለው ይመጡ እንደሆነ እስቲ እናያለን!)
ሌሎች ቀናቶችንም ልጨምር ነበር ግን ቆይ ከዚህ ሁሉ ጭንቀት ሰርጉ ቢቀርስ? ምንድን ነው ይሄን ያህል! ሰርግ ተፈርቶ እስከመቼ ትዳር ይገፋል? (ደስ አይልም!)
ደግሞ ይሄ ሙሽራ ነኝ ብለሽ ፀጉርሽን ከፋፍተሽ ካንተ ጋር ፎቶ እነሳለሁ ብለሽ እንዳታስቢ!(እኔማ እስከዛሬ ያከበርሽውን ሂጃብ ሙሽራ ስትሆኚ እንድታዋርጂው አልፈቅድልሽም!)
እንደው ለአላህ ብለሽ የሜካፑን ነገር! ከቻልሽ ይቅርብሽ! (አሀ የሰርጋችን ቀን ያየሁት መልክሽ በነጋታው ባጣው አንቺ ላይ የወሰለትኩ እንዳይመስለኝ ነዋ! አጓጉል ሜካፕ ተጠቅመሽ ሜካፑ ሲጠፋ በድንጋጤ እንደ ወንድሜ ባይሽስ! ሆ ኧረ እንዳትፈትኚኝ!)
እንደው አላህ ቀልብ ይስጥሽ እኔን ባሌ ብለሽ ስትጠብቂ!
ለማንኛውም ሰርጋችንን ማሳመሩን ሳይሆን የትዳር ህይወታችንን እንዴት እናስውበው የሚለውን በደንብ አስቢበት። ሰርጋችን ትዳራችንን እንዲበልጠው አልፈልግም!
እኔን አላህ ይጠብቅልሽ! (እስቲ አሚን በይ!) ማስጠንቀቅያውን እያሰብሽበት!
:
@Venuee13
@Venuee13
« ታሪክ ቀመስ ፊልሞች ስትመለከቱ ታሪኩን በደንብ አውቃችሁታል ማለት ሳይሆን የተወሰነ ከባዶ የሚሻል ጭላንጭል አገኛችሁ ነው ሊባል የሚችለው። በቀላል ምሳሌ ስለ ኦቶማን ሱልጣኔት እየተሰሩ ወይም የተሰሩ ፊልሞችን ስለተመለከታችሁ ስለ ኦቶማን ሱልጣኔት በደንብ አወቃችሁ ማለት አይደለም። ጭላንጭል የምታወጉትን አገኛችሁ እንጂ! በነገራችን ላይ ታሪኮች ወደ ፊልም መልክ ሲቀየሩ ብዙ አላስፈላጊ ኮተታ ኮተት እና ተጨማሪ የሌሉ ግን ከያኔው ተጨባጭ ጋር የሚመሳሰሉ ታሪኮች ይጨመረበታል። ታሪኩ ላይ ባህሎች፣ ሊተላለፍ የተፈለገውን መልዕክት እና በድብቅ ሊሰራጭ የተፈለገው ሀሳብ ተደበላልቆ ይቀርባል።
ለምሳሌ ስለ ሰለሀዲን አል አዪቢ እየተሰራ ያለውን ፊልም ብንጠቅስ መዓት አላስፈላጊ ኮተቶች አሉበት። ምንም እንኳ ዋና ግቡ ላይ ቢያተኩርም ታሪኩን ለምስል እንዲመች በሚል ከዋናው እውነተኛው ታሪክ ውጪ የሆኑ ሀሳቦችም አሉት። በአጭር አነጋገር አንድ ምክንያታዊ የሆነ ጥያቄ በጥልቀት ብንጠይቅ ሰለሀዲን አል አዩቢን ይገልፃል በሚል የተዋወቀው ገፀ ባህሪ ከእውነተኛው ሰለሀዲን አል አዩቢ ባህሪ እና ማንነት ጋር አንድ አይነት ነው ወይ ብለን ብንል ታሪኩን የምናውቀው ከሆነ ፈፅሞ እንዳልሆነ ይገባናል።
ፊልሞች በብዛት በ Subconscious ወይም በታህተ ህሊናችን ላይ ታስቦ ስለሚሰራ አናስተውልም ነገሮችን። ነገር ግን conscious ወይም ንቁ ሆነን ብንመለከተው ብዙ ልክ ያልሆኑ ነገሮችን እናገኛለን።
እውን ቁድስን ነፃ ያወጣው ያ ባለትልቅ ስብዕና ይሄ ነው ተብሎ በፊልም የቀረበልን ገፀ ባህሪ ነው ወይ ብለን በጥልቀት ብንጠይቅ ታሪኩን ባናውቀው እንኳ ሊላበስ የሚገባው ምግባር ስለምናስብ የሆነ ልክ ያልሆነ ነገር እንዳለ እንረዳለን። መቼ ካልን conscious ሆነን ከተመለከትን።
ፊልሞች ተመልክተን ስለሆነ ታሪክ በደንብ አናውቅም። አውቀናል ብለን ብናወራም በብዛት ስለ ገፀባህሪዎቹ እንጂ ስለ ታሪክ ክስተቶቹ እምብዛም ነው።
ምን ለማለት ነው ስለ ሆነ ታሪክ በዋነኛነት መፅሀፍት፣ ጉዳዩን በሚመለከት በመረጃ ላይ የተመረኮዘ ዶክመንተሪ የተሻለ ግንዛቤ ይሰጣል። »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13
« በሆነ ሰው ህይወት ውስጥ ስትገቡ፣ ወይም ወደ እናንተ ህይወት ሰው ሲገባ እራሳችሁን ሁኑ! የሆነ ሰው ያበላሸውን ነገር የማስተካከል ግዴታ የለባችሁም!
ከሆነ ሰው ጋር እውነተኛ ራሳችንን መሆናችን እንጂ የሌለን ማንነት መላበስ ወይም የሌለንን አብሮን ያለ ሰው ይወደዋል የምንለዉን ባህሪ መያዛችን አይደለም አስፈላጊው።
የሌለንን ባህሪ የውሸት ተላብሰን የምንወደውን ለጊዜው ያስደሰትነው ይመስለናል ነገር ግን አንድ ቀን በአስቀያሚ ሁኔታ ማሳዘናችን አይቀርም።
እወቀው የተሰበረ ልብ ጠጋኝ አይደለህም። ያጣውን ሰው አስረሺ ኮሚቴ አይደለሽም።
አንቺ እራስሽን ነው መሆን የምትችዪው። አንተም እራስህን ሁን! አጓጉል ያለኔ አይሆንለትም አይሆንላትም የሚል ጭምልቅና ውስጥ አትግቡ።
ለምንወዳቸው፣ ለወደድናቸው ሰዎች የሚጠቅማቸውም ሆነ የሚበጃቸው ያስደስታቸዋል ብለን ያሰብነው የሌለን ባህሪ መፈብረክ ሳይሆን እውነተኛ ማንነታችንን መያዛችን ነው። »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13
« እውነተኛ የሆኑ ታሪኮችን ማንበብ ከሚማርካቸው ሰዎች መሀል እገኛለሁ። በተለይ ወደ ኋለኛው ዘመን ላይ የተሰሩ ገድሎችን ሳነብ ለየት ያለ ስሜት ከሚሰማቸው ሰዎች ሳልመደብ አልቀርም። እስቲ በንባብ ከተገኘና ካስቀረሁት አንድ ገድል ሹክ ልበላችሁ። የጣሪቅ ቢን ዚያድን ገራሚ ገድል ላስታውሳችሁ።
እወሮፓዊቷ ሀገር ስፔን በእስልምና ሥርዓት ያሸበረቀች፣ የእውቀትና የሥልጣኔ ማዕከል የነበረች የሙስሊሞች ግዛት ነበረች።
የታሪክ መዛግብት ይህን አስደናቂ ታሪክ ከትበው አውስተዋል። አንደሉስ የስፔን እና የፖርቹጋል ግዛት በአንድ ላይ በአንድ አስተዳደር ስር የነበረበትን ወቅት ለማመልከትም እንደሆነ የታሪክ ሊቃዉንቶች ይገልፃሉ። ለማንኛውም የአሁኗ ስፔን ወርቃማዋ አንደሉስ ነበረች!
አውሮፓውያን በድንቁርና ፅልመት እየዳከሩ በነበሩበት ወቅት ከጽልመታቸው የገዘፈ ብርሀን የያዘው እስልምና በምድራቸው ፈነጠቀ። አንደሉስ በሙስሊሞች ቁጥጥር ስር ገባች።
ነገሩ እንዲህ ነው የሙስሊሞችን ጦር የሚመራው ጣሪቅ ቢን ዚያድ ተራራዎችን ተሻግሮ ባህሮቹን ቀዝፎ ወደ አንደሉስ ደጃፎች ደረሰ። የአንደሉስ መሪ የነበረው ንጉስ ሮድሪክ የጣሪቅ ቢን ዚያድን ሰራዊት መገስገሱን ሲሰማ እጅግ ብዙ ሰራዊት ላከ። ጣሪቅ ቢን ዚያድ ሰራዊቱን በአንድ ላይ ካደራጀ በኋላ ባህሩን ቀዝፈው የመጡባቸውን መርከቦች እንዲቃጠሉ አደረገ። ከሰራዊቱ ፊት ለፊት ቆሞም እንዲህ አላቸው።
«እናንተ ሰዎች ሆይ ወዴት ትሸሻላችሁ ከእንግዲህ መሸሽ የለም። ከበስተኋላችሁ ባህር ከፊት ለፊታችሁ ጠላቶቻችሁ አሉ። ለአላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ እውነተኛና ታጋሽ ከመሆን በቀር የሚጠቅማችሁ ነገር የለም። እዚህ ደሴት ላይ ስትሆኑ ይህን እወቁ ወላጆቹን ካጣ ሰው በላይ ሁሉን ያጣችሁ ናችሁ፣ ከፊት ለፊታችን ያለውን የታጠቀ ጠንካራ ሰራዊት ሰይፎቻችሁን አንስታችሁ በጀግንነት ካልተፋለማችሁ ምንም ሆናችሁ ትቀራላችሁ። ትኩረታችሁን የአላህን ሽልማት ማግኘት ላይ አድርጉ! በዚህ ጦርነት ላይ እኔ ሳልደርስ ብገደል እናንተ በፍፁም አታቁሙ! ወደፊት ገስግሱ! የአላህ ሱብሀነሁ ወተዓላን ቃል በዚህ ምድር ላይ ለማንገስ ተፋለሙ! »
በጣሪቅ ቢን ዚያድ የሚመራው የሙስሊሞች ጦር በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የንጉስ ሮድሪክን ሰራዊት ገጠመ። ጦርነቱም በሙስሊሞች አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ሙስሊሞችም የአንደሉስ መፃዒ እድል ቀይረው በፍትሀዊነትና በጥበብ ለ903 አመታት ድረስ አስተዳደሩ።
ትንሽ ታሪኮቻችንም ገለጥ ገለጥ ስናደርግ ልባችን ረጠብ ይላልና እያነበብን! እየጠየቅን ለማለት ነው። »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13
« በትክክለኛው መንገድ ለሚገባሽ ሰው እንዳታልቂ፣ የልብሽን ቀሚስ ላላፊ አግዳሚው አትግለቢ። አላህ ለማያዝንብሽ ግንኙነት ገላ ብቻ ተሸክመሽ እንዳትኖሪ፣ ልብሽን ዘልዛላ አታድርጊው። እቴ ከአጉራ ዘለል ፍላጎትሽ ጋር አኩኩሉ አትጫወቺ።
ልብሽ አደብ ካልያዘ ዝሙት አይከብድሽም።
እቴ ውበት እና ክብርሽን ካጣሽ፣ ዳግም መታደስ ከፈለግሽ በተውበት በር ዝለቂ። አላህ በቃ እስካላለ ድረስ ምንም የሚያበቃ ነገር የለምና ሰዎች ተስፋ ሲያስቆርጡሽ አላህ ዘንድ ተሸሸጊ። አላህ ጥፋቶችን በመላ ይምራልና ለተውበት አትኩሪ! እቴ ልብሽን ጠብቂ! የምወድሽዋ ሰላም ለልብሽ! »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13
« ብዙ ሰዎች የተውበት(ንሰሀ) ትልቅነት ገና በደንብ በጥልቀት አልተረዱም። የተውበትን ትልቅነት ለወሬ ማድመቅያ፣ ለስብከቶች አፍ መሟሻ ከማዋል በዘለለ እውነተኛ ተውበት ያደረጉትን ለማክበር እና ለመቀበል ብዙ ሰው ያመነታል።
እረፉ ተውበት አይናቅም። ብታውቁ ተውበትን አለማክብር የአላህን ቀደር መሟገት ነው።
እናንተ ወደ አላህ ተመላሾች ሆይ ሁሉም ሰዎች ተውበታችሁን ባይቀበሉ አትዘኑ። የተውበትን ትልቅነት፣ ልቅና የሚያውቁት እነዝያ የአላህን እዝነት የተረዱት እንጂ እውነቱን የማይነሩት አይደሉም።
የአላህ ባሮችን ተውበት የምትንቅ ልብ ወየውላት! ወደ አላህ የተመለሱ ሰዎችን ተውበት የምታጣጥል ነፍስ የአላህን ቀደር እያስተባበለች እንደሆነ ትወቅ! »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13
እያነበባችሁ ወገን! ሸጋ ሸጋ ሀሳቦች ተነስተዋል። አሁንም አልተቋጨም ሀሳቦቻችሁን አካፍሉን። በያላችሁበት ሰላም ለልባችሁ ይሁን! ???
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 5 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 15 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 week, 5 days ago