HAB NEWS 🗣

Description
https://www.youtube.com/@MIERAFMEDIA
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago

1 month, 2 weeks ago

*🔥#ዋርካው_ምሬ_ወዳጆ💪*

ዋርካው ምሬ ወዳጆ አማራ ሰው ባስፈለገው ጊዜ እውነተኛ የህዝብ ጠበቃ ሆኖ የተገኜ ለአንድነት የቆመ ማንነቱን በገንዘብና በጥቅማጥቅም የማይሸጥ የማይለውጥ #እንቁ መሪያችን ነው‼️

ዋርካው ምሬ ወዳጆ ቅንጡ ህይዎቱን ትቶ ለአማራነት የመነነ የቁርጥ ቀን ጀግናችን ነህና ክበርልን ዎርካው‼️#ላንጨርስ_አልጀመርነውም💪#ምረር_አማራ💪#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

13/3/17 ዓ.ም**@hageremedianews

1 month, 2 weeks ago

*🔥#የድሮን_ቅኝት_እና_የጥንቃቄ_መልዕክት‼️*

የአገዛዙ ሀይል በአሁኑ ሰዓት የድሮን ቅኝት እያደረገ ይገኛል። የድሮን ቅኝቱ

👉ደምበጫ ፣ደጋዳሞት (ፈረስቤት) ፣አማኑኤል ሲሆን ከዚህም ሊያልፉ ይችላሉ

👉ረቡ ገብያ( ስናን) ፣ የቦቅላ ፣ ቢቡኝና አካባቢው እንዲሁም ሞጣ ቀጠና ቅኝት እየተደረገ ይገኛልና ጥንቃቄ ይደረግ ሲሉ የንስር አማራ ምንጮች ገልፀዎል ‼️

መረጃው በsms ይዛመት ፣ሼርርርርር ይደረግ‼️#ላንጨርስ_አልጀመርነውም💪#ምረር_አማራ💪#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

ከምሽቱ 5:45
13/3/17 ዓ.ም*©* ንስር አማራ

1 month, 2 weeks ago

መረጃ ጎጃም፣

የአብይ አህመድ ወራሪው ሃይል ስቪል ከመግደል አልፎ  ብልት ተቆርጦ የተጣለበት አውደ ውጊያ !!

ዛሬ ውሎውን የአማራ ፋኖ በጎጃም /3ኛ ክፍለ ጦር )  ውጊያ ሲያደርግ ውሏል።

የአብይ አህመድ ስርዓት አሰጠባቂውን ወራሪው  ሀይል 23ኛ ክፍለ ጦር  3 ሻለቃ  ከዋዝ ቀበሌ  ፋግታ ለኮማ ወረዳ እስከ አፈሳ  ዳንግላ ዙሪያ ወረዳ ድረስ እንዲወር  የተላከውን ወራሪን ሀይል ጋር ከጠዋት 2 :00 ሰዓት የጀመረው ውጊያ አሁን አመሻሽ 12:00 ሰዓት ድርስ እንደቀጠለ ነው።

በዚህም አውደ ውጊያ የ3ኛ ከፍለጦር አናብስቶች ወራሪው ሀይል አስክሪን በአስክሪን በማድረግ እያርበደበዱት ይገኛሉ።

በዚህም  አውደ ውጊያ የተሸነፈው የአብይ አህመድ ሰራዊት ንፅሃን አስቃቂ በሆነ መንገድ አንድ ሲቪልን ግርማው ጊቴ የተባለ  በፋግታ ወረዳ ዋዝ ቀበሌ ገድለው  ብልቱን  ቆርጠው ጥለዋል ።

ይህ ድርጊት የስራዓቱን  እኔ ከሞትሁ ሰረዶ አይብቀል አለች  አህያ አሉ።የዚህ ብሂል አነጋገር አይነት ነው የአብይ አህመድ ስራዓት ያበቃለት መሆኑን በመገንዘብ ተፈጥሮአዊ መከላከልን ሁሉም በአንድነት በመቆም መመከት እንዳለብን እናሳስባለን።

አርበኛ ስለሺ ከበደ

1 month, 3 weeks ago

በድጋሚ ሁሉም እንዲያውቀው !

አብይ አህመድ መራሹ አገዛዝ የታወጀና ያልታወጀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመተግበር በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን የዘር ፍጅት እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ንፁሃን አማራዎችን የሚገድሉ፣ የሚያግቱና የሚዘርፉ ቡድኖች በባህር ዳር፣ በጎንደርና በደሴ ተደራጅተው እየሰሩ እንደሆነ ከውስጥ አዋቂ ምንጮች መረጃ ደርሶናል።

የጎንደርና የደሴን የገዳይና አስገዳይ እንዲሁም የአፋኝና ዘራፊ ቡድን ወደፊት የምንመጣበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በባህር ዳር ከተማ ያለውን የንፁሃን አማራዎች ገዳይ አስገዳይ ቡድን እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡

  1. ቡድኑን በበላይነት እየመሩ ያሉት አካላት፡-

1.1 አቶ ደሳለኝ ጣሰው--------የአማራ ክልል የሰላምና ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ
    1.2 ኮሚሽነር ደስዬ ደጀን------የአማራ ክልል ፓሊስ ፖሊስ ኮሚሽነር
   1.3 ረ/ኮ/ር ዋኘው -----የአድማ ብተና ም/ል አዛዥ ከላይ በሥም የተሰጠቀሱት የአማራ ክልል የሰላምና የፀጥታ አመራሮች የክልሉን መንግሥት መዋቅርና አቅም ሙሉ በሙሉ በመጠቀም ማንም የማያውቀው ስውር አደረጃጀት በመፍጠር በበላይነት የሚመሩ ናቸው፡፡

ይህን ስውር ገዳይና አፋኝ እንዲሁም ዘራፊ ቡድን በአብዛኛው ያደራጁት ከክልሉ የፀጥታ መዋቅር ውስጥ ማንም ሳያውቀው ወታደራዊ ብቃት አላቸው የሚሏቸውንና በጥቅም ሰንሰለት የያዟቸውን አባላት ከተለያዩ የፀጥታ ዘርፎች በመመልመል ነው፡፡

እነዚህ አመራሮች ባደራጁት የስውር ቡድን አማካኝነት በየቀኑ ማን መገደል፣ መታፈንና መዘረፍ እንዳለበት መረጃ ይቀበላሉ፤ በተገኘው መረጃ መሰረት ደግሞ ለገዳዩ የቡድኑ ክንፍ ማን መቼ መገደል እንዳለበት፤ ማን ምን ያህል ገንዘብ ከፍሎ መቼ ከእገታ ይውጣ፤ ማን በምርመራ ሥም በቀል ይፈፀምበት….ወዘተ እያሉ ስምሪት ይሰጣሉ፡፡     

በአጠቃላይ እነዚህ በአማራ ክልል ራሳቸውን አድራጊና ፈጣሪ ያደረጉ አመራሮች የብልፅግናው አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰድ በስውር በአደራጁት ቡድን የነቁ አማራዎችን እያስገደሉ፣ እያሳፈኑና እያዘረፉ ከፍተኛ የሆነ ሐብትና ንብረት እያካበቱ ያሉ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ለእነሱ ስውር አደረጃጀት አይመችም የሚሉትን በየደረጃው ያለውን የክልሉን አመራር በሐሰት መረጃ ወደ ተለያዩ ማጎሪያ ጣቢያዎች እንዲጋዝ እያደረጉ ይገኛል፡፡

  1. በባህር ዳር የተቋቋመው ገዳይና አፋኝ ቡድን ሁኔታ የአፋኝ ቡድኑ አባላት 31 ናቸው፡፡ ከቀጠናዊ ስብጥር አንጻር ከጎንደር 27፣ ከጎጃም 2 እና ከወሎ 2 ናቸው፡፡  ይህ በእነ ደሳለኝ ጣሰው የተቋቋመው የባህር ዳሩ ገዳይና አፋኝ ቡድን ለስውር ሥራው የሚጠቀማቸው ትጥቅና ተሽከርካሪዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

እነሱም፡-  4 ፓትሮል መኪናዎች፣  2 ዲሽቃዎች፣ 2 ብሬን፣  2 እስናይፐር፣  ቀሪዎች በቁጥራቸው ልክ ክላሽና ሙሉ ትጥቅ፣ የእነዚህ ስውር ገዳይና አፋኝ አባላት ጥቅማጥቅም  እንደማነኛውም የአድማ ብተና አባላት ቋሚ ደምወዝ ያገኛሉ፡፡ ሌላው በልዩ የፀጥታ ሥራ ላይ ናቸው እየተባለ ከወር እስከ ወር ከክልሉ የሰላምና ደህንነት ቢሮ አበል ይከፈላቸዋል፡፡ ባለሐብቶችንና ነጋዴዎችን በማ*ገት ከሚሰበሰበው ገንዘብና የዓይነት ሐብት ኮሚሽን  ይከፈላቸዋል፡፡

ይህ 31 አባላት ያሉት የገዳይና አፋኝ ቡድን በእነደሳለኝ ጣሰውና በእነ ኮ/ር ደስዬ ደጀን በስውር ከተቋቋመ ጀምሮ በባህር ዳርና አካባቢው ከፈፀማቸው ተግባራት መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎች ናቸው፡፡ ከባህር ዳር ከተማ 13 ወጣቶችን አፍኖ በመውሰድ ገድሎ መንገድ ላይ ጥሏቸዋል፡፡

ከ50 በላይ ባለሐብቶችን በማፈን እንደመክፈል አቅማቸው ከ50 ሽህ እስከ 4 ሚሊዮን ብር ተቀብላል። ገንዘቡን የተቀበሉት  አብዛኞችን አፍኖ ወስዶ በማሰር ሲሆን አንዳንዶችን ደግሞ በቤታቸው እንዳሉ ይህን ያህል ብር አምጡ ካልሆነ ትታሰሩና ትገደ*ላላችሁ ብሎ በማንገራገር ነው። በርካታ የመንግሥት ተሸከርካሪዎችን የአማራ ፋኖ ወሰዳቸው በሚል ሽፋን የውስጥ እቃዎቻቸውን በመፍታት አዲስ አበባ እየሄዱ እንዲሸጡ አድርጓል፡፡

የተለያዩ ባለሐብቶችን ተሸከርካሪዎች መንግሥት ለግዳጅ ፈልጎታል በሚል ሰበብና በእገታ በመያዝ እንዲሁ በቁማቸው እያረዱ ሸጠዋል፡፡ አገዛዙ ከአሰራቸው ውጭ በዚህ አፋኝ ቡድን ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ የባህር ዳር ነዋሪዎች በተለያዩ ቦታዎችና በግለሰብ ቤቶች ታፍነው ይገኛሉ፡፡ 4 የስውር ቡድኑን አባላት ረሽኗል፡፡ ስውር ቡድኑ ሲቋቋም አባላቱ 35 የነበሩ ሲሆን 4ቱን መረጃ አውጥታችኋል በሚል በእስር ሲያማቅቋቸው ቆይተው ረሽነዋቸዋል፡፡

ከእነዚህ መረሸን በኋላ እነ ደሳለኝ ጣሰው፣ ኮሚሽነር ደስዬ ደጀንና ረ/ኮ/ር ዋኘው ቀሪዎቹን 31 አባላት ሰብስበው በሚሰጣችሁ ተልዕኮ ዙሪያ መረጃ የምታወጡ ከሆነ እጣ ፈንታችሁ እንደ እነሱ መረሸን ነው ብለዋቸዋል፡፡ የተረሸ*ኑትን የስውሩ ቡድን አባላት ማንነትና የትውልድ አካባቢ ወደ ፊት የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

ከላይ እንደተባለው ይህ መረጃ በባህር ዳር ከተማና አካባቢው የተቋቋመውን ስውር ቡድን የሚመለከት ሲሆን በሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ ተግባራት እንደሚፈጽም የመረጃ ምንጫችን አረጋግጧል፡፡ የዚህ ስውር ቡድን ዋና ዓላማ የፖለቲካ ንቃት ያላቸውን አማራዎችንና የቡድኑ መሪዎች የማይፈልጓቸውን አማራዎች መግ*ደልና አጋጣሚውን በመጠቀም ሐብትና ንብረት ማካበት ነው፡፡

በመሆኑም የፌደራልም ሆነ የክልሉ መንግሥት በየራሳቸው መንግሥታዊ መዋቅሩን በመጠቀም እንዲህ የማፍያ ቡድኖችን በማደራጀት ስለሚሰሩ ይህን መረጃ ወስደው በማጣራት ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳሉ ተብሎ አይታሰብም፡፡ ይህ መረጃ የሚጠቅመው ለአማራ ክልል የከተማ ነዋሪ ሲሆን ሕዝቡም በሕግ ማስከበር ሥም እየገደለው፣ እያገተው፣ ሐብትና ንብረቱን እየዘረፈው ያለውን ስውር ቡድን በሚገባ አውቆ የሚችለውን ሁሉ እንዲያደርግ ከአፋኙ ቡደን አባላት መካከል የደረሰንን መረጃ ለማሳወቅ ነው።

(nkuamhara)

1 month, 3 weeks ago
HAB NEWS 🗣
1 month, 3 weeks ago
HAB NEWS 🗣
1 month, 3 weeks ago
~ የአማራ አንገቱ አንድ ነው!

~ የአማራ አንገቱ አንድ ነው!

"ከእንግዲህ ወዲህ ማንም ቢመጣ ተነሳሁ የሚለው አማራው ሕዝብ ላይ እንጂ ለይቶ የሸዋ፣ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የወሎ አይልም፡፡

እኛም ወደድንም ጠላንም የአማራው አንገት አንድ መሆኑን ማወቅ አለብን። ስለዚህ አማራው መተባበር አለበት"

ደጃዝማች ፀሐዩ ዕንቁስላሴ 1965 ዓ.ም

1 month, 3 weeks ago

በገዛ ወገኑ ላይ ጦር ሲያዘምት የነበረው ግንባር ቀደሙ ባንዳ 50 አለቃ አስናቀ ወንድማገኝ ላይመለስ ተሸኘ።

በጀግናው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር አስማረ ዳኜ ብርጌድ የፋኖ አባላት ላይ ጥቃት ለመፈፀም በተለያየ አቅጣጫ አሰፍስፎ የወጣው የአገዛዙ ቡድን በጀግናው የአስማረ ዳኜ ብርጌድ የፋኖ አባላት ተቀጥቅጦ በርካታ ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ተመለሰ።

ህዳር 5/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ በተለያዩ አቅጣጫዎች የተሰጠውን ሰይጣናዊ ተልዕኮ ፈፅሞ ጌቶቹን ለማስደሰት ያሰበው የብልፅግናው ወንበር ጠባቂ ቡድን በጀግናው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር አስማረ ዳኜ ብርጌድ ብርቱ ክንድ በደረሰበት የፀረ ማጥቃት ዘመቻ በርካታ ሙትና ቁስለኛውን ተሸክሞ ፈርጥጧል።

በተያያዘ ዜና ጀግናው የአስማረ ዳኜ ብርጌድ ተወርዋሪ የፋኖ አባላት ህዳር 6/2017 ዓ.ም ሌሊት ጊና አገር ከተማ ሰርገው ገብተው በፈፀሙት የደፈጣ ጥቃት በአሳግርት ወረዳ በሚሊሻ ጠርናፊነት የወረዳውን ህዝብ ሲገድልና ሲያስገድል የነበረው ሀምሳ አለቃ አስናቀ ወንድማገኝ ማን አለብኝ ብሎ እቤቱ እንደተኛ የማያዳግም እርምጃ ተወስዶበት እስከ ወዲያኛው መሸኘቱ ታዉቋል።

✍️የአማራ ፋኖ ሸዋ የህዝብ ግንኙነት ክፍል
ድል አለማራ ፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ

1 month, 3 weeks ago

መረጃ!!

እሁድ በሚካሄደው ታላቁ ሩጫ ላይ የመንግስት ካድሬዎች ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ታወቀ።

ከየወረዳው ከ100 እስከ 200 የሚሆኑ የሰራም ሰራዊት የተባሉ ሰዎች ተመልምለው በሩጫው ላይ ይሳተፋሉ፤ ለብልጽግናም የድጋፍ ጩኸት ያሰማሉ ። በሩጫው ላይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው አቅጣጫም ተቀምጦላቸዋል።

(FanoPress16)

1 month, 3 weeks ago

ፋኖዎቻችን ጥንቃቄ አይለያችሁ!!

ዛሬ በተለያዩ ቀጠናዎች የድሮን ጥቃቶች ሊኖሩ ይችላሉ።

  • በደቡብ ጎንደር
    እስቴ እና ስማዳ ቀጠና
  • በምዕራብ ጎንደር
    ቋራ መተማ
  • ምስራቅ ጎጃም
    አማኑኤል ዙሪያ፣ ፈንድቃ፣ መሶቢት
    *በሰሜን ሸዋ
    ይፋት እና ሬማ ቀጠና፣

*በሰሜን ወሎ
ወልዲያ፣ ስሪንቃ፣ ተኩለሽ እና ቃሊም ቅኝት እና ጥቃቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ መዘናጋት እንዳይኖር።

*ወደ ባህርዳር ጄት ተልኳል። ስለሆነም ሰሜን ጎጃም ቀጠና  እስከ መርጦለ ማርያም ያሉ ቀጠናዎች ላይ ጥንቃቄ አይለየን።

ምናልባት የአየር ጸባይ እና መሰል ሌሎች ምክንያቶች በተጠቀሱት ቦታዎች ቅኝቶች ካልተደረጉ በቡሬ፣ ፍኖተ ሰላም  ሰከላ እና ቲሊሊ  ቅኝት ሊደረግ ስለሚችል ፋኖዎቻችን እንድታውቁት ይሁን።
ተስፋየ ወልደስላሴ

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago