?አቡ ዒክሪማ ?أبو عكرمة الحبشي

Description
ይህ ቻናል የተለያዩ አስተማሪ የሆኑ ትምህርቶችን፣
ሙሃደራዎችን፣ የቀደምት አኢማዎችን ንግግሮች እንዲሁም የተለያዩ በጊዜያችን ያሉትን የሱና ዑለማዎች ፈትዋና ንግግር የምናቀርብበት ቻናል ነው።ሀሳብና አስተያየት ካሎት በዚህ @AbuEkrimasbot ይላኩልን
We recommend to visit

Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 8 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 3 weeks, 1 day ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች

? ውጤቶች

? የጨዋታ ፕሮግራሞች

? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 months, 2 weeks ago

2 months, 2 weeks ago

ኒቃብ ያደረገች ሴት ከሌሎች ሴቶች ግድ ልትለይባቸው የሚገቡ ጉዳዮች
? አደብ( ስርኣት) ሊኖራት ይገባል
?ንግግሯ የተስተካከለ መሆን አለበት
?አካሄዷ በእርጋታ የተሞላ መሆን አለበት
?ከሀሜት ልትርቅ ይገባል
?ወሬ ምታበዛ መሆን የለባትም
?አለባበሷን የማይመጥን ቦታ መገኘት የለባትም ወዘተ…

? አንዳንድ ኒቃብ ለባሾች ግን ለምን እንደለበሱት ሁላ የሚያውቁ አይመስሉም።
አሳፋሪ ይሆኑብሃል❗️*
ታክሲ ውስጥ በል መንገድ ላይ …ሀረካት በሀረካት እንዴ? ተረጋጉ እንጂ
❗️ሰከን በሉ❗️***

?ሲጀመር ለሌላ አላማ የተለበሰ በሚመስልክ መልኩ እንዲህ መንቀልቀል ተገቢ አይደለም❗️
ሴት ልጅ ባጠቃለይ ረጋ ስትል ያምርባታል ?ኒቃብ ያደረች ከሆነ ደግሞ በተለየ መልኩ ሀያት(እፍረት) እንዲሁም እርጋታ ያስፈጋታል። ካልሆነማ የኒቃሙ ጥቅም ምኑ ጋር ነው
እራስሽን ከሃራም ካልደበቅሽበት ሰዎችንም ከፈተና ካልጠበቅሽበት ትርጉም አልባ ነው ሚሆነው እንደውም ሌሎች ይህን የተከበረ ልብስ ሊለብሱ አስበው እንደአንቺ አይነቷን ሲያዩ እስልምናን ከማሰድብ ብለው ይተውታል በርግጥ ልክ አይደሉም ዑዝርም አይሆናቸውም አላህ ዘንድ ከመጠየቅም አያድናቸውም።
? አንቺ ግን ሰዎችን ከመልካም ነገር አባራሪ ንፁህ የዲን ሴቶችን አሰዳቢ ነሽ።
እውነት እውነቱ ይወራ ከተባለ በጣም ጋጠወጥ ሴቶች አሉ ምንም እፍረት የሌላቸው ቅብዥብዥ ያሉ ።
? እናም አንዳንዱ ዋልጌ እንደዚህች አይነቷን ስርኣት አልበኛ አይቶ ሁሉም ኒቃም ለባሽ ዝርክርክ ይመስለዋል ሊተናኮል ሊያናግርም ይቃጣዋል።
እንዲህ አይነት ሰው በየታክሲው ሌላም ቦታ ሲያጋጥማችሁ ጠንካራ የሚያስደነግጥ መልስ መልሱ
ፀጥ ብላችሁ ወሬውን አታዳምጡ❗️

አሏህ ሷሊሆችን ይጠብቅልን?

ለሁሉም ነገር ወሳኙ ተቅዋ ነው።❗️አላህም እንዲህ ይላል፦

وَلِبَاسُ ٱلتَّقْوَىٰ ذَٰلِكَ خَيْرٌ

አላህን የመፍራትም ልብስ የተሻለ ነው
   وَلِبَاسُ ٱلتَّقْوَىٰ
አላህን የመፍራት ልብስ ሲባል ሙፈሲሮች የተለያየ ገለፃን አስቀምጠዋል እሱም፦ ኢማንእፍረትአላህን መፍራት ወዘተ…
?ከምንም በላይ አስፈላጊው ጉዳይ አላህን መፍራት ተቅዋ ነው። ተቅዋ የሌላት እንስት መጀመሪያ ያሉባትን መጥፎ ባህሪያቶች፣ መጥፎ ጓደኞቿን ርቃ ጥሩ ሁኔታ ላይ ስትሆን ጊዜ ኒቃሟን ብትለብስ ጥሩ ይመስለኛል ካልሆነ ግን ከሷ አልፎ ሌሎችን በሚያስተች ሁኔታ ላይ ሆኗ መልበሷ ካልተቀየረችበት መጥፎ ባህሪዋን ለሌሎች ታጋባለች።
ውስጧ የተበላሽለ ቀልቧ የደረቀባት ሴት ቶሎ ብላ ወደ አላህ ካልተመለሰች አደጋው ከባድ ነው። በዱንያ ጭንቀት በአኼራ ደግሞ ውርደትን ትከናነባለች።

? አንድ ጊዜ ከመድረሳ ወጥቼ እየሄድኩኝ ሳለ አንዲት ኒቃብ ያደረገች ሴት ድምፇን ከፍ አድርጋ ታወራለች የምታወራው ነገር ወላሂ ልቤት ትርክክ ነው ያደረገው አላመንኩም ጮክ ብላ ማንቼ እንዴት ሆነ ተሸነፈ አሸነፈ ትላለች لاإله إلا الله ድርቅና ወላሂ አሁን እንዲህ አይነቷ ምን ትባላለች

?አንቺ ሙተነቂብ እህቴ ሆይ አስተውዬ ይህ ልብስ ተራ ልብስ አይደለም ይህ ልብስ ለውበት ፣ለአይነናስ፣ ለትዳር ማምጫ ተብሎ በተበላሸ ኒያ የሚለበስ ነገር አይደለም።   ይህ ልብስ የነብዩ ባልተቤቶች ይለብሱት የነበረ የክብር የጥቡቅነት መገለጫ ነው።  ግዴታም ጭምር ነው።

ዛሬ የምንሰማቸው ነገራቶች ግን ወላሂ ልብ ይሰብራሉ❗️ በጥቂት ሰዎች ምክንያት የነዛ ድምፃቸው እንኳ የማይሰማ ጥቡቅ እንስቶች ስም አንድ ላይ ሲነሳ ልብ ያደማል ❗️
ቆይ ግን ምን ማለት ነው ኒቃብ አድርጋ ለወንድ ፎቶ መላክ
ኒቃም ስትለብሺ እኔ ጥቡቅ ነኝ እያልሽ እኮ ነው አልገባሽም እንዴ ሲጀመር እንኳን ፎቶ መላክ ይቅርና ማውራት ራሱ መች ተፈቅዶልሽ
ብልሽትሽ የጀመረው ፎቶ የተነሳሽ ቀን ነው። በጣም ነውር ወላሂ በጣም አሳፋሪ ድርጊት ነው።
ነገ አላህ ዘንድ እርቃንሽን የምትቆሚበት ቀን ይመጣል
በአፈር የተከበበውን ጨለማውን የቀብር ቤትሽንም አትዘንጊው

?ስህተት የቅፅበት ነች ፀፀት ግን የእድሜ ልክ ነው።
? ወደ መጥፎ ሊገፋሽ የሚችልን ነገር በሙሉ ራቂ በተለይ ስልክና መጥፎ ጓደኛን❗️****

[እኔ ይህን ብያለው እናንተ ብዙ ልታውቁ ትችላላቹ አላህ ደግሞ ሁሉምን አዋቂ ከሱ የሚደበቅ ነገር ፈፅሞ የለም❗️**

አንዳንዴ ላለመታመም ለራሴ የምላት ነገር አለች ካፊሮች ይሆናሉ አውቀው ወንጀልን ለማለማመድ ልብሱን ለማጠልሽት ሲሉ**](https://t.me/AbuEkrima) ግን… ምኞት ነው።

اللهم استرنا اللهم أصلح شبابنا وشباب المسلمين ?

?https://t.me/AbuEkrima

2 months, 2 weeks ago

ዛሬ ከዙሁር ሰላት በኋላ ከአንድ ወንድሜ ጋር ከመስጂዳችን በረንዳ ጋር ቁጭ ብለን ሳለ አንድ ጀመዓ የሰገደ አይቼው የማላውቀው ሰው ሰላምታን አቀረበልን ከዛም እዚህ እናንተ ጋር ልጆቼን ከትምህርት ቤት አስወጥቼ ባመጣቸው ትቀበሉኛላችሁ አለን
እኔም ሀላፊዎች ስላሉ እነሱን ብትጠይቅ ይሻላል ምክንያቱም ትምህርት ከተጀመረ አራት ወር አካባቢ ስለሆነ እነሱን ብታነጋግር ይሻላል አልኩት።
?ሰውየውም እኔ ሳልጠይቀው ቀጠል አደረገና የአካደሚ ነገር እኮ በጣም ከበደ የልጆችን ተርቢያ መቆጣጠር አልቻልንም ታዛዥም አይደሉም ❗️እንደውም ከሚሰማው ጉድ አኳያ ባልወለድኩኝ ያስብላል አለኝ።
ሁኔታው በጣም እጅግ በጣም ከባድ ነው። ብቻ አላህ ይድረስልን እናንተንም አላህ ያግዛቹ ብሎን ሄደ።

?ይህ ሀሳብ የዚህ አንድ ግለሰብ ሃሳብ ብቻ እንዳልሆነ በደንብ አውቃለው በጣም ብዙ ሰዎች ልጆቻችንን የት እናድርጋቸው ያሉበት ደረጃ ደርሰዋል ። አዎ ጊዜው ከባድ ነው ፈተናው አደገኛ ነው። ልጅህን ሊነጠቅህ የሚፈልጉ አካላቶች በጣም ብዙ ናቸው።
ሰለ ትምህርት ቤት ሚሰሙ ጉዶች እንዲህ ነው አይባልም አብዘሃኛው ሰው ያውቀዋል። ከፆታዊ ግንኙነቶች አንስቶ አደንዛዥ እፅ እስከመጠቀም የሚደርሱት በዚሁ አካዳሚ ውስጥ ነው በል እንደውም ቅመው አሽሽ አጭሰው የሚገቡ ከወንድም ከሴትም ተማሪዎች እንዳሉ ይታወቃል እንደውም የዘመኑ የሚባሉነ ት/ ቤቶች እዛው ጊቢው ውስጥ ይዘው ገብተው የሚጠቀሙም አሉ።
ምን ይሄ ብቻ በቡድን ሆነው የሚያዩት የእርቃን ፊልሞችስ ልጅህን ጤነኛ ያደርጉልሃል? ብሩህ አይምሮ ያለው ወጣት ይሆናል እንደው አብዘሃኛው ከቤት ወደ ት/ ቤት ዝም ብሎ ይኳትናል እንጂ አንዲትንም እውቀት አይሽትም በጣም ጥቂት ሰዎች ሲቀሩ ምክንያቱም አይምሮው በሃራም ነገር የተተበተበ ልጅ ከየት መጥቶ ነው እውቀት ሚገባው ሀሳቡ ሌላ አላማው ሌላ ።
በነገራችን ላይ ስለ አካዳሚ ተወርቶ አይጨረስም ብዙ ባህሪን አውዳሚ ነገራቶች አሉት ።
ትውልድ የሚሞትበት ስፍራ ነው እኛ ሙስሊሞች ደግሞ አንድ ሆነን ለትውልድ የሚጠቅሙ ነገራቶችን ልንሰራ ይገባናል።
እኛ እንጂ ማንም ምድርን እንድትስተካከል መልካም እንዲሰራባት የሚፈልግ የለም። ሙስሊሞች አንድ ከሆኑ ብዙ ነገራቶችን ያስተካክላሉ።
አንድ እንሁን❗️

?https://t.me/AbuEkrima

2 months, 2 weeks ago

ትውልድ ቁርኣን ስለ ቀራ የነብዩን ሀዲስ ስለ ተማረ መቼም ኋላ ቀር አይሆንም❗️*
?አንዳንድ አመለካከታቸው የተንሸዋረረ ሰዎች የሰለፍዮችን መድረሳ ትውልድ መግዳያ ነው ይላሉ ።
ወላሂ በጭራሽ አይደለም
❗️*** የሰለፍዮች መድረሳ ተርቢያን ሚማሩበት ቁርኣን ሚያፍዙበት ሀዲስን የሚማሩበት ለነገ ለአኼራቸው ሰንቅን የሚያከማቹበት ቦታ ነው።
ትውልድ የሚሞተው ወንድና ሴት ተቀላቅለው በሚማሩባቸው ቦታዎች ነው

እኛም እናንተም ብዙ እናውቃለን ሁላችንም ግን ጆሮ ዳባ ልበስ ብለናል።
ምን ያህል አስፈሪ ጊዜ ላይ እንደሆንን እናውቃለን ለልጆቻችን የወደፊት እጣፋንታ ልናስብና ሁሉንም ነገር ሸሪዓው በፈቀደው ልክ ሊያገኙ የሚችሉበትን መንገድ ልናመቻችላቸው ይገባል❗️

ለትውልድ የሚጨነቁትን ትውልድ ገዳይ አድርጎ ሂጃብሽን ስትፈልጊ አውልቀሽ ለአላማሽ ስትይ ተማሪ የሚሉት ዳዒዎች የዲን ተቆርቋሪ አድርጎ ማስቀመጥ ትልቅ ግፍ ነው

سوف ترى إذا انجلا الغبار أفرس تحتك أم حمار
አቧራው ሲጠራ ከስርህ ያለው ፈረስ ነው አህያ የሚለው ይገለፅልሃል

?https://t.me/AbuEkrima

2 months, 3 weeks ago

من روائع اللّغة العربيّة:

صرخ شخصٌ فقال: وا كرباه، فنادته "الكاف" وقالت: اصرخ من أعماقك بالكلمة من دوني فأنا ذاهبة.
فقال: إلى أين؟!
فقالت: اصرخها من دوني وستعلم.
فصاح ذلك الشّخص: وا ربَّاه!

أليس الله [بكافٍ] عبده

2 months, 3 weeks ago

‏قال الشيخ عبدالرحمن بن ناصر السعدي رحمه الله:

"ومن تغافل عن عيوب الناس، وأمسك لسانه عن تتبع أحوالهم التي لا يحبون إظهارها سلم دينه وعرضه".

الفواكة الشهية/ لابن السعدي ١١٢.

2 months, 3 weeks ago

لَيَأْتِيَنَّ علَى النَّاسِ زَمانٌ، لا يُبالِي المَرْءُ بما أخَذَ المالَ، أمِنْ حَلالٍ أمْ مِن حَرامٍ

ነብዩﷺእንዳሉት በሰዎች ላይ የሆነ ዘመን ይመጣል አንድ ሰው ስለሚያገኘው ገንዘብ ማይጨነቅበት
ያ የያዘው ገንዘብ ሀላል ነው ወይም ሀራም ነው ሳይል የሚይዝበት ዘመን በሰዎች ላይ ይመጣል

?አሁን ያለንበት ነባራዊ ሁኔታ ሚያሳየን ይህን ነው። አብዘሃኛውን ሰው ስትመለከተው የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው አይነት ጨዋታ እየታጫወተ ነው ያለው። ይህ ሚያመለክተን ነገር ቢኖር ከአላህ ተግሳፅ የራቅን የአላህ ፍራቻም ከልባችን የተገፈፈ መሆኑን ነው።
?ሰዎች ሀራም ሀላል የሚባል ነገር እንደረሱ ይበልጥ ምትረዳው ደግሞ በወለድ ሲገበያዩ ወይም የወለድ ገንዘብ ሲበሉ ስትመለከት ነው። ይህ በጣም ከባዱ ወንጀል ነው። በዚህ መልኩ የመጣም ገንዘብ በረካ የለውም። አላህም እንዲህ ብሏል፦
?አላህ አራጣን በረካውን ያጠፋል። ምፅዋትን ያፋፋል።

?https://t.me/AbuEkrima

5 months, 3 weeks ago

*? የዛሬዋ ቀንና የነቢያችን ሞት!*

? በሚል ርዕስ የተዘጋጀ መደመጥ ያለበት ገሳጭ እና መካሪ የሆነ ሙሓደራ።

?️ በኡስታዝ አቡ ሙሰየብ ሃምዛ ቢን ረሻድ አላህ ይጠብቀው።

? ቅዳሜ 28/01/2015E.C ?️

? በፉርቃን መስጂድ አ/አ አለም-ባንክ

ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ???
? https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/17198 ♡ㅤ   ❍ㅤ     ⎙ㅤ     ⌲
ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ     ˢʰᵃʳᵉ

5 months, 3 weeks ago

??ሙሓደራ②

?ሴት ልጅና ተውሂድ
? ጁሙዓ ዙልቂዕዳ 27/1444

? በኡስታዝ አቡ ዒክሪማ አብዱረዛቅ حفظه الله

???
?https://t.me/AbuEkrima/682

5 months, 3 weeks ago

?ወጣቶችን የተመለከተ?

ሸይኸ ኢብን ኡሰይሚን (الله ይዘንላቸውና)እንዲህ አሉ ። ወጣቶች ከትክክለኛው መንገድ የመዘንበላቸው ዋናው ምክንያት ስራ ፈትነት ነው‼️❗️
ስራ ፈትነት በሽታ ነው አመለካከትን አይምሮን እንዲሁም ችሎታን ገዳይ ነው ስለዚህ ማንኛዋም ነፍስ እንቅስቃሴ እንዲሁም ስራ ያስፈልጋታል: ከነዚህ ነገሮች የተራቆተች ከሆነ አስተሳሰብ ይደንዛል ይዝጋል አይምሮ ይደክማል ነፍስያም ትደክማለች ይህ ከሆነ ደግሞ አጓጉል አመለካከቶች ወስዋሶች ልቡን ይቆጣጠሩታል: የዚህ ነገር መዳኒቱ ወጣቶች እራሳቸውን ሚመጥናቸው ከእውቀት ፍለጋም ይሁን ከንግድ ወይም ሌላ ነገር ከዚህ ስራ ፈትነት የሚያወጣቸው ነገር ላይ ማሳለፍ ይጠበቅባቸዋል ።
( من مشكلات الشباب) ص15–14

???
?https://t.me/AbuEkrima

6 months ago

?ጥያቄ፦የወር አበባ ወቅት ላይ ያለው ህመም የሴቲቱን ወንጀል ያራግፍላታል?

?መልስ፦
ሰዎችን የሚያሳምም ነገር በሙሉ
ሀሳብ ትካዜን የሚያመጣ ነገር በሙሉ
እሾህ እንኳን ሳይቀር አንድ ሰውን ከወጋ ለወንጀሉ ማስማሪያ ትሆናለች። አላህ ከወንጀሉ የተወሰነውን ይሰርዝለታል። በደረሰበት ሙሲባ ልክ ማለት ነው።
ከዛም በደረሰበት ነገር ላይ ከታገሰና ከአላህ የሚያገኘውን ምንዳ ኢህቲሳብ ካደረገ አላህ ምንዳን ይሰጠዋል።

? ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚን

?️?️ሉን?

?https://t.me/AbuEkrima

We recommend to visit

Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 8 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 3 weeks, 1 day ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች

? ውጤቶች

? የጨዋታ ፕሮግራሞች

? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 months, 2 weeks ago