ኬልቅያስ

Description
ኬልቅያስ የቴሌ ግራም ቻናል ኦርቶዶክሳዊ የነፍስ ማዕዶችን የሕይወት ቃል ወንጌለ መንግሥት የምስል ( vidio ) ትምህርቶች ፣ ያሬዳዊ መዝሙራትን ፣ የቅዱሳን ዜና ሕይወት ፣ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃዎች፣ የአብያተ ክርስቲያናት እና የገዳማት ታሪክ ፣ የአባቶች ምክር ፣ የጠቢባን የአባቶች አባባል ፣ መንፈሳዊ ጥቅሶች እና ኪነ - ጥበባዊ ልዩ ልዩ አውዶች የሚቀርብበት ነው።
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад

3 months, 3 weeks ago

ያለ መገኘት የጽዋ ማህበሩን አባላት ቅር ያሰኘ ቢሆንም ባለቤታቸው ያለ መኖራቸውን አሳስበው ስለነበረ ተጽናንተው ሁላቸው ጽዋውን ይዘው ከነበሩበት በሕብረት ሲነሱ የአቤል እንባና ጸሎት ግን እንደቀጠለ ነበር። በአጠገቡ ሲያልፉ ከማሕበርተኛው ልቡ ተነክቶ ያላዘነለት አልነበረም። የመሪጌታ ባለቤት ሳያስተውሉ እያወሩ ካለፉ ኋላ ሰዉ ሲያወራ ሰምተው ዞረው ቢያዩት " ውይ እኔ አፈር ልብላ የልጄ ጓደኛኮ ነው" ብለው ወደ አቤል ሲመለሱ አንድ ወዳጃቸው "ጸሎት ላይ ነው አይረብሹት ይፈጽም" ሲሏቸው ከአንዱ አጸድ ስር ተቀምጠው አንጀታቸው እየነዋወጸ ይጠብቁት ጀመሩ። አቤል ቆይታው ትዕግስታቸውን ተፈታትኖ ተነስተው ሄደው ከጸሎቱ ሊያቋርጡት ከወሰኑ በኋላ ነገሩ ተገጣጥሞ እርሱም ፈጽሞ ባለበት ቁጭ አለ። አጠገቡ ደርሰው "ምነው ልጄ ብዙ አሳሰብከንኮ ይህን ያህል ቀን ከወዴት ጠፍተህ ነው? ምን ነካህ?" አሉት። ቀና ብሎ ሲያያቸው ዓይናቸው ከዓይኑ አረፈ። " አፈር ልብላ ዓይንህ እንዲ ደም እስኪለብስ ምነው?" በል ተነስ ወደ ቤት ሄደን ታርፋለህ። ሁሉንም ተረጋግተን እንጨዋወታለን። እኔ እናትህ ከልጆቼም አልለይህ ምን ቢከፋህ ነው እንዲ መሆን? በል ተነስ" ብለውት ሁለቱም ተያይዘው ወደ ቤት አቀኑ።

እቤት ሲደርሱ ስሙር ከክፍሉ ጋደም ብሎ እንቅልፍ አሸልቦታል። የስሙር እናት ለልጆቻቸው ከያዙት ጻድቅ አንድ ቁርጥ ዳቦ ሰጥተውት " እቺን ቅመስ የጣድቁ የአቡዬ በረከት ነው። እስከዚያ ሻይ ነገር ላፍላ" ብለውት ወጡ። አቤል ወደ ስሙር ክፍል ራመድ ብሎ ሲያየው ተንጋሎ ተኝቷል። ተመልሶ ተቀመጠ። የስሙር እናት ተሯሩጠው እንደ ወትሮአቸው ሁሉ እንግዳ ከማይጠፋበት ቤታቸው ለእንግዳ መሆንን ተክነውበታልና ወዲያው ከቁርስ ያለፈ ለምሳ መዳረሻ የሚሆነውን አሰናድተው ከፈላው ሻይ ጋር ይዘው ከተፍ አሉና ወደ ስሙር ክፍል ገብተው ቀስ ብለው ቀሰቀሱትና ተነስቶ ተከትሎአቸው ወደ ሳሎን መጣ። ሁለቱም አፋቸው ተሳሰረ የሚሉት ጠፋቸውና ፈዘው ቀሩ። "ምን ሆናቹሀል ሰላም አትባባሉም እንዴ?" አሉ የስሙር አናት። ተቃቅፈው ቆዩና ሰላምታ ተለዋውጠው ወደ ማዕዱ ቀረቡ። አቤልና ስሙር ረጅም ዓመታት አብሮ ኖሮ እንደ ተነፋፈቀ ሰው በስስት እየተያዩ የቀረበውን እየበሉ ያወጉ ጀመሩ። አቤል ተመልሶ አሁን ቤት እስከ ገባበት ያለውን ሲተርክላቸው ስሙርና እናቱ መዳፋቸውን በእጃቸው ጭነው በመደነቅ ይሰሙት ጀመሩ። ስሙርም ከአቤል ተለይቶ ከመጣበት ጀምሮ የሆነውን እንዲሁ ሲያወጋ አቤልም ተደነቀ። የስሙር እናት እየሳቁ አንዴም እያዘኑ እየሰሙአቸው አንድ ነገር ትዝ አላቸውና "ስሙርዬ አባ ትህትና አልመጡም እንዴ እስካሁን? በተስኪያንም የሉምኮ" ሲሉት ዝም ብሎ ቆየና " አዎ አልመጡም። ይገርማቹሀል በቀደም ይዘውኝ ወተው..." ብሎ እርሱና ሰላም ያዩትን ነገራቸው። ቀጥሎም "እና እንዴት እዚህ ሳይኖሩ ይህን አወቁት ብዬ ብዙ ተደነኩ። ሌላም ስለርሳቸው መናገር የማልፈልገው የሚደንቀኝ ብዙ ነበረና እከታተላቸው ጀመር። ሌሊት ሲነሱ ጠብቄ የት እንደሚሄዱ ላይ ተከተልኩ" አለ ስሙር። እናቱ ቀበል አድርገው "ልፋ ቢልህ እንጂ ከበተስኪያን ውጭ የት ይሄዳሉ" አሉት። እርሱም ቀጠለ " ከመቅደስ በካህናቱ መግቢያ እስኪገቡ ጠብቄ ገባሁ። ውስጥ ስገባ እርሳቸውን ከቅኔ ማሕሌት አጣኋቸው። መቅደስ እንደሆኑ እርግጠኛ ሆኜ ሲወጡ በሚታየኝ ቦታ ቆሜ ጠብቅ ጀመር። እምብዛም አልቆዩ በዚያው ሌሊት ሰአታቱ ላይ እርሳቸው ከመቅደስ ወተው በካህናቱ በር ሲወጡ ፈጥኜ ወጣው በወንዶች በር" አለ ስሙር። እናቱ ፈገግ ብለው "እሺ አያልቅበት" ሲሉት " አባ ትህትና ወደ ቤተልሄም ሲሄዱ ብርሃኑ ወገግ ያለ ስለነበር በትክክል እያየዃቸው ከቤተልሄሙ በር በጣም ግዙፍ አንበሳ ወቶ ፊታቸው ተንበረከከ ጎፈሩን ዳብሰው እላዩ ሲቀመጡ ተነስቶ ዞሮ ቤተልሄም ገባ" ሲላቸው ሁለቱም እኩል "ምን!" አሉ። አቤል በጨለማ ውስጥ እልፍ ያለው አንበሳ የአባ ትህትና ፈረስ መሆኑ ገባውና ግን ደግሞ ማመን ቸገረው። "ውሸት ነው!" አሉ የስሙር እናት። አቤል ለምስክርነት ከተራራው ሲወርድ ያየውን ሲነግራቸው ስሙርና እናቱ "እውነትህን ነው?" አሉት። በድንገት አባ ትህትና "ደና አረፈዳችሁ!" ብለው ገቡባቸው ሶስቱም ደንግጠው ቆሙ።

💠 ይቀጥላል 💠
💢መስከረም 8 2017 ዓ.ም ባሌ ሮቤ💢

3 months, 3 weeks ago

👤👤👤👤👤 ህቡዕ ገጽ 👤👤👤👤
👤👤 ህቡዕ ገጽ 👤👤
👤 ህቡዕ ገጽ 👤

💢💠 ከክፍል 218 የቀጠለ 💠💢

አቤል ወደ ጫካው በቀረበ ቁጥር የኋላውን ትቶ ከፊቱ ስላለው ጥቅጥቅ ደን ማሰብ ጀመረና የበለጠ ፈርቶ ከጫካው ሳይገባ ባለበት ሊያነጋ አስቦ ቆም አለና ወደ መጣበት ሲዞር ከአንድ ተአምር ጋር እይታው ገጠመ። ልቡ ቀጥ አለ። ከኋላው ያየው ለማመን የሚከብድ ድንቅ ነገር ከምኔው እልፍ እንዳለ አጣው። አቤል በድን ሆኖ ቀረ። ያየውን ማመን አቃተው። በህልሙ እንጂ በዚህ ዓለም መቼም ሊሆን የማይችል ነገር እንደሆነ ቆሞ ከራሱ ይሞግት ጀመር። ያ በሀሳቡ ፍርሀት የሞላበት ባለ ጎፈር አስፈሪ አውሬ በአዋሽ ቆላቲ አንዳንድ ሰዎች ዘንድ እንደ አፈ ታሪክ የሚወራለትን ተአምር ከመሀል አዲስ አበባ እንግዳ ሆኖ ለተገኘው አቤል ሁሉ በእውን ሲሆን ታየው። አቤል ግን እያየ " በፍጹም መሆን አይችልም! ምትሀት ነው!" አለ ድምጹን አሰምቶ። ምትሀት ነው ብሎ ሙሉ ለሙሉ እንዳያምን ደግሞ አውሬው ተመልሶ ሊመጣ እንደሚችል ታሰበውና ፍርሀቱ ወደ እውነት ገፋው። አቤል ደንግጦ እንዳለ ዞሮ ሲያየው ከመቅጽበት አውሬው ከዓይኑ ተሰወረ። አቤል አንበሳው ወደ አዋሽ ጫካ ለማመን ከሚከብደው ምሥጢር ጋር ሲገባ ሲያየው ወደ ሙሲቾ ምሥጢራዊ ተራራ መመለስ አሰበና ነገሩ የማይሆን ስለመሰለው ሳያመነታ ባለበት አንግቶ ቀጥ ብሎ ትግሉን ሁሉ ፍለጋውን ሁሉ በቃኝ ብሎ አቁሞ ወደ ቀደመ ሕይወቱ መመለስ እንዳለበት ተስፋ በመቁረጥ ወስኖ ባለበት ቁጭ አለ።

💢💠🌿 ክፍል 223 🌿💠💢

አቤል ለንጊት ጥቂት ሰዓታት የቀሩት ቢሆንም ጭንቀትና ፍርሀት በአንድ ተባብረውበት ጊዜውን የዓመታት ያክል አረዘሙበት። አቤል ፍርሀት ናጠው። ከምሥጢራዊው ተራራ ግርጌ የተቃረበው በሕይወቱ ምሥጢር ፍለጋ በምሥጢር በብዙ የደከመው አቤል ከተራራው ግርጌ ከአጠገቡ በድንገት ያጣቸው ሰዎች ከወዴት እንደተሰወሩበት አስቦ ምንም እንዲህ ነው የሚለው ሀሳብ ከአዕምሮው ባይሳል " ለዚህ ባልታደል ነው። አዎ ሲሆን ይሆን ነበር ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም!" አለ ድምጹን አሰምቶ እንባው እንደ ክረምት ዝናብ ከዓይኑ እየወረደ። የራሱ ድምጽ ደግሞ መልሶ አስደነገጠው። አሁን ተስፋ በመቁረጥ ብቻውን ባለበት በዚህ ስፍራ ላይ መርፌ ቢወድቅ ድምጹ ሊሰማ የሚችልበት ተላቅ ጸጥታ ውስጥ ነው። አቤል አስሬ እየተዟዟረ ዙሪያ ገባውን ይቃኛል። እርሱና እረሰሱ ብቻ ነው። ጨረቃዋም ያደመችበት መሰለው አቤል የመጨረሻ ተከፋ። አንጋጦ እያያት በተማጽኖ እየተመለከታት ጨረቃ ከሀሳቡ የተጣላች ይመስል ቀስ እያለች ብርሃኗን ልትነሳው በጥቂት በጥዊቱ አካሏን ሸፍና ሙሉ በሙሉ ስትጠፋ አቤል እየተዟዟረ የሚያየው እንደተስፋ የቆጠረው ብርሃን ከምንም ከለከለው። አቤል ያኔ የተወለደበትን ቀን ረገመ። የስከዛሬ ድካሙ መና ሆነበት። ምርር ብሎ አጽናኝ በሌለበት አነባ። የዋጠውን ጨለማ ሲመለከት እየነጋ ሳይሆን የርሱ ሕይወት እየጨለመ የሚሄድ ፍሬ ቢስ እንደሆነ በራሱ ደመደመ። ራሱን አብዝቶ ጠላው። ማንነቱን ተጠየፈው። እድሉን አብዝቶ ኮነነው። ወደዚህ ዓለም የመጣባትን ያቺን የልደት ቀኑን ደጋግሞ ረገማት። እንባው አካሉን አጠበው። ልብሱ ራሰ። መጽናናትን አልወደደም በሀዘን ባሕር ውስጥ ተዘፈቀ። በድንገት ድጋሚ ልቡ ቀጥ እስኪል ድረስ በዚያ እንዲቆይ ምክንያት የሆነው ነገር ከዓይነ ጥቅሻ በፈጠነ በአጠገቡ ወደ ምሥጢራዊው መንደር ወደ ታላቁ ተራራ እልፍ ሲል አቤል ልቡ ምቷን አቆመች። በአጠገቡ ያለፈውን ዞሮ ሊያይ አልደፈረም። ያመልጠው ይመስል ዓይኑን ከደነ እንጂ። ልይ ቢልም ምሥጢራዊው ፈረስ ባለ ጎፈሩ አውሬ ምሥጢር ከሆነው ጨለማ ውስጥ ተሰውሮ አይታይም። አቤል ከደቂቃዎች በኋላ በቀስታ በታላቅ ጥንቃቄ ሊበላው አጠገቡ አፉን ከፍቶ የቆመ ይመስል በፍርሀት ዓይኑን ገለጠ። ከጨለማው በቀር ምንም የለም። እልፍ ያለው ምሥጢራዊው አውሬ መዳረሻው ከምሥጢራዊው ተራራ ሊሆን እንዲችል ስላሰበ አቤል በተቀመጠበት ቆይቶ ጨለማው ድንግዝግዝ ሲል ንጋት ሲቃረብ እያለቀሰ ወደ አዋሽ በተስፋ የወጣውን አቀበት ተስፋ በመቁረጥ ቁልቁል ወረደ። እንባው ትኩሳቱ ፊቱን እየለበለበው አቤል ደኑን ከፍሎ ፊቱን እንጂ ኋላውን ደግሞ እንኳን ላያይ እስካሁን የታገለውን ትግል ዳግም ላይደግመው ቆርጦ ከሕይወቱ የጣለው ያክል እየተሰማው ወደ አዋሽ ቆላቲ መንደር ገሰገሰ። ይቺን ቀን መቼም እንደማትረሳው አድርጎ ከልቡ ጽላት ላይ ከተባት። አዎ ዛሬ ሕይወቱን የበደለችውን ያህል ዛሬ ተፈጥሮን አስተባብራበት ሁሉ በእርሱ ያደመበትን ያህል ቀን አይቶ አያውቅም። ዛሬ ቁልቁል ወደ አዋሽ እየወረደ እንኳን ቁልቁለቱ የአቀበት ያክል የማይገፋ ሆኖበት መንገዱ አላልቅ ብሎት ላቡ ጠብ እያለ ልቡ እየነደደ ይጓዛል። አቤል ቢሆን ቢሳካለት የንስር ክንፍን እንኳ ቢታደል አሁን ምኞቱ ወደ መጣበት አክናፋቱን እያማታ መመለስ ብቻ ነው። ያም ግን አይሆንም። ምክንያቱም አክናፉን ሊያማታ እንኳ ተስፋ ያሻዋል። አሁን ተስፋ የሚባል ከውስጡ ተኖ አልቋል። በተስፋ መቁረጥ ጫካውን ጥቅጥቅ ያለውን ደን አጋመሰው።

ጠዋት አራት ሰዓት ሲሆን አቤል ጫካውንና በውስጡ የነበረውን ጉዞውን አጠናቆ ምሥጢራዊቷ ምንጭ አጠገብ ሲደርስ ወደርሷ ጎራ ብሎ ቢያያት ንጽሕናዋ እያሳሳው በመዳፉ እየጨለፈ ፊቱን ታጠበ። ውኃው ሲነካው አንዳች ስሜት ተሰማው። ኃይሉ የታደሰ መሰለው። በጉዞው የነበረው ድካም የለቀቀው ያክል ተሰማውና ተነስቶ ወደነ ስሙር ቤት አቀና። እየተጓዘ የዘነጋቸው ጥያቄዎች ተከሰቱለት። ሰላም ወደ ምሥጢራዊው ተራራ ከቀናት በፊት አልፋ ሄዳለች የት ደርሳ ይሆን? ስሙርስ እንደወሰነው ወደ ቤት ተልሶ ይሆን? ንፍታሌምና መሪጌታስ? እነዚያ መንታ ያማረ ደምግባት ያላቸው ወጣቶችስ? እያለ ገና በመጀመሪያው ወደ ሙሲቾ ተራራ አቅጣጫ ባደረጉት ጉዞ ከፍኖቱ ተካፋይ የነበሩትን አንድ በአንድ አስታውሶ መልሶ ራሱን ይኮንን ጀመር። " ምነው ስሙር ወደ ቤት እንመለስ ሲለኝ እሺ በጀ ብዬ በተከተልኩት?" ይላል ድምጹን አሰምቶ። " ምን አልከኝ!" አሉት አስተውሎ ሳያያቸው በአጠገቡ እያለፉ የነበሩ አንድ ሰው። ደነገጠና " ሰላም አደሩ! አይ ወዲሁ ነው" ብሎአቸው አለፈ። ቀኑን ለማስታወስ አልቸገረውም ቀኑ አምስት ስለ ነበረ በርካታ ሰዎች ከቤተክርስቲያን ቆይተው እየወጡ መሆኑን ሲያይ ከነስሙር ቤት ያሰበውን ወደ ቤተክርስቲያን ሊሄድ ወስኖ ወደ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን አቀና። ጊቢ ተሳልሞ ሲገባ ጸጸት ያሳድደው ጀመር። ንፍታሌምን በመኮነን በርሱም በመፍረድ ቆይቶ ለመጨረሻ ጊዜ ከዚህ መቅደስ የቆመበት እለት ግን የንፍታሌምን ድብቅ ማንነት ያመለከተውን ያን ጊዜ አስታውሶ ምሬቱ ከፋ። " እኔን ብሎ ሰው መዛኝ እኔን ብሎ ፈራጅ። ያው የፈረድኩበት ጸንቶ እስከ ተፈቀደለት በትጋት ሲጓዝ ፈራጁ እኔ ባክኜ ባክኜ ዛሬም እዛው። መላልሶ መድከም ማብቂያ የሌለው ክብ ሩጫ። ማስተዋል አልባ እርምጃ ፍሬ አልባ ድካም" አለና በቆመበት በጉልበቱ ወደቀና ተንበርክኮ እጆቹን ዘርግቶ ይማጸን ስለ ትናንቱ ይናዘዝ ይቅርታን ይሻ ጀመር። ከይሉንታ ዓለም ወቶ ድምጹን ከፍ አድርጎ ሰው ሰማኝ ሰው አየኝ ሳይል አሰምቶ ያማጸናል መላልሶ ይለምናል። የጻዱቁን ዝክር አዘካሪዎች አንዳንዶቹ ከነበሩበት ወተው በአጠገቡ ሲያልፉ ከንፈር እየመጠጡለት ጭንቅላታቸውን እየነቀነቁ በአጠገቡ ያልፋሉ። በእለቱ በዝክሩ ላይ የየኔታ አመሀ

4 months ago

ብላ እንባ ያዘሉ ዓይኖቿን ለራሄል አስቃኝታ " ማርታን ምን አድርጊያት ነው ያን የሚያህል ያሳዘንኳት!" አለች አቀርቅራ። ራሄል ግራ ገባትና ጠየቀቻት። ሁሉንም ስታስረዳት ራሄልም ስለ ማርታ ምንም ማለት ቸገራት። "ለሁሉም የርሷ ቀላል ነው እኔ ነኝ የማናግራት ለዚህ አትከፊ!" አለች ራሄል። ሁለቱ እያወሩ የኤርምያስ እናት ከቤት ውስጥ " ስልክሽ እየጠኣ ነው ራሄል!" አሉ። ራሄል ስትከንፍ ደረሰችና አንስታ " ሄሎ!" አለች። ቆፍጠን ያለ ጎርናና የወንድ ድምጽ " ሰላም ጤና ይስጥልኝ ልጅ ጠፍቶቦት ነበር?" አላት። ራሄል ተኮለታትፉ "አን ንፍታሌሜን አ..ነ..አዎ" አለች። ጠፍቶ የተገኘ ልጅ እኛ ጋር ስላለ ነው የከተማው ፖሊስ መምሪያ ይምጡ!" ራሄል የምትይዘው የምትጨብጠው ጠፋት።

💠 ይቀጥላል 💠
💢መስከረም 1 2017 ዓ.ም ባሌ ሮቤ💢

6 months, 1 week ago

ተስፋዬ ጎባ ከተማ መግቢያ ላይ ጥቂት አረፍ ብሎ እስኪነሳ እብዱ ከዋናው መንገድ ዳር ላይ ወዳለው የባህርዛፍ እጅብ ያለ ተቆርጦ የበቀለ ቁጥቋጦ ውስጥ ገብቶ ከዓይኑ ተሰወረና ለደቂቃዎች ከቆየ በኋላ ከገባበት ወጥቶ " ተከተለኝ!" ብሎት ከፊቱ በርቀት ይመራው ጀመር። ዋቤ ሸበሌ ሆቴል ጋር ሲደርሱ ከዋናው መስመር እብዱ ወደ ቀኙታጥፎ በዋቤ ሸበሌ ሆቴል አጥር ስር ወደ ምዕራብ አቀና ተስፋዬ በሚሄድበት ሁሉ ከኋላው ተከተለው። ኋላ በሆቴሉ አጥር ጀርባ ወደ ግራ እንደታጠፈ ቆም ብሎ ጠበቀውናተስፋዬ ሲቃረብ መሄድ ጀመረ። ተስፋዬ እየተከተለው እብዱን አልፈውት አጠገቡ የደረሱ በእድሜ ጠና ያሉ እድሜያቸው ከሰባዎቹ የሚገመቱ ሁለት ሽማግሌዎች እርስ በእርሳቸው ስለ እብዱ የሚሉት ከተስፋዬ ጆሮ ገባ። " አይ ዝምተኛው ጠፍቶ ነበር ከየት መጣ ደግሞ!" ይላሉ አንዱ። ሌላኛው ደግሞ " እርሱ እንኳን እብድ ነው ለማለት ይቸግራል ይገርሞታል አንድ ጊዜ ስለርሱ አንድ ተከትሎት ተከታትሎት ጉዱን ያየ ሰው ምን ነገረኝ መሰሎት " በዚህ በገዳሙ በኩል ከከተማ ወጥቶ እንጨት ለቅሞ ባዶውን በራሱ አስሮ ተሸክሞ ይመጣና ሸጦት መንገድ ወድቀው የሚበሉት ላጡ ይሰጣል አሉ" ሲሉ ሌላኛው " ኧረ ሰዉ የሚያወራው አጥቶ እንጂ ኢሄ እብድ አዕምሮውን የሳተ ሰውዬ ምን ሆንኩ ብሎ ነው ጤናኛው የማያደርገውን የሚያደርገው እንዴትስ በምን ተአምር!" እየተባባሉ ሲያልፉት ሰማና በሁለት ሀሳብ መሀል ያለው እርሱ ብቻ ሳይሆን ስለዚህ እብድ ብዙ ሰው ሁለት መንታ ሀሳብ እንዳለው ማወቅ ቻለ። ይህንንም አውቆ ግን እብዱን በአርምሞ ተከተለው። ወደ ተክለ ሃይማኖት ገዳም በሚወስደው መንገድ አቀበቷን ሲጀምሩ ተስፋዬ እብዱን በትክክል ማመን ጀመረ። ለዚህም ትናንትን ማስታወስ በቂው ሆነ። ትናንት በችግሩ አጠገቡ የነበረ የማያውቀው ምስኪን ጊዜውን ለርሱ ሰውቶ አብሮት የቆየ ያስታመመው ምሥጢሩን የተካፈለው ወልደ አዳም በዚህች አቀበት በኩል ወደ ደልዳላው የሕይወት መንገድ መርቶት ነበር ያን ሲያስታውስ እብዱ በትክክል ከወልደ አዳም ጋር ሊያገናኘው እየሄደ መሆኑን አመነ። የጎባ ደብረ ታቦር ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ጋር ሲደርስ እብዱ ወደ ተክለ ሃይማኖት ገዳም የሚያቀና መስሎት ሲጠብቅ እብዱ ወደ ስላሴ በሚወስደው መንገድ ወረደና መግቢያ በሩን አልፎ ቁልቁለቱን ወደ ታች ወረደ ተስፋዬ ያላሰበው ቢሆንም ተከተለው። እብዱ ወንዙ ጋር ደርሶ አምቦጫርቆ ተሻግሮ ወደ ግራ ወደ ገዳሙ አጥር አቀናና የገዳሙ አጥር ጋር ሲደርስ ቆም ብሎ " እኔ ከዚህ አልፌ አልገባም ፈራለው ወልደ አዳም የት እንዳለ ያወኩት ከሰዎች ነው። ወደ ገዳሙ ገብተህ አንድ እርሱ የሚቆይባቸው አባት አለ ሲሉ ሰምቻለው ስማቸውን ግን ዘነጋውት። ሄደህ አጠያይቀህ አግኘው። እርሱን በማግኘት ውስጥ ራስህን ታገኘዋለህ። እራስህን በማግኘት ውስጥ እንደኔ ከመሆን ትድናለህ። ከራስህ ከኅሊናህ መሸሽህ ማብቂያ እንዲያገኝ ድፈር አትፍራ እንደኔ። እኔ እንኳን ደፍሬ ዝም ብዬ እርሱ ወዳለበት ብሄድ እርግጠኛ ነኝ ድናለው። ግን ፈራለው። እንደኔ እንዳትሆን ቀድመህ ፍርሀትህን አስወግድ ራስህን አሸንፍ። ነጻነትህ ከእጅህ ነው ነጻነትህን በራስህ አትንጠቅ። ታከምና ዳን እንደኔ አትበድ እንደኔ አትበድ እንደኔ አትበድ እንደኔ ከትበድ እንደኔ አትፍራ እንደኔ አትበድ" እያለ እየጮኸ ዞሮ ወደመጣበት ሲሄድ ተስፋዬ በድንገት ዓይኑ እንባ አቅሮ ሲመለከተው ከኋላው " አትቁም ልጄ ጊዜ ጥሎህ ይሄዳል!" የሚል ድምጽ ሲሰማ ደንግጦ ዞረ።
? ይቀጥላል ?
?? ሰኔ 24 2016 ዓ.ም ባሌ ጎባ ??

6 months, 1 week ago

????? ህቡዕ ገጽ ?????
?? ህቡዕ ገጽ ??
? ህቡዕ ገጽ ?

?? ከክፍል 210 የቀጠለ ??

" እርግጠኛ ናችሁ ግን እረሰሱ ነው?" አላቸው ፖሊሱ " እራሱ ነው የሚል መረጃ ነው የደረሰን እንግዲ። ግን ተጨማሪ ኃይል አያስፈልገንም እብዱን ለመረጃ አንድ ቦታ ላይ ለማቆየት?" አለ ኤርምያስ። ፖሊሱ የሙያዊ ምላሽ ሰጥቷቸው በደቂቃዎች ውስጥ የተስፋዬ መኖሪያ ጊቢ ጋር ደረሱ። ተስፋዬ እነ ኤርምያስ በመኪና እንደሚመጡ ስለተነጋገሩ እነርሱ መሆናቸውን ሲያውቅ እብዱ አንዳች ነገር ስለ ተስፋዬ ምሥጢር ተናግሮ እንዳይዙት በመፍራት ከሚኖርበት ጊቢ ጀርባ ባለው ቦዶ ጊቢ ውስጥ ወጥቶ ከአካባቢው በፍጥነት ተሰወረ። ሻንጣውን ይዞ ግራ ቀኙን እያየ እየቃኘ ሲሄድ የጅ ስልኩ ጮኸችና ከኪሱ አውጥቶ ሲያይ Ermi ይላል " ሃሎ!" አለ ስልኩን አንስቶ። " ምን! አሁንኮ ከደቂቃዎች በፊት የኔ በር ደጃፍ ላይ ነበር። ወዴት ሄዶ ነው ታዲያ?" ሲል ከነክብሮም ጋር የነበረው ፖሊስ "መረጃ ሰጪው ቤቱ ኢሄ ነው? ብሎ ወደ ተስፋዬ ጊቢ የወዳደቀችውን በር ከፍቶ ሲገባ የቤቱ በር ቁልፍ ነው ማንም የለም። " የት ሄዶ ነው በዚህ ያህል ደቂቃ ውስጥ?" አለ ፖሊሱ። ፖሊሱ ሲጠይቅ በስልኩ ውስጥ ለተስፋዬ በደንብ ይሰማው ነበርና ደነገጠ። ኤርምያስም " አሁን አንተ የት ነህ ፈልገን አጣነው ምንም ነገር የለም። አንተ የት ነህ?" ሲለው ተስፋዬ ያለበትን ሊናገር ልቡ አስቦ ምላሱ ተሳሰረ " ንገራቸው ያለህበትን አብረን ነን በላቸው። እኔን ለመረጃ አንተን ለወንጀል ያግኙን ንገራቸው" አለ እብዱ ከኋላው። ተስፋዬ ስልኩን ዘግቶ ቆመ።

??? ክፍል 214 ???

ተስፋዬ ምንም ምን መናገር አቅቶት እብዱ ላይ ፈጦ ቀረ። እብዱ ትልቅ ዲንጋይ አነሳና " ለምንድነው የጠራኻቸው? ይዘውኝ ኸዛስ ምን እንዲፈጠር? ምን ወንጀል ሰርቼ ነው ፖሊስ የጠራኸው ተናገር" አለው ቆፍጠን እንዳለ። " እኔ አልጠራዋቸውም!" ተስፋዬ መለሰ። እብዱ " እንግዲያውስ የምትዋሸኝ ከሆነ የተፈጠረው ይፈጠር ያንተም ጉድ ይውጣ የሚፈልጉኝም ያግኙኝ? ልጩኽ?" አለ በጁ የያዘውን ድንጋይ ጥሎ በሁለት እጁ ጆሮውን ይዞ። " የለም አትጩኽ አዎ በቃ እኔ ነኝ የጠራዃቸው" እውነቱን አመነ። " ለምን?" ጠየቀው። " በስልክ እየደወሉ የነበሩት አንተን ማግኘት ይፈልጋሉ ለዛ ነው" አለው። " ለምንድነው የሚፈልጉኝ ከኔ ምን ቀራቸው? ማነው እኔን የሚፈልገኝ?" በኃይለ ቃል ተናገረው። ተስፋዬ ግራ በመጋባት ስሜት " እነ ኤርምያስ ናቸው የሚፈልጉህ። ኤርምያስ ንፍታሌም የተባለ ሕጻን ልጁ አንተ ተወግተህ ሆስፒታል የገባህና ከሰዓታት በዃላ ከተኛህበት ክፍል የታጣኽበት ቀን ነው የርሱም ልጅ የጠፋው ምናልባት መረጃ የሚሆን ነገር ካገኘን ብለው ነው የሚፈልጉህ" አለው። " እኔ ለራሴ በራሴ ስለራሴ እንደራሴ የምኖር ጤነኛ ሰው ነኝ ጤነኛ። እንዴት ሆኖ ነው ከእብዶች ጋር የሚያገናኘን ነገር የሚኖረው ምን አገናኘኝ እኔ ከእብዶች ጋር" አለውና " እሺ የነርሱን ተወው አንተ ለምን አታለልከኝ መዋሸቱ ለምን አስፈለገ። አስቤበት ውሳኔዬን አሳውቅሀለው ቆየኝ ብለኸኝ እየጠበኩ አንተ ጭራሽ ከሌሎች ጋር ተመሳጥረህ የእብዶች ጥያቄ ውስጥ ልትከተኝ። ደግሞስ ንጹህ ከሆንክ ምን አስፈራህ ለምን ትሸሻለህ? እከተልሀለው የትም አታመልጥም እኔንም እንኳ ብታመልጠኝ ከአዕምሮህ የት ሸሽተህ ልታመልጥ ነው እንዲህ ከጥፋት ወደ ጥፋት የምትሸሸው? አሁን ምን ይሁን ምርጫው እጅህ ላይ ነው" አለ እብዱ። ተስፋዬ አብሮት የሚያወራው ሰው እብድ ይሁን ጤነኛ መለየት ተሳነው። አለባበሱን አይቶ አነጋገሩን ሲመለከት ይኼማ ጤነኛ ነው ይልና ተመልሶ በየመሀሉ ሲያደርግ የሚያየውን ነገር ሲያጤን ደግሞ እርሱን ብሎ ጤነኛ ይላል ተመልሶ። " አሁን የወልደ አዳምን ነገር ምን ወሰንክ መንገደኛ ነህ? ነው ልታገኘው ትወዳለህ? ጊዜህን አታባክን ምርጫህን አሳውቀኝ" ሲለው ተስፋዬ " ወልደ አዳም ካለበት አድርሰኝ ላገኘው እወዳለው" አለው ሳያመነታ ከጤነኞች ዓለም ውስጥ ከእብዶች መደብ የሚኖረውን ምስኪን እብድ። " በል ተከተለኝ አንተም ትድናለህ እኔም ነጻ እሆናለው!" አለውና ጤነኛውን እቡዱ እየመራው ተያይዘው በእግር ወደ ጎባ ከተማ አቀኑ።

ተስፋዬ ጥቂት ተከትሎት ከድንጋጤው ሲላቀቅ " ታዲያ ወዴት ነው የምትወስደኝ!" ጠየቀ። " ተከተለኝ አዚችው ጎባ ነው አንርቅም" አለ እብዱ። " ጎባ? እኮ ጎባ በእግራችን ነው የምንሄደው?" አለ ተስፋዬ ከፊቱ ያለውን ርቀት በኅሊናው ስሎ እያሰበው። " እንግዲህ ምን አማራጭ አለ አኸኸኸኸኸኸ በሰማይ በራሪ በአውሮፕላን አንሄድ ነው የግል መኪና አለህ? እንጂ እብዶቹ ተመልሰው ድጋሚ ካላበዱ እንዴት እብድ ነው ከሚሉት ሰው ጋር በአንድ ልንሄድ እንችላለን? እኔስ እነርሱ ቢስማሙ ጤነኛ መሳይ እብዶችን አምኜ እንዴት አብሪያቸው እሄዳለው?ጰበል ና ተከተለኝ እንሂድ። ደግሞም ስትፈልገው ወደ ነበረው ነገር ሳደርስህ ደክመህ ለፍተህ ሲሆን ነው ለነገሩ ክብደት የምትሰጠው። በል አብረኸኝ ስትሄድ የሚያዩህን ጤነኛ ንጹህ ልብስ ውስጥ የተደበቁ እብዶች ትኩረታቸው አንተ ላይ እንዳይሆን ከፊትህ ቀድሜ በቅርበት ትከተለኛለህ" ብሎት እብዱ ቡቱቱውን ተስፋዬ መጠነኛ ሻንጣውን እንደተሸከሙ ፊትና ዃላ በውስጥ ለውስጥ ወደ ተነጋገሩበት አቀኑ። በየመንደሩ ውስጥ ሴቶችና ህጻናት ድንገት ሳያስቡት እብዱ በአጠገባቸው ሲያልፍ እየተጯጯሁ ተስፋዬ ጤነኛነቱን አምኖበት የሚከተለው የእብድ ልብስ ውስጥ የተደበቀው ሰው በየመሀሉ ደግሞ ውስጡም የተደበቀውን ልብሱንና አለባበሱን ሆኖ ሲያገኘው ላለመከተል የመጣው ይምጣ የሚል ሀሳብ እያየለበት ደግሞ ወዲያው በምሥጢር ተሰውሮ ያለ ከባድ ወንጀሉ በእብዱምክንያት ዘብጥያ የሚያስጥለው እየመሰለው ሳይወድ በግዴታ ይከተለዋል። በድንገት መንደር ውስጥ እየሄዱ እብዱ ከፊት ተስፋዬ በቅርብ ርቀት እየተከተለው ለገላጋይ ያስቸገሩ ሁለት ጠበኞች ጋር ሰዎች ለግልግል እየታገሉ እብዱ ደረሰና በድንገት ማንም ሳያየው ከጠቡ ደርሶ የሚያስደነግጥ ድምጽ አሰምቶ ገላጋይ ተደናግጦ ሕዝብ ሲሸሽ ሁለቱ ጠበኞች ብቻ ሲቀሩ እብዱ ድንጋይ አንስቶ እንዳይመታቸው በእነርሱ አቅጣጫ ሲወረውር ሁለቱም ተደናግጠው እግሬ አውጪኝ አሉ ሁለቱም በተለያየ አቅጣጫ " ፈሪ ሁላ ዛሬ እብዶችን ጤነኛው አሸነፈ። ሰዎች ግን እብዱ ጤነኞችን ገላገላቸው እያሉ አሙ። አዎ ልክ ናቸው እብድ ነኝ ለጠብ እብድ ነኝ ለክፋት" እያለ እየጮኸ በመንደሩ ውስጥ አልፎ ሲሄድ ተስፋዬ ዘንግቶኛል ብሎ ባሰበ ቁጥር " ዓይኖቼ አንተ ጋር ናቸው እሸሻለው አመልጣለው ብትል አዳው ላንተ ነው" እያለ ሌላውን አስመስሎ ሲናገረው በቃ ወደ ሚሄደው ተከተለው። እንዲህ ባለ ተስፋዬና እብዱ ከከተማው ወጥተው ወደ ተባባሉበት ተጓዙ።

6 months, 2 weeks ago

እየመሻሸ ነው ፀሐይም አዘቅዝቃለች ከተራራው ላይ የሚያዩት ጨለማ ብርሃን የለበሰውን አካባቢ ሁሉ ሊሸፍነው የፀሐይ ብርሃን ጊዜ ሊገባደድ ተቃርቧል። "ለቀናት ከበረታን ከዚሁ ስለምንቆይ የተሻለ ስፍራ አይተን ከዚያ እንረፍ!" አሉ ዝምተኛው አባት። አቤል ግን ነገሩ የተዋጠለት አይመስልም " የቱን አካባቢ ነው የምንመርጠው? እዚሁ ስፍራ ላይ ልንቆይ ነው እንዴ? እዚህ ውለን ልናድር? ነባራዊ ሁኔታውን እያየን? ለፈተና ራስን መስጠት አይሆንም ግን?" አለ ወደ ዝክረ ጻድቅ ጆሮ ጠጋ ብሎ። " ኤውሎት አባቴ እዚያች ተክል ነገር እሚታይባት ጋር እንሁን!" አሉ ሌላኛው አባት። ተስማምተው አራቱም ብቻዋን ወዳለች አንዲት አጭር ቅጠል የበዛባት ተክል ደርሰው ከበታቿ ተቀመጡና ዝምተኛው አባት አቆፋዳ የመሰለ እቃ መያዣቸውን አፉን ከፍተው ከውስጡ በቅጠል የተጠቀለለ ዝክረ ጻድቅ ከሰፊው ሜዳ ላይ ተኝቶ ሲነሳ ተቀምጦ ያገኘውን እርሳቸው አንስተው ከእቃ መያዣቸው የከተቱትን አሁን አውጥተው የተጠቀለለበት ቅጠል ከፍተው ባርከው " እንካችሁ" ብለው በጥቂቱ ለሌላኛው አባት ቀጥሎ ለዝክረ ጻድቅ ሰጡአቸው። ሁለቱም ተቀብለው ረሀባቸውን ለማስታገስ በስስት የተሰጣቸውን መብላት ጀመሩ። የተሰጣቸውን ግን መጨረስ ከበዳቸውና አመስግነው ጠግበው ለጸሎት የፀሐይ ብርሃን ጠፍቶ ከጨለማው ውስጥ ብዙ ከቆዩ በኋላ ለጸሎት በአንድ ቆሙ።

ስሙር የዛሬ ትኩረቱ ልዩ ነው በዝምታ ውስጥ ሆኖ እያንዳንዱን የሚሆነውን መከታተል ተያይዞታል። ለደቂቃዎች ለጸሎት በጋራ ቆመው ሲፈጽሙ በያሉበት አረፍአረፍ አሉ። ሁለቱ ዘጣቶች ጎን ለጎን ተቀምጠው ሁለቱ መነኮሳት ደግሞ ጎንለጎን እንዳሉ "ወጣቶ አልደከማችሁም እንዴ? ለነገሩ የወጣት ጉልበት..." አሉ አቤልን አላሳልፍ ካለው የጨለማ ቅጽር አሳልፈው ከዚህ ያደረሱት አባት። " ደክሞናል እናርፋለን እናንተ አረፍ በሉ" አለ አቤል። " ኋላስ ሳናርፍ አይሆን በሉ ምንም እንዳትፈሩ ከቤትም እግዜር ካልጠበቀ ከሜዳው ይብሳል ከሜዳ ደግሞ እግዜር ሲጠብቅ ከቤት ይልቅ ይደላል። ሰላም እደሩ!" ብለው ሁለቱ መነኮሳት ጎናቸውን አሳረፉ። አቤልና ዝክረጻድቅም ጨለማው ውስጥ ከቤት ለብሰው መሪጌታ አመሀን ተከትለው በወጡበት ፎጣ ተከናንበው ለረጅም ደቂቃዎች ተቀምጠው ቆይተው እንቅልፍ ሲያንጎላጃቸው እነርሱም ጎናቸውን ከመሬት አሳርፈው ክንዳቸውን ተንተርሰው ፍርሀታቸው በእንቅልፍ ተሸንፎ ለድካም እጅ ሰጡ። ወጣቶቹ እንቅልፍ እንደጣላቸው መነኮሳቱ ከተጋደሙበት ተነስተው ድምጻቸውን ዝግ አድርገው የራሳቸውን ምሥጢር ያወሩ ጀመር። 5:00 ሰዓት ሲሆን ከተናፋቂው ተራራ የብርሃን ብልጭታ ይታይ ጀመር። ብልጭታውን ሲመለከቱ የሁለቱም ልብ ወዲያው ሸፈተ። ሰዓቱ ወደፊት በሄደ ደቂቃ በተጨመረ ቁጥር የብልጭታው መጠን እየጨመረ ሲመጣ ለ 6:00 ሰዓት እሩብ ጉዳይ ሲሆን ጣፋጭ መአዛ ከተራራው አናት እታች ድረስ ለሁሉ ታደለ። መነኮሳቱ ናፍቆታቸው እንደ አዲስ ልዩ ሆነባቸው። ሁለቱም መነኮሳት በድንገት ከተቀመጡበት አንዳች ነገር ሲያዩ ዘለው ተነሱ። አንድ ከነርሱ ጋር ሳይነጋገር የሚግባባ ፍጡር አጠገባቸው ቆሞ ሲያዩ ወደናፍቆታቸው ተፋጠኑ። አንበሳው ከቆመበት ሳይንቀሳቀስ የሚያገለግላቸውን ጠበቃቸው። ሁለቱ መነኮሳት ግን አዘኑለት ወደዱት አከበሩት ራሩለት እንደወትሮው በዚህ ምሽት አልሆነም። አንዳቸው የሆነ ነገር ተናግረው አንበሳው ወዲያው ተለያቸው ሁለቱ ግን ብርሃን ወደ ሚብለጨለጭበት የውዳሴ ቤት ምሥጢራዊው ተራራ ገሰገሱ ነፍሳቸው ምስጋናውን ተርባለች ከዚያ ተራራ እልፍኝ ያለ የኅብረት የፍቅር ሰማያዊ አገልግሎት እንኳን ቀምሰው ላጣጣሙት ሲነገር ለሰሙትም የሚናፍቅ ነው። ሁለቱም እንደ ቀኑ አልዘገዩም በፍጥነት ከተራራው አናት ተገኙ። ወደ ስውሩ መቅደስ ከመግባታቸው በፊት የሚገባውን ስረአት ፈጸሙ። በዚያ ምሽት ግን ለተከታታይ ቀናት የሆነው ሁሉ ሆነ። መሪጌታ ከአካባቢው ከጠፉበት ቀን ጀምሮ እኩለ ሌሊት እንዳለፈ የሚያስደነግጥ የአንበሳ ግሳት እንዳለፉት ቀናት ዛሬም ተሰማ። ሰዓቱ 7:30 ሆኗል። ምስጢራዊው መቅደስ በሰማያዊ ምሥጢር ደምቋል። ምሥጢረኞቹ በአንድ ልብ በአንድ ቃል አንድ ሆነው ሲያዜሙ ለሰማ የምድራውያን ምስጋና ሳይሆን የመላእክት መዝሙር ነው እሚመስለው። በዚህ ላይ የተወደደው መአዛ መቅደሱን አልፎ አንዳንዴ አዋሽ ገብረመንፈስ ቅዱስ ድረስ ይወርዳል። " ኧኧኧኧኧ" ሲሉ በመንፈስ የተቀኘው ብዙ አንድ ድምጽ ልብን ያሳርፋል ሀሴት ያድላል። ሁለቱም ወደ ተወደደው ስውር መቅደስ ተቀላቀሉ። አገልግሎቱ ቀጠለ። ቅኔ ማህሌቱ ሰማያውያንን በእንግድነት የተቀበለ ነው እንጂ ነጫጭ ለብሰው የሚያዜሙት ምድራውያን አይመስሉም። ምክንያቱም በእነርሱ ዘንድ ልዩነት ጥል ክርክር የለም በመንፈስ ቅዱስ አንድ መሆንን ታድለዋል። አገልግሎቱና የነ አቤል እንቅልፍ ሁለቱም እንዳለ ቀጠለ። ሌሊት 9:45 ሲሆን ዝክረ ጻድቅ ከድካሙ ነቃ። አጠገቡ ሲመለከት አቤል ብቻ ተኝቶ አገኘው። ከዚህ ቀን በፊት ያወደው ልዩ መአዛ አወደው። ባለበት ቁጭ ብሎ ያስብ ጀመር።

? ይቀጥላል ?
?? ሰኔ 21 2016 ዓ.ም ባሌ ሮቤ ??

6 months, 2 weeks ago

????? ህቡዕ ገጽ ?????
?? ህቡዕ ገጽ ??
? ህቡዕ ገጽ ?

?? ከክፍል 109 የቀጠለ ??

" የምንሄድበት መንደር የኛ አይደለም ልዩ ነው። አንተ የመሀል ሀገር ሰው ነህ። ይህ ከፊታችን ያለ መንደር እንደ አዲስ አበባ እንደሌሎቹም ከተሞች አይደለም በውስጣቸው ያሉቱ እኛን መሰል አይደሉም እነርሱ የነፍስ ልዕልና ላይ የደረሱ ናቸው። እንደኔ አይነቱ ወደዚያ መሄድ አይገባውም ለዚህ ነው ምፈራው" አሉት። አቤል ፍርሀት ልቡን ቀስፎ ያዘው። እያወሩ ተራራውን ካዩት እንኳ ብዙ ተጉዘው ረጃጅሞቹን የሙሲቾ ቅጽሮች ዘመን ያስቆጠሩትን ዘንባባዎች በጨለማ መካከል በደንብ ማየት ቻሉ። ጉዞው ወደ ፊት ቀጠለ አቤልና አረጋዊው ከሰዓታት ጉዞ በኋላ ከተራራው ግርጌ ሲደርሱ ባርያውንና አንድ ሌላ አረጋዊ አባት ወደ ተራራው ምሥጢራዊ መወጣጫ ጋር ከተራራው ስር ተቀምጠው አገኟቸው። ከባሪያው ጋር የነበሩት አባት አቤልንና አብረውት ያሉትን አባት ሲያዩ እንደ ፀሐይ የሚያበራ ውብ ፈገግታ ከገጻቸው ታየ። ከአቤል ጋር ያሉትም እንዲሁ ገጻቸው በራ። አቤል ደስ አለው። ዝክረ ጻድቅም ሀሴት ሞላው ከተቀመጠበት ተነሳ። አብረውት ያሉት አባትም ተነሱ። አቤልና ባሪያው ሮጠው ተቃቀፉ ሁለቱ አባቶች ባሉበት ቆመው ቀሩ። በልዩ ደስታ ለረጅም ደቂቃዎች ብዙ ተለያይቶ እንደተገናኘ ሰው ተቃቅፈው ቆዩ። አቤልና ዝክረ ጻድቅ እየመሩ ከዚህ ወዳደረሷቸው መሪዎቻቸው ሲዞሩ ሁለቱም አባቶች የሉም።

??? ክፍል 113 ???

ባሪያው ዝምታን ከተላበሱት አባት ጋር የሚያውቃትን ዓለም ትቶ ርቆ ወደማያውቃት ሌላ ምድር አንዳች የእረፍት ቦታ ጉዞ መጀመሩን ሰውስጡ እርግጠኛ ሆኖ ነበር። በተለይም ንግግራቸው ከተመጠነው አባት ጋር ጥቂት ባወራቸውና ከርሳቸው በሰማው ቃላቸው ናፍቆቱ ሊሞላ ጊዜው መድረሱን ባለሙሉ ተስፋ ነበር። ባሪያው ወደ ምሥጢራዊው ተራራ መውጫ ስውር ደጅ ላይ ሲደርሱ እኚያ አባት "ደግሞ ቲኒሽ አረፍ ብንል" ብለውት ነበረ የተቀመጡት ሲያጣቸው ግራ ገባው። አቤልም ከመንገድ ያገኛቸው ፈራለው ያሉት ሰው በዚህ ቅጽበት በምን ተአምር ከየት ደረሱ ብሎ ተደነቀ። ዝክረ ጻድቅ ከአቤል ጋር የመጡት አባት አንዳች የሚያውቁት ነገር እንዳለና የበቁ እንደሆኑ በውስጡ ሲያስብ አቤል ደግሞ ከዝክረ ጻድቅ ጋር የነበሩት አባት ምሥጢር አዋቂና ልዩ ጥበብ እንዳላቸው በውስጡ አሰበ። " ወዴት ሄደው ነው?" አለ ችኩሉ አቤል። " ወደ ሀገራቸው ደርሰው ይሆናል የተለዩን!" አለ ዝክረ ጻድቅ። "በዚህ ቅጽበት?" አለ አቤል ማመን ቸግሮት። " የት ነው ሀገራቸውስ?" ጠየቀ አቤል መልሶ " እነርሱ የነርሱ አይደሉም የአምላካቸው እንጂ እርሱም የርሱ መሆናቸውን ስለሚያውቅ የርሱን ሁሉ ይሰጣቸዋል። ለርሱ በዚህ ቅጽበት አይባልምየርሱ ለሆኑትም እንደዛው። ከእንግዲህ ምንም ባይ አይሆንም አልልም ያየሁት ብዙ አስተምሮኛል። ማንንም በኔ አልለካም። የነርሱ አያሳስበኝም ሲነሱ መነሻቸውን ያውቁ ነበር ሲደርሱ ከመነሻቸው የሚያውቁት ሆነ። እኔ ነኝ እንጂ ኖሬ ያልኖርኩት" ብሎ ዝክረ ጻድቅ ዓይኑ እንባ ተሞልቶ። አቤል ዓይኖቹን በእንባ ተሞልተው ሲያይ የርሱ ቀደመው። ምንም ሳይናገር መንታ መንታ እየሆነ በጉንጩ ላይ የእንባ ዘለላ ወረደ። ከተራራው ስር ወደ ምሥጢራዊው የጥበብ የቅዱሳን ቅዱስ ቦታ ቀርበዋል። ቀና ብለው ሲመለከቱ ጨለማና በጨለማው ውስጥ ምሥጢራዊውን የሙሲቾ ተራራ ከቦ ያለ ረጃጅም እድሜ ጠገብ የዘንባባ አጸዶች በጭላንጭል ይታያቸዋል። ዓይናቸውን ከተራራው አንስተው ደግሞ ወደ መጡበት የበረከት ቀዬ ሲያዩ ጨለማ ከቶውንም የለም። አቤል ወደዚህ ለመድረስ ከቀናት በፊት አጥር የሆነበትን ከተፈጥሮ ህግ ውጪ የሆነ ጨለማ አስታወሰና ዛሬ ግን ምንም ምን ከልካይ ሳይኖር በብርሃን አሁን እስካለበት መምጣቱን ድጋሚ አስቦ እያደነቀ መልሶ ደግሞ ዓይኖቹን በርቀት ሲጥል ከተራራው ስር ወደ ተራራው ሳይወጡ ሁለቱም አባቶች ከተራራው ግርጌ በስተ ሰሜን በኩል ይደርሳሉ ተብሎ ከማይታሰብበት ተመለከተና "ዝክረ ጻድቅ!" አለ እጁን አንስቶ ወደርሱ የዞረውን ዝክረ ጻድቅን ከርሱ ጀርባ በጣቱ እያመለከተ። ዝክረ ጻድቅ ሲዞር ደስ ብሎት እንባ የተሞሉ ዓይኖቹ እንባ አወረዱ። ሁለቱም ይመሩናል ብለው ተስፋ ወደ ጣሉባቸው አባቶች ተፋጠኑ።

ሲመለከቷቸው እርምጃቸው ዝግ ያለ ቢሆንም ባሰቡት ፍጥነትና ጊዜ ሊደርሱባቸው አልቻሉም። በተለይም አቤል ከስሙር ይልቅ ዘግይቶ በድካም እነዚያ አባቶች ጋር ሊደርሱ በስተግራቸው ምሥጢራዊውን ተራራና የሸፈነውን ጨለማ እያዩ በስተ ቀኛቸው ወገግ ያለ ብርሃን እየተመለከቱ ወደ ፊት ሲያቀኑ ከሁለቱ አባቶች ፊት ለፊት የሰማይ ስባሪ የሚያህል አንበሳ እየተንጎማለለ ወደነርሱ ሲመጣ አይተው አቤልና ዝክረ ጻድቅ ሁለቱም አንበሳ ብለው ለመናገር እንኳ አፋቸው ተሳስሮ ቆመው ቀሩ። ሁለቱም ሮጠው ለማምለጥ ውስጣቸው ቢፈልግም እንደማያመልጡ ውስጣቸው አውቆ ከዚህም በላይ ደግሞ ሰውነታቸው በድን ሆኖ አልላወስ ቢላቸው ደርቀው ቀሩ። አቤልና ዝክረ ጻድቅ እየተመለከቱ ሁለቱም አባቶች የእጅ መስቀላቸውን በእጃቸው እንደያዙ ከአንበሳው ወደ ኋላ አፈገፈጉ። የአንበሳው እርምጃ ቀድሞ ዝግ ያለ ቢሆንም ከፊቱ ያሉት ባፈገፈጉ ቁጥር ግን እርምጃው የበለጠ ዝግ እያለ በቀስታ እየተራመደ ወደነርሱ አቀና። ሁለቱም እያፈገፈጉ አቤልና ስሙር ጋር ሲደርሱ " ልጆች ይህ ናፍቀን ፈልገን የመጣነው የጠቢባን መንደር ጠባቂ አለው! አሁን ከጠባቂው ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተናል። እንዳትፈሩ ወደዚህ ተራራ ያልተፈቀደለት ሊወጣ አይቻለውምና ይህ ጠባቂ መቶብናል መመለስ አለብን። ከማይቻለው ጋር አተካራ አንገጥምም። ፊታችሁን ወደ ኋላ አዙሩ ምንም አትደንግጡ እንመለስ" አሉ አዝክረ ጻድቅ ጋር የነበሩት አባት። ከአቤል ጋር የመጡት ደግሞ የሚሉት ጥርት ብሎ ባይሰማም ጸሎት ሲያነበንቡ ይሰማል። ዝክረ ጻድቅና አቤል እንደታዘዙት የኋሊት ዞረው ሥጋን በጣጥሶ ለሚጥለው አንበሳ ጀርባቸውን ሰጥተው ወደ ፊት መራመድ ጀመሩ። ይህን ማድረግ ለሁለቱም ቀላል አልነበረም። ከአሁን አሁን ከኋላችን መጥቶ ተከመረብን እያሉ ሲሰጉ " ወደ ኋላ ዞራችሁ እንዳታዩት ከዚህ በላይም አትፍጠኑ" አሉ እኚያ አባት አሁንም ለሁለቱ። ጸሎት የሚያደርሱት ግን አልጨረሱም ጸሎታቸውን እያደረሱ ዝክረ ጻድቅና አቤል ሰቀቀን ገድሏቸው ከ 40 ደቂቃ ያላነሰ መንገድ ወደ ኋላቸው ሳይዞሩ ከተሰጣቸው ትዕዛዝ ውልትፍ ሳይሉ ተጉዘው " ከእንግዲህ ወደዚህ ተራራ ለመጠጋት ፈቃደ እግዚአብሔር ያስፈልገናል።ዳግመኛ ተመልሰን ጠባቂውን ወዳገኘንበት በንመለስ የሚደርስብን ቅጣት ይከፋል። እንግዲህ ከዚህች ኮዳ ያለችውን ውኋ ለጥም እየተቃመስን ለዚህ ልጅ ከተበረከተው እርሱን ሳገኘው ካገኘሁት በቅጠል ከተጠቀለለ ከዚህ ማዕድ በመጠኑ አፋችን ላይ እየጣልን ከወዲያ ፈቅ ብለን ምልክት እስኪሰጠን በጸሎት ልንቆይ ይገባል" አሉ ዝምተኛው አባት። አቤል ቆመው ይህን ሲናገሩ ሲሰማ ፈርቶ " እንቁም እንዴ?" አለ መቆማቸው ለአደጋ እንደሚያጋልጣቸው በማሰብ። ከአቤል ጋር አብረው የመጡት አባት " አሁንማ ብንቆምም ባንቆምም ምንም የለም!" ሲሉ አቤል ተከልክሎ ወደ ቆየው እንደ ሎጥ ሚስት ግን በልቡ ማየት ወደተመኘው ወደ ኋላው ሲዞር ከተራራው በስተቀረ ምንም አይታይም። በረጅሙ " ኡፍፍፍፍፍፍ!" አለ አቤል። ቀኑ

6 months, 2 weeks ago

ሊያካፍሉት ከፊታቸው ካዩት ነገር ፊት እጅ ነስተው ወደ ስሙር መለስ አሉና " ኢትዮጵያ ምሥጢር ሀገር ነች ምሥጢርነቷ ከተዋህዶ ነው። ልጅ ስሙር ከፊትህ ምን ይታይሀል ኢኸው እዚያ ተመልከት እስቲ!" ብለው ጠቋሚ ጣታቸውን ወዳዩት ነገር አመለከቱት። ስሙር ከዛፉ ላይ አይኑን ጣል አድርጎ በትኩረት ተመለከተ። የሚያየው ነገር ቅርጹን የሚለዋውጥ ቢሆንም በእይታው ውስጥ ግን በቋሚነት የሚመለከተው ነገር አንድ የሚያውቀውን ሃይማኖታዊ የሰው ልጆች ተስፋ አስታውሶት በፍርሀት እርሱም እጅ ነሳ።

? ይቀጥላል ?
?? ሰኔ 20 2016 ዓ.ም ባሌ ሮቤ ??

6 months, 2 weeks ago

በርካታ ቀኖች ተቆጠሩ። የአካባቢው ሰው ሰምቶ ፍለጋ ተባበረ። ብዙው ሰው ግን ደፍሮ ወደ ሙሲቾ ተራራ አቅጣጫ ሊሄድ የወደደ አልነበረም። ምክንያቱም ከልብስ የሚያራቁተው አንበሳ ታሪክ የብዙውን ሰው ልብ አሸብሯል። ሰዉ ሁሉ ፍለጋ ሲደክም አንድም ቀን አባትህ ከብቶቹን ፍለጋ ከቤታቸው አልወጡም። የሚፈልጉትን አትድከሙ ከማለት በቀር። እርሳቸውም ከቤታቸው ፍለጋ ሳይወጡ የወጡትም ከብቶቹን ሳያገኙ ሁሉም ተስፋ ቆርጦ ፍለጋው ቆመ። ክረምቱ ገብቶ አንድ ቀን በዚህ መንደር ተሰምቶ የማይታወቅ አንድ ነገር ተሰማ። ቀኑ ሰንበት ነበር መሪጌታ ከገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ከቅዳሴ ላይ እያሉ ሕዝቡ ሁሉ እያስቀደሰ "የሚያስደነግጠው የአንበሳ ግሳት ጩኸት ተሰማ። መነጋገሪያ የሆነው ግን ሆኖ በማያውቅ መልኩ ያ ድምጽ ሶስት ጊዜ ደጋግሞ ተሰማ። የሐገር ሽማግሌዎች አረጋውያን አባቶች ቅዳሴ ሲያልቅ " ሆኖ አይተን የማናውቀው በቀያችን ሆኗል ሁላችንም ሶስት ጊዜ የአንበሳ ግሳት አስፈሪውን ድምጽ ሰምተናል። ጎበዝ ከቀያችን እግዜርን የሚያስቆጣ አንዳች ነገር ሳይሆን አልቀረም እግዚኦ እንበል"አሉ ስመ ጥሩ ያገር ሽማግሌ እጅ አውጥተው። ሌላኛው ቀበል አድርገው " አዎ ይቺ ቀዬ የኚህን መልካም ሰው ሀብት ሸሽጋለች ከዚህ ሚበልጥ በደልም የለ" አሉ ወደ መሪጌታ አመሀ እጃቸውን እያመላከቱ። " ስለዚህ ሰልችተን የተውነውን የርሳቸውን ከብቶች ፍለጋ አጠናክሮ መቀጠል አልያ ለመሪጌታ ተነጋግረን የሚሆነውን ማድረግ። እስከዚያም ለመቆየት ግን የሰማነው አስደንጋጭ ነገር ያስፈራልና ማረን ብለን እግዚኦ ብንል" ብለው ተቀመጡ። ቀጣዩ ሽማግሌ ከዘራቸውን እየነቀነቁ " ኦሮሚፋነን ዱበዳ ወኒ ገንደ ከነቲ ሀርአ ጉረ ኬኘ ገዬ ኩን ዋቀ ሙፈቺሱ ኬኘ አገርሲሰ። ኤ ሌንጪ ኩን ከነ ዱረስ ዋን ነመ ሆጂ ረቢ ሂን ጃለኔ ሆጄቱ ሰን ጎዴ ሁንዱ ሂን ቤክነ አመስ ሴናዳን ተኤ ከን ሂን ቤክኔ ኢየ ዮ ሰዲ ሀርአ ደጌኜ ከናፍ ዋቀዮ አራራ አከ ኑፍ ጎዱፍ ሀከደኑን ጄደ" ብለው ሀሳቡን አጠናክረው ተቀመጡና ሕዝቡ ሁሉ በፍርሀት ሆኖ እግዚኦታ ተደርሶ ሰዉ ወደየ ቤቱ ሲመለስ በቀዬው ድንቅ ተአምር በአደባባይ ታየ። ያን ጠንቋይ ጨርቁን ቀዳዶ እርቃኑን ያስቀረው አንበሳ ጠፍተው የከረሙትን የአባትህን ከብቶች ሰው ሁሉ ጉድ እስኪል ገሚሱ ፈርቶ እስኪሸሽ ከብቶቹን እየነዳ ወደ ቤት አስገብቶ ከበረታቸው አግብቶ ከሰው ዓይን ተሰውሯል። በዚህና በልሎችም ነገሮች ጭምር ነው መሪጌታ በዚህ መንደር በተለየ የሚከበሩት" አሉት። ስሙር ፈዞ ሲያዳምጥ ቆይቶ " እንዴት ያለ መንደር ነው ኢሄ መንደር! እኔ እንኳን ወደ ሙሲቾ መሄድ አሁን ከሌሎቹ ጋር ካለሁበትም ቀዬ መኖር አይገባኝም። ኢሄ ከአሜሪካም ከቻይናም ከነጮች የስልጣኔ ምድር መራቀቅ በላይ የረቀቀ ምሥጢር መንደር ነው!" አላቸው። " ልክ ነህ በል አሁን ተነስ እንግባ" ብለውት ከተቀመጡበት ተነሱ።

ስሙር ምንጯን ለማየት ከቤቱ ወጥቶ ለማንም እንዲ ሆንኩ ብሎ ቢነግር ማንም የማያምነውን ሌላ እርሱጋ ብቻ ምሥጢር ሆኖ ለርሱም ምሥጢር ሆኖ የሚቆይ ምሥጢር በምሥጢር ተካፍሎ ያየውን ማመን ቸግሮት የሆነው ሁሉ የህልም ዓለም ነገር መስሎ እየተሰማው ኅሊናው ጥያቄ አዝሎ ወደዚያች ብቻውን በጸጥታ ተቀምጦባት በእርጋታ የከረመበትን ስልጡን የተባለ የነጮች መንደርና አሁን ያለበትን ኋላ ቀር የሚል ቅጽል የተቀጸለለትን ቀዬ ግና ማንም ያልደረሰበት ልዩ ምሥጢር ያዘለች ቲኒሽ መንደርን በእርጋታ ደግሞ ሊያመዛዝናቸው ከአባ ትህትና ጋር ወደ ቤታቸው አቅጣጫ ፊታቸውን አዙረው ጉዞ ጀመሩ። " አባ ይቅርታ ያድርጉልኝና አንድ ነገር ውስጤን እረፍት ነሳኝ ብጠይቆት" አለ በትህትና " ምነው የእናቴ ልጅ ምንድነው? ከማይረባው ሰው መልሱን አምታገኝ ከሆነ በል ጠይቅ" አሉት አንደበታቸው የተቃኘው አባ ትህትና። " ከምንጩ ከጠገብ እያለን አንድ ነገር ላይ ዓይኔ አረፈ። ያን ልዩ ፍጡር ወደኛ ከቃል በላይ በሆነ ፍጥነት ሲመጣ አየሁት ከዚያ በኋላ አሁን ከቆየንበት ስፍራ ላይ ተቀምጠን እስከነቃውበት ያለውን ጊዜ ምን እንደተፈጠረ ያላወኩት እንዴት ሆኖ ነው? ማነው እዚያ ያደረሰኝ? ያ ወደኛ እንዲያ በየር ላይ አካል እንደሌለው ፍጡር ሲሳብ የነበረው አውሬስ?" አላቸው ዳግመኛ ኅሊናው ላይ ተስሎ እየታየው። " በድንገት እራስህን ሳትክና ወደክ! አሁን አየው የምትለውን አውሬ ዓይን ላይ ተስሎ ስላየኸው ደንግጠ ይሆናል። ለመሆኑ ያየኸው ምንድን ኖሯል?" ጭራሽ ወደ አንበሳው ትክ ብለው ሲያዩ የነበሩት ሰው ምን አየህ ብለው ሲጠይቁት ጥያቄ ቀንስ ብሎ ሌላ ጥያቄ በራሱ ጨመረ። " ከምንጩ አጠገብ እያወሩኝ ወደ ምሥጢራዊው የሙሲቾ ተራራ ትኩር ብለው ሲያዩ ዓይኖትን ተከትዬ ዓይኔን ስጥል የሚያስፈራ ግዙፍ አንበሳ አየሁ!" ሲላቸው አባ ትህትና " እውነትህን ነው በትክክል አንበሳ አይተሀል? ምናልባት በዚህ መንደር ስላለው ምሥጢራዊ አንበሳ ሰዎች ታሪክ ነግረውህ ከኅሊናህ ተስሎብህ ያየህ መስሎህ የሆን? እንጂ እንዴት ወደኛ እየሮጠ አይተኸው አሁን እዚህ ተገኘን?" ሲጠይቁት እርሳቸውን ወደ ማመኑ ራሱን ወደመጠራጠር መጣ። " እንጃ አባ በትክክል አይቼው ነበረ.....ግን....." በቃ ምንም ማለት አቃተው። " በቃ በአዕምሮህ ተስሎብህ ኖሯል!" አሉት። " እሺ እርሱ ይቅር ከምንጩ አጠገብ ከነበርንበት ወደዚህ ማን አመጣኝ ተሸክሞ?" ሲላቸው አባ ትህትና መጠነኛ ሳቅ ስቀውበት " እንግዲህ የአንበሳውን ታሪክ እንደነገርኩህ ለደጋጎቹ አገልጋይ ነው አሉ የመሪጌታ ልጅ መሆንክን አውቆ እኔንም በአንድ ተቀምጠንበት አምጥቶን ይሆናላ!አኻኻኻኻ" ብለው እውነቱን በቀልድ ውስጥ ነገሩት። " አባ እውነቴን ነው!" አለ ስሙር " በድንጋጤ ራሱን ለሳተ ሰው ባለመድኃኒቶች ከተፈጥሮ ጥበብ ተካፍለው ከሚበቅለው ከቅጠሉ ፈውስ ዘንድ ያደርሳሉና ምንጩ አጠገብ ያገኘሁት አንድ መንገደኛ ነው እርሱን አውቃለው ብሎ በሚያስደንቅ እግዜር ባዘጋጀው መጓጓዣ ወዲህ ጭኖ ያመጣህ። እኔን እንኳ በእግሬ እንዳልሄድ ከአንተ ጋር በአንድነት እንድቀመጥ ከባለቤቱ ፈቃድ ሆኖ እዚህ ድረስ መጣን። ያ ሰው ተሳፍረን ከመጣነው ፍጡር ላይ አውርደንህ ካሳረፍንህ በኋላ ከዚያች ምንጭ በኮዳው የቀዳውን ውኃ ቆርጦ በእጁ ካሸው ቅጠል ጋር በአንድነት በራስህ ላይ ቢያንጠባጥበው መተንፈስ ጀመርክ እኔም እጹብ እያልኩ ከምሥጢራዊቷ ቀዬ ዓይኖቼ ምሥጢር ተካፍለው ያ ደገኛ ሰው እኔና አንተ ተሳፍረን እዚህ ድረስ በመጣንበት መጓጓዣ እያየሁት ተሰናብቶኝ ወደ ተራራው አቅጣጫ አቀና ፍጥነቱ ምሥጢር ነው ማን ይገልጠዋል" አሉት ስሙር አባ ትህትናን አመናቸው መቀበል የሚያቅተውን አማራጭ አቶ አሜን ብሎ ተቀበለ። " ልጅ ስሙር ይህ ቀዬ ምሥጢር ነው። ዘመን ጠብቆ የሚገለጥ ጥበብ ያለበት" አሉት አባ። " ስሙር አባ ትህትናን መጓጓዣው ምን አይነት ነበረ?" ብሎ ሊጠይቅ አሰበና "የቆላ ነገር ግልጽ ነው በቅሎ ነው ሚሆነው" ብሎ አስቦ ተወው። በዚህ ሁሉ ውስጥ አባ ትህትና የመሪጌታን ልጅ በጥቂቱ ከምሥጢር ሲያካፍሉት አይቶት ደንግጦ በወደቀ ጊዜ በፈራው ፍጡር ጭነው አባቱን በሚያገለግላቸው አንበሳ ወገብ አርፎ ከጠቢባን ጥበብ ፈውስ በአባ እጅ ተካፍሎ ድኖ በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን አንዴም አባ ትህትናን ለዚህ የበቁ መሆናቸውን ለቅጽበት እንኳ ሳያስብ ተከትሏቸው ከቤት እንደወጣ ተከትሏቸው ወደ ቤት አቀኑ። ብዙ ከተጓዙ በኋላ አባ ትህትና ከአንዱ አጸድ ላይ ሌላ የአዋሽ ታፍሶ የማይጨረስ ልዩ ምሥጢር ለርሳቸው በሚገባ መጠን ተካፍለው ስሙርንም

9 months, 2 weeks ago

አለው መልሶ እውነቱን እየነገረው። ማርታ ቀበል አድርጋ " አዎ ብዙ ሰው በዚህ አይሄድም እዚያች መሀል ላይ ያለችውን ጨለማ ሽሽት በቀጣዩ መንገድ ነው ሰው የሚያዘወትረው። እውነቱን ነው ሰው በዚህ አይሄድም። ለዚያም ማታ ማታ ታስፈራለች ጸጥ ረጭ ትላለች እቺ የኛ መንገድ" አለች። " ይገርማቹሀል በሚደንቅ ቁልፉ መኪናው ላይ ነው!" አለ ኤርምያስ ፈገግ ብሎ። ክብሮም ማመን አቅቶት ካለበት ዘሎጰወደ መኪናው መግቢያ የገቢና በር ደርሶ ሲያይ ቁልፉን ከተሰካበት እንዳለ አየውና በደስታ ፈገግ ብሎ ወዲያው እንዴት በሚል ጥያቄ ምላሽ ፍለጋ አዕምሮውን አመራመረ። " ቆይ እንዴት?" አለ ቢኒያም " መጀመሪያውኑ ሳታዩ ቀርታችሁ ነው" አለ ደግሞ። " ኧረ በፍጹም አልነበረም!" አለ ክብሮም። " እኔም አረጋግጫለው እንጂ ቁልፉ አልነበረም። እሺ ኢሄ ምን ይባላል?" አላቸው እየሳቀ። ሁሉም ከመደነቅ በቀር ምንም ማለት አልቻሉም።

አራቱም ቆመው የተፈጠረውን የየራሳቸውን መላምት ስለ ቁልፉ ሲያስቀምጡ ክብሮም ወደ መኪናው ደብቶ ከወንበሩ ቁጭ እንዳለ የመኪናውኝን ሞተር አስነሳ። " በጣም ቅርባችን ሆኖ እየተከታተለን ያለ ሰው ስላለ አንድከም በሉ ሁላችንም ወደየቤታችን እንሂድ ስላደረጋችሁልን ሁሉ በጣም እናመሰግናለን!" አለ ኤርምያስ። ቢኒያም ፈገግ ብሎ በኤርምያስ ሀሳብ መስማማቱን አንገቱን እየወዘወዘ ገልጦ " ማርታ ግን እብዱን ድጋሚ የምታገኚው ከሆነ ቅረቢው አትፍሪ የሚልሽን በደንብ ስሚ። ከተቻለ ባገኘሽው ቅጽበት ለኔ ወይ ለነሱ ደውይ ከዚህ ውጪ ምንም አማራጭ የለም" አለ ብርዱ እያንቀጠቀጠው። ማርታ " እንዳላችሁት አደርጋለው። አዲስ ነገር ካለ እናንተም አሳውቁኝ በሉ ደና እደሩ!" ብላ ወደ ቤቷ ስትገባ ቢኒያምም ከቆመበት ወደ መኪናው ሲገባ ኤርምያስም ተከተለው። ክብሮም ወዲያው መኪናዋን አስነስቶ ወደ ቢኒያም መኖሪያ ቤት አቀና። እርሱን አውርደው ተሰናብተውት በሆስፒታሉ ጋር ወደ ዋናው መንገድ እያወሩ ምንም እንዳልተፈጠረ እየተጨዋወቱ ጉዞአቸውን ቀጠሉ። " ተናድጄ በስሜት ስለተቆጣውህ በጣም ይቅርታ!" አለ ኤርምያስ። "እረዳለው አልተቀየምኩም። በእርግጥ እኔም ቁልፍ መንቀል ነበረብኝ!" አለ ክብሮም በትህትና። እያወሩ ወደ ዋናው መንገድ ገቡና ክብሮም የመኪናውን ፍጥነት ጨምሮ እያሽከረከረ መንገዱን ከሁለት ከፍሎ ካለው ችግኝ ከተተከለቀት ማዶ ላይ ያንን የሚፈልጉትን ከኋላው ተከትሎት ያመለጠውን እብድ ከማዶ ሲያየው " ያውና ያውና" አለ። ኤርምያስ ማመን አቅቶት "የታለ?" አለው። " በዚህ አይደለም በዚያኛው መንገድ!" አለው ክብሮም ወደ እብዱ ለመድረስ የሚዞርበትን እየፈለገ። " ፍጠን አዙረው አዙረው መኪናውን!" አለ ኤርምያስ። " እዚህጋ አያዞርም ወደ ማዶ የሚያዞረው ከፊትለፊት ነው ያርቃል። ከኋላችን ያለው ቅርብ ይመስላል ወደ ኋላ ልንዳ?" አለ ክብሮም። " ዝም ብለህ በፍጥነት ወደ ፊት ንዳ ዞረን እንመለሳለን!" አለውና መኪናዋን በፍጥነት ወደ ፊት አስወነጨፋት። ብዙ ተጉዘው የኋሊት እብዱን ወዳዩበት ተመለሱ። ከቦታው እስኪደርሱ ያለችው ቲኒሽ ደቂቃ የዓመት ያክል ሆነባቸው። መድረስ አይቀር ሲደርሱ መኪናውን አቁመው ከመኪና ወርደው ሁለቱም አካባቢውን እየተዘዋወሩ መቃኘት ጀመሩ። ካዩበት ግን እብዱን አላገኙትም። የባሰ ግራ ተጋቡ። " አሁን አይተነው የነበረው እዚህጋ አልነበረንዴ?" አለ ኤርምያስ። " አዎ አዚህ ጋ ነው ያየነው። ያው ማዶ እዛጋ ሆነን ነው እይ ብዬ ያሳየውኽ የት ሄደ በዚህች ደቂቃ?" አለ ክብሮም ተዟዙሮ አካባቢውን እያየ። " ና ግባና ወደ ፊት ጠጋ እንበል እስቲ" ሲለው ክብሮም ወደ መኪናው ገበና ወደ ፊት አቀኑ። ያገኙት ያዩት ግን ምንም አልነበረምና እንደገና በቀኛቸው ዞረው ወደ ሮቤ እንቆቅልሽ የሆነባቸውን አጋጣሚ እየተጨዋወቱ ጉዞ ቀጠሉ። እየተጓዙ የኤርምያስ ስልክ የጥሪ ድምጽ ሲሰማ ስልኩን አውጥቶ " ሃሎ!" አለ። ተስፋዬ ነበር። " ሃሎ ተስፋዬ ነኝ ሰላም ዋልክ! ምን አዲስ ነገር አለ ብዬ ልጠይቅህ ነው መደወሌ!" አለው። " ሰላም አመሸህ ተስፋዬ ኢኸው አሁን ገና ከጎባ እየገባን ነው። አንድ እብድ እዚያ ተገኝቷል ብለውን እርሱን ፍለጋ ቆይተን" ሲለው " አገኛችሁት?" አለ ተስፋዬ ተቻኩሎ " አይ ማግኘት ነገሩ ከባድ ነው። እንዲህ ቀላል አይደለም ነገሩ" አለው ኤርምያስ። ተስፋዬ ወዲያው ተረበሸ። ወልደ አዳም ለስለላ ወደርሱ የመጣ ሰው እንደሆነ ኤርምያስ የገጠማቸውን ከነገረው ነገር ተጠራጥሮ ወዲያው ተሰናበተውና በነጋታው ጓዜን ጉዝጓዜን ሳይል ከተማዋን ለቆ ሊወጣ ወዲያው ልብሱን በሻኝጣው አስተካክሎ ይከት ጀመረ። ይህን እያደረገ በድንገት " አጥሩ ከፈራረሰ ጊቢ የገቡ ሰዎች የተስፋዬን ቤት ሲያንኳኩ ተስፋዬ " ማነው!" አለ። መልስ የለም ዝም። በድጋሚ ተንኳኳ " ማነው!" አለ ሽጉጡን በቀኝ እጁ ይዞ።

? ይቀጥላል ?
?? መጋቢት 19 2016 ዓ.ም ??

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад