ELAF TUBE ኢላፍ ቲዩብ

Description
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago

1 week, 3 days ago
ሰላት አላህ ጋር መገናኛ ናት።

ሰላት አላህ ጋር መገናኛ ናት።

ሰላትን የተውክ ሆይ!

ግን ምን አታሎህ ይሆን የሰማያትና የምድር ፈጣሪ ከሆነው አላህ ጋር መገናኘትን የጠላሃው!?
-----------------------

T.me/elaftube

1 month, 4 weeks ago

ብዙዎቻችን ቁርኣን ስንቀራ ከፍተነው ከንፈራችንንና ምላሳችንን ሳናንቀሳቅስ ዝም ብለን በቀልባችን ብቻ እንቀራለን። ይሄ እንደቀራን አይቆጠርም። ከእያንዳንዱ ሐርፍ የሚገኘውንም ሐሰናህ አያስገኝም። ዑለሞች ስለዚህ ጉዳይ ሲናገሩ፤ ቢያንስ ሌላ ከልካይ ድምፅ (ጫጫታ ነገር) ከሌለ በስተቀር የሚቀራውን ራሱ እስኪሰማው ድረስ ማንሾካሾክ አለበት። ምላስና ከንፈር ካልተንቀሳቀሱ የፊደላቶቹ ሐቅ (መኻሪጅ) ተጠብቆ አልተቀሩም፤ ታዲያ የተጅዊድ አንዱ ክፍል መች ተተገበረና! ይሄ ሶላትም ላይ ሲሰገድ ያካትታል። ባይሆን እንደዛ ሲባል ከመጠን በላይ አልፎ በጎናችሁ ያለውን ሰው የመወስወስ ደረጃ ላይ መድረስ የለበትም። በአጭሩ ሶላትም ላይ ሆነ ቁርኣን ስትቀሩ በትንሹ ማንሾካሾክ ግድ ነው። በጀህር ሶላቶችና ቁርኣን ላይ በደንብ ጩኻችሁም መቅራት ትችላላችሁ። ምላስና ከንፈር ማንቀሳቀስ የተባለው threshold የሆነውን ለማለት ነው።

T.ME/ELAFTUBE

2 months, 3 weeks ago
2 months, 3 weeks ago

በመላኢካዎች ተቀፍድዶ የጀሐነም በራፍ ላይ ቆመ። ዓይኖቹን አሻግሮ ሲመለከት ጓደኞቹ የሉም። ወደ ኋላው ዞሮ ወላፈኑ እየለበለበው የታሉ ጓደኞቼ በማለት መላኢካዎቹን ጠየቀ። ካንተ ሞት በኋላ ቶበቱ ዓቢድ ሆነው ጌታቸውን ተገናኙ ብለው ይመልሱለታል።

2 months, 4 weeks ago

ኃጢአትን መተው ተውበትን ከመፈለግ ይቀላል።
T.me/elaftube

4 months, 2 weeks ago
4 months, 2 weeks ago

ሂጃብ ላለመልበስ የተለያዩ ምክኑቶች ከሚያቀርቡ ሴቶች ጋር የተደረገ ውይይት

እርሷ:- እኔ ሂጃብ ባለብስም አሏህን እወዳለሁ ስለዚህ አላህን መውደዴ በቂየ ነው።

መልስ:-
" ﻗُﻞْ ﺇِﻥ ﻛُﻨﺘُﻢْ ﺗُﺤِﺒُّﻮﻥَ ﭐﻟﻠَّﻪَ ﻓَﭑﺗَّﺒِﻌُﻮﻧِﻰ ﻳُﺤْﺒِﺒْﻜُﻢُ ﭐﻟﻠَّﻪُ ﻭَﻳَﻐْﻔِﺮْ ﻟَﻜُﻢْ ﺫُﻧُﻮﺑَﻜُﻢْۗ ﻭَﭐﻟﻠَّﻪُ ﻏَﻔُﻮﺭٌ ﺭَّﺣِﻴﻢٌ "
"በላቸው አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ ተከተሉኝ አላህ ይወዳችኋልና ኀጢኣቶቻችሁን ይምርላችኋልና።
አላህም መሓሪ አዛኝ ነው።" 【ዒምራን 31】
አላህንማ ብትክክል የምትዎጅ ከሆነ መልእክተኛውን ባግባቡ ትከተይ ነበር

እርሷ:- በሙቀትና በፀሃይ ሰአት ሂጃብ ስለሚያስቸግረኝ መልበስ አልፈልግም

መልስ:-
"ِّۗ ﻗُﻞْ ﻧَﺎﺭُ ﺟَﻬَﻨَّﻢَ ﺃَﺷَﺪُّ ﺣَﺮًّﺍۚ ﻟَّﻮْ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ ﻳَﻔْﻘَﻬُﻮﻥ "
"የጀሃነም እሳት ተኳሳነቱ የበረታ ነው በላቸው የሚያውቁ ቢኾኑ" 【አት–ተውባህ 81】
በመገላለጥሽ ምክኒያት ነገ በአኼራ በእሳት ከመቀጣት ዛሬ በአዱኒያ ያለውን ሙቀት ተቋቁመሽ ጀነት መገባት አይሻልሽምን?

አርሷ:- አሁን ገና ልጅ ነኝ ትልቅ ስሆን ሂጃብ እለብሳለሁ

መልስ:- ሞት ልጅና ትልቅን አይመርጥም ትልቅም ትንሽም ይሞታል
ትልቅ ሳትሆኒ ብትሞችስ?

እርሷ:- እባክህ የኛ ማሃበረሰብ ሴቶች ሁሉም ተገላልጠው ነው የሚሄዱት እኔ ብቻየን ሂጃብ ስለብስ ይደብረኛል

መልስ:- ወላሂ አሁን ያልሽው በጣም የከፋ የጀሃነም ሰዎች ንግግር ነው። እነርሱ በርግጥ እንዲህ ይላሉ
" ﺑَﻞْ ﻗَﺎﻟُﻮٓﺍ ﺇِﻧَّﺎ ﻭَﺟَﺪْﻧَﺎٓ ﺀَﺍﺑَﺎٓﺀَﻧَﺎ ﻋَﻠَﻰٰٓ ﺃُﻣَّﺔٍ ﻭَﺇِﻧَّﺎ ﻋَﻠَﻰٰٓ ﺀَﺍﺛَٰﺮِﻫِﻢ ﻣُّﻬْﺘَﺪُﻭﻥَ "
"ከቶውንም እኛ አባቶቻችንን በሃይማኖት ላይ አገኘናቸው እኛም በፈለጎቻቸው ተመሪዎች ነን አሉ።" 【አዝ–ዙኽሩፍ 22】
አርአያሽን የሰፈርሽን ሴቶች ሳይሆን እነዚያን ብርቄየ ሱሃቦች አድርጌ!

እርሷ:- በቃ ካገባሁ በሗላ እሸፈናለሁ

መልስ:- ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ "አንድ ባሪያ በሚሰራት ወንጀል ሪዝቅን ይከለከላል" 【አህመድ ዘግበውታል】 ጥሩ ባል ከአላህ የሆነ ሪዝቅ ነው በወንጀልሽ ምክኒያት እንዳይከለክልሽ ተጠንቀቂ
ግን እመትሸፈኒው ለአላህ ነው ወይንስ ለባል? በዚህ አባባልሽ መሰረት ካገባሽ በሗላ ባልሽ መሸፈንሽን ባይፈልግ እርሱን ላለማጣት ስትይ አትሸፈኒም ማለት ነው?
ስለዚህ አንች ጌታሽን አምላኪ ሳትሆኒ ባል አምላኪ ነሽ ማለት ነው!

እርሷ:- እባክህ ዋናው የልብ ንፅህናነው ልቤ ንፁህ ከሆነ ከመሸፈኑ ምን አለኝ

መልስ:- ወስጥሽማ በተስተካከለ አካልሽም ይስተካከል ነበር ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ:- "ንቁ በሰውነት ውስጥ ቁራጭ ስጋ አለች እርሷ ከተስተካከለች አካል ሁሉ ይስተካከላል እርሷ ከተበላሸች አካል ሁሉ ይበላሻል ንቁ እርሷ ቀልብ ነች"
በነቢዩ ምስክርነት የውጫውይ ገፅታሽ እንዲህ መበላሽቱ የውስጥሽን መበላሸት ይጠቁማል!
ደግሞም ውስጥሽ ቢስተካከል ኑሮ እንዲህ ባልተገላለጥሽ ነበር እንዲህ የተገላለጥሽው ውስጥሽ ስለተበላሸ ነው።
T.me/elaftube

4 months, 2 weeks ago
4 months, 3 weeks ago

አዲስ የተጀመረ ብልሹ ዐቂዳህና መንሃጅ መጥቷል አሉ። መጥተው የነበሩት እነ አሕባሽ ወደመጡበት ሳይመለሱ ሌላ ደግሞ እየተሳበልን ነው።

ይህ አዲሱ ዐቂዳ እነ ዶ/ር ጀይላንና ሌሎችም ታዋቂ ኡስታዞች በሚገኙበት አየር ጤና አንሷር መስጂድ መሰበኩ ደግሞ አሳሳቢ ነው። በርግጥ ዶ/ር ጀይላን ከደርሱ በኋላ ረድ ሰጥተዋል የሚል መረጃ ሰምቻለሁ።

የሚያሳዝነው አንዳንድ የአየር ጤና ወንድሞች አዲሱን አካሄድ «ትክክል ነው!» ብለው ለመከራከር እየሞከሩ ነው አሉ።

ለማንኛውም ስለዚህ መንገድ ቀደም ብሎ ሰበካው ያገኘው ኡስታዝ አቡበከር ሑሴን በቪድ የሚያውቀውን ያክል በሚገባ አብራርቷልና የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ ስላለው ከራሱ አንደበት አዳምጡት።

በመስጅድ፣ መድረሳና ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ ሽፋን የሚመጡ አዳዲስ አካሄዶች (በተለይም ይህ አብርሃማዊ ኃይማኖቶች) የሚለው እሳቤ ተያይዘው እንዳይመጡ መጠንቀቅ ያሻል የምንለው ለዚህ ነው።

ለገንዘብ ተብሎ ትክክለኛ ዐቂዳህ አይሸጥም። ከትክክለኛ ዐቂዳችን ጋር ድህነታችን ይበልጥብናል

ይህ አዲሱ ዐቂዳህ ግን የምን አራቱ አኢማዎች፣ የምን መዝሃብ፣ የምን ሰለፎች… ሁሉንም የሚያንኮታኩት አደገኛ አካሄድ ስለሆነ ሳይስፋፋ በአስቸኳይ ከሃገር መውጣት አለበት።

ከዘገየ ግን እያንዳንዱ የጥመት ተጣሪ ተከታይ አያጣም። እንኳን እነዚህ አስመሳዮቹ በፍቅርሲዚም የሚያምን ከንቱ መች ይጠፋል!

||
t.me/MuradTadesse

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago