ሐበሻ Creation

Description
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад

8 months, 1 week ago

ለሰፈራችን ሰዎች የሰርግ መጥሪያ ካርድ ስጥ ተብዬ እኛ ሰፈር ያሉ ቤቶች በሙሉ እየገባው በየተራ እየሰጠሁ ነው በመጨረሻም ጥቂት የሚባል የሰርግ መጥሪያ ወረቀት ቀርቷል እጄ ላይ መጀመሪያ ላይ ያለውን አየሁት አቶ ሰይፈ ይላል ፈጠን ብዬ እየተራመድኩ ወደነ ጋሽ ሰይፈ ቤት ሄድኩ እዛም ስደርስ እንደለመደብኝ በሩን በስሱ ኳኳኳኳ አረኩት ከጊቢው ውስጥ ኸረ ቀስ በሉ በሩን ልትሰብሩት ነው እንዴ" የሚል ድምፅ ሰማው...አርግጠኛ ነኝ ጋሽ ሰይፈ ናቸው... ጋሽ ሰይፈ ማለት የሰፈር ሰው በሙሉ የሚያወቃቸው እና የሚፈራቸው ሰው ናቸው ይሄ ሁሉ እሳቸውን የመፍራታችንን ምክንያት ባላውቀዉም አንድ ጊዜ በማታ  ወተው እኛ ሰፈር ያስቸግሩ የነበሩ ሌቦችን ከዘራ አፈር ከድሜ አብልተዋቸዋል የጋሸ ሰይፈ ባህሪ ነጭናጫ፣ተቆጪ፣ኮስታራ እና አንዳንዴ ደሞ ቀልደኛ ነገር ናቸው ግን ሁሌ በሁሉም ነገር መነጫነጭና መቆጣት ልማዳቸው ነው ፡በሩ ክፍት ስለነበር በትንሹ ከፈት አድርጌ አንገቴን ብቻ አጮልቄ ወደ ጊቢው ሳይ ጋሽ ሰይፈ በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው አረቄ እየጠጡ ጋቢ ለብሰው ተቀምጠዋል በሩን በደንብ ከፍቼ "ሰላም ነው ጋሼ" እያልኩ ወደጊቢው ገባሁ እሳቸውም "እንዴ አንተ ነህ እንዴ ና ግባ" ብለው በትንሹም ቢሆን አቀባበል አደረጉልኝ እኔም ግርግር ሳላበዛ ለሳቸው ያመጣሁትን የጥሪ ካርድ አውጥቼ "ይኸው ጋሼ ይሄን ተልኬ ነወ" ብዬ ካርዱን የያዘውን እጄን ዘረጋሁት ከመቀበላቸው በፊት ምንድነው? ብለው ቆጣ አሉ...የሰርግ መጥሪያ ካርድ ነው ጋሼ" ብዬ ቁጣቸውንአበረድኩት "እእእእ ነው እንዴ" ብለው ከእጄ ላይ መንተፍ አርገው ወሰዱት...ያው እኔም ፀባያቸውን ስለማውቀው ምንም ሳይመስለኝ ፊቴን አዙሬ ልወጣ ስል "የማነው ሰርጉ? አሉኝ የኤፍሬም ነው ብዬ ቆምኩኝ
ኤፍሬም ይሄ ወጠጤው?
"አው ጋሼ ብዬ" ፈገግ አለኩ
ምን ያስገለፍጥሀል አንተም ከሱ የባስክ አደለህ ሲሉኝ ፈገግ ያለው ጥርሴ ወዲያው ሸፍን አለ...ስማ ደሞ ያ ለማ ሚባል ሰውዬ እዚ ሰርግ ላይ ተጠርቷል እንዴ?...ብለው አፈጠጠብኝ...ለማ ማን እንደሆነ ለማስታወስ እየሞከርኩ "አልተጠራም" ብዬ ዝም አልኩ
የታባቱ ይሄ ሌባ የእቁብ ብር ዘርፎ ድሮስ ማናባቱ ሊያስጠጋው...አረቄው ነው መሰለኝ እኔን አቁመው የባጥ የቆጡን ማውራት ጀመሩ... ለመሄድ ብፈልግም እሳቸው እያወሩ ሄድኩኝ ማለት የሚደርስብኝን መከራ እኔ ነኝ የማውቀው እሳቸው ሚያወሩትን ወሬ አንዱንም ሳልሰማ ጭልጥ ያለ ሀሳብ ውስጥ ገብቻለው...ድንገት ና ቁጭ በልና ከኔጋ አረቄ ጠጣ" የሚል ድምፅ ሰማው ...ደንገጥ ብዬ "አይ አልጠጣም ጋሼ" አልኩለኝ
ተናደዱ "ና ኮ ነው ምልህ" ብለው ፊታየወን አረገፋብኝ "እርሶ ሰውዬ ግን አላበዙትም እንዴ የሰፈር ልጆች ስለሚፈራዎት እኔም ግዴታ እርሶን መፍራት አለብኝ እንዴ? አሁን ደሞ ጭራሽ በግድ አረቄ ሊያስጠጠኝ ነው? አልጠጣም! ልል አሰብኩና አጠገባቸው ያለውን ታሪካዊ ከዘራ ሳየው ሀሳቤን ቀየርኩ ፡ እግሬ መሮጥ ቢያምረውም አጠገባቸው ያለው ትንሽዬ ወንበር ላይ ፈጠን ብዬ ቁጭ አልኩ ። ይኸው አሁን የአረቄ መጠጫ ላምጣልህ ብለው ሲሄዱ ነው ይሄን የፃፍኩት

አሁን ከዘራቸውን ይዤ ልጥፋ ወይስ አርፌ ልቀመጥ?
ከተቀመጥኩ ደሞ አረቄ ሊያስጠጡኝ ነው?

መጡ.......መጡ......መጡ
jᵒⁱⁿ⇝ @Habesha_Edit

8 months, 3 weeks ago

የገባሁበት ታክሲ በጣም ከመሙላቱ የተነሳ ረዳቱ እራሱ ወርዶ ከታክሲው ኃላ እነሮጠ ሂሳብ-ወጣ ወጣ አርጉ እያለ ነው ሚከተለን... አውቄ ነው እቤት እኔኮ ሳጋንን አያምጣው ነው...ይሄን ያክል ማጋነን ምን ይሉታል አሁን? በርግጥ ታክሲው ሚጭነው 12ሰው ቢሆንም ታክሲ ውስጥ ያለነው ግን ወደ 2ዐ ገደማ ነን..እንደውም ማጋነን ሲያንሰኝ ነው..ታክሲው ጉዞውን ጀምሯል...የተቀመጥኩት ከሹፌሩ ኋላ ያለው የታክሲው የፊለፊት ወንበር ላይ ነው ለሁለት ሰው እንኳን የማይበቃው የታክሲ ወንበር 3ሰው ሹጥጥ ብሎ ተቀምጦበታል...ከተቀመጥነው ሶስት ሰዎች መሀል ላይ ያለሁት እኔ ነኝ መሀል መቀመጥ ምን ያክል እንደሚጨንቅ የሚያቀው ተቀምጦ ያየው ብቻ ነው...ወዲያወኑ ግን መሀል ላይ የመቀመጥን ጭንቀት የሚያስረሳኝ ነገር ተፈጠረ... ከኔ በግራ በኩል ወይም በመስኮቱ በኩል የተቀመጠችው
ቆንጅዬ ልጅ ስልክ እያወራች መጨቃጨቅ ጀምራለች...እኔም ምስጥ ብዬ ወረዋን ማደመጥ ጀምሬያለው

''እዚጋ ሂሳብ" አለ እረዳቱ

እሷ ምታወራው ወሬ ስለሳበኝ ረዳቱን ቀና ብዬም ሳላየው  ከኪሴ ብር አውጥቼ ሰጠሁት...እወነት የኔ ፍቅር አንተ እንዳሰብከው አደለም ትላለች...በጭቅጭቁ መሀል ላይ ወሬወን ለመስማት በጣም ከመጓጓቴ የተነሳ ከስልኩ ሚመጣውን ድምፅ አንዳንዱን እየሰማሁ አንዳንዱን ደሞ እየገመትኩ መስማቴን ቀጠልኩ ምንም እንኳን ጭቅጭቅ ቢሆንም ልጅቷ ስታወራ የሆነ ውበት አለው  "እንደሱ አደለም ቆይ ስማኝ" አሁን ተቆጣች...ሲመስለኝ ታክሲ ውስጥ የታጨቀው ሰው ሁሉ ሰምቷታል...እሷም እሱን አውቃ ነው መሰለኝ ጎንበስ ብላ እጇን ከአፏ እና ከስልኩ ፊለፊት አስደግፋ ማውራት ቀጠለች
በጣም ተናደድኩኝ፤ ምክንያቱም እስካሁን ስሰማ የነበረው ወሬ አሁን መስማት አልቻልኩም...እንደዚህ ለመስማት እንደጓጓሁ አልቀርም፤ የሚል አልህ ቢጤ ያዘኝና እኔም በትንሹ ጎንበስ ብዬ የጓጓሁለትን ወሬ መስማት ጀመርኩ...ተፈጥሮዬ ሆኖ ጆሮዬ በቀኝ አንድ ግራ ደግሞ አንድ ቢሆንም ለዛሬ ግን ሁለቱንም በግራ በኩል አድርጌ እየተገለገልኩባቸው ነው...አፏን በእጁ እንደሸፈነች ማውራቷን ቀጥላለች "ማታ አያቴ ጋር ነውያደርኩት ስልህ ለምን አታምነኝም?...ስትል ሰማኋት ኸረረረረረ..ጭራሽ ውጪ አድራ ነው? ከስልኩ የሚመጣውን ድምፅ ለመስማት በደንብ ጠጋ ብልም መስማት ግን አልቻልኩም
ያለኝ አማራጭ የሷን እየሰማሁ የስልኩን ደሞ መገመት ነው ገመትኩ..፤ አያትሽ ጋር የት? ይላል ብዬ አሰብኩ...አው እዛ ነበርኩ ስላልነገርኩህ ይቅርታ" አለች ቲሽ.... የገመትኩት ልክ አልነበረም  ድምዷን ከቅድሙ የበለጠ ዝቅ አርጋ "አሁን ወዳንተ እየመጣሁ ነው" ስትል ሰማኋት
ድንገት "እዚ ጋ ወራጅ! ወራጅ ወራጅ!" በሚል ድምፅ ታክሲው ተናወጠ...ደንገጥ ብዬ ስዞር ከኔ በቀኝ በኩል የተቀመጠው ሰው ነው ለመውረድ እንደዚ ሚጮኸው...አቆመለት ሰውየውም እየተቻኮለ ከታክሲው ወረደ
''እኔም እዚጋ ወራጅ ነኝ አሳልፈኝ'' አለችኝ
ተናደድኩ! እንዴት እዚጋ ትወርዳለች ምናለ የጀመረችውን ብትጨርስ? እያልኩ አሳለፍኳት...እሷም ቀልጠፍ ብላ ወረደች አሁን ለሶስት ተጨናንቀን የተቀመጥንበት ወንበር ላይ ብቻዬን ፈልሰስ ብዬ ተቀምጫለሁ ፈልሰስ ብዬ መቀመጤ አንድ ነገር አስታወሰኝ
ስልኬን!
ስልኬስ?
ኸረ ስልኬን ከኪሴ አጣሁት ጎበዝ?‍♂

jᵒⁱⁿ⇝ @Habesha_Edit

9 months, 1 week ago

ስህተት ወይስ ምን?...ክፍል 5

አይኗ እንደታሰረ በቦታው ደረሱ
ቀስ ብሎ ከመኪናው ካወረዳት በኋላ አይኗ ላይ ያለወን ጨርቅ እንድትፈታ ጠየቃት
እሷም የአይኗ መታሰር ምቾት ነስቷት ስለነበር ወዲያው ጨርቁቱን ከአይኗ ላይ ፈታችው
ዙሪያዋን ስትመለከት ግን ማንም የለም
አጠገቧ ሆኖ ጨርቁን እንድትፈታ የነገራት ነቢልንም ከአጠገቧ ልታገኘው አልቻለችም...ግራ ተጋባች መጮህ አማራት ባለችበት ቦታ እየተዟዟረች የት እንዳለች ማየት ጀመረች ቦታው ብዙ ዛፎች ያሉበትና ፀጥ ያለ ነው ፀጥታውን በትንሹ ሰብሮ ለመግባት የሚሞክር ለስላሳ ሙዚቃ ከሩቅ ይሰማል የኤማ ትኩረት ሙዚቃው ላይ ሆነ...በትንሹ የተከፈተወን ሙዚቃ መስማት ብትችልም ድምፁ ከየት እንደሚመጣ እና ምን አይነት ሙዚቃ እንደሆነ ማወቅ አልቻለችም ኤማ ግራ ተጋብታ በቆመችበት ቆየች..ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ "ኤማ" የሚል ድም ሰምታ ድምፁን ወደሰማችበት አቅጣቻ ስትዞል ነቢል በእጁ አበባ ይዞ ራቅ ብሎ ቆሟል...ነቢል ምንድነው? ኤማ ግራ ተጋባች
ነቢል ፈገግ እያለ በዝምታ ቆየ
'ምንድነው ነቢል ንገረኝ እንጂ፤ ኤማ ከድንጋጤዋ ብዛት መቆጣት ጀመረች ነቢል አሁንም ፈገግ እያለ "መልካም ልደት ኤማ" በስሱ ይሰማ የነበረው ሙዚቃ አሁን ድምፁ ከፍ ብሏል ሙዚቃው ከሁሉም ሰው የ ደስታ ቀን ጀርባ የማይጠፋው "ልዩ ቀን ነው ልዩ.... የሚለው የ ሄኖክ አበበ ሙዚቃ ነው...
ኤማ የሚሰማት ስሜት ተደበላለቀባት ደስታ ይሁን ሀዘን ይሁን ድንጋጤ መለየት አቅቷታል
ኤማ ዛሬ የተወለደችበት ቀን ነው የዛሬ 2ዐ አመት የካቲት 17 ቀን ነበር የተወለደችው..እስከዛሬ ድረስ አንድም ቀን ልደቷን አክብራ አታውም ዛሬ ግን ነቢል በእጁ አበባ እና ኬክ ይዞ ለመጀመሪያ ግዜ ኤማን መልካም ልደት አላት...
ኤማ ስሜቷን መቋቋም አቃታት ነቢልን ትኩር ብላ እያየች እንባዋ መውረድ ጀመረ...
የዛን ቀን አሪፍ የሚባል የፍቅር ጊዜ አሳለፉ...
ከዛን ከን ቀኋላ ኤማ ስለ ነቢል የሚሰማት ስሜት መቀየር ጀመረ...ያቺ ሰው አላምንም ሰው አልወድም ሰው አልጠጋም የምትለው ኤማ አሁን ሙሉ ለሙሉ ራሷን ፍቅር ውስጥ ገብታ
አገኘችው...አበደችለት ሳታየው መዋል እስከሚያቅታት ድረስ ለሱ ያላት ስሜት ተቀየረ ያኔ በሳምንት አንዴ ምታገኘውን ነቢል አሁን ቀኑን ሙሉ ፍላጎቷ እሱ ብቻ ሆኖ ቀረ በሱ እቅፍ ውስጥ መዋል የሷ አለም ሆነ የሱን ድምፅ መስማት ሁሌም የምትናፍቀው ሱስ ሆኖባት ቀረ ቀስ በቀስ ብላ የማታውቀውን የፍቅር አለም መልመድ ጀመረች ለመጀመሪያ ግዜ የኤማን ከንፈር በከንፈሩ የነካው ነቢል ነበር የዛን ቀን ለሷ የመጀመሪያው አስፈሪም አስደሳችም ቀን ነበር። ያኔ ሲስማት
ያፈረችው ኤም አሁን ያለምንም ፍርሀት ግጥም አርጋ ትስመዋለች። ያኔ ሲያወራት ለመልሷ ምትቆጠበው ኤማ አሁን ከሱ ጋር እንደልቧ ማውራት ጀምራለች። ከሱ ተለይቶ ለትንሽ ሰአታት መቆየት ማለት ለሷ ትልቅ ህመም እየሆነባት መጣ ሳታውቀው ያለሱ መኖር ማትችልበት ደረጃ ላይ ደረሰች
ከሱ ጋር ብዙ ነገር ማድረግ ፍቅር እንጂ ብልግና መሆኑ አልታይ ብሏታል። እናቷ ፊት ልብሷን እንኳን መቀየር ምትፈራዋ ልጅ አሱ ፊት ምንም ማፈር አቁማለች።
ቀናቶች እያለፉ በመጡ ቁጥር ለሱ ያላት ፍቅርም እየባሰ መጣ ትምህርቷን አቁማ ሁሌ ከሱ ጋር ብትውል ደስታዋ ነበር። ከትምህርት ቤት ስትመለስ ነቢል ቤት ደረስ ይሸኛታል አንዳንዴም ወደቤት ይገባል።
አንድላይ ሆነው በጣም ብዙ ነገር ማድረግ ጀምረዋል መሆን ሚገባትን ሁሉ ሆናለታለች አለኝ የምትለውን የሂወቷን ውድ ነገር ሰታዋለች። ምንም እንኳን ደፍረው ወሲብ ባይፈፅሙም ከሱ ማይተናነስ ነገር ነበር አብረው ሚያደርጉት። ሁለቱም የሚያደርጉት ነገር ልክ እንዳልሆነ ያውቃሉ ላለማድረግ ቢሞክሩም ሁሌ ስሜታቸው እንደ አዲስ ይፈካል..በዚህም ምክንያት ብዙ ጊዜ ይጨቃጨቃሉ ብዙ ጊዜም ይኮራረፋሉ...
አንድ ቀን በዚሁ ምክንያት እንደተኮራረፉ ኤማ ትታመማለች ነቢልም እቤት ድረስ መቶ ይጠይቃትና መድሐኒት ሊገዛላት ተጣድፎ ይወጣል። በችኮላ ሲወጣ ስልኩን እዛው ረስቶ ነበር የወጣው.. ኤማ በተኛችበት ቦታ ላይ ስልክ ሲጠራ ትሰማና ተነስታ ስልኩን ታየዋለች የጠራው ስልክ የነቢል ነበር... ኤማ ስልኩን አንስታ ነቢል እንደሌለ እና ሲመለስ እንደሚደውል ተናግራ ስልኩን ትዘጋዋለች። ነቢል መድሀኒቱን ገዝቶ ሲመለስ "ነባ ቅድም ስልክህን ረስተህ ወተህ ሲጠራ ነበር" አለችው እዛው በተኛችበት
ነቢል በድንጋጤ ስልኩን አንስቶ አየና "አንስተሽ አውርተሻል እንዴ? አለ በቁጣ ድምፅ
አዎ.. አሁን የለም ሲመለስ ይደውላል ብዬ ዘጋሁት
ለምን? ነቢል ከቅድሙ የባሰ ተቆጣ ነቢል የመቆጣቱ ምክንያት ባይገባትም ቀስ ብላ ልታስረዳው ሞከረች
ምናልባት የስራ ስልክ የሆናል ብዬ ስላሰብኩ አንስቼ ስትመለስ እንደምትደውል ተናግሬ ዘጋሁት ምነው ችግር አለው?
አ.አ.አይይይ ችግር የለውም ግን ማን እንደሆነ ነግሮሻል?
ስላመመኝ ነው መሰለኝ ምንም ነገር አልሰማሁም ብቻ ግን ሲመጣ ይደውላል ብዬ ነው የዘጋሁት
ነቢል ሳይታወቀው ኡፍፍፍፍ ብሎ በረጅሙ ተነፈሰ ይሄን የሰማችው ኤማ መጠራጠር ጀመረች...ወዲያው ከተኛችበት ተነስታ በጥያቄ አፋጠጠችው

ማነው የደወለው?

ማንም የስራ ስልክ ነው መሰለኝ

ታዲያ ለምን ተቆጣህ?
አ.አ።.አይይይይይ

ሴት ናት?

ይቀጥላል...
ፀሀፊ የአብስራ

jᵒⁱⁿ⇝ @Habesha_Edit

[​](https://telegra.ph/file/a82371ff2eb0d70e86345.jpg)ስህተት ወይስ ምን?...ክፍል 5
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад