Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

Description
"ከወሰን መተላለፍና ከመንሸራተት ተጠብቆ ታማኝ የሆነውን የተቀና አቋም የተቸረ ታድሏል።!"

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ
{{«ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡}}
      [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ]

በአላህ ፈቃድ ኢስላማዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል
http://t.me/Abdurhman_oumer
http://t.me/Abdurhman_oumer
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 месяц назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 месяц назад

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 2 недели, 1 день назад

1 month, 1 week ago

-      #የጎዳና_ኢፍጣር_!!

ረመዳን ማብቂያ፣ ሃያ"ዎቹ ሲደርስ፣
የጎዳና ኢፍጧር፣ የፍክክር ድግስ፣
የቢድዓ ሰዎች፣ አምጥተዋል አዲስ፣
ባልታዘዙት ነገር፣ ሱናን ለማደፍረስ፣
ጭቅጭቅ ለማስፋት፣ ግጭት ለመቀስቀስ፣
ከመከበር ይልቅ፣ ውጭ ወቶ ለመርከስ፣
ሱና እንዳያብቃቃ፣ ይሄን ዲን ለማፍረስ፣
ነግቶ ያዘልቃሉ፣ ፋሽን በመጠንሰስ!!
- - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -
አህባሽና ሱፍይ፣ በመውሊድ ሲያምታቱ፣
ኢኽዋንና ጄሌው፣ ስልጣን ወንበር ሞቱ፣
ልታይ ልታይ ይላል፣ ወጥቶ በየ-አስፓልቱ፣
ሰልፍ ሰልፍ እያለ፣ ነበረ ጩኸቱ፣
ሌላ አጀንዳ አገኘ፣ በዛው በአይነቱ፣
ወጥቶ መታየት ነው፣ ሀደፉ ምኞቱ!!

- - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -
ፋሽኑ ያብቃበት፣ ድራሹን ያጥፋልን፣
ከእምድር አስወገዶ፣ ጭራሽ ይገላግለን፣
ከስሜት ሰዎች ጋር፣ ሳያነታርከን፣
ዘንድሮ አይመጣብን፣ በጥሩ ያፁመን!!
- - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -
ሴት ወንዱን አውጥቶ፣ በአንድ ማስተያየት፣
በፎቶ ቀርፆ፣ ይባስ ማሰራጨት፣
ለካፊር መዝናኛ፣ ሴት ልጅን ማምቻቸት፣
ስንቱ ይጠቀሳል፣ የቢድዓ ውጤት፣
የጎዳና ኢፍጣር፣ ብዙ ጉድ አበት!!

- - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -
ጃሂል አላዋቂ፣ ምን አለበት ይላል፣
የተራበው ሁሉ፣ ድሃው"ም ይበላል፣
ይሄን ምክንያት ይዞ፣ ሳያውቅ ያራግባል፣
የሱናን መሠረት፣ መች ለይቶ ያውቃል፣
መረጃው ምንዲን ነው፣ መች ይጠይቃል፣
የመጣውን ሁሉ፣ አምኖ ያካሂዳል!!
- - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -
የዲን አስተምሮት፣ ምን ቢያንስም ቢገዝፍ፣
ነብዩ አላስቀሩም፣ አብራርተዋል በገፍ፣
የጎዳና ኢፍጣር፣ ይሄ አዲሱ ፍልስፍ፣
መልካም ቢሆን ኖሮ፣ በኢስላም ቢደገፍ፣
እነዚያ ሰሀቦች፣ የነበሩ ቅልጡፍ፣
ይቀድሙ ነበረ፣ ለመልካም መጣደፍ፣
ከነሱ ለመሆን፣ አብሮ ለመሰለፍ፣
የሰሩት ይሰራል፣ የለም የሚታለፍ፣
የተውት ይተዋል፣ ይህ ነው የሚያፀይፍ!!

- - - - - - - - - - - - - - - - - - - -
ሚስኪን እንደ ማብላት፣ በማዘጋጃው ብር፣
በየ ቤቱ ገብቶ፣ መርዳት ለሚቸገር፣
አስቤዛ ቢያሟሉ፣ ደብቀው በሚስጥር፣
እንደት ትርፋማ ነው፣ ለሚያስብ ለቀብር፣
አለበለዚያ ግን፣ ይህ የታይታ ነገር፣
ምንም አይፈይድም፣ የአንድ ቀን ግርግር፣
የጋጋታ ሥራ፣ የጎዳና ኢፍጣር!!

አብዱረህማን ዑመር
ረመዳን 12/ 1444 ሂጅራህ
የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
https://t.me/Abdurhman_oumer/4398
https://t.me/Abdurhman_oumer/4398

Telegram

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

የዲን አስተምሮት፣ ምን ቢያንስም ቢገዝፍ፣ ነብዩ አላስቀሩም፣ አብራርተዋል በገፍ፣ የጎዳና ኢፍጣር፣ ይሄ አዲሱ ፍልስፍ፣ መልካም ቢሆን ኖሮ፣ በኢስላም ቢደገፍ፣ እነዚያ ሰሀቦች፣ የነበሩ ቅልጡፍ፣ ይቀድሙ ነበረ፣ ለመልካም መጣደፍ፣ ከነሱ ለመሆን አብሮ ለመሰለፍ፣ የሰሩት ይሰራል፣ የለም የሚታለፍ፣ የተውት ይተዋል፣ ይህ ነው የሚያፀይፍ!! ሙሉ ግጥሙን ለማንበብ ***👇*** https://t.me/Abdurhman\_oumer/4398

- [**#የጎዳና\_ኢፍጣር\_!!**](https://t.me/Abdurhman_oumer/4397)
1 month, 1 week ago
«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር
1 month, 1 week ago

🚫 የአልከሶ ጉድ

➧ አልከሶ በስልጤ ዞን የሚገኝ አነስተኛ የቀበሌ ከተማ ሲሆን እንደ አብዛኛዎች የሀገራችን ክፍሎች ከአላህ ውጪ የሚመለክ በሕይወት የሌለ የሸይኽ ቀብር ያለበት ቦታ ነው። እዚ ቦታ ላይ የአልከሶ ሸይኽ (አልከስዬ) እና ሌሎች ወደ ስድስት አካባቢ የሚጠጉ ቀብሮች ይመለካሉ።

➽ እነዚህ ቀብሮች አብዛኞቹ በግንብ የተገነባ ቤት (ዶሪሕ) ያለባቸው ሲሆን የተወሰኑት በጭቃ የተሰሩ ናቸው። በተለይ የአልከስዬ ቀብርን የልጅ ልጅ ነው የሚባለው አቶ ነስሮ ከሪያድ መጥቶ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የሚጎርፉ ሰዎች የሚያመጡትን ስለትና ቤዛ የመሰብሰቡን ሀላፊነት ከተረከበ በኋላ በልዩ ሁኔታ ያስጌጠውና የቀብር አምላኪዎቹን ልብ በሚስብ ሁኔታ እንዳስዋበው ይነገራል

↪️ ይህን ቀብር ለማምለክ የሚመጡ ሰዎች ወደ ግቢው የሚገቡት በባዶ እግራቸው ሲሆን ቀብሩ አካባቢ ሲደርሱ አብዛኞቹ ፍፁም በሆነ የተዋረደ ስሜት ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ተዋርደው ተናንሰው ያዩናል በሚል ስሜት ኮሽታ ሳያሰሚ ወደ ቀብሩ ይጠጋሉ። ከዛም ተበርክከው፣ ተደፍተውና ስጁድ ያደርጋሉ በዚህ ሁኔታ በሁለመናቸው ወድቀው ችግራቸውን ፍላጎታቸውን የደረሰባቸውን መከራና ጭንቅ ተናግረው እንዲፈርጁዋቸው ከጭንቅ እንዲያወጡዋቸው እንዲያሽሩዋቸው እንዲያከብሩዋቸውና ዘር እንዲሰጡዋቸው በእንባ እየታጠቡ ከለመኑ በኋላ ተነስተው ጠዋፍ ያደርጋሉ

➼ በአብዛኛው እንዲህ አይነቱ የኩፍር ተግባር የሚፈፀመው በመውሊድ ጊዜ ነው። የዚህ አይነቱ ሽርክና ኩፍር በአይነቱ የሚሰራበት አልከሶ በየአመቱ መውሊድ ሲደርስ ከየቦታው በሚጎርፉ ሰዎች ይጨናነቃል። ፖሊስና የፀጥታ ሰዎች ቢዚ ይሆናሉ።

➲ በመውሊዱ ጊዜ ከሚሰሩ የኢስላምን ገፅታ ከሚያጠለሹ ተግባራት ውስጥ አንዱ "ቹፒሳ" የሚባለው የአልከሶ መውሊድ ጭፈራ ነው። የዚህ አይነቱ ጭፈራ በተለያየ ግሩፕ የሚከናወን ሲሆን ዘፋኞቹ ገሪባ የሚባሉ ሙሪዶች ናቸው።

➜ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ራሱን ሴት አድርጎ ሻሽ አስሮ በሴቶች መካከል ሆኖ ነው ሴቶችን የሚያስጨፍረው ተራ ጭፈራ ቢሆን ይቀል ነበር እነዚያ ሴቶች ሁሉ ከአላህ ውጪ ላለ አካል እንዲሰግዱና ሩኩዕ እንዲያረጉ የሚደረግበት ነው። ከአጅ ነብይ ወንድ ጋር መጨፈራቸው እንዳይገርምህ ይህ በጣም ቀላሉ ነው ምናልባት በስሜት ሲቀልጡ ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም

➝ በዚህ ቀን በዝሙት የሚወለደው ልጅ ወልይ ነው ሊባልና ከህፃንነቱ ጀምሮ ሊመለክ ይችላል። የዚህ አይነት ሽርክና ኩፍር ቢዳዓና ዘግናኝ ወንጀል የሚሰራበት አልከሶ ማህበረሰቡ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ሙስሊም ነው።

➔ ውስጥን የሚያደማውና የሚዘገንነው ይህን ከአላህ ውጭ የሚመለክና ዘግናኝ የአምልኮ ቦታ ያለበት አልከሶ ላይ ሸይኽ ነስሮና ኢማዱዲን የሚባሉ የዲን መሪ ተብዬዎች መኖራቸው ነው መኖራቸው ብቻ ሳይሆን በአልከሶ ከተማ በሚገኙ መስጂዶች ላይ ስለ አልከሶ ሽርክና ኩፍር በዝርዝር እንዳይነገር መከልከላቸውም ነው ኢማዱ ኡስታዝ ነው ነስሮ ሸይኽ ነው ኩቱቡ ሲታ ያስቀራል ይባላል

➛ የሚገርመው ኢማዱ የሚባለው በመውሊዱ ጊዜ የሚያደርገው ዳዕዋ ለመውሊድ የሚመጣው ሰው መኪና እንዳይገጨው ምን መደረግ እንዳለበት ነው።

➞ እነዚህ ሁለቱ የዲን መሪ የሚባሉት አካላት ማህበረሰቡን በቁጥጥራቸው አድርገው እነሱ ከሚሉት ነገር እንዳይወጣ አስተማማኝ ስራ ሰርተዋል። አይደለም ተራው ሰው አብዛኛውን የመንግስት አመራርን ጭምር በኔት ወርካቸው ውስጥ በማስገባት ሶስት የከተማ ሽማግሌዎች ብለው በሰየሙዋቸው የእነርሱን መመሪያ በሚያስፈፅሙ ሰዎች አማካይነት ነው ከተማዋ የምትመራው

➪ አላህ በየጊዜው እንዲህ አይነቱን ሽርክና ኩፍር የሚዋጉ እሱ ብቻ እንዲመለክ ሰዎች ፍጡርን ከማምለክ አላህን ወደ ማምለክ የሚጣሩ ይፈጥራልና አልከሶ ላይም ይህ የኩፍርና የሽርክ ተግባር ኢስላምን አይወክልም ብለው የተውሒድ ዳዕዋ ለማህበረሰቡ ለማድረስ የተነሱ ወንድሞች አሉ

➩ ይሁን እንጂ እነዚህን ወንድሞች በእንጭጩ ለማስቀረትና ሰዉ በቀብር አምላኪነቱ እንዲቀጥል ለማድረግ በእስር ከሀገር በማባረርና የወጣቶቹን ቤተሰቦች ከማህበራዊ ኑሮ በማስወጣት የማይሰሩት ነገር የለም ነገር ግን እነዚህ ወጣቶች ይህ ሁሉ ሳይበግራቸው ባገኙት አጋጣሚ የተውሒድን ብርሃን ጮራ ወደ ሰዎች እንዲደርስ በማድረጋቸው ብዙ ሰዎችን ከዚህ ሽርክ ለማውጣት ችለዋል

➵ እነዚህ ይህ ሽርክና ኩፍር አይወክለንም ኢስላምንም አይወክልም ያሉ ሙስሊሞች በዚህ ረመዳን አንድ የተተወ መስጂድ ጠርገውና አስተካክለው ፈርድ ሶላትና ተራዊሕ መስገድ ይጀምራሉ ብዙም ሳይቆዩ ከተማውን በኔት ወርክ በሚመሩት ሸይኽ ነስሮና ኢማዱ ዲን ትእዛዝ ሽማግሌዎችና የፖሊስ አባላት መስጂዱ እንዲዘጋና እንዲወጡ ይደረጋሉ እሺ ውጪ እንድንሰግድ ይፈቀድልን ሲሉ የፖሊስ አባላቱ ውጪ መስገድ ትችላላችሁ ይሏቸዋል። መስገድ ይጀምራሉ። ብዙም አልቆየም የኔት ወርኩ አካል የሆነ የተደራጀ የዱርዬ ቡድን እንደ ገጀራና ፌሮ የመሳሰሉ ድምፅ አልባ መሳሬያ በመያዝ ለቀው እንዲሄዱ ያደርጋል

➺ በዚህን ጊዜ በከተማው ውስጥ የዚህ አይነቱ ሽርክና ኩፍር ኢስላምን የነብዩን ዲን አይወክልም ብለው የጠሉ አንድ እናት መጋዘናቸውን ለወጣቶቹ ሰጥተው ቁርኣን እንዲቀራበት አድርገው ነበርና ለረመዳን እንዲሰግዱበት አስፈቅደዋቸው እዛ መስገድ ጀመሩ። ብዙም አልቆዩም የኔት ወርኩ አካል የሆነው የሽማግሌ ቡድን አሁንም አይቻልም ከበላይ እንደማይቻል ተነግሮናል በማለት አቁሙ ይላሉ። የበላይ የሚባሉት ኢማዱና ነስሮ ናቸው

➻ እነዚህ ሽርክና ኩፍር አንቀበልም የኛ እምነት አይደለም ያሉ ሙስሊሞች መብታቸው የሚጠይቁበት አጡ። በሚቀጥለው ቀን የዱርዬው ቡድን መጋዘኑን ሰብሮ በመግባት ለሶላት የተነጠፈውን ምንጣፍና የተካፈለበትን መጋረጃ እንዲሁም ቁርኣኖችን ሰብስቦ ይዞ በመሄድ ምንጣፍና መጋረጃውን ገበያ መሀል በማቃጠል ቁርኣኑን የት እንዳደረሰው አይታወቅም።

➛ ይህ ነገር ከተከሰተ በኋላ የከተማው የፀጥታ ሀላፊ የመስጂዶች ኮሚቴ ቦርድና እነዚህን ወንድሞች ሰብስቦ ካነጋገረ በኋላ በራሳቸው መድረሳም ሆነ መስጂድ ካላቸው መማርም ሆነ መስገድ ይችላሉ ብሎ የወሰነ ቢሆንም የዱርዬ ቡድኑ ለህግ የማይገዛ በመሆነ በተሰጣቸው መጋዘን መስገድ አልቻሉም። አቅም ያላቸው ወጣቶች ከከተማው አንድ ኪሎሜትር ወጣ ብሎ በያዙት ቦታ ላይ እየሰገዱ ሲሆን ሴቶችና አዛውንቶች በረመዳን ቁጭ ብለው ነው ያሉት።

➻ በጣም የሚገርመው ከሀገራችን የኢኽዋን መሪዎች አንዱ የሆነው ካሚል ሸምሱና ግበረአበሮቹ ከዚህ በፊት በዚህ መውሊድ ላይ ተገኝተው ነው ከኛ ምን ትፈልጋላችሁ ምን እናድርግ ያሉዋቸው።

➼ አሁን የድሮዎቹና አዲሶቹ ኢኽዋኖች ከሱፍይና አሕባሽ ጋር ሆነው የሚመሩት መጅሊስ የአልከሶ ሙስሊሞችን መብት ማስከበር አልቻልም። ይልቁንም አዲስ መጤ ሰለፍዮች ናቸው በሚል ሊያጠፉዋቸው ለሚሰሩት ሽፋን ይሰጣሉ።

➧ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ያላችሁ የአልከሶ ተወላጅ የነብዩን ዲን ሶሐቦች ዋካ የከፈሉለትን ኢስላም የምትወዱ የሆናችሁ የእነዚህን ወንድሞች እንባ ጥረጉ። አለን በሉ መብታቸው እንዲጠበቅ ቁርኣንና ሐዲስ ሩሕ ኖሯቸው በስራ ላይ እንዲውሉ አድርጉ ኢማዱንና ነስሮን አትወክሉንም በሉዋቸው። የተውሒድ ባንዲራ በአልከሶ ምድር ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አድርጉ።

➔ በየቦታው ያላችሁ ሰለፍዮች አላህ አልከሶና የመሳሰሉ ቦታወች ላይ ሽርክን አርክሶ ተውሒድን አንገሶ እንዲያሳየን ዱዓእ እያደረጋችሁ ከወንድሞቻችን ጎን እንድትቆሙ አደራ እላለሁ።

https://t.me/bahruteka

3 months, 1 week ago

ለዛም ነው
👇
قال الإمام أحمد رحمه الله تعالى:
((قبور أهل السنة من أهل الكبائر روضة ، وقبور أهل البدعة من الزهاد حفرة ، فسّـاق أهل السنــة أوليـاء الله ، وزهــاد أهل البدع أعداء الله)).اهـ
📚 طبقات الحنابلة (1/184)
አላህ ይዘንላቸው ኢማም አህመድ  የሚከተለውን ብለዋል፡-
  {{የአህሉ ሱና መቃብሮች ከትላልቅ ወንጀሎች ባለቤቶች (ቢሆኑ እንኳ ከጀነት ጨፌ የሆኑ) ጨፌ  ናቸው፣ የቢድዓ ሰዎች መቃብሮች ደግሞ፤ ከዛሂዶች (ቢሆኑ እንኳ ከእሳት ጉድጓድ የሆኑ) ጉድጓዶች ናቸው። የሱና ሰዎች ሥነ ምግባር የጎደላቸው ቢሆኑኳ የአላህ ወዳጆች ናቸው። የቢድዓ ሰዎች ዛሂዶች ቢሆኑ እንኳ የአላህ ጠላቶች ናቸው))
📚 ጦበቃቱል ሀናቢላህ (1/184)

➻ወንጀልህ በዝቶ መልካም ሥራህ ካነሰ ሰለፎች (ደጋግ ቀደምቶች) የሚሉትን አድርግ
‏ﻗﺎﻝ اﻟﻔُﻀَﻴﻞ ﺑﻦ ﻋﻴﺎﺽ:
"ﺇﺫا ﻋﻠﻢ اﻟﻠﻪ ﻋﺰ ﻭﺟﻞ ﻣﻦ اﻟﺮﺟﻞ ﺃﻧﻪ ﻣُﺒﻐِﺾٌ ﻟﺼﺎﺣﺐ ‎ﺑﺪﻋﺔ ﻏﻔﺮ ﻟﻪ ﻭﺇﻥ ﻗﻞَّ ﻋﻤﻠُﻪ"
شرح السنة للبربهاري(1/138)

ታላቁ ዛሂድ (በጣም አላህን ፈሪ በመሆኑ የሚታወቀው) የቀደምት ዓሊም ፉዶይል ኢብኑ ዒያድ እንድህ ይላል
{{አንድ ሠው መልካም ሥራው እንኳ ትንሽ ብትሆንበት ነገር ግን የቢድዓ ባለቤትን የሚጠላ ከሆነ  ይችን ተግባሩን አላህ ስለሚያውቅለት ወንጀሉን ይምርለታል}}

➻ ደጋግ ቀደምቶች የፈለገ አላህን ፈሪ ቢመስል ሙብተዲዕ ከሆነ ፈጽሞ ቦታ አይሰጡትም።

قال الإمام البربهاري رحمه الله تعالى: وإذا رأيت الرجل مجتهدا في العبادة متقشفا محترقا بالعبادة صاحب هوى فلا تجالسه ولا تقعد معه ولا تسمع كلامه ‏ولا تمشي معه في طريق، فإني لا آمن أن تستحلي طريقته فتهلك معه"
[شرح السنة:١٢٤]
አላህ ይዘንላቸው ታላቁ የቀደምት ሊቅ ኢማሙ አል በርበሀሪ እንዲህ ይላሉ፦
{{በዒባዳው ላይ ታጋይና በጣም የናጠ፣ ለጋሽም ዛሂድም የሆነን (ግን) የሥሜት ተከታይ (የቢድዓ ሰው) ካየህ ከሱ ጋር አትቀማመጥ፣ ንግግሩን አትስማ፣ በመንገድም ከሱ ጋር አትሂድ፣ (ምክንያቱም) ያለበትን የጥመት መንገድ #አቅልለህ ታየውና ከሱ ጋር ትጠፋለህ ብየ እፈራልሃለሁ}} (ሸርሁ ሱና 123)

3 months, 1 week ago

መተናነስ ከዓሊሞች እንማር!

ወሳኝ ሙሃዶራ

ርእስ:- የእውቀትና የአዋቂዎች ደረጃ!!

🕌በቂልጦ ከተማ ጥቅምት 19/2015 የተደረገ

🎙 الشيخ حسين بن محمد بن عبد الله السلطي الإثيوبي

🎙በመተናነስ ጥግ የሚታወቁት ታላቁ ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢይ (ሀፊዘሁላህ)

በአላህ ፈቃድ ተጨማሪ ጥቆማዎችን ለማግኘት
👇
https://t.me/Abdurhman_oumer/6774

3 months, 1 week ago

https://t.me/HussinAssilty/29

Telegram

قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد

3 months, 2 weeks ago

አሰላሙ ዓለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ የተከበራችሁ ሰለፍዮች በዚህ ቻናል በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል የተባለው ወድ የሆነው የጉራጌው ፕሮግራም ላይ ድንገተኛ የግል ጉዳይ ያጋጠመኝ በመሆኑ ላልገኝ እችላለሁ!! ሆኖም ግን ከደረስኩ በተቻለኝ እሞክራለሁ!!

3 months, 2 weeks ago

➻ #የምስል ( የፎቶ የቪድዮ) #ጉዳይ!! ምስል (ፎቶ ቪድዮን) አስመልክቶ በርካታ ውዝግቦች እየተነሱ ነው። https://t.me/Abdurhman_oumer/6712 ወደ ጉዳዩ ከመግባታችን በፊት በመጀመሪያ እንደጥቅል የምስል ጉዳይ መጫዎቻ ሆኗል ማለት ይቻላል። ለምን?እንዳው ኢጅቲሀድ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን እናዘግየውና ምስል ይዘቱ ምን ያህል ነው? ኢጅቲሀድይ ነው በሚለው ብንሄድ ራሱ!! ኢጅቲሀድይ…

Telegram

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

***➖*** #የምስል ጉዳይ! https://t.me/Abdurhman\_oumer/5147        ***👆*** የኔ አቋም ፎቶ በማንሳት ጉዳይ ሀራም ነው በሚሉት ዓሊሞች ነው የምጓዘው። ነገር ግን ባለፈውም ዛሬም የማነሳው መሰዓላው የመንሀጅና የዓቂዳ መስዓላ ነው ወይ!? ልክ ምንም ኺላፍ የሌለበት ድሮ የነበረው ምስል ጋር አንድ ነው ወይ? https://t.me/Abdurhman\_oumer/6542         ***👆*** ለምሳሌ በሌላ…

3 months, 2 weeks ago

#የምስል ( የፎቶ የቪድዮ) #ጉዳይ!!

ምስል (ፎቶ ቪድዮን) አስመልክቶ በርካታ ውዝግቦች እየተነሱ ነው።
https://t.me/Abdurhman_oumer/6712
ወደ ጉዳዩ ከመግባታችን በፊት በመጀመሪያ እንደጥቅል የምስል ጉዳይ መጫዎቻ ሆኗል ማለት ይቻላል። ለምን?እንዳው ኢጅቲሀድ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን እናዘግየውና ምስል ይዘቱ ምን ያህል ነው? ኢጅቲሀድይ ነው በሚለው ብንሄድ ራሱ!!
ኢጅቲሀድይ ማለትኮ ሁለት አቋሞች ኖረው ከሁለት አንዱ ትክክል ይሆናል የሚባልበትና አንድ ሰው አላህን ፈርቶ በጥንቃቄ ራጅህ የሆነለትን የሚመርጥበት ማለት ነው። ይሄ እንግዲህ በማንኛውም የኢጅቲሀድይ ጉዳዮች ናቸው በሚባሉ ነጥቦች ሁሉ ሲሆን፤ ከዚህ የከፋው ግን የኢጅቲሀድይ መሰዓላዎች ሁሉ እኩል ናቸው ወይ? የሚለው ሲዳሰስ ነው። በጣም ቅርንጫፍ በሆኑ በውዱእ አደራረግ በዘካ አሰጣጥ በሌሎችም ጥቃቅን በሆኑ ዝርዝር እንደታዎች የሚደረገበት የኢጅቲሃድ ጉዳይና የአላህ እርግማን ይውረድበት ከተባለው ይገባል ወይስ አይገባም በሚል ኢጅቲሀድ የተደረገበት ጉዳይ እኩል የሚዘናጉባቸው ናቸው ወይ?
የምሰል ጉዳይ የዑለሞችንም ትተነው! እንበልና አላህ በሚያውቀው ትክክለኛ ሁክሙ ፈጽሞ የኢጅቲሀድ ባይሆንና ነብያችን ካወገዙት ሙሉ በሙሉ የሚገባ ቢሆን፤ "ኢጅቲሀድይ በሚል ስም እንደፈለገ የሚምቦጫረቅበት ሰው" ምን አይነት ክሰረት ነው የሚገጥመው? ከአላህ ፊት ኢጅቲሀድይ ነው የሚል አቋም ስላለኝ ነው እንደፈለኩ የተምቦጫረኩት ብሎ ሊመልስ ነውን? ኢጅቲሀድይ የሚለውን ተቀበልክ ማለትኮ አመዛኝ የሆነልህን ተቀበልክ ማለት ነው እንጅ በዛ ምክንያት ገብተህ ልክ ሳይኖርህ እንደፈለክ ዋኝ ማለት ነው እንደ?
➻የምስል ይዘትን አስመልክቶ ሌላው ታሳቢ ልናደርገው ከሚገባ ነገር ከፊል ዑለሞች በበርካታ ሁኔታ ያወገዙት መሆኑ ነው። ይሄም በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ዱዓቶች ሲገለጽ የምናየው ነው። የፈለገ የኢጅቲሀድ ርዕስ ነው ብንልና አቋማችን ከሌሎች በተቃራኒ በኩል ቢሆንኳ፤ ከሌሎች የሚነሳው መረጃ ምንም ድንግጥ የማያደርገን ከዛቻው ነጃ የወጣን የማይመለከተን ደነዞች እንሁን ማለት አይደለም።
አሳዛኙ ደግሞ ወንድሞቻችን እንደገለጹት ዛሬ ኢጅቲሀድይ ብለው በር የሚከፍቱት ለአካሄዳቸው ለማምቻቸት ቲቪ ለመውጣት!! ወዘተ ሆኖ ከሆነ ደግሞ ጉዳዩ ከባድ ነው። በዚህ መልክ አላማ አንግቦ ከራሱ አቋም አንፃር ለክቶ በፍርደ ገምድልነት ኢጅቲሀድይ ነው ለሚል አካል፤ አበደን! ኢጅቲሀድይ አይሆንለትም።

➻የምስል ይዘትን አስመልክቶ ሌላም ከዚህ በተጨማሪ ምስል (ቪድዮ ፎቶ) በውስጡ ምን ችግሮች አሉት?? የሚለው ይነሳል።
ምስል ከመልካም ይልቅ ፈሳድን (ብልሽትን) ለማስፋፋት ከፍተኛ አቅም አለው።
በሱ ምክንያት ሺርክ ኩፍር ይሰራል ፎቶ የሚያመልኩ ሰዎች በርካቶች ናቸው።
በአጭሩ ተቆጥረው የማያልቁ ችግሮች ያሉበት ጉዳይ ነው።
ዝሙት በፍጥነት እንዲስፋፋና በከፍተኛ  ሁኔታ በአደባባይ ሳይቀር መረቡን እንዲዘረጋ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ያለ ነገር ነው።

ይሄ ሁሉ ከመሆኑ ጋር ሌላው አንዳንድ ሰው ዘንድ የምንመከተው ሁል ጊዜም በሆነ ርዕስ ላይ ተነስቶ፤ "ጉዳዩን በልኩ እንያዘው!" ይልና ልኩን አልፎ በጣም በአሳዛኝ ሁኔታ ዲን ላይ ይጫወታል።
   በምስል ዙሪያ በልኩ እንያዘው በሚል ተነስቶ ሌሎች መሰመር የሳቱ ሰራዎችን ይሰራል። ከዛም ውስጥ አንዱ ጽፎት ሰሞኑን ካየሁት እነ"እገሌም ምስል ይጠቀማሉ ይሄው በግ አርደው ያሳያሉ ብሎ በዚህ መልክ ምስልን በቻናሉ ይለጥፋል። ለዚህም ሰው ከላይ ለተባሉት እንለዋለን!! የፈለገ ኢጅቲሀድይ ነው ብትልና ኢጅቲሀድ ነው ያሉ ብቻ ሳይሆን ሀራም አይደለም ከሚሉት ብትሆን ራሱ በዚህ መልክ ነው በአላህ ዲን ላይ የምትጫወተው? ሞንም ጥቅም ለሌለው እነ እገሌ ምስል ይጠቀማሉ በግ አርደው የታረዱ በጎችን ምስል ተጠቅመው ብለህ ለዚህ ለዛዛታ ነገር፤ ያን ምስል ያልከውን ነገር ራስህ ታሰራጫለህ?
እንዲህ ለመጨዋቻነት ለመጠቀም ነውን ሀራም አይደለም የሚሉ ሰዎች ራሱ ሀራም አይደለም ያሉት? እነዛ የታረዱ በጎችን በመቅረፅ አንድ ምሰል ተጠቀሙ ያልካቸው ሰዎች? ከባድ ለሆነ ዶሩራ ይጠቀሙት አይጠቀሙት ባናውቅም እነርሱን ተሳስተዋል ብንልኳ፤ አንተ ግን ያን ማሰራጨትህ ምን ባይ ነህ? ይሄ ነው ምስልን በልኩ መያዝ? ምንዲን ነው ጥቅሙ? ያለ ምንም ጥቅም ምስል ላይ እንዲህ መዝናናት በልኩ መያዝ ነው? ወይስ ለማጠልሸት የሚጠቅም መስሎህ?
   ወደ ጉዳዩ ስንመለስ። ከላይ ከዳሰስነው ሁሉ በላይ የምስልን ጉዳይ በጣም አስፈሪና ከባድ የሚያደርገው?  ከድሮው ስዕል ጋር ምንም አይለይም የሚሉ ሰዎች ወደ ቁርጠኝነት የቀረበ የሆነ ምን መረጃ አላቸው የሚለውን ስትመራመር ነው። ኢጅቲሀድይ ነው ካልክ ደግሞ በዚህኛውም በኩል መመራመር አለብህና!!
አንድ ምሳሌ ላስቀምጥ የሚዳሰስ ቅርጽ ያለውን እንተወውና በቀለም የሚሰራውን ሰዕል ወይም ፎቶ ስንመለከት፤ ማለትም ሰዓሊዎችን ይመስል ይህ ተግባራቸው ከዛ በነብዩ (ዓለይሂሶላቱ ወሰላም) አንደበት ከተረገመው ሰዕል ይገባል ወይስ አይገባም? ሁላችንም በትክክል ይገባል በሚል የምንስማማ ሲሆን ታዲያ በካሜራ የወጣ ፎቶና ያኛው ምን ያህል ልዩነት አለው? የሚለውን ሰታስተነትን እውነትም ጉዳዩ በጣም አስፈሪ ነው። ጉዳዩን በልኩ እንያዘው ማለትም ይሄ ነው።

https://t.me/Abdurhman_oumer/6714
👆
ሁለተኛውን ገጽ በዚህ ታገኛላችሁ

Telegram

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

***🟢***ግመል አይበርም ***👉***የእነ ኢብኑ ሙነወር ፣ ኢሊያስ አህመድና የሰሊም አል ሂላሊ ሰዎች ተልቢስ። ***📵***የምስል ጉዳይ የኢጅቲሃድ ነውን? ***🔊***የአሸይኽ ሳሊህ አልፈውዛን እና የአሸይኽ ሱለይማን አሩሀይሊይ መልስ ተያይዟል። https://t.me/Abuhemewiya/2803?single ስለምስል ሀራምነት ስንትና ስንት መረጃዎች እና የኡለማዎች ፈታዋ ቢደረደሩም እምቢተኞች ግን በአመፃቸው  ጠንክረው ቀጥለዋል።…

3 months, 3 weeks ago

ዛሬም በሀቁ ጎዳና ላይ ያሉ መሻይኾችን በመተዋቅ ላይ

ሌላ ወሳኝ ሙሓዶራ

ርዕስ – "የተውሂድ አንገብጋቢነት"

🎙በዱክቱር ሸይኽ ሑሴን ብን ሙሐመድ  ሃፊዞሁሏህ

ህዳር ‐ 12 ‐ 2015

🕌በባህር ዳር ከተማ ቡኻሪ መስጅድ የተሠጠ ሙሓዶራ

ተጨማሪ ጥቆማዎችን ለማግኘት
👇
https://t.me/Abdurhman_oumer/6641
.

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 месяц назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 месяц назад

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 2 недели, 1 день назад