★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 3 weeks ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 8 months ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month, 3 weeks ago
እግዚአብሄር የረዳኝ አንዳንድ ፀሎቶቼን በመመለስ ብቻ ሳይሆን ባለመመለስም ጭምር ነው!
ለማይገባን ስራ
ለማያስፈልገን እድል
ለማይጠቅመን ቦታ
ለማይመጥነን ትዳር
ለሚያሳምመን ስጦታ ፀልየን እንቢ ስላለን ፣ስላልሰጠን እግዚአብሄር ይመስገን!
ከራሳችሁ ፀሎት እና ፍቃድ ይሰውራችሁ.....የእርሱ ስጦታ ሁል ጊዜ ፍፁም ነው ግን የለውም!
ፍለጋው አብቅቷል 😍❤️ እኔም እሺ ብያለሁ!
ብዙ ፅፌ አጥፍቻለሁ
ችሎታዬም ጥበቤም አቅም አጥቷል!
አንዳንድ፡ነገሮችን ለመግለፅ ቃላቶች ይሰንፋሉ ወደፊት የምፅፈው ፣የምመሰክርላችሁ ብዙ ስለሚኖረኝ ለጊዜው ዜናው ላይ ላተኩር!
ለማንኛውም የምትወዱኝ የምትቀርቡኝ ወዳጆቼ ፀሎታችሁን በምስጋና ቀይሩ!
ሩትን ከማይመጥናት ህይወት የገላገላት ሰው ትዝ አላችሁ?
እሱን የመሰለ ሰው ለእኔም ቦኤዝ ሆኖ ተልኳል!
የኔ ስሁል መቷል/ ዶክተሩ፣ የምገዛለት ሰው፣ ሸሚዝ ለባሹ፣አብሬው መጽሐፎችን የምፅፈው፣አብሬው የምሰራው፣መካሪዬ፣ የህልሜ አትክልተኛ፣ ብዙ ስራ ስለሚሰራ ረዳት የምሆንለት፣ ቪዥን ቦርዴ ላይ የፃፍኩት፣ ፀሎት ደብተሬ ላይ ያብራራሁት፣ ደግሞም አጠገቤ ላላችሁ ሰዎች የነገርኳችሁ
እግዚአብሄር ልጁን ከከፈለበት ከነብሴ መዳን ቀጥሎ
፤ከአንተ የሚበልጥ ስጦታ ተሰቶኝ አያውቅም እሱንም በልቤ ደስታ ፣ላንተ ባለኝ ፍቅር ፣በውስጤ መረጋጋት፤የት እንደገቡ በማላውቃቸው ግኖቼ/ጥያቄዎቼ ፣በምስጋናዬ ብዛት አረጋግጫለሁ!
አንድ ነገር አውቃለሁ አንተ ልጅ እያለሁ ካለምኩት አጋሬ፣ ተምበርክኬ በፀሎት ከጠየኩት፣ ሰዎች እንዲህ እንዲያ ያለ ሰው ብታገቢ ብለው ከተመኙልኝ ወይም ሊገናኙኝ ከሞከሩት ፣ ከዚህ ቀደም በዙሪያዬ ከመጡት ወደ ፊትም ከሚመጡት ሁሉ ለእኔ ትበልጣለህ!
ከዚህ በላይ ምን እፈልጋለሁ?
በርግጥ አንተ ከጠየኩት በላይ ነህ.
ምን መልካምነት ቢገኝብኝ ይሆን እንዳንተ ያለ ሰው የተገባኝ እላለሁ?
አንድ አሳ ማጥመድ ብርቅ የሆነባቸው አሳ አጥማጆች ጌታ እየሱስ ያላቸውን በተቀበሉ እና እንደ ተባሉት oባደረጉ ጊዜ ከዓሣው ብዛት የተነሣ መረቡን መጐተት አቃታቸው።
ጴጥሮስም የተደረገውን ባየ ጊዜ “ጌታ እኮ ነው!” አለው።
ዮሐንስ 21:7
እኔ መረቤን፡በተባልኩበት ጥዬ ተባርኪያለሁ ለእናንተም ይሄ ይሁን
#ዱባይ #IEA #Award
ሙሴ የቱን ወደ ላይኛው ከፍታ ቢወጣ እግዚአብሄር ወደ እሱ ዝቅ ካላለ በስተቀር አምላኩን ሊያወራውም ሊያገኘውም ሊደርስበትም አይችልም!
እግዚአብሔር (ያህዌ) በሲና ተራራ ጫፍ ላይ ወረደ፤ ሙሴን ወደ ተራራው ጫፍ.... ወጣ።
ዘፀአት 19:20
እናንተ የራቃችሁን ነገር እንድትደርሱበት ወደ እናንተ ጠጋ ያደርገዋል።
ፀጋ እንደዛ ነው ....የራቀን ያቀርባል.....
እግዚአብሄር ለእናንተ መውጣት በሆነው ነገር ላይ ይውረድላችሁ።
የማትደርሱበት የሚመስላችሁ የትኛውም ከፍታ ይቅረባችሁ.....
በእኔ ሁኔታ፣አዕምሮ ፣ችሎታ እና የገንዘብ አቅም መሆን የማይችሉ ነገሮች እየሆኑ ነው። እግዚአብሄር ለእኔ እንዲሁ ነው ያደረገው
ምስሌን ፍለጋ ሀሙስ በሻርጂያ የሴቶች ፎረም በሚኖረን ስልጠና ላይ ያገኙታል!
ነገ ደግሞ በአትላንቲስ ዘ ፓልም ሽልማታችንን እንወስዳለን!
እግዚአብሄር ይክበርበት!
#የእኔ_ልደት_እና_ገዢው_መንግስት
ነገሩ ፖለቲካ የሆነበትን ምክንያት ከታች አንብቡት !
(ጉዳዩ ላይ ይበልጥ ለማተኮር እና ለመረዳት እንዲጠቅማችሁ ከኢትዮጲያ መንግስት ውጪ አስቡ) አንድ ሰው የአንድ ሀገር ጠቅላይ ሚኒስቴር ከመሆኑ በፊት እያንዳንዱ የግል እና የቤተሰብ ጉዳይ ፣ ጥቃቅን እና ትልልቅ የቤት ውስጥ ሀላፊነት ያስጨንቀዋል።
ወደ መንግስት ስልጣን ከመጣ በኋላ ግን ስለሚበላው ምግብ ፣ ስለመኪናው ነዳጅ፣ ስለተገዛው አስቤዛ ወይም ሌላ ጥቃቅን ወጪዎች አይመለከተውም።
መሪው ጥሩ ይሁን መጥፎ ፤ትክክል ቢሰራም ባይሰራም - የቀን እና የሌሊት ሀሳቡ መንግስት እና የመንግስት ጉዳይ ይሆናል።
ታዲያ በዚህ ጊዜ አስቀድሞ ያስጨንቀው የነበረውን የግል ጉዳዮቹን የሚያስፈጽም እና የእርሱ ጉዳይ የሚያስጨንቃቸውን ሰዎች መንግስት ይመድባል። እርሱ ትኩረቱን መንግስት ላይ ሲያደርግ መንግስት ደግሞ ትኩረቱን እርሱ ላይ ያደርጋል።
በተለየ መልኩ ለሚበላው ፣ ለሚለብሰው ፣ ለሚቀመጥበት፣ለሚጠጣው ሻይ ሳይቀር ሳይቀር ሀላፊነት በሚወስዱ ሰዎች ይከበባል ለዛም የሚሆነውን በጀት የሚመድበው መንግስት ነው!
እናንተ የእግዚአብሄር ጉዳይ ላይ ስታተኩሩ እግዚአብሄር የእናንተ ጉዳይ ላይ ያተኩራል። እናንተ የእግዚአብሄር መንግስት ዋናችሁ ሲሆን የእግዚአብሄር መንግስት የእናንተን ጉዳይ ዋናው ያደርጋል። ይበልጥ ወደ እግዚአብሄር መንግስት ስትጠጉ ይበልጥ የእግዚአብሄር መንግስት በእናንተ ጉዳይ ሀላፊነት ይወስዳል።ቤተመንግስት አካባቢ ስትጠጉ የመንግስት ያህል ትጠበቃላችሁ…አንድ ባለስልጣን ሌላ ሀገር ሲሄድ እንዴት ደንነቱ እንደሚጠበቅ ሰምቼ ነበር ጉዳዩ የግለሰብ ሳይሆን የመንግስታት ጉዳይ ይሆናል።
በቃ ይሄው ነው
ገዢው እና ትልቁ መንግስት የሰማዩ ነው!
ስለዚህ፣ ‘ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?’ ብላችሁ አትጨነቁ፤ አሕዛብ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ለማግኘት ይጨነቃሉና፤ የሰማዩ አባታችሁም እነዚህ ሁሉ ለእናንተ እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል። ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን እሹ፤ እነዚህ ሁሉ ይጨመሩላችኋል።
ማቴዎስ 6:31-33
ያለፈው አመቴ በብዙ መናወጥ እና በጣም ትልልቅ ድሎች ነበሩት ግን ጉዳዬ ሁሉ በቁጥጥሩ ውስጥ እንደሆነ ደጋግሜ ተረድቻለሁ። ፈተናዎቼ ቀጠዩን መጽሐፎቼን ወልደዋል ፤በመልካምም ሆነ በክፉ በህይወቴ ውስጥ የነበሩት ሰዎች ደግሞ የመጽሐፉ ገፀ ባህሪ ሆነው የራሳቸውን አሻራ አኑረዋል።
???የ28ተኛ አመት የልደት ቀኔ ላይ ሆኜ ለራሴ እንዲ እለዋለሁ አይንሽን ከራስሽ ጉዳይ ላይ አንሺ ....የእግዚአብሄር ጉዳይ ዋናሽ ይሁን!
የበለጠ ትኩረት የሚስበውን የፖለቲካ ወሬ ስለሆነ ይህንን መልዕክት እንድታነቡት እድሉን ልጠቀም ብዬ ነው ጉዳዩን መንግስታዊ ያደረኩት። ይቅርታ ??
ዛሬ እንዲ ሆን.....
የተሰበረ የመሰላችሁ ነገር መልሶ እንደገና ይሰራላችሁ!
በሸክላ ሰሪው እጅ ተይዛችሁ ቅሩ! እንደገና ለመሰራት ከእርሱ መራቅ አይሁንባችሁ....
እጄ ላይ የነበረን ነገር ተበላሸ በቃ ብዬ በተለይ ዛሬ በጣም ከፍቶኝ ነበር!
ደሞ በሌሊት እንዲህ አለኝ መፍትሄውንም ነገረኝ
ከጭቃ ይሠራው የነበረውም ሸክላ በእጁ ላይ ተበላሸ፤ ሸክላ ሠሪውም በሚፈልገው ሌላ ቅርጽ መልሶ አበጀው።
ሸክላ ሠሪው እንደሚሠራው፣ እኔ በእናንተ ላይ መሥራት አይቻለኝምን?” ይላል እግዚአብሔር፤ “የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ጭቃው በሸክላ ሠሪው እጅ እንዳለ፣ እናንተም እንዲሁ በእጄ ውስጥ ናችሁ።
ኤርምያስ 18:4-6
የሚናገረው፣ የሚሰማው ፣ የሚያየው አንድ አምላክ ይቅረባችሁ!
እኔም #ባለጊዜ ነኝ!
በከባዱ የተፈተነች በከባዱ የተሸለመች
ድካሟን እየተሸፈነላት ስኬቷ ያደመቀላት
ልወድቅ ነው እያለች እጇን ይዞ ያሻገራት
ውለታዋን ያልከፈለች የምንጊዜም ባለዕዳ ፣በምህረት ኑሪ የተባለች ፣ እስትንፋስ የተቀጠለላት ፣ ሳይገባት በአምላኳ የተወደደች እሷ ባለጊዜ ሴት እኔ ነኝ!
በህይወት እስካለን፣እግዚአብሄር እድሜ እስከጨመረልን ድረስ እስትንፋሳችን ካልቆመ እኛም ባለጊዜ ነን!
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 3 weeks ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 8 months ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month, 3 weeks ago