ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ!
➮የሃገር ቤት ትኩስ ትኩስ መረጃዎች
➮የአፍሪካ መረጃዎችን በሙሉ
➮የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ሙሉ መረጃ
➮ቁጥራዊ መረጃዎች እና ዳሰሳዎች
➮ጨዋታዎችን በቀጥታ ከየስታዲየሙ
ለማስታወቂያ ስራ @Promotion_4_3_3_Bot
⓸-⓷-⓷ስፖርት በኢትዮጵያ| 2017
Last updated 12 hours ago
ሙሌ ስፖርት ስፖርታዊ መረጃዎችን ከእሁድ እስከ እሁድ ያገኙበታል
የሃገር ቤት መረጃ
የአውሮፓ ሊግ መረጃ
ቀጥታ ስርጭት
የዝውውር ዜና
ለማስታወቂያ ስራ @Mulesporta
@Teme_Ayu
ስልክ ቁጥር +251911857852
Last updated 1 month, 2 weeks ago
👉 ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ ቻናል ነዉ። ይህ ቻናል ስለ ውዱ ክለባችን ማንችስተር ዩናይትድ 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደ እናንተ ያደርሳል።
ለማንኛዉም አስተያየት
@wizhasher
@wiz_hasher
Group 👉 @Man_United_ethio_fans_Group
{ስልክ ቁጥር}
0919337648
Last updated 1 day, 16 hours ago
ዴክላን ራይስ ከቡድኑ ጋር አልተጓዘም !
እንግሊዛዊው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዴክላን ራይስ ለነገው የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ወደ ጣልያን እንዳልተጓዘ ተገልጿል።
ተጨዋቹ ወደ ጣልያን ያልተጓዘው ለቅድመ ጥንቃቄ መሆኑ ሲገለፅ ከባድ ጉዳት እንዳላጋጠመው ተጠቁሟል።
በሌላ በኩል ጉዳት ላይ የቆየው ኖርዌያዊው አማካይ ማርቲን ኦዴጋርድ ከቡድኑ ስብስብ ጋር አብሮ መጓዙ ተመላክቷል።
“ አርሰናል ከአውሮፓ ምርጥ ክለቦች አንዱ ነው “ ሲሞን ኢንዛጊ
የኢንተር ሚላኑ ዋና አሰልጣኝ ሲሞን ኢንዛጊ የነገ ተጋጣሚያቸው አርሰናል በዚህ ሰአት ከአውሮፓ ምርጥ ክለቦች አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።
ነገ ከከባድ ተጋጣሚ ጋር ጨዋታ እንደሚጠብቃቸው የገለፁት አሰልጣኙ " አርሰናል ከአውሮፓ ምርጥ ክለቦች አንዱ ነው " ብለዋል።
አሰልጣኝ ሲሞን ኢንዛጊ አክለውም አርሰናል የዘንድሮውን የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ የማሳካት እድል ካላቸው ክለቦች አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።
" የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ምርጥ ውድድር ነው ባለፉት ጥቂት አመታት ወደዚያ የመሄድ እድሉ ነበረኝ ነገር ግን እኔ በኢንተር ሚላን ደስተኛ ነኝ።" ሲሞን ኢንዛጊ
💥 የአውሮፓ ምርጥ ተጫዋቾችን የምናይበት የሻምፕዮንስ ሊግ ፍልሚያ ዛሬ ምሽት ቀጥሏል!
ዛሬ ምሽት ሩበን ሞሪም የመጨረሻውን የሻምፕዮንስ ሊግ ጨዋታ ከቀድሞው ቡድኑ ጋር ያደርጋል!
🇵🇹Sporting vs 🏴Man City ከምሽቱ 5:00 ሰዓት
👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ ፣ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሜዳ ፕላስ ፓኬጅ ይከታተሉ!
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et
ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh
#ChampionsLeagueAllonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
አርባምንጭ ከተማ ተከታታይ ድሉን አሳካ !
በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ስድስስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርባምንጭ ከተማ ከፋሲል ከነማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የአርባምንጭ ከተማን የማሸነፊያ ግብ አበበ ጥላሁን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
ፋሲል ከነማ በውድድር ዘመኑ የመጀመሪያ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።
አዲስ አዳጊው ክለብ አርባምንጭ ከተማ በውድድር ዘመኑ ተከታታይ ሁለተኛ ድሉን ማሳካት ችሏል።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
8️⃣ ፋሲል ከነማ :- 7 ነጥብ
9️⃣ አርባምንጭ ከተማ :- 7 ነጥብ
ቀጣይ መርሐ ግብር ?
እሁድ - ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አርባምንጭ ከተማ
ማክሰኞ - ፋሲል ከነማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ለምን ተመራጭ ሆኑ ?
ፖርቹጋላዊው የስፖርቲንግ ሊስበን አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ባለፉት ወራት ስማቸው ከታላላቅ ክለቦች ጋር ሲነሳ ነበር።
አሰልጣኙ አሁን ላይ ማንችስተር ዩናይትድን በሀላፊነት ለመረከብ ከጫፍ መድረሳቸውን ታማኝ የመረጃ ምንጮች አረጋግጠዋል።
አሰልጣኙ ከሁለት አመታት በፊት ክለባቸው ስፖርቲንግ ሊስበንን ከ 19ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን የሊግ ዋንጫ እንዲያሳካ ረድተዋል።
በተጨማሪም ባለፈው የውድድር አመት ተጨማሪ የሊግ ዋንጫ ለክለባቸው ማሸነፋቸው በታላላቅ ክለቦች አይን ውስጥ እንዲገቡ አድርጓል።
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በዘንድሮው የውድድር ዘመን ስፖርቲንግ ሊስበንን እየመሩ ያደረጓቸውን ዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች በማሸነፍ በሀያ ሰባት ነጥቦች ሊጉን እየመሩ ይገኛሉ።
በዘንድሮው የውድድር ዘመን ስፖርቲንግ ሊስበን በዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች ሰላሳ ግቦችን በተጋጣሚዎቹ ላይ ሲያስቆጥሩ የተቅጠሩበት ሁለት ግቦች ናቸው።
ሩበን አሞሪም ምን አይነት አጨዋወት ይከተላሉ ?
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በ 3-4-3 እንዲሁም 3-4-2-1 የጨዋታ አሰላለፍ እንደሚመርጡ ያላቸው ቁጥራዊ መረጃ ያስረዳል።
አሰልጣኙ ኳስ የሚቆጣጠር ፣ ተለዋዋጭ የማጥቃት ባህሪ ያለው እና ጠንካራ የመከላከል መሰረት ያለው ቡድን በመገንባት እንደሚታወቁ ተገልጿል።
አሰልጣኙ በስፖርቲንግ ሊስበን ቆይታቸው ኑኖ ሜንዴዝ ፣ ኑኔስ ፣ ማኑኤል ኡጋርቴ እና ፓልሂንሀን የመሳሰሉ ባለተሰጥኦ ተጨዋቾችን ማብቃት ችለዋል።
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በቀጣይ ማንችስተር ዩናይትድን ከተረከቡ ከቡሩኖ ፈርናንዴዝ እና ማኑኤል ኡጋርቴ ጋር ዳግም አብረው የሚሰሩ ይሆናል።
ማርቲን ኦዴጋርድ መቼ ወደ ሜዳ ይመለሳል ?
የመድፈኞቹ አማካይ ማርቲን ኦዴጋርድ የተወሰኑ ቀላል ልምምዶች መጀመሩን አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።
ተጨዋቹ አሁንም ለመመለስ የተወሰነ ነገር ቢቀረውም በሚቀጥሉት አስር ቀናት ወደ ሜዳ ይመለሳል የሚል እምነት እንዳላቸው አሰልጣኙ ጠቁመዋል።
ጋብሬል ማግሀሌስ በበኩሉ ያጋጠመው ጉዳት “ ከባድ አይመስልም “ ያሉት ሚኬል አርቴታ በቅርቡ ወደ ሜዳ ይመለሳል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ጁሪየን ቲምበር በሊቨርፑል ጨዋታ ተቀይሮ የወጣው በድካም እንጂ በጉዳት ምክንያት አለመሆኑን አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አያይዘው ተናግረዋል።
አሰልጣኙ አክለውም ሪካርዶ ካላፊዮሪ ለተወሰኑ ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ አስታውቀዋል።
በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሪያል ማድሪድ ከመመራት ተነስቶ ዶርትመንድን 5ለ2 ሲያሸንፍ አርሰናል ሻክታር ዶኔስክን 1ለ0 መርታት ችሏል።
የሎስ ብላንኮዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ቪንሰስ ጁኒየር 3x ፣ ሩዲገር እና ቫዝኩዌዝ ከመረብ ሲያሳርፉ ለዶርትመንድ ማለን እና ጊቴንስ አስቆጥረዋል።
አርሰናልን አሸናፊ ያደረገች ግብ ሪዝኒክ በራሱ ግብ ላይ አስቆጥሯል።
ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ የሰራው ቪንሰስ ጂኒየር የጨዋታው ኮከብ በመባል መመረጥ ችሏል።
በሌሎች ጨዋታዎች
- አስቶን ቪላ ቦሎኛን 2ለ0
- ስቱትጋርት ጁቬንቱስን 1ለ0 ሲያሸንፉ
- ፒኤስጂ ከፒኤስቪ ጋር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
ከበርካታ አመታት በኋላ ወደ ሻምፒየንስ ሊግ የተመለሰው አስቶን ቪላ ያደረጋቸውን ሶስት ጨዋታዎች በማሸነፍ ሻምፒየንስ ሊጉን እየመራ ይገኛል።
የዛሬ ምሽት ጨዋታዎች ውጤት ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።
ዋልያዎቹ ሽንፈት አስተናግደዋል !
የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታውን ከጊኒ ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 3ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
የጊኒን የማሸነፊያ ግቦች ሴርሁ ጉራሲ 2x እና ቱሬ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
የዶርትመንዱ የፊት መስመር ተጨዋች ሴርሁ ጉራሲ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች አምስት ግቦችን አስቆጥሯል።
ዋልያዎቹ በማጣሪያው ካደረጓቸው አራት ጨዋታዎች በሶስቱ ሲሸነፉ በአንዱ አቻ ተለያይተዋል።
የምድብ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
*2️⃣ኛ. ጊኒ :- ስድስት ነጥብ
*4️⃣**ኛ. ኢትዮጵያ :- አንድ ነጥብ
ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ!
➮የሃገር ቤት ትኩስ ትኩስ መረጃዎች
➮የአፍሪካ መረጃዎችን በሙሉ
➮የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ሙሉ መረጃ
➮ቁጥራዊ መረጃዎች እና ዳሰሳዎች
➮ጨዋታዎችን በቀጥታ ከየስታዲየሙ
ለማስታወቂያ ስራ @Promotion_4_3_3_Bot
⓸-⓷-⓷ስፖርት በኢትዮጵያ| 2017
Last updated 12 hours ago
ሙሌ ስፖርት ስፖርታዊ መረጃዎችን ከእሁድ እስከ እሁድ ያገኙበታል
የሃገር ቤት መረጃ
የአውሮፓ ሊግ መረጃ
ቀጥታ ስርጭት
የዝውውር ዜና
ለማስታወቂያ ስራ @Mulesporta
@Teme_Ayu
ስልክ ቁጥር +251911857852
Last updated 1 month, 2 weeks ago
👉 ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ ቻናል ነዉ። ይህ ቻናል ስለ ውዱ ክለባችን ማንችስተር ዩናይትድ 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደ እናንተ ያደርሳል።
ለማንኛዉም አስተያየት
@wizhasher
@wiz_hasher
Group 👉 @Man_United_ethio_fans_Group
{ስልክ ቁጥር}
0919337648
Last updated 1 day, 16 hours ago