ጦብያን በታሪክ

Description
ኖር

— ስለ ኢትዮጵያ የማነባቸውን /አልፎ አልፎም ጉዞዎቼን/ እዚህ አስቀምጣለሁ ደስ ካላችሁ አንብቡ። ሌሎች ከኢትዮጵያ ያልሆኑ ነገሮችን ባጋራም አብዛኛው ከወዲህ ነው፡፡

Predominantly (but not strictly) about Ethiopia and Ethiopian history. @hewansemon
We recommend to visit

A place to learn English easily.

Owner - @Samson_G

Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian

Last updated 1 month, 3 weeks ago

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት ??
@mujaabot

For Advertisement??
@atcads

Last updated 2 months, 1 week ago

NGO, የመንግስት እና የግል ድርጅቶች የስራ ማስታወቂያ እና ነፃ የትምህርት እድሎችን ያገኛሉ ቤተሰበ ይሁኑ ሌሎችንም ይጋብዙ

ለማስታወቂያ @Human133 ላይ አናግሩን
We need promoters
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12

Last updated 1 week ago

1 week, 1 day ago

ሰላም ጤና ይስጥልኝ፡

ሸዋ ሮቢት አካባቢ ያላችሁ ወዳጆች፡ ሸዋ ሮቢት ውስጥ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም የምትባል ቤተ ክርስቲያን አለች? የምታውቁ ብትጽፉልኝ ወሮታ እመልሳለሁ።

እግዚአብሔር ይስጥልኝ

------------------------
Update:

አመሰግናለሁ። ከንግዲህ አትጨነቁ -- የጻፉልኝ ሰዎች አግዘውኛል

1 week, 2 days ago
ዮሐናን አመስግኑልኝማ

ዮሐናን አመስግኑልኝማ https://youtu.be/L3I7G9CyJrs?si=I3TVACwdHKGdJqKM

1 week, 4 days ago
ይኸውላችሁ፡ ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 9 …

ይኸውላችሁ፡ ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 9 ሰዓት ላይ (CFEE) የፈረንሳይ ኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል (ጃንሜዳ ያለው) ይሄን ውይይት በZOOM ያካሂዳል።

ርዕሱ፡ The Stelae Culture Complex in the Horn of Africa
By Dr. Ayele Tarekegn

On presential at the CFEE Library (Jan Meda)

Topic: FMSEH - CFEE 2025 Seminar Series (1)
Time: Jan 31, 2025 03:00 PM Nairobi
Join Zoom Meeting
https://univ-grenoble-alpes-fr.zoom.us/j/93176792250?pwd=FKbwRHGsjPAodxfRT1VfVPNDKhBt5y.1

Meeting ID: 931 7679 2250
Passcode: 875984

ለተጨማሪ መረጃ፡ https://cfee.hypotheses.org/10997

2 months, 2 weeks ago
ጦብያን በታሪክ
2 months, 2 weeks ago
አቤ ጉበኛ አንድ ለናቱ መግቢያ ላይ …

አቤ ጉበኛ አንድ ለናቱ መግቢያ ላይ የጻፈውን አይታችኋል? እዩትማ:

ጳውሎስ ኞኞ “ይህን ሥራ ስሠራ ከሚስቴ ውጪ ያገዘኝ ማንም የለም። ደኅና እንሁን ብቻ” ካለው ጋር ተመሳሰለብኝ ?

ሁለቱም የቴዎድሮስ ታሪክ መጽሐፎቻቸው ላይ ነው ደግሞ እንዲህ ያሉት። የካሳ ወኔ ነሸጥ እያረጋቸው ነው?

2 months, 3 weeks ago
የሚመጣው ሳምንት ረቡዕ ኅዳር 18 ቀን፣ …

የሚመጣው ሳምንት ረቡዕ ኅዳር 18 ቀን፣ በኢትዮጵያ ሰዐት አቆጣጠር 8 ሰዐት ላይ “Rethinking Political Legitimacy: Tewodros II and the Fekkare Iyesus” በሚል ርዕስ ፐሬዘንቴሽን/ሌክቸር አቀርባለሁ። መሳተፍ የምትፈልጉ በዚህ ዙም አድራሻ መቀላቀል ትችላላችሁ።

https://uni-hamburg.zoom.us/j/92260268033?pwd=YkpBUXNlV3kzdEZhT3p4TUJONlpFQT09

2 months, 3 weeks ago

Prague የሚዘጋጀው የአፍሪካ ጥናት ኮንፍረንስ call for papers/abstracts ከተለቀቀ ሰንብቷል፡

https://www.ecasconference.org/2025/call-for-papers/

3 months ago

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል የአሁኑ ሐሙስ እና አርብ አንድ ጉባኤ እና ዐውደረ‍እዕይ ያካሂዳል። ስለባርያ ንግድ ነው። ማስታወቂያው ይኼው:

3 months ago

ሰላም ጤና

ኢቲቪ/አሁን EBC/ የሚሠራ ሰው አለ እዚህ? ወይ እዛ የሚሠራ ሰው የሚያውቅ? ከarchives ክፍል መረጃ ፈልጌ ነው። አመሰግናለሁ

3 months ago

በጎንደር ዘመነመንግሥት ከሮ ስለነበረው የተዋሕዶዎች እና የቅባቶች የሃይማኖት ክርክር

የቅብዓቶች ባህል «የእግዚአብሔር ቃል በድንግል ማርያም ማኅፀን ሲፀነስ ከእርስዋ የተነሣው ሥጋ በመንፈስ ቅዱስ ቅብዓት የአብ የባሕርይ ልጅ ሆነ» ሲል
የተዋሕዶዎች ደግሞ «የእግዚአብሔር ቃል በድንግል ማርያም ማኅፀን ሲፀነስ ከእርስዋ የተነሣው ሥጋ በተዋሕዶ የአብ የባሕርይ ልጅ ሆነ» የሚል ነው።

ታድያ በጎንደር ዘመነ መንግሥት የነዚህ ሁለት ዕይታዎች ክርክር በየዘመኑ እየተነሣ እርስበርስ ሲሸናነፉና በአዋጅ ሲያስነግሩ ኖረዋል።

ለምሳሌ፡

«በአእላፍ ሰገድ ዮሐንስ ዘመን፣ 1672 ዓ.ም. ጥቅምት 10 ቀን የሃይማኖት ጉባኤ ቆሞ ነበርና የቅብዓቶች አፈ ጉባኤ አባ አካለክርስቶስና የተዋሕዶዎች አፈ ጉባኤ አባ ኒቆላዎስ በየበኩላቸው ከመጻሕፍት እየጠቀሱ በንጉሡ ፊት በብዙ ተከራከሩ። በክርክሩም ላይ አባ አካለክርስቶስ ተረትቶ ጳጳሱና እጨጌው አወገዙት። ንጉሡ አእላፍ ሰገድ ዮሐንስም የተዋሕዶዎችን መርታት የቅብዓቶችን መረታት አይተው «ከበረ ሥጋ በተዋሕዶ» ተብሎ አዋጅ እንዲነገር አደረጉ። እርሳቸው ራሳቸው ግን የግል እምነታቸውን ሲገልጡ «እኔ ራሴ በተረቺዎቹ በኩል ነኝ» ብለው ተናገሩ ይባላል።»

እንዲሁም፡ «ቅብዓቶች በአድራር ሰገድ ቴዎፍሎስና በአድባር ሰገድ ዳዊት ዘመን አሸናፊዎች ሆነው ነበርና «በቅብዓት የባሕርይ ልጅ» እንዲባል ዓዋጅ እየተነገረላቸው ደስ የተሰኙበት ጊዜም ነበር።»

ምንጭ፡ ትዝታዬ - ስለራሴ የማስታውሰው (1891–1923)
በመርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ገጽ 112–113

We recommend to visit

A place to learn English easily.

Owner - @Samson_G

Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian

Last updated 1 month, 3 weeks ago

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት ??
@mujaabot

For Advertisement??
@atcads

Last updated 2 months, 1 week ago

NGO, የመንግስት እና የግል ድርጅቶች የስራ ማስታወቂያ እና ነፃ የትምህርት እድሎችን ያገኛሉ ቤተሰበ ይሁኑ ሌሎችንም ይጋብዙ

ለማስታወቂያ @Human133 ላይ አናግሩን
We need promoters
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12

Last updated 1 week ago