Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

Fuad Muna (Fuya)

Description
የኛ እዉነታ የሌሎችን ስጋ ለብሶ ሲቀርብ!
በፅሁፍ ያስነበብኳችሁን በድምፄ ስትሰሙት!

ለአስተያየትዎ
@fuadmubot


ዩቲዩብ ቻናል http://Www.YouTube.com/c/FuadMuna
የፌስቡክ አካውንቴን ለማግኘት www.facebook.com/fuadmuna14
ለፒዲኤፍ ብሎግ www.fuadmuna.wordpress.com
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 2 weeks ago

1 month, 2 weeks ago

አለሁ ለማለት ያኽል!

ሰሞኑን በተከታታይ ኢፍጣር ላይ ፖስት አደርጋቸው የነበሩት ፅሁፎች የተቋረጡት ስልኬ ከተራውሂ መልስ በሚገርም ሁኔታ ስለተሰረቀ ነበር፡፡ ከተራውሂ ስትመለሱ ተጠንቀቁ ቀምቶ የመሮጥ እና በተዘጋጁ መኪናዎች የማምለጥ የስርቆጥ አይነት ተበራክቷል፡፡

መጥፋቴን ልብ ብላችሁ በግል ስልኬ የደወላችሁ መልዕክት የፃፋችሁ ሁሉ በአላህ ስም ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ ወንድም እህት ማለት ያለ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ስንጠፋፋም መፈላለግ ነው፡፡ አላህ ያክብርልኝ! አላህ ጀነትን ይመንዳችሁ!

በነገራችን ላይ የስልኬ ኻቲማ አሪፍ ነበር፡፡ ማለቴ የኑር ሙሰላን የቀጥታ የዚክር መሰናዶ እየሰማንባት ዚክር እያለች ነው የሄደችው 😄😄

አለይከ ረበና ቢሁስኒል ኺታሚ ያረበና ቢሁስኒል ኺታሚ! ይላሉና ጌታችሁን መጨረሻዬን አሳምርልኝ በሉት የስራ ውቡ መጨረሻው ያማረ ነው!

ከዚህ በኋላ ትንሽ ልጠፋ እችላለሁ! በሰላም ነው! አልሀምዱሊላህ አላ ኩሊ ሀሊን! ረመዳኑ ልሂድ እያለ ነው፡፡ አላህ የቀረውን እንድንጠቀምበት ይርዳን! በርቱ!

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@FUADMU

1 month, 2 weeks ago

ረመዳን 9

ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

ከውርደት ሁሉ ትልቁ ውርደት ሰው ፊት ትልቅ ሆኖ አላህ ፊት መቅለል ነው። እናም አላህ ሆይ ባንተ ዘንድ የተዋረድኩ አታድርገኝ በሉት!

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው።

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!
.
@Fuadmu

1 month, 2 weeks ago

የጎደሉ አሉ
ፕሮጀክት 2
ዝግጁ????

ስለምን ይመስላችኋል?
.
@Fuadmu

3 months ago

ስለአስተያየትዎቻችሁ
(ፉአድ ሙና)

የሁላችሁንም አስተያየት አንብቤያለሁ። ሁላቹንም ለአስተያየትዎቻችሁ ከልብ አመሰግናለሁ። በተደጋጋሚ የተጠየቁና ቢመለሱ ተገቢ ናቸው ብዬ ያሰብኳቸውን ጥያቄዎች ከዚህ እንደሚከተለው መልሻለሁ።

¤ እውነተኛ ታሪክ ነው?
ፅሁፉ የእውነት ነፀብራቅ ነው። በቀጥታ ከአንድ ግለሰብ የህይወት ማህደር የተቀዳ ግን አይደለም። የብዙ ትዝብቶች ጥርቅም ነው። ልብወለድ ነው።

¤ በገሀዱ አለም ሴት ልጅ ሳትጋበዝ ይህን ያህል ወንድን ለማማለል ትሞክራለች?
አዎን! በደንብ! ልብወለዱ ላይ ከተጠቀሰውም በላይ የሚሄዱ አሉ።

¤ የራስህ ታሪክ ነው?
የሁላችንም ታሪክ እንደመሆኑ የእኔም ታሪክ ከመሆን አያመልጥም። ታሪኩ በቀጥታ ከኔ ህይወት የተገለበጠ ግን አይደለም።

¤ የሙተነቂቦችን ነገር
ከልብወለዱ በፊት ያሉ ስራዎቼን እንዲሁም መፅሀፌን ያነበበ ለሙተነቂቦች ያለኝን ስሜት ይረዳል። የወከልኩበት መንገድ ስህተት አይታየኝም። ከዚያ ይልቅ ለሁላችንም የማንቂያ ደወል የሚሆን ይመስለኛል። በዚህ ድፍረት ውክልናውን ስጠቀም በእውነት አለም ተመሳሳይ ነገሮች መብዛታቸውን ትረዱኛላችሁ ብዬ እገምታለሁ።

¤ የSexual ነገር ገለፃ ለምን በዛ?
በዚህ ለረበሽኳችሁ በመጀመሪያ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ፅሁፉን እንዲያነብ የተፈለገ ቡድን ስላለ እሱን ቡድን fish ለማድረግ ተግባራዊ የተደረገ ነው። ስልቱ እንደሚረብሻችሁ እንዲሁም የነገሩን ጉዳት በደንብ እረዳዋለሁ። ግን ይህ ልብወለድ እንዲያነበው የተፈለገ Target audience ስላለ እሱን ለማግኘት የተደረገ ነው።

¤ ለምን ፋአድ ሙና የሚባል ገፀ ባህሪ አስፈለገ ?
የልብ ነገር የሁላችንም ታሪክ ነው። ትረካው በአንደኛ መደብ እንደመተረኩ አንባቢው እኔን እያሰበ እንዲያነበው እና የበለጠ Closness እንዲኖረው ለማድረግ የተደረገ ነው። ይኼ በሌሎች ፀሀፍት ዘንድም የተለመደ ነው።

¤ ሁሉም ለምን ስኬታማ ሆኑ? በተለይ ኢክራም እና ሰሚራ?
ኢክራም ስኬታማ መሆን አለመሆኗ አልተገለፀም። ግን የወደደችውን አጥታለች። ሰሚራ ወደ አላህ ለመመለስ የሚሞክር ልብ የነበራት እንስት ናት። በዚህ ሂደት ላይ ላሉ ሁሉ ከሀራም እና ሀላሉ የቱ እንደሚሻል ንፅፅር እንዲሰሩበት የሆነ ነው። ተውበት ካደለን ሁሉም ቆንጆ ይሆናል። ኢንሻአላህ!

¤ ሙና ስለሚባለው የነገርከን እውነት ነው?
እሱ እውነት ቢሆንማ ፈሪሀ የምትባል የቀድሞ ሚስት፣ ኢክራም የምትባል ex እና ኪፋያ የምትባል ማረፊያ በኖረኝ ነበር። ሰው ለታሪኩ ቅርበት እንዲኖረው የገባ ነው። ገለፃው የተፈበረከ ነው።

¤ በየቀኑ የሚሰጡህ አስተያየቶች የታሪኩ ይዘት ላይ ተፅዕኖ ነበራቸው?
የታሪኩ መዋቅር ቀድሞ የተጣለ ስለነበር የሚሰጡት አስተያየቶች ያመጡት ለውጥ አልነበረም። ሆኖም በጣም ለመፃፍ የሚያነሳሱ ነበሩ።

¤ ፈሪሀ "የኔ ጌታ" ብላ ባሏን መግለጿ እንዴት ይታያል?
የኔ ጌታ የሚለው ቃል አስተዳዳሪነትን የሚጠቁም ነው። በሀገራችንም ተግባራዊ የሆነ፤  በቋንቋ ስርዓታችን ውስጥ የነበረ ቃል ነው። አንዳንድ ሰፈር የተውሂድ ዳዕዋ የማህበረሰቡን ተጨባጭ ሳይረዳ ወደ ሀይማኖታዊ ትርጓሜ ወስዶት ይመስለኛል። በአረብኛውም ይህ አጠቃቀም አለ። ክፍለሀገር ሄደህ ከብቶች እያሳዩህ «የዚህ ጌታ ማነው?» ብለው ቢጠይቁህ «አላህ!» ብለህ አትመልስም። ምክንያቱም ጥያቄያቸው ባለቤቱ ማነው? የሚል ነው። የፈሪሀም ከዚህ አንግል ነው። የተውሂድ ጥያቄም የሚነሳበት አይደለም።

¤ ዘፈኖቹን ከየት አወቅካቸው? ለምንስ ገቡ!
የዘፈኖቹን ግጥሞች ያስገባሁት አንባቢ relate እንዲያደርግ ነው። በዚህ ወንጀል ውስጥ ያሉ ሰዎች ሲያነቡት በደንብ ወደ ራሳቸው ህይወት ያቀርባቸዋል። እኔ የፃፍኩት ከፅሁፉ ጋር የሚሄዱ ዘፈኖችን ሰርች በማድረግ ግጥሞቹን ከአንዳንድ ሳይቶች በማግኘት እንዲሁም በዚያ መልኩ ያላገኘኋቸውን እየሰማሁ በመገልበጥ ጭምር ነው። ዜማቸውን ለማያውቅ ግጥም ናቸው። ለሚያውቅ ዘፈን ናቸው።

ከአስተያየትዎቻችሁ ተደጋጋሚዎቹን መልሻለሁ። ቅዳሜ ምሽት ከ3:00 ጀምሮ በቴሌግራም ቻናሌ ላይ ባለኝ ላይቭ መሰናዶ ላይ ሌሎች ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ይቻላል። በሰፊውም ለመመለስ ይመቸኛል።

ቅዳሜ 3:00 ላይቭ እንገናኝ! ኢንሻአላህ!
.
@Fuadmu
@Fuadmu

3 months, 1 week ago

አስተያየት መዘርገፊያ

ሁሌም የምለው አንድ ነገር አለ። የእኔ አንባቢዎች ቁጥሮች አይደሉም። ቤተሰቦች ናቸው። በርካታ ኸይር ስራ ላይ በአጅር የተሳሰሩ፤ በተለያዩ ፅሁፎች የተጋመዱ ቤተሰቦቼ ናቸው።

እንደሁልጊዜው ስለ የልብ ነገር የተሰማችሁን ለቀጣይ የሚጠቅም አስተያየትና ቢመለስልን የምትሉትን ጥያቄ ፃፉልኝ። ስትፅፉ ብትችሉ በአማርኛ ታይፕ ቢሆን መልካም ነው። ካልሆነም ግልፅ በሆነ መልኩ ክተቡት። የሁላችሁንም አነባለሁ። አንብቤም ፖስት በማድረግ ምላሽ የሚያስፈልጋቸው ላይ ምላሽ እሰጣለሁ።

የኛ እውነታ የሌሎችን ስጋ ሲለብስ!

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@Fuadmu
@Fuadmu

3 months, 1 week ago

የልብ ነገር ሲደመደም
(ፉአድ ሙና)

የልብ ነገር የእኛ ታሪክ ነው። በሌሎች ስጋ ውስጥ ተቀርፆ የቀረበ የእኛ የሁላችንም ታሪክ! «እኛ እኮ!» እያልን ራሳችንን ከሰቀልንበት የውሸት ብፅዕና አውርዶ የደረስንበትን የወንጀል ውድቀት የሚያሳይ የአኗኗራችን ነፀብራቅ ነው። ዛሬ የፃፍኩትን ይህን ታሪክ ከ5 አመታት በፊት ተፅፎ ባነበው ተጋነነ ብለው ከሚከራከሩት ውስጥ በሆንኩ ነበር። በዕድሜያችን ልክ የማወቅ ተጋላጭነቱ የሚኖሩንን አኗኗሮች አሉ። የልብ ነገር እንደዚያ ነው።

የልብ ነገር የወንጀልና የተውበት ጉዳይ ነው። ብዙዎቻችን እያለቀስንለት ያለው የእኛ ገመና ነው። እዝነቱና ሲትሩ ፅንፍ የሌለው ጌታችን ምስጋና ይገባው። ቆመን እንሄዳለን። ሲትሩ ባልነበረ ለራሳችን ማዘን የምንችል አልነበርንም። አላህ ካለንበት የወንጀል ትብታብ ነፃ ይበለን። ከመረጣቸው ባሮቹም ያድርገን።

ይህን ፅሁፍ ስፅፍ ከጎኔ የነበራችሁትን አንባቢዎቼን ከልብ አመሰግናለሁ። ያለእናንተ ድጋፍ መፅናቱ ከባድ ነበር። ለፅሁፉ ያላችሁ ጉጉት እኔም ማቋረጥን እንድፈራና 25 ቀናትን ያለማቋረጥ በኸልዋ እንድቆይ አድርጎኛል።

የልብ ነገር Live Fiction ነበር። እንደከዚህ ቀደሙ ተፅፎ አልቆ እየተፖሰተ የነበረ ሳይሆን፤ በየቀኑ እየተፃፈ የሚለቀቅ ነበር። ይህ ለደራሲው እጅግ ፈታኝ የሆነ አፃፃፍ ነው። ወደ ኋላ ተመልሼ ላስተካክል ቢል አንባቢ ጋር ደርሷልና ምንም ማስተካከል አይችልም። እስካሁን ካስነበብኳችሁ ድርሰቶች በዚህ የLive fiction ዘውግ የተፃፉት ነጫጭ ጥቁረቶችና የልብ ነገር ናቸው። ለእኔ ቢከብድም አሪፍ ትግል ነበር።

አላህ ሳይቆይ ከዚህ በተሻለ ልብወለድ የምንገናኝ ያድርገን!

በቀጣይ አስተያየት የምትፅፉበት ፅሁፍ እለቃለሁ።

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@Fuadmu
@Fuadmu

3 months, 1 week ago

«ፉአድ ሙና ነኝ።»
ጠብ እርግፍ አለችልኝ። እህቷ ነበረች። ተሰናብቼያት ዘጋሁት። ለምን ስልኩን እንደያዘችው እንኳን አልጠየቅኳትም። ወደ ቀበጧ ነጋዴ ደወልኩ። ወደ ታናሽየዋ!
«ድመቴን ገዝተህልኝ እንዳይሆን ..... » ተፍለቀለቀች።
«አዎ ነገ ምናምን ይደርሰኛል። ይዤልሽ እመጣለሁ።»
«እና እንዴት ነህ?»
«አለሁልሽ! ሚስቴ እንዴት ናት?»
«የምናባህ ሚስት ፈተሀት የለ እንዴ? ያልነገረችኝ መስሎህ ነዋ?»
«እሺ የቀድሞ ሚስቴስ?»
«አሁን ልክ ነው! ደህና ናት ከማጂላን ጋር ሳትጋባ አትቀርም!»
«በሀገርኛ ሲተረጎም?»
«ሀገር ለሀገር እየዞረች ነው።»
«ለመዝናናት ነው?»
«ኧረ International expert ሆናልሀለች።»
«ውይ ደስ ይላል በጣም! ስልኳን ስደውል እኮ ትልቋ አነሳችው።»
«አዎ ሰገጤው ነው የያዘው¡» ተሳሳቅን። ለታላቋ የሰጠቻት የኮድ ስም ነው።
«እና አሁን የት ሀገር ናት?»
«ዛሬ ማድሪድ መሰለችኝ .... ትንሽ ቆይቶ ሌላ ሀገር መሄዷ አይቀርም። ወያላ በላት!» ትስቃለች።
«በምንድነው የምትደዋወሉት?»
«ዋትሳፗ ይሰራል ..... በሱ ነው! ናፈቀችህ እንዴ?»
«በጣም! የምር በጣም! እኔ እዚህ መስላኝ ነበር እኮ!»
«የጣልከው ቦታ ማን ቁጭ ይላል ብለህ ነው?»
«ነገረኛ ሆነሻል! የምር ላገባት እፈልጋለሁ!»
«እንደገና .... ፍቅር እንደገና .... እንደገና ....መውደድ እንደገና .... እንደገና ..... አይገኝምና! ሲል አልሰማኸውም ማህሙድን?» አዜመችው!
«አንቺ አትለምኚልኝም?»
«እኔ እወድሀለሁ ፉዬ! ብትጋቡ ደስ ይለኛል። ግን ጀለስ ሳያከር አልቀረም። ይቅርታ ብሎህ ምናምን ገግመህበት አልነበር።»
«ማን ፋዘር ነው?»
«አዎ .... ብቻ እሷ ከፈለገች ግን እንቢ አይላትም። አንተ እሷ ላይ ወጥር! እሷ ከተስማማች ባባን በደካመ ጎኑ መግባት ትችላለህ።»
«ምንድነው ደካማ ጎኑ?»
«ሽማግሌ ሰብስበህ .... ሰንጋ ጭነህ .... ጫት ደግሞ በዛ አድርገህ ይዘህ መምጣት ነው! እና አንድ 20 እሽግ ቸኮሌት!»
«ቸኮሌቱ ላንቺ መሆኑ ነው?» ሳቅኩኝ።
«አዋ ኮሚሽኔ!»
«እሺ በቃ!»
«ሀዬ ይቅናህ!»
ተሰነባበትን። ወደ ዋትሳፕ አካውንቴ ገባሁ። ፌሪ ቦልካኛለች። ደነገጥኩ። ፌሪ እኔን? ለምን አስፈለገ መቦለክ? መልሼ ወደ እህቷ ደወልኩ።
«እሺ ሰውየው!»
«ስሚ ብሎክ አድርጋኛለች።»
«ብሎክሽን አጠጣችሻ¡» ሳቋን ለቀቀችው።
«እስኪ ካንቺ ጋር ያወራነውን ንገሪያት! ደውይልኝ ብሏል በያት።»
«እንዳያሳስብህ ..... ባይሆን ድመቴን ይዘህልኝ ና!»
ተሰነባበትን።

ትናንት እንደፈለጋችሁ ታገኙት የነበረን ሰው .... ከእቅፋችሁ የማይጠፋን ጠረን .... ተለመነኝ ሲላችሁ የነበረን ነብስ .... ከጊዜ በኋላ ማግኘት ሰማይን የመንካት ያህል ሊርቅ ይችላል። አጠገባችን ያሉ ሰዎችን እናክብራቸው .... የሚገባቸውን ክብር እንስጣቸው .... እንንከባከባቸው። አንጉዳቸው! ነገ ከስህተታችን ስንመለስ እንደምናስበው በእጆቻችን ርቀት ልክ ላይኖሩ ይችላሉ። ፌሪ ማለት እኮ የኔ ጌታ የምትለኝ ሴት .... አለቃዬ ብላ ራሷን ያወረደችልኝ ፍቅሬ ነበረች። አንተ ካልክ ይሁን የምትል ውድ ነበረች። ዛሬ ብሎክ? ይገባኛል። ግን ለምን? የምጨቃጨቅ ሰው አልነበርኩም። መፋታት ማለት መጣላት አይደለም ተባብለን ነበር። በእርግጥ ሴቶች የሚሉትና የሚያደርጉት አንድ አይደለም። ተጎድታ ነበር። አሁን ሚስቴ የነበረችውን ሴት ድምጿን እንኳን መስማት አልቻልኩም። ድንገት ቴሌቭዥኑ ትዝ አለኝ። ከፈትኩት። ከዩቲዩብ ላይ ኢሜይል አድራሻዋን ወስጄ ፃፍኩላት። ምንም ምላሽ የለም። ዘግይታ ካየችው ትመልስልኝ ይሆናል ብዬ ተፅናናሁ። ዩትዩቡ በእሷ ኢሜይል አድራሻ ስለሆነ የምትሰማቸውን ሙዚቃዎች ያሳየኛል። ለመጨረሻ ጊዜ የሰማችውን ሙዚቃ ከፈትኩት። ማዲንጎ ነበር። ድሮ ይኼን ሰውዬ ስታዳምጠው ሰምቼ አላውቅም።
«ካምናው ካልተማርኩኝ ተመልሼ፣
እኔም፣ ዛሬም ከደገመኝ፣
እርምን አላውቅ ብዬ፣ እንደገና፣
አዬ ሰው ማመን፣ ካመመኝ፣
አሀ ሞኙ ልቤ፣ አሀ ያልታደለ፣
አሀ ምን ሊፈይድ፣ አሀ ተታለለ?»
ክው ብዬ ቀረሁ! ስለኔ ያስገጠመቻቸው ስንኞች መሰሉኝ። ጆሮዬን ቀስሬ ግጥሙን መስማት ጀመርኩ።
«የካብኩት ተናደ፣ ባለማወቅ፣
ስገነባው ፈርሶ፣
ባፀዳው፣ ቆሸሸ እንደገና፣
የፀዳው ደፍርሶ!
ወርቅ አይደለ ነገር፣ አይጣራ፣
በእሳት አልፈትሸው፣
የቸገረ ነገር፣ ግራ ገባኝ፣
በምን ይለያል ሰው!»
እንባዬ አይኔን ሞላ። ሺህ ጊዜ አፅድታኝ፤ ሺህ ጊዜ ቆሽሼያለሁ።
«ቀድሞ አለመጠንቀቅ፣
ጥንቱን አለመፍራት፣
ኃይለኛ ዱላ ነው ያረፈብኝ፣
ማገገሜን እንጃ፣ ምን ተሻለኝ?»
ከዚህ በላይ መስማት ከበደኝ። ዘጋሁት። የምትሰማቸው ሙዚቃዎች እንኳን እኔ ስለፈጠርኩባት ቁስል መሆናቸው ከፋኝ። እያስታወሰችኝ እንደሆነ ሳስብ ደስም አለኝ። እያነቡ እስክስታ አይነት ስሜት አለው። ሳላስበው እንባዬ ከአይኔ መውረድ ጀመረ። ናፈቀችኝ። ቤቱ ውስጥ ያለው እቃ በሙሉ ከእሷ ጋር ምን ስንሆንበት እንደነበር አፍ አውጥቶ አወራኝ። ብዙ ወጪ የወጣበት እኔና ኢክራም ያዘዝነው አልጋ መጋዘን ተቆልፎበታል።

ከምሽቱ 2:00 ሲል ሰሚር መጣ። ወደ ቤት ሲገባ እንዲጨብጠኝ እጄን ዘረጋሁለት። ፊቱ ላይ ድንጋጤ አለ። ክው ብሏል። እጁን ወደ ኋላ እየደበቀኝ በትከሻው ብቻ ገጨኝ። ጣቶቹ እንደቀፈፉት ገባኝ። ወይኔ ሰሚር!
«ሂድና ሻወር ቤት ታጠበው!» ሳቅኩኝ።
ከሻወር ቤት ጣቶቹን እያሸተተ መጣ።
«አንተ የእጅ መታጠቢያው ሳሙና ጠረኑ በጣም ደስ ይላል።»
«መሪዬን በእሱ እጅህ አልያዝከውማ?»
«አልነካሁትም .... በፎጣ ነው የያዝኩት¡»
ክው ብዬ ቆምኩ!
«ሰሚራ ጋር አልነበር እንዴ የሄድከው?»
«ነበር!»
«እና?»
«አብረን እንሂድ እያልኩህ!»
«ሆነ?»
«አይ የፒያኖ ሰዓት ብቻ!»
«ያምሀል እንዴ? የአህመድ ሚስት እኮ ናት!»
«የደረሰብኝን ዊስዋስ አላየህም!»
«ምንስ ብታደርግህ? ሰሚራን?»
«በፒያኖ ያለፈው ስንት ታግያት ነው። ይኼ እንዳይሆን ነው ና ያልኩህ!»
«ከዚህ በኋላ አጠገቧ እንዳትደርስ!»
«ድረስስ ብትለኝ?»
«አሁን አህመድ ፊት በምን ድፍረት ትቆማለህ?»
«እሱ እኔ ፊት በድፍረት ቆሞ አይደል?»
«ልጅቷ ምንድነው ፍላጎቷ?»
«ሁለት ማንነት ነው ያላት! ጥሩ ሴትነት ሲሰማት አርፋ ከባሏ ጋር ትቀመጣለች። ባለጌው እሷነቷ ሲቀሰቀስ እኔ ጋር ትደውላለች።»
«ሴት ማለፍ አትችልማ?»
«አህመድ ነው እኮ ፋውል የገባው! እኔ አይደለሁም!»
«ብትነግረውስ እሷ?»
«ማገጥኩ ብላ?»
የሁለታችንም ስልክ እኩል ጠራ።
«ማነው?»
«ሰሚራ! አንተስ ጋ ማነው?»
«አህመድ!»
ግራ ተጋብተን ስልካችን ላይ አፈጠጥን!

ይቀጥላል!
.
@Fuadmu
@Fuadmu

3 months, 1 week ago

የልብ ነገር
ክፍል ሀያሁለት
(ፉአድ ሙና)

ሳብ ሳበውና
የገፋኸውን፣ በእሳት በአለንጋ፣
እንደለመድከው
ለሊቱን ሙሉ፣ ስታለቅስ አንጋ!

አልቅስ አልቅሰው
አይወጣለትም፣ የወዳጅ ልቡ፣
አያስኮንንም
የገፋኸውን፣ ዞሮ ማሰቡ።

ሁሉም ምዕራፍ መደምደሚያ አለው። ለእነሱ ብለን አላህን ያስቀየምንላቸው ሰዎች ጥለውን ይሄዳሉ። ኢክራም ቤተሰቧን ላለማስቀየም ስትል ተወችኝ። አልተቀየምኳትም። ይኼ የአላህ ሱና ነው። የአላህን አጥር ዘለን የቀነጠስነው እሸት ጊዜ ጠብቆ ያንቀናል። አትተወኝም ብዬ ስተማመንባት የነበረችው ሴት .... ኢክራም እንኳን አልዋጥ አለች። ሚስቴን የተውኩላት እንስት .... እንደቀልድ ቻው አለችኝ። ልቤን በዚህ ልክ እሷ ላይ ማንጠልጠል አልነበረብኝም። የደስታዬን ቁልፍ ጠቅልዬ እጇ ላይ ጥዬው ነበር። ሰው ናትና ደስታዬን ይዛው ሄደች። ተደገፍኳት .... ሸሸችኝ። አሁን ከተራራ ላይ እየተንከባለለ እንዳለ ሰው አይነት ስሜት ይሰማኛል። ምናልባት ጌታዬ በፈሪሀ እጅ ከመሰበር ይታደገኝ ይሆናል። ሲደላን ትዝ የማይለን አላህ .... የመከራችን አዝማች ነው። ጭራሽ አማክረነው ያመፅነው ይመስል «ግን ለምን?» ብለን እናማርረዋለን። ለእሱ ፍቅር በልባችን ውስጥ የተከለለው ቦታ ላይ የፍጡር ፍቅር ሞላንበት። ልባችን ውስጥ ለእሱ የሚሆን ፍቅር ስለጠፋ ስናምፀው ቅንጣት ታህል አልከበደንም። ለወደድነው ሰው ደስታ የጌታችንን ትዕዛዝ ተረማመድንበት። ያለ አንዳች የፍርሀት ስሜት ‘ረጋገጥነው!

የአላህ ፍቅር የሌለበት ልብ እንዴት ደስተኛ ሊሆን ይቻለዋል? ኢብኑልቀይም «ያለምንም ጥርጥር በአለም ላይ ትልቁ የእርካታ ምንጭ አላህን የማወቅና የማፍቀር ደስታ ነው። አላህን ማወቅና ማፍቀር በዚህች አለም ላይ አንድ ሰው ሊያስተናግደው የሚችለው የደስታ ጫፍ ነው። በተቃራኒው ሌላው አለማዊ ነገር የሚሰጠው ደስታ ከባህር ላይ እንደምትወሰድ ጠብታ ያህል ያነሰ ነው። እጅጉን አስደሳች የህይወት ጎን አላህን መውደድ ሲሆን በጀነት ውስጥ ትልቁ የደስታ ጣራ ደግሞ አላህን ማየት ነው።» ይላሉ። በእርግጥ በወንጀል የሚሸመትን ደስታ ፀፀት ይከተለዋል። በሰዓቱ አስደሳች ቢመስልም ካለፈ በኋላ ለዘላቂ ቁጭት ይሰጣል። ሲልም እንደኔ ቤተሰብ ያስበትናል። ከሚወዷት ሚስት ያፋታል። አላህም በእርሱ ፍቅር ላይ ማጋራትን አስመልክቶ እንዲህ ይላል።
«وَمِنَ النَّاسِ مَن يَتَّخِذُ مِن دُونِ اللَّهِ أَندَادًا يُحِبُّونَهُمْ كَحُبِّ اللَّهِ ۖ وَالَّذِينَ آمَنُوا أَشَدُّ حُبًّا لِّلَّهِ ۗ
ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን (ጣዖታትን) አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ አልሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡»
ለአላህ የምንፈጥራቸው ባላንጣዎች የተጠረቡ ሀውልቶች ብቻ አይደሉም። በአላህ መሻት እና በነብሳችን መውደድ መሀል ያስበለጥናቸው የስሜት ጣዖቶቻችን ናቸው። ልማዳችንን ጣዖታችን አድርገን ቀርፀናል። በስሜታችን እየተሸነፍን የአላህን ፍቅር ገፍተን ለወንጀል ጣዖታችን ሰግደናል። አሰጋገዱ ግንባር መድፋት አይደለም። የአላህን ክልከላ መጣስ ነው። የምር ባመንን ግን ከስሜታችን የጌታችን ፍቅር በቀደመብን .... ዝሙትን ያህል ወንጀል ላይ ከመውደቅ አላህን ያስቆጣዋል ብለን በተሰበሰብን .... ነበር። አላህን አላፈቀርነውም። የደህንነት ካሜራ አይነት ቦታ የሰጠነው ይመስላል። የሚያይ ግን የማይቆጣ አድርገን ተረድተነዋል። ከአላህ ፍቅር ጎድለን ነብስ የሌለው ተንቀሳቃሽ በድን ሆነናል።

የአላህ መልዕክተኛ (ሰዐወ) እንዲህ ይላሉ። «ሶስት መልካም ባህሪዎች አሉ። እነሱን የተላበሰ የኢማንን ጥፍጥና ያገኛል። እነሱም አላህና መልዕክተኛውን ከእነርሱ ውጪ ካሉ ነገሮች ሁሉ አብልጦ መውደድ፣ ሰውን ለአላህ ብቻ ብሎ መውደድ፣ አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ከመራው በኋላ ወደ ክህደት መመለስን እሳት ላይ መወርወርን ከሚጠላው በላይ መጥላት ናቸው።» አላህን ስለመውደድ ሲነሳ አራተኛዋ ሴት ሳትነሳ አታልፍም። ራቢዓተል አደዊያ .... የኢራቋ እንስት .... የበስራዋ ፍሬ .... የቤተሰቦቿ አራተኛ ልጅ .... የቲሟ ህፃን .... ባርያዋ ወልይ .... መንፈሳዊዋ ሴት .... አፍቃሪዋ! በሂጅራ አቆጣጠር አንድ መቶ ላይ ተወለደች። የአስር አመት ህፃን ሆና እናት እና አባቷን ወደ ቀጣዩ አለም ሸኘች። በባሪያነቷም በጨዋነቷም ጊዜ የጌታዋ አፍቃሪ ነበረች። በአንድ ወቅት «አላህን ትወጂዋለሽ?» ተብላ ተጠየቀች። «አዎን እንዴታ!» ስትል መለሰች። «ይህ ማለት ሰይጣንን ትጠይዋለሽ ማለት ነው?» ጠያቂዎቹ ቀጠሉ። ራቢያም «ለአላህ ያለኝ ፍቅር ሸይጧንን የመጥላት ድርጊት ውስጥ ከመሳተፍ ይከለክለኛል።» ስትል መለሰች። የራሷ የሆኑ በርካታ ጥበባዊ የአምልኮ ስንኞች ተመዝግበውላታል። ከእርሱ ውስጥ ቀዳሚው «ጌታዬ ሆይ! አንተን የምገዛህ የጀሀነም እሳትን ፍራቻ እንደሁ .... በጀሀነም ለብልበኝ። አምልኮዬ ጀነትህን በመከጀል እንደሆን ከጀነትህ አቅበኝ። ግን አንተን የምገዛህ ስላንተ ብቻ ብዬ ከሆነ ዘላለማዊ ውበትህን አትከልክለኝ።» ይል ነበር።

ቀበጧ ሴት .... ውቧ ንግስት .... ባለሂጃቧ ፍቅሬ ..... ቻው አለችኝ። ቻው! ከሰሚር ጋር ከአዳራሹ እንደወጣን ወደ ፈሪሀ ደወልኩ። አልተነሳም። ብትኮራብኝም ሲያንሰኝ ነው። ለፈፀምኩባት ክህደት አስራ ብትገርፈኝ አይበዛብኝም። ወደ መኪናችን ተመለስን።
«ስማ ፉዬ!»
ወደሱ ዞርኩ።
«ዛሬ ከሰሚራ ጋር ቀጠሮ ነበረን።»
«ማናት ያቺ?» ወደ መኪናችን አንዲት የሰርገኛ ልብስ የለበሰች እንስት እጇን እያወዛወዘች እየመጣች ነበር። ዞር ብሎ አያት።
«የሪዞርቱ ፍሬ ናት!»
ከመኪናው ወርዶ አወራት። ወይ ሰሚር! ወደ መኪናው እየተመለሰ «የኢክራም ዘመድ እኮ ናት!» አለኝ።
«ምንድነው የምትልህ?»
«አመሰግናለሁ ነዋ!»
«ለምኑ?»
«አንተን ይዤህ ስለመጣሁ?»
«እኔ አይደለሁ እንዴ ይዤህ የመጣሁት?»
«እሱ አንተን የመሰለህ ነው። ኢክራም እንዳትቀር የማድረግ ሀላፊነቱን ለእኔ ሰጥታኝ ነበር። በነገራችን ላይ ይህቺን ቃጭል እየደወልኳት ነው።»
«አንተ የማትደውለው አለ እንዴ .... ተንከሲስ!»
«በቃ አሁን ፈሪሀን መልሰህ አግባት!»
«ከሰሚራ ጋር ቀጠሮ .... እያልከኝ ነበር።»
«አዎ አብረን እንሂድ ልልህ ነበር?»
«ለምን?»
«በቃ ዛሬ ለምን አህመድን እንዳገባችው እንጠይቃት!»
«አስፈላጊ ነው?»
«አዎ በቃ ይለይለት!»
«ዛሬ ደክሞኛል። ወይ አንተ ጠይቃትና ትነግረኛለህ።» ቤት ገብቼ ፈሪሀን እስካወራት ቸኩያለሁ። ቤት እንደደረስን መኪናዬን ይዞ ወጣ።
ልብሴን አወላልቄ ፈሪሀ ጋር መቀጥቀጥ ጀመርኩ። ስልኩ ተነሳ።
«ፌሪ ....»
«ማነህ?» የሌላ ሴት ድምፅ ነበር።
«ፌሪ የለችም?»
«ውይ የለችም። ስልኳን እኔ ነኝ የምይዘው!»
«አንቺ ማነሽ?»
«ደውለህ ማነሽ?»
«የሰው ስልክ ነው የያዝሽው .... ለዚያ ነው።»
«አንተ ማነህ?»

3 months, 1 week ago

ምንድነው የተፈጠረው? ወይኔ ድንጋጤዬ! ሀዘን ሲከብድ እንዲህ ነው። የተባለ ያልተባለውን እየደባለቀ ልብን ሰላም ይነሳል። የፌሪ ታናሽ እህት ናት። ቀበጧ ነጋዴ! የቤታቸው ታናሽ እሷ ናት። ከእኔ ጋር በጣም ቅርብ ነን። ይህ ድንጋጤ የተፈጠረው ፌሪዬን ምን ያህል እንደምወዳት ሊያስታውሰኝ ይሆን? እንኳንም ሆነ! እንኳን አለቀስኩ። የለቅሶዋን ከፊል ተጋራኋት።
ወደ ውሳኔዬ ልሂድ! ወደ ፌሪዬ! ወደ ፍቅሬ! ለመደወል ስልኬን አነሳሁ። ግን ደግሞ ኢክራምን መክዳት እንዳይሆንብኝ ሰርጓ እስኪያልፍ ድረስ መጠበቅ አለብኝ።

ሰሚር ከእጄ ላይ ካርዱን ተቀብሎ ተመለከተው።
ካርዱን ከትከሻዬ ጋር እያጋጨ «እንሄዳለን!» አለ።
«ወዴት?»
«ወደ ሰርጉ ነዋ!»
«የምርህን ነው?»
«ጠሪ አክባሪ ነው¡»
«አትቀልድ!»
«ሌላው ቢቀር ኢክራምን እናያታለን።»
ተስማማን። ሰርጉ ቅዳሜ ቀን ነበር። ቀኑ ሲደርስ ሙሽራ መስለን ወደ ሸራተን ነዳን። ስንገባ ከጋሽ በርጊቾ ጋር ተገጣጠምን። ምንም ያልተፈጠረ ይመስል አክብሮ ሰላም አለኝ። ቦታችንን ይዘን እንደተቀመጥን ሙሽሮች መግባት ጀመሩ። በጣም ግራ ገባኝ። እኔና ሰሚር መተያየት ጀመርን። ሰውየው ሱፉን አሳጥሯል። የኢክራም ፊት ላይ የሀዘን ድባብ አይታይም። ፈገግ ብላ ታወራዋለች። ስልጥኛ ዘፈን ተበርግዷል። እናቶች፣ አባቶች፣ ወጣቶች፣ ህፃናት ሁሉ እየዘለሉ ነው። ኢክራምና ሙሽራውም በሚዜዎቻቸው ተከበው ይነጥራሉ። እንደሁሉም ዘር ስልጤም በራሱ ዘፈን መጨፈርን ሀላል ያደርገዋል። ዘፈን መስሎ የሚሰማቸው አማርኛ ዘፈን ይመስለኛል። ለነገሩ እኛም ትግሬዎቹ ብንብስ እንጂ አንሻልም። አለመጨፈር በትግሬ ሰርግ የሚታሰብ አይመስለኝም። ባይሆን ዘፈኑ በሙሉ ትግርኛ መሆን አለበት። ዘረኝነቱም ተመሳሳይ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ከጥቂት ብሔሮች ውጪ አብዛኛው ዘረኛ ነው። በተለይ ደግሞ ሀብታም ቤተሰብ ሲሆን ዘረኝነቱ ይከብዳል። ጎላ ብለው ከወጡት ብሔሮች መካከል አደሬ በዘረኝነት የወርቅ ሜዳሊያውን የሚወስድ ይመስለኛል። ትግሬ የብር፣ ስልጤ ደግሞ የነሀስ ሜዳልያ! ልጆች ከተዋደዱ በኋላ አይሆንም ብሎ መከልከል ማለት በሀራሙ እንዳሻችሁ እንደማለት ነው። አብዛኛው በእነዚህ ዘር ያሉ ወጣቶች የራሳቸውን ዘር የሚያገቡት ከሌላ ዘር ፍቅረኛቸው ጋር በእንባ እየተለያዩ ነው። ቤተሰቦች እነሱ ጋር ያለውን ዘረኝነት ወደ ልጆቻችን ካላጋባን ብለው ግብግብ የገጠሙ ይመስላል። እርስበርስ ብንከባበርና ስልጣኔው ኖሮን ነብያችን ቆሻሻ ካሉት ድርጊት ብንርቅ ሸጋ ነበር። አላህ ዘር የሰጠን እንድንተዋወቅበት እንጂ እንድንለያይበት አይደለም። ይህን ስል ግን በሁሉም ብሔሮች ውስጥ አላህ የባረካቸው ከዘረኝነት ቆሻሻ የፀዱ ቤተሰቦች የሉም ማለት አይደለም። በጠራናቸው ዘሮች ውስጥ ብዙም ባይሆኑ ከሌላ ዘር ጋር የተዛመዱ አይጠፉም።

ኬክ ተቆረሰ! ፅዋ ተነሳ! ኢክራም አየችኝ .... ፈገግ አለችና በእጇ ቻው አለችኝ። ቻው ፉአድ .... ቻው! አስተናጋጁ ከሙሽሪቷ የተላከ ነው ብሎ ወረቀት ሰጠኝ። ከፈትኩት። በኮምፒዩተር የተፃፈ ነው። አዘጋጅታው የመጣችው መሆኑን ተረዳሁ።
«ጥሪዬን ተቀብለህ ስለመጣህ ደስ ብሎኛል። ላደረግክልኝ ሁሉ አመሰግንሀለሁ። በህይወቴ ቤተሰቤን አስደስቼ አላውቅም። ካስደሰታቸው .... ካንተ ጋር ያለኝን ግንኙነት አቁሜ ያሉትን እያገባሁላቸው ነው። እንደከዳሁህ አይሰማህ። ወደ ፈሪሀ ሂድ። ትዳርህ እሷ ናት። የሰው ሀቅ መንጠቅ ይብቃኝ! የራሴን ሀቅ ልሞክር! እወድሀለሁ አልልህም! ምክንያቱም በደንብ ታውቀዋለህ። ቻው! ፉዬ ቻው!» ከፅሁፉ ስር የከንፈሯ ምልክት በሊፒስቲኳ ታትሟል።
ቀና ስል ተያየን። እጇን አየር ላይ ሳመችና በስንብት አወዛወዘችልኝ። እኔም እጄን ስሜ አወዛወዝኩ። ቻው የትልቁ ወንጀሌ መጀመሪያ! የትልቁ ወንጀልሽ መጀመሪያ .... ይወድሻል .... ቻው!
ከሰርጉ እንደወጣን ያለምንም ማንገራገር ወደ ፈሪሀ ደወልኩ። ወደ መጀመሪያዋ ፍቅሬ .... ሁሉን ወደ ጀመርኩባት የፍቅር አድባር! ከዚያ ሁሉ መገፋት በኋላ እሺ ብላ ትቀበለኝ ይሆን? ልቤ በጣም እየመታ ነው።

ይቀጥላል!
.
@Fuadmu
@Fuadmu

3 months, 2 weeks ago

«ለምን?»
«አያስፈልግም ብሎን ነው፤ እስኪ መላ በሉት አሉኝ ስጠይቃቸው!»
«ለምንድነው የማያስፈልገው? ከሷ ቤት የሚመጡት ሴቶች እኛን ሊበሉ ነው?»
«ቢበሉንማ ሙድ አለው¡» ሳቁን ለቀቀው።
«ግን ቁምነገር ምንልሁን ብሎ ነው? ገንዘብ አለው! ምንድነው ችጋራም ችጋራም የሚጫወተው?»
«ሞዴሌ ምናምን ኡስታዝ ቤት ምንም አልተዘጋጀም ነበር አለ።»
«ይኼ አበዛው የምር! ኡስታዙ ጠብሾት ባያዘጋጅ ...... የሚኮረጅና የማይኮረጅ ነገር አይለይም እንዴ?»
«ውረድና የሆነ ነገር በለው ቤተሰቦቹም ሊያሳፍረን ነው ብለው ደብሯቸዋል።»
ከመኪናው ወርጄ ወደ አህመድ ቤት ገባን። «አህመድ!»
ደንግጦ ቀና ብሎ አየኝ።
«ምግብ እስኪ ስጠኝ .... »
ተወዛገበ። ወደ እናቱና እህቶቹ ዞሮ ሲያይ በእጃቸው የለም አሉት። በነገራችን ላይ ይህቺን ቀመር ሰሚሬ ሰርቷት ነው።
«ውይ የለም መሰለኝ .... ደውዬ ልዘዝልህ!»
«እንዴት በሰርግ ቀን ምግብ የለም? ያምሀል እንዴ?»
«የምወደው ኡስታዝ እኮ .... »
«የምትወደው ኡስታዝ ገደል መግባት ይችላል። ለቅሶ ላይ እንኳን እኮ ምግብ አይጠፋም። ለምን ስለራስህ ስሜት ብቻ ታስባለህ? ቤተሰቦችህን ለምን ታሳፍራለህ? ብር የለህም? ከሆነ ንገረኝ እኔ ልክፈልና ይሰራ!»
«ኧረ አይደለም እኮ ፉአዴ .... »
መልስ ጠፋው!
«አንተ ጭንቅላት አለህ አይደል እንዴ? በኡስታዝህ ሳይሆን በራስህ ጭንቅላት አስብ! ኡስታዝህ ቸግሮት ምግብ ባያሰራ እኛን በረሀብ ልትደፋን ነው እንዴ? ተጨባጭ የሚባል ነገር አለ እኮ! ደግሞ ብትደግስና ሰው ብታበላ ሰደቃ አይደል እንዴ? አጅሩን አታስብም? አላህ በኡስታዝህ ጭንቅላት እንድታስብ ቢፈልግ ለምን ጭንቅላት ሰጠህ?»
ጓ ብዬ ወደ መኪናዬ ወጣሁ። ሰሚር ተከተለኝ።
ሰሚሮ «ስማ ይኼ ልጅ ግን ኡስታዜ አካልጉዳተኛ ነው ብሎ እግሩን እንዳይቆረጠው ፍራ! እኛ እኮ የፈለገ ብናፈላ መጥፎ እና ጥሩን ጠንቅቀን እናውቀዋለን።» አለ።
እያወራን አህመድ መጣ።
«ፉአዴ ኡስታዜ እኮ ምግብ እንዳይኖር ያደረገው አንተ እንዳልከው ቸግሮት አይደለም። በጣም ጥበበኛ ስለሆነ ነበር።»
እኔና ሰሚሬ እየተያየን የአህመድን ጤነኝነት መጠራጠር ጀመርን። ሳቃችንም እየታገለን ነው።
«እስኪ ጥበቡን ንገረን .... ነብዩላሂ ሱለይማን (ዐሰ) ነበር እንዴ ኡስታዝህ?»
«ቤተሰቦቹ ዲነኛ አልነበሩም። ማለቴ ጠንካራ አይደሉም። ሰርግ ላይ ይጨፍራሉ ምናምን! እና ምን አሰበ ምግብ ከሌለ አይጠግቡም፤ ካልጠገቡ ደግሞ አይጨፍሩም ብሎ አሰበ። ደግሞ እንዳለው ምግብ ባለመኖሩ ተናደው አልጨፈሩም! የእኔዎቹንም ታውቃለህ! ለዛ ብዬ ነው እኮ!»
ሰሚሮ ፈጠን ብሎ «ቤተሰቦችህ ላይ አሸድ መሆን እኮ አሪፍ ዲነኝነት አይደለም። አስበርግገህ ልትደፋቸው ነው እንዴ?»
«ስማ ያልጨፈሩት እኮ ቀልባቸው ተሰብሮ ነው። ደግሞ መጨፈር ሴቶችን ማን ከለከለ? ሌላውን ተወው! እናትህ የስንት ሰው ሰርግ በልተው ባንተ ሰርግ ቀን አንገት ልታስደፋቸው ነው?»
«አዎ ለምን ዲኑን ግን እስር ቤት ታስመስሉታላችሁ?» ሰሚሮ አምርራ ትከራከራለች።
«አንተማ ቺክ እንዳታጣ ነው።»
«ለእኔማ አስርበህልኝ አሪፍ አጋጣሚ ነው እንጂ የፈጠርከው! ልጋብዝሽ ብሎ መሳብ ነው አንዷን!»
«እሺ በቃ ዛሬው በዛሬው ምን ይደርሳል?»
«እሱን ጥበብ እናትህ በደንብ ታውቀዋለች።»
መስማማቱ ደስ እያለን ወደ ቤተሰቦቹ ይዘነው ሄድን። ቤተሰቦቹ ፈነደቁ። በስፒከር የሰርግ ነሺዳ ከፈቱ። በእኔና በሰሚር ስራ ልባቸው በጣም ተደስቷል። እናትየው በቆምንበት ምርቃቱን ማዥጎድጎዱን ተያያዙት። በሬ እና በግ የመሳሰሉትን በስልክ ደንበኞቻችን ጋር ጨራረስን። ገንዘብ ግን ጥሩ ነው። ለአንዳንዱ የሳምንት ስራ የሆነውን በገንዘብ ኃይል በሰዓታት ቋጨነው።

የአህሜ ቤት ውስጥ የነበረውን ችግር ከፈታን በኋላ ቀሪውን ለሴቶቹ ትተን ወደ ሚስቱ ቤት ጉዞ ጀመርን። አህመድ እኔ መኪና ውስጥ ተቀምጦ የሙሽራው መኪና ባዶውን እየሄደ ነው።
«ስማ ግን አህሜ ሚስትህ ስሟ ማነው?»
«ሰሚራ!»
«ማሻአላህ የሰሚር ሞክሼ ናታ!» ተሳሳቅን።
ሴቷ ቤት እንደደረስን ምንም የሰርግ ድባብ ስናጣ ደነገጥን።
«ምንሼ?» ከሰሚሬ ጋር ተያየን።
«እሷም ኡስታዟ ሳትደግስ አግብታ ነው?» ሰሚሬ ሳቁን ለቀቀው።
አህሜ «ኧረ ድግስ የለም ስለተባባልን ብዙ ሰው አልጠራችም። ለዛ ነው።» አለ።
ከአህሜ ጎን ሆነን ሽማግሌዎቹን እየመራን ወደ ግቢው ዘለቅን። ሰፊ ግቢ ነው። የሴቶች የጭፈራ ድምፅ ይሰማል። የምግብ ብፌ ተዘጋጅቷል። ልክ ወደ ቤቱ ልንገባ ስንል በመስኮት ሴቶቹን አይተን ክው አለን። እኔም ሰሚርም እኩል «ፈሪሀ!» አልን። አህመድ ትቶን ወደ ውስጥ ገብቷል።

ይቀጥላል ....
.
@Fuadmu
@Fuadmu

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 2 weeks ago