ብእሬ ትናገር

Description
እኔ ከማወራ ቃላት ከምቸገር
ደሟን እየተፋች ብእሬ ትናገር
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад

2 months, 2 weeks ago

ንገሯት
ሞቶልሻል በሏት በጥበቃ
ሳይተኛ እንደነቃ
ከበሩ ደጃፍ ትክል ብሎ
የስንቱን ግልምጫ ሁሉን ችሎ
አርፎልሻል በሏት ዛሬስ ሁሉን ጥሎ
አደራ ንገሯት
ግራ ብትጋባ ስሜ ቢጠፋትም
ማን ነበር ብትልም
ያስታወሰች እንደሆን.....
ሃበሻ ነችና ለቀብሬስ አትቀርም።

2 months, 2 weeks ago

መጠኑ

እንደው ለመሆኑ
ውበትሽ ስንት ነው የአልኮል መጠኑ
ተንገዳገድኩልሽ!!
እንደው ለመሆኑ
ልኬቱ ስንት ነው የውበትሽ ስበት
ስንት ዜሮ አለበት?
ስንት ኒውተን?
ብቻ እሱን ትተን....
እንደው ለመሆኑ
ምን ብሎ ፈጠረሽ 
ሊያሳይብሽ ይሆን የጥበቡን ስፋት
ወይስ ለኔ ጥፋት
ሳይሽ ለምውለው
ባንቺ ለምምለው
ወይስ አፈሩን ለማንሳት ወርቅ እንቁ አነሳ
ወይስ ሰው መሆንሽን ሲፈጥርሽ ረሳ
እንደው ለመሆኑ
ስንት ነው መጠኑ

2 months, 3 weeks ago

*ትዝብት

ትዝብት ነው ብቻ!!
ፎሎወር ስናሳድድ፣
ያንዱን ስራ ሌላው ሲንድ፣
ሚበላው ጠፍቶ ደሃ እያጣ፣
ዱቄት ተለቃልቀን ስንነጣ፣
ትዝብት ነው ብቻ!!
............
ሆድ ለባሰው ማጭድ አዋሽ፣
የወሬ ወንዝ የወሬ አዋሽ፣
ሰው ሰውነቱን ረሳነው፣
ስንከፍል ስንሸነሽን፣
በምላስ ጦር ስንረሽን፣
በዘር ወንፊት ስንጣለል፣
ስንወርድ ስንቃለል፣
ያልሞተውን ስንገለው፣
ሃቀኛውን ስናገለው።
ትዝብት ነው ብቻ!!
.......
ባህል ረስተን ያገር ወጉን፣
ስንረክስ ጥግ ጥጉን፣
ነገር ሴራ ስንጎነጉን፣
ስንጥስ ቃሉን ህጉን፣
ስንሳለቅ በደሃ እንባ፣
ሰው አንሶብን ከዘንባባ፣
እስኪ እግዜር ሆይ ጣልቃ ግባ።

ከደጅህ ርቀን ውሎዋችን እዛው ነው*😁

5 months, 3 weeks ago

" መድህኔ"

ግቢ ከገባሁኝ
የቀረብኳት በጣም
ሁሌ ማገኛት
ስገባም ስወጣም
ሳላያት የማልውል
ስሟን ሳላነሳው
ጠረኗን ሳላሸት
ጣዕሟን ሳልቀምሰው
እጅግ ተናፋቂ
የአንጀቴ ማራሻ
እሷን ያጣሁኝ ቀን
አጣለሁ መድረሻ
ፈጥኖ ደራሽ ሁሌ
ሊገለኝ ሲቃጣ ጠኔ በኔ ብሶ
የረሃብ መድህኔ ሁሌም ለኔ በሶ።?

እስኪ የበሶ ወዳጆች?‍♂️?‍♂️

5 months, 3 weeks ago

"ግርሻ"

ያኔ ተለያይተን
አይንህ ላፈር ብለሽ
አይንሽ ላፈር ብዬ
ኮብለሽ ኮብልዬ
ስንለያይ በጥል
ጉዞአችን ለየቅል
ከልቤ የፃፍኩት ፍቅርሽ ሲደበዝዝ
የአንቺ የሆነውን ስሰርዝ ስደልዝ
ታዲያ...
በአመታት እድሜ
ቢያገናኘን ግዜ ያለያየን መንገድ
በፅኑ መሰረት የተከልኩት ልቤ
ይል ጀመር ገድ ገድ
ከልቤ ያኖርሽው ጠባሳዬ ሽሮ
ዛሬም ተመኘሁሽ አንቺን እንደድሮ
ይኸው የፈራሁት በኔ ላይ ደረሰ
ከጅምሩ ይልቅ ግርሻው በኔ ባሰ።

6 months ago

"አለም ዘጠኝ"

አንዱ አለም ዘጠኝ ሌላው አለም አስር
ልክ አይደሉም ብዬ ጣቴንም አልቀስር
እኔ ግን ብናገር እድሉ ቢሰጠኝ
አልል አለም አስር አልል አለም ዘጠኝ
በእውነቱ....
እየኖርን ሳለን በራሳችን አለም
ከሁሉ ሚለየን ሰጥቶን ልዩ ቀለም
አልገባም ቆጠራ
ጣቴንም ድርደራ።
ይልቁንስ ስሙኝ....
አይደል አለም ዘጠኝ
አይደል አለም አስር
አለም በሰው ስፍር።

6 months ago

ውስጥ ውስጤን በልቶ
ቢያደርሰኝ ከሞት ጫፍ
ታሪክም ባልሰራ ታሪክ ሆኜ ልፃፍ
ሲቀረኝ አንድ ሐሙስ የቀናቶች እድሜ
ዛሬም አልተቋጨ የካች አምናው ህልሜ
ስንት ለሊት ያለምኩት
ሆዴ ልለምንሽ ሳሚኝና ልሙት።

6 months ago

ሰማሁ!
አንቺማ ሰምሮልሽ
በአነባሁት እንባ መስኖ ጀምረሻል
እኔ ዳስ የለኝም ጎጆ ቀልሰሻል
ይባሱንም ብሎ ሁለት አድርሰሻል
ይመስገነው ላንቺ
ይመስገነው ለኔም
ባጣሽ ከህይወቴ
አንብቼ አንብቼ
ቆረጠልኝና ሆኖልኝ ምኞቴ
ማሰብ ጀምሬያለሁ
እውላለሁ ሰላም
ይከፋሻል ብዬ እንደ ድሮ አልሰጋም
አንቺን ለማስደሰት ሌት ተቀን አልተጋም
የት ገባች የት ወጣች ትቻለሁኝ ከቶ
ፍቅርሽም ኮብልሏል ቤቴን እኔን ትቶ
ታዲያ ምን ይሳነው!
አምላክ ይመስገና
አንቺም ባለሽበት 
እኔም ባለሁበት እንኑር  በደህና።

6 months, 3 weeks ago

እኔን ብሎ ገጣሚ!!
ይኸው ትላንትና
ባነሳው ብእሬን
ላነሳት እምዬን
ላወሳት ሃገሬን
ከቃል ባህር ውዬ
ስንኞች ልጨልፍ
ቀኑን ሳሰፈስፍ
ሀ አልኩኝ
ኢትዮጵያዬ አልኩኝ
ሞነጨርኩ ጀመርኩት
ታዲያ ምን ያረጋል
በሃገር ጀምሬ በስምሽ ጨረስኩት።

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад