Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 6 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 month ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 weeks ago
ሀገሬ ተማሪ ልንገርሽ እንግዲ
ድግሪ ዲፕሎማ ሳይሆን ፒ ኤች ዲ
ከሀ ሁ ጀምሪ ወይም አባ ጫ ዳ
አሊፍ ባ ታ ካሻሽ አቦጊዳ
ብቻ በፈለግሽው ፊዳላት ቁጠሪ
ተማሪ በታሪክ ካለፈው ሂስትሪ
=====================
ያኔ ደጉ ዘመን ይህ ሳይመጣ አፍጦ
ቀሳውስትሽ በልተው ለሙስና ሌጦ
ንጉስሸ መልሷል ፍትህን አብልጦ
የሰው ልጅ እንደከብት ሊታረድ ሲነዳ
ጉባኤም አይተሻል ጉደ ቦሩ ሜዳ
አራት አገር አንድ ያደረገ መሪ
አንዴ ለምደሽዋል አንቺ ግፍ አትፈሪ
ያንን ያገር ኩራት ብለሻል ወራሪ
ላንቺ አይሆንም ተይው! መሳብና መግፋት
ገንብተሽ አፍርሰሽ አፍርሰሽ መገንባት
አደግሽ ሲባል መዝቀጥ ከወጣሽው መግባት
በፍትሃዊዊ ሀገር ፍትህ ሲቀለበስ
ሲቀየር አይተሻል ማበስ በማስለቀስ
የቱ አስከብሮ? የቱ አስወቀሰሽ?
የቱ በአለም ላይ ዝናሽን አናኘሽ?
ንገሪኝ እምዬ ሀገር የለኝ ሌላ
ተራመድሽ ሲባል ወደቅሽ ወዳኃላ
የሞጣው ጨፍሯል መስጅዱን አንድዶ
እንደ ቀልድ አልፎዋል ባንድ ሰሞን መርዶ
እንዳይመጣ ፍሪ አንድ ጀግና ወልዶ
ፆመኛ አስፈጠረች ጎንደር ጥይት ጋብዛ
ምን ይሻል ሐገሬ ዝም ሲሉሽ በዛ
እንዴት ላብራራልሽ ውስጤን ዋጥ አድርጌ
ትንኮሳው አይሏል በቤተ-ጉራጌ
ማይሰማ የለም መቼም በጉድ ሀገር
ደሞ ከሰሞኑ አልፈሻል ቀይመስመር
ካለፈ አትማሪም አይደለሽም ሀገር?
ያለፈውን ስርዓት የከተተው ገደል
በቅርብ አይተሽዋል ጉልበት አንሶት አይደል
ግፉ አዳልጦት ነው የፈፀመው በደል
ወይ መንደር አይደለሽ ይህ ምታክይ ሀገር
እንዴት ያቅትሻል ከትላንቱ መማር?
ስሚኝ ከሰማሽኝ ይህ አይደለም ዛቻ
ሙስሊሙን አትንኪ ጠብቀሽ አሳቻ
ካባቶቹም አለው ፅናት የወረሰው
ኢስላሙን ተነጥቆ ቆሞ ከሚባል ሰዉ
ሙስሊም ሆኖ ሞቶ ይጎተታል ሬሳዉ
ትከሻው እስኪላጥ እስኪያወጣ ሰምበር
በሬው ችሎችሎ ከሰበረ ቀምበር
በምድርሽ አይኖርም ሰላም የሚሆን በር
ኃላ ቀርተሽ ራሱ ኃላ ያስቀርሻል
አንቺ እዛው ቆመሽ ይነጋል ይመሻል
ተይ ተማሪ ሀገሬ ስሚኝ ይሻልሻል!
✍ ሸምስ ሙዘሚል
http://t.me/+J451rJLdmYowMWZk
ወላሂ አንለምድም❗️
~~~~
ነፍሱ በአካሉ~~ እስካለ በምድር
አማኝ በእምነቱ አይቀርብም ድርድር
ሙዕሚን ሰው አይደለም ግፍ ለምዶ ሚያድር
**መንገድ ጠፋን እንጂ ዝግጁ ነን እኛ
ሲለመን አይወድም ጥንትም በደለኛ
በዚሁ ከቀጠለ ይህ ግፍ ሄዶ ሄዶ
መምጣቱ አይቀርም አንድ ጀግና ወልዶ**
?ኢብን ሙዘሚል
http://t.me/+J451rJLdmYowMWZk
በጨርቅ ቤት ሲኖር በተንቀሳቃሽ ዳስ
የሚሰራው መስጅድ ውብ ነው ሰማይ ጠቀስ!
የግጥሜ ርዕስ
አብሽር ሀምዱ ቋንጤ
ከዛሬ ጀምሮ አትባልም ላጤ
ሀምዱን ያሸነፈች ማናት ጀግና ንግስት
………………………… የምትደነቅ ሚስት
https://t.me/oumershaer/285
Telegram
عمر الشاعر
የግጥሜ ርዕስ አብሽር ሀምዱ ቋንጤ ከዛሬ ጀምሮ አትባልም ላጤ ሀምዱን ያሸነፈች ማናት ጀግና ንግስት ………………………… የምትደነቅ ሚስት https://t.me/oumershaer/285
?**አግብቷል ሀምዱ
بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في خير
ዘገየህ አትበሉት አልዘገየም ሀምዱ
መቀመጫ አቶ ነው የቆየው ከደጁ
ፀሃይ እስክትወጣ እስኪደምቅ ኑራ
እኛ ሳናውቅለት ሲጠብቅ ነበረ
በርግጥ ማይደበቅ እውነታ የነበር
ብዙ ተዋድቆዋል ለላጤዎች ግንባር
እጅ አልሰጥም ብሎ ታግሎ አታግሎ ነበር
ትዳሩ ይስመርለት በሉ ይቅናው መንገዱ
አድርጓል ተራጁዕ አግብቷል ሀምዱ!
ለአይኑ መርግያ ለልቡ ሰኪና
በፍቃደኝነት ተጠልፏል በሱና
የትላንቱ ላጤ የዛሬው ሙሽራ
የልጆችህ አባት የነጌ አባወራ
ጆሮህን አውሰኝ ስለ ትዳር ላውራ
ትዳር እንዲሰምር ህይወት እንዲያብብ
ቢበዛ ቢያንስም ከጅህ ያለው ገንዘብ
አርቆ ማሰብን ሰፊ ማገነዘብ
ከጦር ሜዳ በላይ ይፈልጋል ጥበብ
2 3 4 ስትል ከንግዲህ ተጠንቀቅ
መኖር አልመኝም አንተን በመነጠቅ
''በድንገት አድርገው ዙሩ ካለ ክርር
ጠረዼዛ ዙርያ ይሻላል ድርድር'' አሁን ላንተም ይስራ የመከርከን ምክር
ሙሽሪትም ይሁን ትዳራችሁ ቀና
ማሻ አላህ ሚባል ይሁን ሚያስቀና
ዱኒያን ይሻገር ይዝለቅ እስከ ጀና
ያንቺ ንግስትነት የእሱም ንግስና
ባንቺ ብልህነት ስልጣናችሁ ይፅና
ከስር ያለው ኡማ ሊስተካከል ህዝቡ
አገር የማቀናት ያንቺ ነው ጥበቡ
መዋደድ ያለበት ፍቅር የሞላው ቤት
ጀነት መዳረሻ ለሙእሚን ነው ሀሴት
መቼ ትጥማለች ዱኒያ ያለ ሴት
ብሎ እስኪፈልግ የት ሄዶዋል ልቤ
እሰሪው ጠፍሪው በፍቅርሽ ሸቤ
መቼም ያው ገብቶሻል ግልፅ ነው ሀሳቤ
በምላስሽ ሳይሆን ተግባርሽ ካለ እምቢ
ሀላሉን አግርቶ ፈቅዶለታል ረቢ
ምትቀናቀንሽ ይፈልጋል ደርቢ
አብዝተሽ አንጥፈሽ የምቾትን ምንጣፍ
አደራ ሙሽሪት ብዕሩን እንዳይነጥፍ
ከግዜው ያካፍለን ያጋራን ኒስፍ ኒስፍ
ባ'ካል እንዳልገኝ የሀምዱን ሰርግ ለት
ልቤ ተንጠልጥሎ ገድቦኛል ርቀት
አልመጣ በርሬ አይደለሁ አሞራ
የፕሌኑን ነገር ትንሽ ኪሴ ፈራ
ሰርግህን ባልገኝ ባልገባም ከዳሱ
ሰድጄልሃለው ድምፄን በንፋሱ
✍ኢብን ሙዘሚል**t.me/ibnmuzemil/546
በአፍ ''እኩልነት'' በተግባር ግን ደባ
በደሃ ልጅ አፅም በሚስኪኖች እምባ
እንደዚህ ነው አሉ! ሐገር ሲገነባ
ኢብን ሙዘሚል
https://t.me/ibnmuzemil/520
*?ሀጅ?*
ለበይክ የሚለው ቃል በምኞት የሚያከንፍ
ቀልብ ስልብ አርጎ ውስጥ ሚያንሰፈስፍ
አለው ልዩ ስሜት በተስፋ ሚያንሳፍፍ
ከ'አለም ተሰባጥሮ ለሀጅና ዑምራ
ተልቢያ እያለ ጌታን እያጠራ
ተመመ ሀጃጁ ሊገባ ኡሙል ቁራ
ከጥቁር ከነጩ ከአረብ ከአዕጀም
ከአለም ተሰብስበው በይቱላሒል ሀረም
በበለዱል አሚን ሊጠጡ ነው ዘምዘም
በመናሲከል ሐጅ ላኼራው ሊለፋ
ሊያድር በሚና ሊሄድ ሙዝደሊፋ
ደግሞ በሀጁ ሩክን ሊቆም ነው አረፋ
ከአደን ርቆ አውሬም ይሁን አእዋፍ
በካባ ዙሪያ ሊያደርግ ጠዋፍ
ሊሸምት ላኼራው ለነፍስያ ቀለብ
አንድ ጊዜ ረጋ አንዴ በዱብዱብ
ሊመላለስበት በሰፋና መርዋ
ሊያጣጥሙ ነው የምህረትን ፅዋ
በመቃሙ ኢብራሂም ከቻለ ሊሰግድ
ሊስም ሊያመላክት ወደ ሀጀረል አስወድ
መውጣቱ ከዳገት መውረዱ ቁልቁለት
ሳያግድ ሳይደክመው ሳይናፍቀው ዕረፍት
ለጠጠር ውርወራ፣
ይሄዳል ጀመራ፣
የእስልምና ጥበብ ሚገርም ነው ሁሌ
ሀብታምና ድሃ ንጉስ ሳይል ሎሌ
አጀሙ ዐረቡ ጥቁሩ ሳይቀር ነጭ
ጥሎ በአካሉ ከጨርቅ ሁለት ቁራጭ
ባንድ ቦታ :ግዜ ፀጉሩ ነው ሊላጭ
የተረጋገጠ በኪታብ በሱና
ስርዓቱን ጠብቆ በህጉ ለፀና
ምንዳ የለም ለሃጅ ቢሆን እንጂ ጀና
አሏህ የወፈቀው መብሩር ለሆነ ሀጅ
ንፁህ ነው ከወንጀል እንደ አንቀልባ ልጅ
ትከሻው ሊሸከም አቅሙ የደረሰ
ማን ነው የሚቀረው ለሀብቱ እየሳሳ
ካልሆነ በስተቀር ወኔው የፈሰሰ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ለብዛት ላይነቱ ባይኖረው ደርቻ
ወንጀሌን ላራግፈው፤
ጌታዬ አታርግብኝ ሀጅን ምኞት ብቻ
ኢብኑ ሙዘሚል
01/10/14**https://t.me/ibnmuzemil/517
ከውቢቱ አዳማ ከናዝሬት ከተማ የሚያስደስት ዜና አየሁ ሰማሁና ልነግራችሁ ወደድኩ ግጥምም ቢጤ ሞከርኩ ኡመር F S R ያ አይናፋር ሾፌር ያሱንይ ሰለፊ ያቸር ሆደ ሰፊ እሽግ ያልተፈታች ታርጋ ያለጠፈች በሱና ኒካ አስሮ ሊብሬውን አዙሮ በአዲሱ መንገድ በከነፈ እስፒድ ናዝሬት ጭኖ ገባ ከአዲስ አበባ ከንግዲህ ቃጤራ አምጥተህ ሙሽራ አይደለም ልትሰራ የለሊት በረራ ስታወራ በስልክ በድንገት ከተያዝክ…
እንዳልከትብ ስንኝ ስለ ጀምዒያ
ማን አለ ማያውቀው? ያየ ሰለፊያ
ሚታወቅ ማሳወቅ መድከም ነው ጣጣው
መኃላችን ሁሉም አንቅሮትን የመጣው
ለማያውቅህ ተዋብ ለላየህ ሰው ተኳል
ለልቀመሰህ ጣፍጥ
ላኖረህ ተጋጋጥ
ከራስ ተወዳድረህ እራስህን ብለጥ
እዛው በመንደርህ እንዳሻህ ተላላጥ
መንሃጃችን ማዓሱም እኛ ነን ተሳሳች
ዲኑ አይለካም በደካማ ሰዎች
እንደማይቻለው ሀይን ሰው መከፈን
ውሸታም በማለት እውነትን መሸፈን
እርምህን አውጣ አትችልም አትልፋ
አይ እምቢ ካልክም ታየዋለህ ግፋ!
ኢብን ሙዘሚል
https://t.me/ibnmuzemil
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 6 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 month ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 weeks ago