Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 5 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 15 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 week, 5 days ago
📵 ለልጆጃችሁ ከኢንተርኔት ጋር የተገናኘ ሞባይል ስትሰጧቸው ይህንን አስባችሁ ታውቃላችሁ?
👉 ምንድነው የሚመለከቱት?
👉 ከማን ጋር ነው የሚገናኙበት?
👉 ምን ዓይነት አስተሳሰብ ነው የሚገበዩበት?
👉 የሚገናኟቸው ሰዎች ታማኝ ናቸውን?
👉 ሰላምና አሰተማሪ ነገር ያገኙበታልን?
👌 መውለድ የالله ስጦታ ሲሆን እነዚህን ልጆች በእስላማዊ ተርቢያ ማሳደግ ግን አማና ነው እንጠየቃለን ልብ ያለው ልብ ይበል !
➡️ እንዴት አንድፍሬ ለሆኑ ሴትና ወንድ ልጆቻችን ኢንተርኔት ውስጥ ያለጠባቂ እንዲገቡ እንፈቅዳለን
👆 ይህ ማለት ልጆቻችንን ጭው ባለ አውሬ የበዛበት ጫካ ውስጥ ያለ መሳሪያ ብቻቸውን እንደመልቀቅ እንደሆነ ገብቶናልን?
ወላጆች ሆይ!
✅ ልጆችን አውዳሚ የሆነው የኢንተርኔት ጫካ ውስጥ ከመልቀቅ በዚህ አስፈሪ የአውሬ ጫካ ውስጥ መልቀቅ በጣም የቀለለ ነው !
እንዴት? አትልኙም?
👍 ነገሩ ወዲህ ነው ይህ አስፈሪ ጫካ ውስጥ ያሉ አውሬዎች እነዚህን ልጆች አካላቸውን ያጠቃሉ ይቦጫጭቁታል ነገር ግን ነፍሳቸው ንፅህናዋን እንደጠበቀች እንደተከበረች ወደ ጌታዋ ትሄዳለች ። ከዚህ በላይ ምን ክብር አለ?
🔥 የኢንተርኔቱ ጫካ ውስጥ ብቻቸውን የተውናቸው ጊዜ ግን ስነምግባራቸውን ትቦጫጭቀዋለች እምነታቸውን ትቦረቡራለች ማንነታቸውን ትሰልበዋለች በውስጣቸው ሰርፆ ያለውን እርጋታና ጤንነት ነጥቃ ልክፍተኛ ታደርጋቸዋለች በቃ ምን ልበላችሁ ምህራባዊያንን ከልጆቻች ጋር ያላቸውን እንዳንድ ታሪኮች ያነበበ በቂ እማኝ ያገኛል
والموت خير من الفتنة
ወላጆች ሆይ ‼
ኢንተርኔት ውስጡ ሁሉ ነገር አለ መልካሙም ክፉዉም አለ ። ክፉው ግን እጅጉን የበዛ ነው ለጋ ልጆቻችን ይህንን መርጠው የመጠቀም ጥበቡም አቅሙም የላቸውም የሚበጀውን ከአውዳሚው አይለዩም ተቀባይነት ያለውን ከሚተወው አይነጥሉም
ኢንተርኔት ውስጥ ጎጂ አስተሳሰቦች የተበላሹ ዐቂዳዎች አመፀኞች የስነምግባር ሌቦች አስቀያሚ እዚህ ፁሁፍ ላይ ሊዘረዘሩ የሚከብዱ እኩይ ተግባራት የሚለቀቁበት ስምጥና ዳርቻ የሌለው ውቅያኖስ ነው ።
እባካችሁ ወላጆች ለልጆቻችሁ ወራዳነትን አትምረጡላቸው ‼
ለልጆቻቹ ልቦናቸውን በብረሀንና በእርጋታ የሚያስውበውን ቁርአንን አሳፍዟቸው ስነምግባርና ሰውነትን የሚያስተምሩትን የነብያችንን صلى الله عليه وسلم ሐዲሶችን አስተምሯቸው ከሰውና ከአጋንንት ጉትጎታዎች ምሽግ የሚሆናቸውን አዝካር አስጠኗቸው ይህ ነው አናትነት ይህ ነው አባትነት ይህ ነው አማናን መወጣት ይህ ነው ለአኼራ መጨነቅ ይህ ነው ልጆች ከልብና የእውነት መውደድ
ልጆችን በስልጣኔ ስም ልቅነትንና ዋልጌነትን ማስተማር ስይጣኔ ነው ‼
የአይን ማረፊያ ልጆቻችሁን ነገ አይናችሁን እንዲያጠፉ አድርጋችሁ አታሳድጉ
የኢንተርኔት መረብ እንደስሙ ነው በመረቡ ሙስሊሞችን እያደነ ስንት አደጋ ላይ ወርውሯልና ልጆቻችሁን አሳልፋችሁ ለዚህ መረብ አትጋብዙ
ነብያችን صلى الله عليه وسلم ብለዋል
" كلكم راع وكلكم مسؤول عن رعيته "
"ሁላችሁም ጠባቂ ናችሁ በጥበቃችሁም
ትጠየቃላችሁ"
ወላጆች ሆይ በልጆቻችሁ ጉዳይ الله ን ፍሩ ‼
ብር አለን ብላችሁ በሺዎች የሚቆጠሩ ብሮች አውጥታችሁ ለልጆቻችሁ ሞባይል ከመግዛታችሁ በፊት ሺ ጊዜ መላልሳችሁ አስቡ አስተውሉ ‼
👆ተወስዶ ተጨምሮ ተቀንሶ የተተረጎመ
✏️ አቡ አብዲልመናን ኻሊድ ጠይብ
እህት ወንድሞቻችንን እናስታውስ
👉 @tewihd
እነዚህን ጥያቄዎች አስተውለክ ታውቃለህ?
▪ ﻟﻤﺎﺫﺍ ﺍﻟﻤُﺴﻠﻤﻴﻦ ﻣُﺴﺘﻀﻌﻔﻴﻦ ؟
▪ ሙስሊሞች ለምን ደካማ ሆኑ?
▪ ﻓﻲ ﻛﻞ ﺍﻟﺪُﻭﻝ ﻭﻣﺨﺬﻭﻟﻴﻦ ؟
▪ በሁሉም ሀገር ላይ የተዋረዱት?
▪ ﻭﻣُﺸـﺮﺩﻳـﻦ ﻭﻣُﺸﺘﺘﻴـﻦ ؟
▪ የሚባረሩት የሚሰደዱት?
▪ ﻭﻳﻘﺘـﻠـﻮﻥ ﻭﻳﻐﺘﺼﺒـﻮﻥ ؟
▪ የሚገደሉት የሚዘረፉት?
▪ ﺇﻗــﺮﺃ ﺍﻟـﺠﻮﺍﺏ:-
▪ለመልሱን ⇩ አንብብ:-
ﻗﺎﻝ ﺷﻴﺦ ﺍﻹﺳﻼم ﺍﺑﻦ ﺗﻴﻤﻴﺔ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﻏﻔـﺮ ﻟﻪ ورفع درجته في المهديين -:
⚠️ ﻭﺇﺫﺍ ﻛﺎﻥ ﻓﻲ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦ ﺿﻌﻒ
⚠️ ﻭﻛﺎﻥ ﻋﺪﻭﻫﻢ ﻣﺴﺘﻈﻬﺮًﺍ ﻋﻠﻴﻬﻢ
⚠️ ﻭﻳﺬﺑﺤـﻮﻥ ﻭﻳﺸﻨﻘــﻮﻥ؟
⬅️ ﻛﺎﻥ ﺫﻟﻚ ﺑﺴﺒﺐ ﺫﻧﻮﺑﻬﻢ ﻭﺧﻄﺎﻳﺎﻫﻢ
▪️ﺇﻣﺎ ﻟﺘﻔﺮﻳﻄﻬﻢ ﻓﻲ ﺃﺩﺍﺀ ﺍﻟﻮﺍﺟﺒﺎﺕ ﺑﺎﻃﻨًﺎ ﻭﻇﺎﻫﺮًﺍ
▪️ﻭﺇﻣﺎ ﻟﻌﺪﻭﺍﻧﻬﻢ ﺑﺘﻌﺪﻱ ﺍﻟﺤﺪﻭﺩ ﺑﺎﻃﻨًﺎ ﻭﻇﺎﻫﺮًﺍ ".
⚠️ ሙስሊሞች ደካማ ከሆኑ
⚠️ ጠላታቸው ከበላያቸው ከሆነ
⚠️ የሚያንቃቸውና የሚገድላቸው ከሆነ ይህ የሆነው
➡️ በወንጀሎቻቸውና በስህተታቸው ምክኒያት ነው።
▪️ወይ አሏህ ዋጂብ ያደረጋቸውን ነገራቶች በውስጥም በውጭም በማጓደላቸው ነው።
▪️ወይም የአሏህን ድንበሮች [ወሰኖች] በውስጥም በውጭም በመሻገራቸው ነው።
📕【ﻣﺠﻤﻮﻉ ﺍﻟﻔﺘﺎﻭﻯ【٦٤٥/١١】
✔️ ሞትና ቀጣይ ሂደቶች
- ስሞት አላስብም፣ አልጨነቅም፣
- ገላዬ ፈራሽ ነውና ምን አሳሰበኝ
ሙስሊም ወንድሞቼ መደረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጉልኛል፡፡
1- ልብሴን ያወልቃሉ፣
2- ያጥቡኛል፣
3- ይከፍኑኛል፣
4- ከቤቴ ይዘውኝ ይወጣሉ፣
5- ወደ አዲሱ ቤቴ (መቃብር) ይወስዱኛል፣
6- ብዙዎች ጀናዛዬን ለመሸኘት ይመጣሉ፣
7- እኔን ለመቅበር ሥራቸውንና ቀጠሯቸውን ሁሉ ትተው የሚመጡ አሉ፡፡
ቀጠሯቸ መካከል ምናልባት ላንዳፍታ እንኳን ስለኔ አስበው የማያውቁ ብዙ ናቸው፡፡
8- ቤተሰቦቼ እኔን ላለማስታወስ ያለኝን ነገር ሁሉ አውጥተው ይጥሉ ይሆናል፤ አሊያም በኔ ሥም ይመፀውቱ ይሆናል
- ቁልፎቼ 🔑🗝
- መጽሐፎቼ 📚
- ጫማዎቼ 👟
- ልብሦቼ 👖👔…..
በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡
- በመሞቴ ይህች ዱንያ ሐዘኗ አልበዛም፣ አለች አልፈረሠችም፣
- የዓለም 🌍 እንቅስቃሴም ላፍታ አልቆመም፣
- የኢኮኖሚው 💰 ቀውስም አልተፈጠረም፣
- በሥራ ቦታዬ ላይ ሰው ለመቅጠር ማስታወቂያ🧾 ይወጣል፣
- ንብረቴ 💸🏠🚘 የወራሾቼ ይሆናል፣ በትንሽ በትልቁም ኦዲት የምደረገው ግን እኔ ነኝ፣
- ስሞት መጀመሪያ ከኔ የሚገፈፈው ስሜ ነው፡፡ በሥሜ መጠራቴ ይቀራል፤
- ጀናዛው የታለ እባላለሁ፡፡ ጀናዛውን ዉሰዱ፣ አምጡ እንስገድበት፣ ጀናዛውን እንቅበር … ይባላል
- ሥልጣኔ፣ ከተከበረ ቤተሰብ መሆኔ፣ ጎሳዬ … ሁሉ ዋጋ ያጣል፤
ዱንያ ይህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ነች፤ የምንሄድበት ዓለም ግን አቤት ክብደቱ! ማስፈራቱ! …
በሕይወት ያለህ ወዳጄ ሆይ! በመሞትህ ሦስት ዓይነት ሐዘን አለ
1- የሚያውቁህ ዋ ያ ሚስኪን እኮ ሞተ! ይላሉ
2- ባልደረቦችህ ለሰዓታት አለያም ለቀናት ያዝኑና ወደ ሳቅና ጨዋታቸው ይመለሳሉ፣
3- ትልቁ ሐዘን ያለው ቤትህ ነው፣ ቤተሰብህ ጋ … ሁሌም ያስታውሱህ ይሆናል፣
የዱንያ ታሪክህ በዚህ መልኩ አበቃ ፤ የመጨረሻው ዓለም ታሪክህ ተጀመረ
ሁሉ ነገርህ ተወሰደ፣ ፈረሠ፣ አለፈ፣ ጠፋ!!!
1- መልክህ፣
2- ሀብትህ፣
4- ጤናህ፣
5- ልጅህ፣
6- ቪላህ፣
7- ዝናህ፣
8- ሚስትህ/ባልሽ
ካንተ ጋር ሥራህ ብቻ ቀረ
እውነተኛው ሕይወት ተጀመረ፡፡
እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ/ሽ
ለአኺራህ ምን አዘጋጀህ!! እስቲ በጥልቀት አስብ፡፡
እናም በርታ፣ በርቺ እህቴ
1- በግዴታዎች፣
2- በሱንና ነገሮች፣
3- በድብቅ መፅውት፣
4- መልካም ሥራ አብዛ፣
5- ሌሊት ተነስተህ ስገድ፣
ትድን ዘንድ ጠንክር፣ ይሳካልህ ዘንድ በርታ፡፡
መልካም ንግግር ምጽዋት ነው፡፡ ምንም የለኝም አትበል፡፡ ሌላ ነገር ብታጣ ይህችን በእጅህ የገባችውን ፅሑፍ መጽውት፣ ምንም ጉልበትና ጊዜ አይወስድብህምና አታመንታ፡፡
አስቡ ያሄ መልእክት እናንተ ጋር ብቻ እንዲቆይ አትፍቀዱ ለሌሎችም አጋሩ ወይም ሼር አድርጉ በናንተ ምክንያት ሌላ ሰው አንብቦ ቢጠቀም እናንተ የሱ ምንዳ ተካፋይ ናችሁና።
የጠዋት ስንቅ ለቀልብዎ
[Part: 28]
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ
[Part: 27]
??
https://t.me/tewihd
የጠዋት ስንቅ ለቀልብዎ
?? [Part: 27]
**۞ نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
ባሮቼን እኔ መሓሪው አዛኙ እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው፡፡
وَأَنَّ عَذَابِي هُوَ الْعَذَابُ الْأَلِيمُ
ቅጣቴም እርሱ አሳማሚ ቅጣት መኾኑን (ንገራቸው)፡፡
وَنَبِّئْهُمْ عَن ضَيْفِ إِبْرَاهِيمَ
ከኢብራሂም እንግዶችም (ወሬ) ንገራቸው፡፡
إِذْ دَخَلُوا عَلَيْهِ فَقَالُوا سَلَامًا قَالَ إِنَّا مِنكُمْ وَجِلُونَ
በእርሱ ላይ በገቡና ሰላም ባሉት ጊዜ የኾነውን (አስታውስ)፡፡ (እርሱም) «እኛ ከእናንተ ፈሪዎች ነን» አላቸው፡፡
قَالُوا لَا تَوْجَلْ إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلَامٍ عَلِيمٍ
«አትፍራ፤ እኛ ዐዋቂ በኾነ ወንድ ልጅ እናበስርሃለን» አሉት፡፡
قَالَ أَبَشَّرْتُمُونِي عَلَىٰ أَن مَّسَّنِيَ الْكِبَرُ فَبِمَ تُبَشِّرُونَ
«እርጅና የደረሰብኝ ከመኾኔ ጋር አበሰራችሁኝን በምን ታበስሩኛላችሁ» አለ፡፡
قَالُوا بَشَّرْنَاكَ بِالْحَقِّ فَلَا تَكُن مِّنَ الْقَانِطِينَ
«በእውነት አበሰርንህ፡፡ ከተሰፋ ቆራጮችም አትኹን» አሉ፡፡
قَالَ وَمَن يَقْنَطُ مِن رَّحْمَةِ رَبِّهِ إِلَّا الضَّالُّونَ
«ከጠማማዎችም በስተቀር ከጌታው እዝነት ተስፋን የሚቆርጥ ማነው» አለ፡፡**
[አል-ሒጅር: 49-56]
♻️ያስጨነቀሽ ሁሉ፣ ያሳሰበሽ ሁሉ፣ ያስፈራሽ ሁሉ፣ ወጥሮ የያዘሽ ሁሉ ...
ኃጢአትሽን እያረገፈልሽ ነው፣ ለሁሉም ጊዜ አለው ታገሽ።
??@tewihd
?ጥሩ እናት ለልጇ እንዲህ ብላ መከረች__!!
➖*➖*➖➖➖➖➖➖➖
?ልጄ ሆይ*〰***【عندما يغضب زوجك أغلقي أذنيك وعندما تغضبين أقفلي فمك..وستكون الحياة جميلة】
?ባልሽ በተቆጣ ጊዜ?**? ጆሮሽን ያዢ።**
?አንቺ በተቆጣሽ ጊዜ? ?አፍሽን ዝጊ
ይህ ካደረግሽ የትዳር ህይወትሽ ያማረና የሰመረ ይሆናል።
♡ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
?. ✍. ?.
https://t.me/tewihd
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 5 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 15 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 week, 5 days ago