? የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ? ©ሶፊ

Description
ድርሰት
ደብዳቤ
ግጥም
ወግ
እይታዎች
ዝብርቅርቅ ሐሳቦች
ፖስት ካርድ ስቶሪዎች
ገጠመኞች
ውሎዎች
በዚህ ቻናል ይቀርባሉ።

ወረቀት እና ብዕር የልብ ጓደኞቼ ናቸው።
(የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ )

"I don't write words; i write sentiments."
-®Sofi


@sofimemo
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 4 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 2 days, 12 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 3 days, 10 hours ago

2 Monate, 3 Wochen her
? የ ተ ቀ ደ ደ …
2 Monate, 3 Wochen her
የማን ቆንጆ ናት ይሄን ቆንጆ ስጦታ …

የማን ቆንጆ ናት ይሄን ቆንጆ ስጦታ በልደቴ ቀን ልትሰጠኝ የወደደች ?

ደግሞ ውስጡ እንዲህ ተፅፎበታል...

"መፅሐፍህን የመፅሐፍ መደርደሪያዬ ውስጥ ላየው እፈልጋለኹ"

2 Monate, 3 Wochen her
ነገ ልደቴ ነው...ሶፊ ተወለደ ።

ነገ ልደቴ ነው...ሶፊ ተወለደ ።

2 Monate, 3 Wochen her

**አሁን የሚናደድብኝ ሰው የለም....የሚወቅሰኝ....ለምን የሚለኝ...በቃ ሰላም።

ራሴን በመስታወት እያየሁ ""ሰላም አካል ለብሶን አይደል እንዴ ምመስለው"...እያልኩ እፈግጋለሁ....በቃ ሰላም።

አሁን የማጨሰውን ሲጋራ እየቆጠረ በምምገውና በምተፋው ጢስ ቁጥር ልክ ቃል የሚተፋብኝና ለሚቃጠለው ሳንባዬ ጥብቅና የሚቆም የለም.....በቃ ሰላም።

"ስትሰክር ከእኔ ጋር ጉድ ጉድ እንዳታስብ...."....ብሎ ጀርባውን የሚሰጠኝና ጦም የሚያሳድረኝ የለም...ስሜ እስከሚጠፋኝ ጠጥቼ የምታንጎዳጉደኝን መርጬ ይዤ ገባለሁ....በቃ ሰላም።

"ስራ ስራ እንጂ....ወጣትነትህን እንዲሁ ዝንቦ ዘሪር ሰው በመሆን አትጨርስ...."....የሚለኝ ድምፅ ተኗል....ከመሰሎቼ ጋር እውላለሁ....በቃ ሰላም።

"ይሄ የእጅ አመልህ አንድ ቀን ይገልሀል...ተው ግን ተው አስብ...."....ትለኝ ነበር ኪስ አውልቄ ስገባ....

"ሰው አያልቅስብህ...የሰው እንባ እሳት ሆኖ ያቃጥልሀል...እስቲ አስበው የታመምከው አንተ ብትሆንስ...."...ትለኛለች  ልብሴን ልታጥብ ኪሴን በበረበረችበት ያገኘውን የህክምና ማስረጃ...የመድሀኒት ማዘዣ እና የመሳሰሉትን አንጠልጥላ....

ምንም አልመልስላትም...ምክንያቱም ምንም ስለማይገባኝ...ዛሬ ላይ እስክደርስ ብስጭቷ፣ምክሯ፣እምባዋ ሁሉ ለእኔ ፌዝ ነበር....አሁን አሁን ግን ያቃጥለኝ ይዟል....

ሳምባዬና ኩላሊቴ ተባብረው ሲከዱኝ.... በሽታዬ ከአይኔ ሲያሳብቅ...ሰውነቴ ሲሟሽሽ...ልብሴ እላዬ ላይ መሽተት ሲጀምር....መኖሬን የሚያስተውል ሰው ሲጠፋ...ሞት ሞት ሲሸተኝ....ይሄኔ ኪሳቸውን ካወለቅኳቸው ሰዎች በላይ  የእርሷ እንባ እየፈጀኝ ይመስለኛል...

..አሁን የምምገውን ሲጋራ በምቅመው ክኒን ተክቼ ለመኖር እየታገልኩ ነው....ማሂ ከሄደች ሰነባብታለች....አውቃለሁ አትመለስም....

"ምንም አይቆጨኝም....የቻልኩትን አድርጌያለሁ....ያልቆጨው ደግሞ አይመለስም...."...የመጨረሻ ንግግሯ ነበር.....ይበለኝ።

Inspired by the book
...... "ምክር ለወዳጅ"......

"ያለ ይሉኝታ የሚገስፅህ ወዳጅ ብታጣ እርሱን እስክታገኝ ቢያንስ ያለ ይሉኝታ የሚገስፅህ እብድ እንዲሰጥህ ፀልይ....መልካም መካሪ ካለ ህይወት ቀላል ነው...."**

Shewit

የምታተርፉበት ቻናል ነው...ገባ ገባ እያላችሁ
????
https://t.me/shewitdorka

Telegram

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

ለአስተያየታችሁ @Shedorka

**አሁን የሚናደድብኝ ሰው የለም....የሚወቅሰኝ....ለምን የሚለኝ...በቃ ሰላም።
2 Monate, 3 Wochen her
ስንለያይ...ትተሺኝ ስትሄጂ...

ስንለያይ...ትተሺኝ ስትሄጂ...

አንቺ ያጣሽው እኔን ብቻ ነው።

እኔ ግን ያጣውት አንቺንም እኔንም ነው !

ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ

2 Monate, 4 Wochen her
ብታይ ምንም በኔ ምርጫ የሆነ ነገር …

ብታይ ምንም በኔ ምርጫ የሆነ ነገር የለም።አብዛኛው የሚወደኝም፥ሆነ የሚጠላኝ፣የምወዳቸውም ሆነ የምጠላቸው ነገሮች የኔ ምርጫ አይደሉም፣መልኬ የኔ ምርጫ አይደለም፣ይሄን አፍንጫ ይሄን ጥርስ ይሄን መልክ ስጠኝ አላልኩትም።

ቢገባሽ አሁን ያለሁበትን አካባቢም ሆነ አሁን ያለሁበትን ሁኔታ አልመረጥኩት ይሆናል።ባልመረጥነው ነገር ለምንድነው የሚወቅሱን?የተመረጠልንን ነገር መቀበላችን ጥፋት ነው?ብታውቂ አሜን ብለን ከመቀበላችን በፊት ለመቀየር ብዙ ሞክረናል፥ቶሎ እንዳልተሰጠን ሁሉ ቶሎ መቀየር አልቻልንም።ምናለ እስክንቀይረው ድረስ በወቀሳችሁ ያለንበትን እንድንጠላው ባታስገድዱን?
ሰዎችን ከእነ እንከናቸው የሚወዱ ሰዎች ወደየት አሉ?ገራገር ሰዎች አሉ አይደል?ፈጥረሃል?

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ቢገባሽ ወዳንቺ የመጣሁበትን መንገድ መርጬው አይደለም።ምናልባትም የማውቀው፥ የተመረጠልኝ መንገድ ይሄ ብቻ ነበር።በርግጥ ከማውቃቸው ሴቶች መካከል መርጨሻለሁ።ቢሆንም አንቺን ማወቄ እንጂ አንቺን መውደዴ የኔ ምርጫ አልነበረም።ወደ መንገዱ ያመጣን ማን እንደሆነ ባላውቅም አብረን እነድንጓዝ ፈልጉ ነበር።ምናልባት ያለያየን ወደ መንገዱ ያመጣን ነው።

አንዳንዴ ምንም ሳንሆን መጣላታችን ይገርመኛል፥ታውቂያለሽ አሁቃለሁ ምንም አላጠፋሽም አላጠፋሁም።በቃ አላውቅም አንደበፊቱ እንዳናወራ፣እንደበፊቱ አብረን እንዳስቅ የሚያደርግ የሆነ ነገር አለ፥እሱን ሁለታችንም አናውቀውም።ምናልባት ያገናኘችን ይቺ ወረተኛ አለም እንድንተዋወቅ፥እንጂ አብረን እንድንኖር አላገናኘችንም።

ምናልባት ይቺ ማትረባ አለም በገደብ እና በመደብ አጥር ስላጠረችን፣አጥሩን በፍቅር መሻገር ተስኖናል።

*ውዴ ግማሹ ሰው ሊመርጥ ግማሹ ደግሞ ሊመረጥለት ይሆን የተፈጠርነው?

እኔ አላውቅም አንቺስ?*

ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ

2 Monate, 4 Wochen her
? የ ተ ቀ ደ ደ …
3 Monate her

ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የምከታተለው ትምህርት ነበረኝ። ረፍዶብኛል...ተጣድፌ አንዱ ታክሲ ውስጥ ገባኹ።ታክሲው ሞልተል ፤ ረዳቱ መጥራቱን ቀጥሏል።ሦስት ሦስት አድርጎ ሊያስቀምጠን ነው መሠለኝ።ተጠጋ ሳልባል ቀድሜ ጠጋ ብዬ ለመቀመጥ ስላሰብኹ አጠገቤ የተቀመጠውን ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ አየሁ...ሴት ነች...አየኋት፤አየቺኝ...ተጠጊ እንደማለት አይን ለአይን ተፋጠን ቀረን...ተፋጠጥን።
እኔ በቅርቡ የተጣላዋትን ፍቅረኛዬን መስላኝ ነበር ማፍጠጤ...ሰማያዊ ሁዲ፣በቀሚስ፣ፀጉሯ ፍሪዝ ተሰርታለች።
...በእውነት እሷም የተለያየን ቀን እንዲህ ተመሳሳይ ነገር ነበራት...ይሄ ምስሏም ለወራት በሕሊናዬ ጓዳ እያጮለቀ ከአዕምሮዬ አልጠፋ ብሎ ሰላም እየነሳኝ ነበር። ዛሬ ደግሞ የቀን ቅዠት ይመስል በአካል ባያት ነው ማፍጠጤ...እርሷስ ለምን ይሆን ያፈጠጠቺብኝ?

...እንደገመትኩት ለሦስት አስቀምጦ ጉዞ ጀመርን...በየመሐሉ ሰረቅ አድርጌ አያታለኹ...ሐሳቧን መሰብሰብ ያቃታት ይመስል...ስልኳን ታበራ እና መልሳ ታጠፋለች፣ በመስኮት አሻግራ ትመለከታለች...ከመገናኛ፣በሾላ፣ኢንግሊዝ ኤንባሲ፣ቀበና አድርገን አራት ኪሎ ሥላሴ ቤተክርስቲያን ጋር ስደርስ እርሷ ቀደም ብላ "ወራጅ" አለች ፤ ድምጿ ደስ የሚል ለዛ ነበረው ።

...ወረድኹና እርሷ እስክትወርድ መንገድ የጠፋበት ሰው ይመስል ዙሪያ ገባውን እየቃኘው ጠበኳት። እርሷ ሌላ አንድ ወራጅ ከወረደ በኋላ ተከትላው ወረደች...ስታየኝ እንደመደንገጥ ብላ ወደ ድል ሐውልቱ አቅጣጫ መራመድ ጀመረች።

ተከተልኳት...ስሟን አላውቀውም ማን ብዬ ልጥራት? "እናት እናት..." ዞረች  የማላውቃትን ሴት አናግሬ አላውቅም...ምን ብዬ ላውራት ?..."መተዋወቅ እንችላለን ?" አልኋት እንደምንም ራሴን አደፋፍሬ...እርሷም አላሳፈረቺኝም "ይቻላል።" አለችና እጇን ዘረጋጅልኝ ።ከደስታ ብዛት ፈገግ ብዬ "ሶፊ ሶፎኒያስ እባላለሁ " አልኋት ። "እሺ ዳግማዊት እባላለሁ።" አለች እጄን ሳትለቅ።

"ቅድም አፈጠጥኩብሽ አይደል ? ከቀድሞ ፍቅረኛዬ ጋር ተመሳስለሽብኝ እኮ..." ( አሁን እንዲህ ይባላል ?)
ልጅት ነገረኛ ቢጤ ናት አፏን ሾል አድርጋ " የሚመስላትን ከምትፈልግ ራሷን ይቅርታ ብትጠይቅ አይሻልም? " አለች።
"እኔ መች አጠፋው አልኹሽ?" አልኋት እንደ ከዋክብት የሚያበሩ አይኖቿን ለማየት እየጣርኹ።
ሳቅ አለችና " ያጠፋ ብቻ አይደለም ይቅርታ የሚጠይቀው፤የምትወደውን ላለማጣት አንዳንዴ ይቅርታ ትጠይቃለህ ።"
"መቼ ነው ደግሞ እወዳታለኹ ያልኹሽ?" አልኋት የምር ግራ እየተጋባው።
"ባትወዳት ነው ሰው ሁሉ እርሷን የሚመስልህ ?"
ሳቅኹ...ይቺ ነገረኛ አሳቀቺኝ !
"እኔ እዚህ ጋር ነኝ፣ ክላስ አለኝ" አልኋት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጁ ጋር ስንደርስ።
"ኦ ተማሪ ነህ? " አለች ።
"አዎ ነገረኛ ከመሆን አይሻልም ?" አልኋት ጥያቄዋን በጥያቄ እየመለስኹ።
"ማነው ነገረኛ አንተ ! " አለች ትከሻዬን መታ አድርጋ እየሳቀች።

ሌላ ጊዜ ልንገናኝ ተነጋግረን ስልክ ከተለዋወጥን ልክ ዛሬ አንድ ወር ሆነው። ነገር ግን ተደዋውለንም ሆነ ተገናኝተንም አናውቅም።

ልደውልላት እንዴ ?

ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
(ከሕመሜ ሳላገግም የፃፍኩት።)
©ሶፊ

3 Monate her

ና ብላ ጠራችኝ፤ና ስትለኝ.....ምንም የሚያስቸኩል ስራ ቢኖር ጥዬው ነው ወደ እሷ የምሄደው ፀባይዋን አውቀዋለሁ! የምትፈልገውን ለማግኘት በጣም ችኩል ነች ያሰበችውን ወዲያው አድርጋ እስክትጨርስ እንቅልፍ የላትም...!
ና ልኝ አለችኝ የህይወቴን ብዙ ጊዜ የወሰደውን ፕሮጀክት ጥዬ ሄድኩ...ብዙ ጊዜ የምናዘወትርበት ቤት አለ...ቀድማ ደርሳ እየጠበቀችኝ ነበር ...ደረስኩ ..በር ላይ
አስተናጋጇን ሰላምታ ሰጥቻት ስገባ በፈገግታ "ውስጥ ናት" አለችኝ። ወደ ውስጥ ገባሁ ዘውትር የምንቀመጥበት ቦታ ተቀምጣለች ሳያት ደስ አለኝ...እንደተለመደው ቀለል ያለ አለባበስ ለብሳለች...ጌጥ ማብዛትና መቀባባት አትወድም ለምን ብዬ ስጠይቃት "መንኳተት ነው።" ብላነግራኛለች።ያለኝ ይበቃኛል ብላ ስለምታስብ ይሆን?
...ስገባ ጀርባዋን ሰጥታ ተቀምጣ አገኘዋት። ኮቴዬን አጥፍቼ ተጠጋዋትና አይኖቿን በእጆቼ ሸፍኜ፤ድምፄን አጎርንኜ "እኔ ማን ነኝ?" አልኳት።ደስ በሚለው ፍልቅልቅ ሳቋ እንደታጀበች "የኔ ሶፊ አይደለህ?" አለችኝ። አንገቷን ስሚያት ከፊት ተቀመጥኩ።
"ምነው ስራ የለም?" አልኳት እጇን ልይዛት እጄን እየሰደድኩ።
"ዛሬ አብረን እንድንውል አስፈቅጄ መጣሁ።"
"ዛሬ ምን ተገኘ?"አልኳት መልሷን ለመስማት በመጓጓት...ያለ አንዳች ምክንያት..ከስራ እንደማትቀር አውቃለሁ።
"ምሳ እንድንበላ እና እናወራለን ብዬ ነው" አለቸኝ ፈገግ እንዳለች ። ከፈገግታዋ ላይ አንዳች ሐዘን አነበብኩ ውስጤ ፈራ...ምሳ ተመግበን እንደጨረስን ቡና ወደ ምንጠጣበት ስፍራ አመራን እዛ ለማውራት ይመቻል። ቡናችንን ጠጥተን ወሬ አልቆቡን ተፋጠጥን "ምንድነው የምትነግሪኝ ? " አልኳት። ዝምታውን ለመስበር እጇን እያፍተለችለች ለመናገር ብዙ አመነታች። ዝም ብዬ አይን አይኗን እያየሁ ታገስኳት...ለመናገር ጨንቋት የምታፍተለትለውን እጇን ያዝኩት..ቀስ ብላ አስለቀቀችኝ (እንደቀደመው ጊዜ አጥብቃ አልያዘችኝም) ምንም ቃል ሳትተነፍስ ለልደቷ ቀን ያጠለቅኹትን፤በደስታ እንባ እያነባች የተቀበለችውን ቀለበት አውልቃ መሃላችን አስቀመጠችው።ፈጽሞ ያልጠበኩት ነገር ስለነበር ዱብ እዳ ሆነብኝ አፌ ተሳሰረ..."ምም ምንድነው?" አልኳት በሚርበተበት አንደበት።
...ይሄን ጊዜ የእሷ እንባ እየወረደ ነበር ።ወትሮም እንባ ይቀድማታል።ላባብላት ብፈልግም አልቻልኩም ።እጄን አጣምሬ የሆነውን እንቆቅልሽ ለመፍታት በሐሳቤ መብሰልሰል ያዝኩ።ለዚህ የሚያደርሰን ምንም ፍንጭ አጣኹ።የሁሉን ነገር መልስ አጠገቤ አስቀምጬ እሷ ከምትጨነቅ ብዬ እኔ የማላቀውን መልስ ፍለጋ ብቻዬን ኳተንኩ።ከንቱ ልፋት!
በረጅሙ ተንፍሼ "ምንድነው የተፈጠረው ?" ብዬ በድጋሚ ጠየኳት ።
ጉንጯን ጠረግ ጠረግ አድርጋ መናገር ጀመረች..."ምንም አልተፈጠረም ሶፍ አንተ ምንም አላደረክም አንተ እየቻልክ ያላደረክልኝ፤ ያጎደልክብኝ ነገር የለም ።እመነኝ እኔም ልወድህ አንተ ለኔ እንደኖርከው እኔም ለአንተ ብቻ ልኖር ከራሴ ጋር ታግያለሁ...ግን አልቻልኩም።"
....ቀስ በ ቀስ ሰውነቴ እየከዳኝ ሲሄድ ይታወቀኛል ።አፍና አእምሮዬ አልተባበሩም እንጂ "ምንኑን ነው ያልቻልሽው?" ብዬ ልጠይቃት ፈልጌ ነበር ።
ቃላቶቹን እየታገለች እንደምታወጣቸው ያስታውቃል፤ከልብ የጠለቀ ሐዘኔታን አዝለዋል።ንግግሯን ቀጠለች..."ካንተ ጋር የተገናኘነው በአጋጣሚ ነው....ተቀራርበን ለዚህ በቃን...ግን ፍቅራችን አይመጣጠንም...እኔ አንተ እንደምታስብልኝ አላስብልህም...አንተ እንደምትንሰፈሰፍልኝ..." ሳግ ተናንቋት ንግግሯን ለአፍታ አቋረጠች ..."ከዚያም በላይ ህሊናዬን ያቆሰለው ነገር፤ በስራ አጋጣሚ የተዋወቅነው አለቃዬ ለእርሱ የተለየ ስሜት አለኝ። አንተ እንደዚህ እየሆንክልኝ..እኔ ግን ከአንተ ስሜት በላይ ለእርሱ ስሜት እጨነቃለሁ። ካንተ ሃሳብ በላይ የእርሱ ሃሳብ ያሳስበኛል ። ኋላ ላይ ለአንተ ያለኝን መውደድ ከእሱ ጋር ስመዝነው የእሱ በለጠና ሀፍረት ተሰማኝ ....ከዚህ የህሊና ዳኝነት ለመዳን ይበልጥ ወዳንተ መቅረብ ፈለኩኝ የእርሱን ፍቅር በአንተ መውደድ ልሽር ከራሴ ጋር ታገልኩ...ራስን እንደማሸነፍ ያለ ከባድ ጦርነት የለም።ራሴን ማሸነፍ አቃተኝ ልቤ ለእርሱ አደላ ልብ በስሜት ነው የሚያምነው ለሌላ ሰው ባለን ፍላጎት እንጂ እንደ ህሊና ትክክል ነው ወይም አይደለም በሚል ፍርድ አይመዝንም። ከፈለገ ፈለገ ነው የትኛውም ህግ አያቆመውም፤ፍቅር ውለታንም አይቆጥርም እናም ራሴን ማሸነፍ አቃተኝ፤ አንተንም አብልጬ መውደድ አቃተኝ።
...አሁን የሁለታችሁም መሆንን አልሻም ብቻዬን መሆን ነው የምፈልገው ለእኔ የሚገባኝ ይኸ ቅጣት ነው። ያን ሁሉ ስሜትህን መና ስላደረኩት በጣም ይቅርታ።" ብላ ወደ ጉልበቴ አጎነበሰች በእጄ ደግፌ ቀና አደረኳት...
ጠረጴዛ ላይ ያስቀመጠችውን ቀለበት አንስቼ ለማርያም ጣቴ አጠለኩት...
"ፍቅሬ መና አልቀረም....የሰጠሁሽ እንድትመልሽልኝ አልነበረም ።" ብዬ በእርጋታ ከመቀመጫዬ ተነሳሁና ጉንጯን ሳምኳት...
"ቸር ይግጠምሽ!" ብዬ የብቸኝነት ጉዞዬን ጀመርኩ ።

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ከወራት በኋላ ምሳ ሰዓት ላይ ምሳ ከተመገብኩ በኋላ ቡና እየጠጣሁ Facebook ስጠቀም የሚያስደነግጥ ነገር ተመለከትኩ የእኔ እላት የነበረች አንዲት ሴት በቬሎ ተሞሽራ አየሁ።አይኔን ባለማመን ምስሉን አቀረብኩት ምንም እንኳን make up ብትጥለቀለቅም መልኳ አልጠፋኝም ራሷ ናት።

ጠላኋት!
ከመጀመሪያው ፍቅሬ የአሁኑ ጥላቻዬ በለጠ።

ከተቀደደው ማስታወሻ
©ሶፊ

3 Monate, 1 Woche her
? የ ተ ቀ ደ ደ …
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 4 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 2 days, 12 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 3 days, 10 hours ago