Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 7 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 2 months, 1 week ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 1 month, 2 weeks ago
አስቡት...🤔🤔
ዛሬ ላይ ስልካችን ላይ ከምናጠፋው ጊዜ አንድ አራተኛውን ለቁርዓንና ጥሩ መፅሐፎችን ለማንበብ ብናውለው የት መድረስ እንድምንችል አስባቹታል!!!!
በህይወታችን ትልቅ ተዓምርን መፍጠር እንችል ነበር፤ ከራሳችን አልፈን ለሌላውም የምንበቃበት አቅምን እናፈራ ነበር።
አስቲ እናስብበት!!!
Yeroo ammaa kana sa'aati bilbila keenya irratti dabarsiinu irraa tokko afraffaa isaa osoo quraana dubiisuufi kitaabban gaggaarii dubbiisuudhaaf olchine jireenya keenya keessatti waan ajaa'ibaa fiduu dandeenya ture, waan mataa ofiiti fi ummata keenya ittin gabbifannu argachuuf carraa qabna ture.
Itti haayaannu!!!
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
የአጎቶና የአክስት ልጅ ጉዳይ❗️❗️❗️
አሁን ላይ በጣም ከተዘናጋንባቸው ጉዳዮች አንዱ የአጎቶ ልጅ፣ የአክስት ልጆች እየተባለ ችላ የሚባለው ነገር ነው። ብዙ ወንድምና እህቶች የአጎት ልጅም ሆነ የአክስት ልጅ አጅነቢ( ሊጋቡ የሚችሉ) መሆናቸውን አያውቁም። አብዛኞቻችን ሙህሪም( እነርሱን ማግባት የማይፈቀድ) አድርገን እናስባቸዋለን። አክስት እናት ናት ተብሎ ሲለሚታሰብ የአክስት ልጅም እህት ናት ተብሎ ሴት እህቶቻችን ከአጎታቸውና ከአክስታቸው ለጆች ጋር የሚደረጉ ልቅ የሆኑ ግኑኝነቶች በኢስላም የተከለከሉ ናቸው።
ምንም ዝምድና ቢኖር እንኳን አንዲት ሴት የአጎቷና የአክስቷን ወንድ ልጅ መጨበጥ፣መነካካት፣ አበሮ ለብቻ መሆን(خلوة)፣ በልቅ ማውራት፣ መገላለጥ አይፈቀድም። ልክ ከሌሎች ወንዶች እንደምትሸፈነው ሁሉ ከአጓቷ እና ከአክስቷ ልጆም ልትሸፈን ይገባል። ይህ ካልሆነ ግን የሚመጣው መዘዝ ከባድ ነው። የአጎቴ ልጅ ናት የአክስቴ ልጅ ናት እየተባለ እንደፈለገ የሚቀርባት ከሆነ ሶስተኛቸው ሴይጣን ሆኖ ስህተት ላይ መውደቃቸው የማይቀር ነው።
ይህ ጉዳይ አሁን ላይ ግን የተዘናጋነው ይመስለኛል። ብዙ ነገሮችን እየሰማን እየተመለከትን ነው። ስለዚህ ትኩረት ሰጥተን አላህ ያዘዘንን ልንጠነቀቅ ይገባል።
ልብ ያለው ልብ ይበል!!!!
والله اعلم
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
ምስጋናን ከሰዎች አትጠብቅ!!!!
በምትሰራው ስራ የሰዎችን ውዳሴና ሙገሳን አትጠብቅ። ሰዎች የቱንም ነገር ብታደርግላቸው፣ ምንም ብትሰጣቸው አንድ ቀን ተመልሰው አንተን መስደባቸው፣ አንተን መናቃቸው የማይቀር ነው። አንተ እየቀረብክ በሄድክ ቁጥር ዝቅ ያደርጉሃል፣ ይንቁሃል። ይሄ የአብዛኞቻችን ባህሪ ነው።
ስትሰራ በምትሰራው ነገር ልትረካ ከፈለግክ ለአላህ ብለህ ስራ፤ ለራስህ ህሊና ስትል አድርገው። ያኔ ሰዎች ቢሰድቡህም፣ ቢያንቁዋሽሹህም ደስታ ይሰማሃል፤ ትረካለህ። የሰዎች ምላስ ምንም ሆኖ አይታይህም። ያ ካልሆነ ግን ትጎዳለህ፤ መስራት የሚገባህን ሳትሰራ ወደ ኋላ ትቀራለህ። ሰዎችን ለማስደሰት ስትል የራስህን ደስታ ታጣለህ።
እውነታው ይህ ነው ተቀበል!!!
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
بسم الله الرحمن الرحيم
❤️ አባቴ ምን ብዬ ላመሰግንህ!!!
"" አባቴ!! ለኔ ብለህ የምትከፍለውን ዋጋ አንዴት ብዬ ልግለፀው። ለኔ ስትል የሰው ፊትን አይተሃል፣ ለኔው ስትል ክብርህን አጥተሃል፣ እኔ እንዳምር አንተ ቆሸሃል፣ የኔን መሳቅ ለማየት ስቃይህን ደብቀህ ኖረሃል፣ የቤትህን ሃላፊነት ተሸክመህ ቀን ከሊት ደክመሃል፣ ቤተሰብህ በሰላም እንዲተኛ በዙ ለሊቶችን ያለ እንቅልፍ አሳልፈሃል። ያንተ ነገር ምን ብዬ እንደማወራ አላውቅም። ቃላቶች ያጥሩኛል።
አንዳንዴ ወላሂ የኛ ነገር ይገርማል። ለኛ ብሎ የቆሸሸውን አባት ሰዎች ዘንድ ላለመናቅ አባታችንን እንርቃለን፣ መንገድ እንቀይሳለን። ለኛ ማማር ሰበብ የሆነውን አባት፣ ለኛ ሲል ህይወት ያጎሳቆለችውን የቤት ምሶሶ ሰዎች ዘንድ ክብሩን እንገፈዋለን። ከዚህ በላይ ዝቅተት፣ ከዚህ በላይ ውለታ ቢስነት ምን አለ?? የፈለገውን መብላት፣ መጠጣት፣ መልበስ እየቻለ ልጆቼ ያለን አባት ከብሩን ዝቅ ከማደረግ በላይ ምን ውረደት አለ።
አላህ ይጠብቀን።
አባቴ!!! ረጅም ዕድሜ ከጤናና ኢማን ጋር ይወፍቅህ። ለኔ ስትል ዝቅ ብለሃልና አላህ ከፍ ያድርግህ። ያንተን ደስታ በሁለቱም ሀገር ያሳየኝ። እኔን የምትጠብቀኝ ቦታ አለና በህይትህ አሳይቶህ ያስደስትህ። አላህ ጀነትን ወፍቆህ የረሱል ጎረቤት ያድርግህ? አሚን!!!!
አላህ በህይወት ያሉትን ረጅም ዕድሜ ከጤና ጋር ይሰጣቸው። የሞቱትን አላህ የጀነት ያድርጋቸው??
والله اعلم
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
بسم الله الرحمن الرحيم
" Waan argatteef hin boonin. Argachuun kee nama hunda irra caalmaya qabda jechuu miti. Tarii kan hin argatiin sadarkaa hedduudhaan si caaluu mala. Qabeenya argatte jechuun warra qabeenya hin argatin irra jaallatamta jechuu miti, beekkamtii argatte jechuun isa hin beekkamne irra nama biratti jaalatamta jechuu miti.
Hundinu qormaata, Tarii Rabbiin si qoruuf qabeenyaas ta'ee beekkamti siif kanne ta'a. Kana wallaalte qormaata akka hin kufne of eggadhu!!!!
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
بسم الله الرحمن الرحيم
❤️ እናቴ አላህ ምንዳሽን በጀነት ይክፈልሽ!!!
" ስለ እናት ሲነሳ ሁሉም ስሜታዊ ይሆናል። የእናት ነገር ማንንም አያስችልም። ጤናማ ሆኖ እናቱን የማይወድ የለም። እናት ከቃል በላይ ናት። እናትን እንዲህ ናት ብሎ መናገር ይከብዳል፤ እርሷን ለመግለፅ ቃላቶች ያንሳሉ። የርሷን ውለታ መመለስ የሚችለው አንዱ አላህ ብቻ ነው።
እናት እናት ናት፤ በዚህ ዓለም ተተኪ የሌላት ውድ ናት። የእናትን ነገር ጀምሮ መጨረሱ ይከብዳል። እናት ለኛ የከፈለችው ዋጋ እንዲህ ብሎ የሚገለፅ አይደለም። ብዙ ነገሮችን ደብቃ፣ ለኛ ስትል የሰው ፊት ገርፏት፤ ለኛ ደስታ ብላ በየመንገዱ ተንቃ፣ እኛ አንገታችንን ቀና እንድናደርግ እርሷ ዝቅ ብላ የኖረችልን የአላህ ስጦታ ናት። የኛ እዚህ መድረስ የርሷ ልፋት ውጤት ነው።
እስቲ አንዳንዴ እኛን እንዴት እንዳሳደገችን ጠጋ ብለን እንጠይቃት፤ አንዳንዴ ያለፉ ታሪኮቿን ታውጋን። ወላሂ የበለጠ እንወዳት ነበር፣ ለኛ የከፈለችውን ዋጋ የበለጠ እንረዳ ነበር። እናቶች ብዙ ያልነገሩን በውሰጣቸው የቋጠሩት ታሪክ አለ። እስቲ ዛሬ ሁላችንም ትንሽ ስለከፈሉት ዋጋ በትንሹም እንጠይቃቸው። ታሪክ የሚመስሉ ግን በኛው እናት የተከፈሉ ትልቅ መስዋዕትነትን እንሰማለን። እንደው እስቲ እንጠይቃቸው እመኑኝ ብዙ ያልሰማናቸው ታሪኮች አሉ።
እናቴ ላንቺ ምመኘው ትልቁን ጀነት ነው!!! ምንም እንኳን ውለታሽን መመለስ ባልችልም አላህ እኔን መልካም ያድርገኝና ነገ በልጅሽ ምክንያት ነው ይህን ደረጃ ያገኘሽው ለመባል ሰበብ ያድርገኝ። አላህ ይጠብቅሽ!!
ረጅም ዕድሜ ከጤና ከኢማን ጋር ይለግስሽ?
والله اعلم
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
بسم الله الرحمن الرحيم
እንተዛዘን!!!!
"" ይህች ዓለም የፈተና ዓለም ናት። አንዱ ሲያገኝ አንዱ ያጣል፣ አንዱ ሲደሰት አንዱ ያለቅሳል፤ አንዱ ጋር ሞልቶ አንዱ ጋር ይጎላል፤ አንዱ ሪዝቁ ሰፍቶ ነገሮች ሲመቻቹለት አንዱ ጠብቦት ያለቅሳል። ይሄ የዚህች አጭር ዱንያ ህይወት መገለጫ ነው። ዱንያ ጎዶሎ ናት። ሞላለኝ የሚል አንድም የለም፤ ሊሞላም አይችልም።
አላህ የፈለገውን ይፈትናል። የፈለገውን ሪዝቁ አስፍቶ ይፈትነዋል። የፈለገውን ደግሞ ሪዝቁን አጥቦበት ይፈትነዋል። አንዱን የሚፈልገውን ሰጥቶ ሲፈትነው ሌላውን ደግሞ የሚፈልገውን በመከልከል ይፈትነዋል። ሁሉም ተፈታኝ ነው። አንተ ስላለህ ከሌለው ትበልጣለህ ማለት አይደለም። ምናልባት በላጩ እርሱ ሊሆን ይችላል። አንተ ስላልተፈተንክ ፈተና ከበዛበት ሰው አላህ ዘንድ ተወዳጅ ነህ ማለት አይደለም። ምናልባት እሱ ካንተ በብዙ እጥፍ የተሻለ ሊሆን ይችላል። ብልጫ ልብ ውስጥ ባለ ጠንካራ እምነት ቢቻ ነው።
ታዲያ ወንድሞቼ የተፈተኑ ሰዎች ስንመለከት እንዘንላቸው። ከተቻለን በተቻለን አክል እንርዳቸው። ካልተቻለን በጥሩ ቃላቶች እናፅነናናቸው። የተፈተኑን በእምነታቸው ከሆነ አላህን እንለምንላቸው። እነርሱ ያጡትን እኛ ስላገኘን ኩራት እንዳይሰማን። ችግሯቸው የሚጠይቁን ፣መንገድ ላይ ቁጭ ብለው ከኛ የሆነን ነገር የሚፈልጉ ሰዎች አላህ ሱ.ወ ፈትኗቸው ነው እንጂ እነርሱ ባንተ ቦታ አንተ በነርሱ ቦታ ማድረግ አይሳነውም ። አንዳንዴ የኛ ነገር ያስገርማል። የልብን የሚያውቀው አንድ አላህ ብቻ ነው። እኛ የሰዎችን ልብ አናውቅም። ከኛ የሚጠበቀው ከቻልን መርዳት ካልቻልን ጥሩ ቃልን መናገር ነው። ቁም ነገሩ አንተ ለርሱ ብለህ መስጠትህ እንጂ እርሱ ስለዋሸ ስላታለለ አይደለም ነገሩ። ስለዚህ ሰዎችን ከነፈተናቸው ለአላህ ሱ.ወ ተዋቸው።
እንዘንላቸው!!!!
والله اعلم
@to2success
@to2success
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
አጭር ግን ትልቅ ሞክር!!!
ጋዜጠኛዋ አንዲት ሙስሊም ዶክተርን አንዲህ ስትል ጠየቀቻት "በመጨረሻም ለሙስሊሙ ወጣት የምታስተላልፊው መልዕክት ካለ እድሉን ልስጥሽ" አለቻት
ዶክተሯም እንዲህ ስትል መከረች "" በመጀመሪያ ወጣቶች እራሳችሁ ላይ ትኩረት በማድረግ እራስን በመገንባት ላይ ስሩ። በመቀጠል በእምነታችሁ፣ በስራችሁ፣ ባጠቃላይ በህይታችሁ ሁሌም ቢሆን ባላቹበት ቦታ ብቁ ለመሆን ሞክሩ። ብቁ ሊያደርጋችሁ የሚችሉ ነገሮች ላይ ተጠመዱ።
በመጨረሻም በትንሹም ቢሆን ብቁ መሆናችሁን፣ በራስ ላይ መስራታችሁን እርግጠኛ ስትሆኑ እናንተን ወደ ተሻለ ህይወት ሊያደርሳችሁ የሚችል፣ የወደፊት ህልማችሁን አብሯችሁ እውን ሊያደርግ የሚችልን ሰው ፈልጉና በፍጥነት ወደ ትዳር ግቡ። እንዲህ ማድረጋችሁ ምናልባት አሁን ካላችሁበት 10 እጥፍ የተሻላችሁ እንድትሆኑ ሊረዳችሁ ይችላል።"
ትልቅ መልዕክት ነው። ወጣቱ ቅድሚያ እራስሱ ላይ መስራት ይገባዋል። በተቻለው ልክ ቀድሞ ለወደፊት ህይወቱ በእምነቱ፣ በስራው የተሻለና ብቁ ለመሆን አስፈላጊ የሚባሉት ነገሮች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ይጠበቅበታል። ሰው ብቻውን ምንም ቢሆን ጎዶሎ ነውና ቀጣይ ከጎኑ ሆኖ የጋራ ዓላማን ለማሳካት ከጎኑ ሆኖ ሊረዳው የሚችልን ሰው ፈልጎ መጣመር አለበት።
ጥሩ መልዕክት ከጥሩ አገላለፅ ጋር ነው!!!!
والله اعلم
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
بسم الله الرحمن الرحيم
አንብብ!!!
""የጌታችን አላህ ሱ.ወ የመጀመሪያ መልዕክት አንብብ ነው። የመጀመሪያው ትዕዛዝ አንብብ ነው። የጌታችን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰማው ቃል አንብብ ነው። አዎ የሙስሊሙ ኡማ የአንብብ ትውልድ ነው።
ንባብ የአዕምሮ ምግብ ነው። ያለ ንባብ አዕምሮ ይቀነጭራል፣ ይከሳል። አካል ምግብ ካላገኘ እድገት እንደሚያቆም ሁሉ አዕምሮ ካሆነናል። እድገት ያጥረዋል፤ የአመለካከት አድማሱ ይጠባል፤ የተሻለ ሃሳብ የማመንጨት አቅሙ ይደክማል።
ሰዎች ሲያነቡ አመለካከታቸው ይቀየራል፣ ብስለታቸው ይጨምራል፣ ለነገራት ያላቸው እይታ ይሰፋል። አንባቢዎች ብዙ አያወሩም፣ ሲያዘሩም እንዴት ማውራት እንዳለባቸው ያቃሉ። ስሜታዊነት አያጠቃቸውም። የሚያነብ ማሕበረሰብ ለዕድገት፣ ለለውጥ፣ ለስልጣኔ የቀረቡ ናቸው። ይህንን ለመረዳት ወደ ኋላ ተመልሶ ታሪክን ማጥናት ይቻላል። ሙስሊሞች አንባቢዎች በነበሩበት ዘመን፣ ለንባብ ጥልቅ የሆነ ፍቅር ባላቸው ዘመን የስልጣን ማማ ላይ ለመድረስ ችለዋል፣ ለዓለም ብዙ አበርክተዋል።
ዛሬ ላይ ግን ብዙ ከንባብ በመራቃችን፣ ለእውቀት ያለን ቦታ የወረደ በመሆኑ የሌሎች ተከታይ ሆነናል። ሌሎች እኛ ልንተገብረው የሚገባውን ተግባር በመፈፀማቸው አሁን ላይ የስልጣኔ ማማ ላየ መቀመጥ ችለዋል። ሌሎች ሲያነቡ፣ ለእውቀት ቦታ መስጠት ሲጀምሩ እኛ ወደ ኋላ በመቅረታችን ከኋላ ሆነን እንድንመለከት ተደርገናል። እስቲ አንድ ጥያቄ እራሳችንን እንጠይቅ??
በዓመት ስንት መፅሐፎች እናነባለን???
መልሱን ለናንተው ልተወው!!!
ኑ!!! ወደ ንባብ እንመለስ!!! የኢቅራዕ ትውልድ ነን እና በተግባር እናሳይ!!!
والله اعلم
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
بسم الله الرحمن الرحيم
" ሙስሊሞች ላይ የተከፈተው ዘመቻ ዛሬ የጀመረ አይደለም። የጠሚዎች አባት የሆነው ኢብሊስ ሙስሊም እና የሙስሊም ህግጋት ላይ ጦርነት የከፈተው ዛሬ ሳይሆን ያኔ ለሰው ልጆች አባት አደም መስገድ እንቢ ብሎ እኔ የተሻልኩ፣ በላጭ ነኝ ባለ ጊዜ ነበር።"
"" መገላለጥ የስልጣኔ ምልክት ሳይሆን የድንቁርና፣ ተፈጥሮን የመቃረን መገለጫ ነው።""
"" የኢስላም ጠላት ሴት ልጅ ጋጥወጥ፣ ይሉኝታ የሌላት፣ ከምዕራቡ ዓለም ጋር እኩል እንዲሆኑ ነው የሚፈልጉት። የኢስላም ስምን የተሸከመ ሙስሊም ብቻ መፍጠር ነው ምኞታቸው።""
"" መገላለጥ ሲበዛ ወንዶች ይፈተናሉ። ፈተና ሲበዛ ደግሞ ትውልድ ይመክናል።""
"" ትላልቅ ሁሉም ሚስማማበት ችግር(ድህነት፣ የሰው ነፍስ) እያለ ሂጃብ ላይ መዝመት ኢስላምን ለማጥፋት እንደተነሱ ያመላክታል።""
"" የሴቶች አባቶች፣ ሴቶች ሂጃብ ላይ በሚመጣባቸው ፈተና ሊታገሱ ይገባል። አማኝ ማለት ተፈትኖ ያለፈ ነው።""
"" ሁሉም ሰው ተቻለው ልክ ኋላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።""
✍ ሙሉ ቃል በቃል ባይሆንም ዛሬ ኹጥባ ላይ ከተነገሩ መልዕክቶች( በ ኡ. አህመድ አደም)
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 7 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 2 months, 1 week ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 1 month, 2 weeks ago