Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 6 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 month ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 1 week, 6 days ago
ትራምፕ ቲክቶክ አሜሪካ ውስጥ የተወሰነ ጊዜ ሳይዘጋ እንዲቆይ ማድረግ አስፈላጊ ሊሆን እንደሚችል ገለጹ።
የምርጫ ቅስቀሳ በሚያካሂዱበት ወቅት በቲክቶክ በቢሊዮን የሚቆጠር እይታ ማግኘታቸውን የገለጹት ተመራጩ ፕሬዳደንት የቪዲዮ ማጋሪያው ሳይዘጋ ለተወሰነ ጊዜ እንዲቆይ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
የአሜሪካ ሴኔት ቲክቶክ የብሔራዊ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በመጥቀስ ነበር ንብረትነቱ የቻይናው ባይቲዳንስ የሆነውን መተግበሪያ በአሜሪካ ውስጥ እንዲሸጥ ወይም እንዲታገድ የወሰነው።
የቲክቶክ ባለቤቶች ጉዳዩ በህግ እንዲታይላቸው የሚፈልጉ ሲሆን የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ጉዳዩን ለመስማት ፍቃደኛ ሆኗል።
የአሜሪካና የቲክቶክ ፍጥጫን በዝርዝር ያንብቡ፦ https://bit.ly/3Du5ijO
የዛምቢያ ፖሊስ የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት ሀካንዴ ሂቺለማን ለመግደል ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ጠንቋዮችን ይዣለሁ ብሏል።
ፖሊስ በመግለጫው ላይ እንደጠቀሰው ሁለት ጠንቋዮች በዋና ከተማዋ ሉሳካ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በተለምዶ እስስት የተሰኘችው ተሳቢ እንስሳን ጨምሮ ሌሎች ቁሳቁሶች መያዛቸውንም አመላክቷል።
"ጠንቋዮቹ" ፕሬዝዳንቱን ከገደሉ 73 ሺህ ዶላር እንደሚከፈላቸው ከቀጣሪዎቻቸው ቃል ተገብቶላቸው ነበር ተብሏል፡፡
በቀጣዩ ሊንክ ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://bit.ly/49SV9ct
ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ ተጨማሪ ወታደሮችና ድሮኖች ልትልክ መሆኑን የደቡብ ኮሪያ ጦር ገልጿል።
ፒዮንግያንግ ኢላማቸውን ከመቱ በኋላ የሚወድሙ "ሱሳይድ ድሮኖችን" ለሞስኮ ለመላክ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን ነው ጦሩ ያስታወቀው።
ሴኡል፣ ዋሽንግተን እና ኪቭ 12 ሺህ ገደማ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሩሲያ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
በኩርስክ ግዛት በተደረገው ውጊያ ቢያንስ 1100 የሚሆኑ ወታደሮች ተገድለዋል አለያም ቆስለዋል ያለው የደቡብ ኮሪያ ጦር፥ ፒዮንግያንግ ተጨማሪ ወታደሮችን ለመላክ ተዘጋጅታለች ብሏል።
ዝርዝር ያንብቡ፦ https://bit.ly/4iHyAeO
የ2034 የአለም ዋንጫ አዘጋጅ ሳኡዲአረብያ በስታድየሞች ውስጥ የአልኮል መጠጥ ልትከለክል ነው
በሳኡዲ የአልኮል መጠጥ መሸጥ ክልክል ሲሆን በሀገሪቱ ለዲፕሎማቶች ብቻ የተፈቀደ አንድ የመጠጥ መሸጫ ሱቅ ይገኛል። በኳታሩ የአለም ዋንጫ ፊፋ ለመጠጥ አምራች ስፖንሰሮቹ 40 ሚሊየን ፓውንድ የኪሳራ ማካካሻ ክፍያ መክፈሉ ይታወሳል።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3ZVKWst
ሩሲያ በሚቀጥሉት አስርት አመታት ውስጥ ኔቶን ለመዋጋት መዘጋጀት አለባት ሲሉ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ተናገሩ
መከላከያ ሚኒስትሩ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ያሉት ወታደራዊ እቅዶች ሞስኮ በሚቀጥሉት አመታት ለጦርነት መዘጋጀት እንዳለባት የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3DdMZ23
አወዛጋቢው የኡጋንዳ ጦር አዛዥ ካርቱምን እንቆጣጠራለን ሲሉ ተናገሩ
አወዛጋቢ ንግግሮችን በማድረግ የሚታወቀው የኡጋንዳው ጦር አዛዥ ጀነራል ኬነሩጋባ የሱዳን ዋና ከተማ ካርቱምን እንቆጣጠራለን የሚል አዲስ አነጋጋሪ መግለጫ አውጥተዋል።
https://bit.ly/4gj4oF8
በታህሳስ 2 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ደረሰ?
የግል ንግድ ባንኮች ለአንድ ዶላር ከ122 እስከ 124 ብር መግዣ ከ124 እስከ 127 ብር መሸጫ ዋጋ አቅርበዋል።
ባንኮች ያወጡትን እለታዊ ተመን በዝርዝር ይመልከቱ፦ https://bit.ly/4gdNWGw
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ከወደብ ስምምነቱ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ፊት ለፊት ሊወያዩ መሆኑ ተነገረ
አዲስ አበባ ከራስገዟ ሶማሊላንድ ጋር በባለፈው አመት መጀመርያ የወደብ የመግባብያ ስምምነት መፈራረሟን ተከትሎ የጎረቤታሞቹ ሀገራት ግንኙነት ሻክሯል።
https://bit.ly/3OOgJ8k
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ምርጫን ማን ያሸንፍ ይሆን?
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ምርጫ በየአራት ዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን ላለፉት ሰባት ዓመታት የህብረቱ ሊቀመንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ መሃማት ስልጣን ሊጠናቀቅ ጥቂት ወራት ቀርቶታል።
የአፍሪካ ህብረት ባሳለፍነው ነሀሴ ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ጎረቤት ሀገር ኬንያ፣ ጅቡቲ እና ማዳጋስካር እያንዳንዳቸው አንድ ዕጩ አቅርበው ጸድቆላቸዋል።
ይህን ተከትሎም የኬንያ ፕሬዝዳንት ለመሆን አራት ጊዜ ተወዳድረው የተሸነፉት ራይላ ኦዲንጋ በይፋ የህብረቱ ሊቀመንበር ምርጫ ተወዳዳሪ ከሆኑት መካከል አንዱ ሆነዋል።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4f8IFhV
መንግስት ከሚያቀርባቸው 362 መሰረታዊ መድሃኒቶች ውስጥ በሀገር ውስጥ የሚመረቱት 97ቱ ብቻ ናቸው ተባለ
የህክምና ቁሳቁሶችን ሳይጨምር መሰረታዊ የሚባሉ 362 በላይ መድሀኒቶች በመንግስት እየቀረበ እንደሚገኝ በአገልግሎቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አወል ሀሰን ለአል ዐአይን አማርኛ ተናግረዋል።
ከእነዚህም ውስጥ 97 የሚጠጉ የመድሀኒት አይነቶች በሀገር ውስጥ አምራቾች የሚቀርቡ ሲሆን አጠቃላይ ዋጋቸውም 5 ቢሊየን ብር ድረስ የሚያወጡ መሆናቸውን አገልግሎቱ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢያ አገልግሎት በመጪዎቹ 3 አመታት የሀገር ውስጥ የመድሀኒት ምርት አቅርቦትን ወደ 70 በመቶ ለማሳደግ እየተሰራ ነው ብሏል።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3OzMIcp
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 6 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 month ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 1 week, 6 days ago