Ismaiil Nuru

Description
ዘመንን እናሰልማለን እንጅ ኢስላምን አናዘምንም!
ሀሳብ/አስተያየት፦ @Ismaiilnuru_Bot
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago

2 months, 2 weeks ago
Ismaiil Nuru
2 months, 2 weeks ago

በሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ለማጋራት ይህን የምስል ጥራት ፋይል ያውርዱ!

2 months, 2 weeks ago

«ሰለፍዮች» (ሙርጂአቱል ዐስር) ሲሲ በሙርሲ ላይ አምፆ ሲወጣና መፈንቅለ መንግስት ሲያደርግ ኸዋሪጅ አላሉትም።

የሊቢያው ሀፍተር በቀዛፊ ላይ አምፆ በመውጣቱ ኸዋሪጅ አላሉትም። ይልቁንም ወሊየል አምር ብለው ከርሱ ጎን ተሰልፈው ተዋግተዋል።

ዛሬ ላይ ደግሞ ሱዳን ላይ ሀሚድቲ በቡርሃን ላይ አምፆ  ወጥቶ የሀገሪቱ ሙስሊም በከባድ ሰቀቀን ውስጥ እንዲረግፍ እያደረጉ ነው። ሀሚድቲን ኸዋሪጅ ብሎ ደሙን ሐላል ያደረገ ሙርጂአ ግን አላየንም።  ይልቁንም የፈጥኖ ደራሹን አማፂ ቡድን መሪ ደግፈው ከርሱ ጎን የተሰለፉ አሉ።

በንግግር መሪዎችን መወረፍ ከኸዋሪጅነት ይመደባል ብሎ የሚያምነው «የሰለፊ» ቡድን በመሳሪያ አምፆ የወጣውን ኸዋሪጅ ያላለበት ምክንያት አንድ ብቻ ነው!  እርሱም አማፂው ቡድን በሸሪዐ እመራለሁ ብሎ ስላልተነሳ ብቻና ብቻ ነው።

ሲሲ፣ ሀፍተርና ሀሚድቲ ከነርሱ በፊት የነበሩ መሪዎችን የፈነቀሉት በቁርኣን ለማስተዳደር ቢሆን ኖሮ ኸዋሪጅ ብለው ፈትዋ ለመስጠት ጊዜ አይወስድባቸውም ነበር።

የላኢላሃ ኢለላህን ባንድራ አንግቦ የሚዋጋ አካል ምንም የኸዋሪጅ ዐቂዳን ባይሸከም እንኳን እነርሱ ዘንድ ኸዋሪጅ ነው። የእውር ባንድራን ይዞ የተነሳ ደግሞ ምንም እንኳን ቁርኣንን አሽንቀንጥሮ የወረወረ ቢሆን እነርሱ ዘንድ ወሊየል አምር ነው።

በዚህ ጥመታዊ እምነት ዛሬ የሱዳን ሙስሊም የሚጮህለት እንኳን ሳይኖር በረሀብ እየረገፈ ነው።የጦርነቱ ውጤት አንድ ነው፤ ወይ ሀሚድቲ ወይ ቡርሃን ያሸንፋል።ሁለቱም ቢያሸንፉ የሚመሩት በጣጙቱ ዲሞክራሲ ነው። ያ ማለት ሙስሊሙ ይህን ያህል በላእ አልፎበትም ጠብ የሚልለት አንድ ጥቅም የለም።

ለአንዳንድ «ሰለፍዮች» አማፂዎቹን የሚደግፉበት ገፊ ምክንያት ያለፉት መሪዎች ኢኽዋንነት ነው። ኢኽዋኖች ዐልማኒዮች ናቸው ብለው ስለሚያምኑ። የሚደንቀው ግን የሚደግፏቸውም መሪዎች የሚያስተዳድሩት በዐልማኒያ መሆኑ ነው። ፈኢለላሂል ሙሽተካ! 

የቴሌግራም ቻናል ፦ t.me/ismaiilnuru

2 months, 2 weeks ago
2 months, 2 weeks ago

ሴቱን ውለታ ዋይ ወንዱን ውለታ ተቀባይ ያደረገው ማነው?

አንዱ ሷሒቤ ደወለልኝና « ልጅቱ ውጭ ነበረች በሲዋክ ነበር የተጋባችው እና አሁን ሊፋቱ ነበር ምንድን ነው የሚሰጣት?» አለኝ። እኔም « ተገናኝቷታል ወይስ አልተገናኛትም?» አልኩት። « አይ እሷም ውጭ ናት እርሱም እዚሁ ነው አልሄደም ነበር ተገናኝተው አያውቁም» አለኝ። «ኸይር ስራ ቦታ ና »... አልኩትና መጣ... ያው የሲዋኩን ግማሽ እንደሚሰጣት ነገርኩትና ለማንኛውም እስኪ እዚህ ሸይኽ ጋር ደውል አልኩና የሸይኻችንን ሸይኽ ዐብዱለጢፍ (አላህ ከእስር ነፃ ይበላቸውና) ሰልክ ሰጠሁት። ደወለ ... ላውድ አድርገው አልኩት.... ጠየቃቸው.... «ያው ሲዋኩን ገምሶ ይስጣታ እንግዲህ ምን ይደረጋል » ብለው በጣም ሳቁ ። እኛም ደ..ከ.. ምን። ስልኩን ተቀበልኩትና ዘይሬያቸው እየተሳሳቅን ሰላምታ ተለዋውጠን ዘጋሁት።

ሐቢቢ ሠሃባ ስንል ሱና የሆነን ሰደቃህ(ምፅዋት) ለመስጠት ተራራ ላይ ወጥቶ እንጨት የሚሰብር ትውልድ ማለታችን ነው። ለሱና ይህን ያህል ከሆኑ ዋጂብ ለሆነው ሚስት ማስተዳደር ምን እንደሚሆኑ መገመት ቀላል ነው። ሓላፊነትንና ሸሪዐን በደንብ የተገነዘቡ ህዝቦች! እነዚህን በሲዋክና በብረት ቀለበት አይደለም አይፈቀድም እንጂ በነፃም ቢገቡ የሚቆጭ አልነበረም !

የሞባይል ካርድ ከውጭ ለሚሞላለት ወጣት በሲዋክ አገባሀለሁ ማለት ስንፍናን ማስተማር ነው። በዚያ ላይ Mentality ን የሚያማክል ጉዳይ መሆኑም መዘንጋት የለበትም። አንዲት ልጅ አንድ ልጅ በሲዋክ ፍቃደኛ የሆነችለትኮ ችግር ሲመጣ ሲዋክን በቁስ ለክቶ እንዲወረውርላት አይደለም! ሱናን ከማላቅና ለልጁም የፍቅር ቦታን ከመስጠት ነው። ወላሂ የነገሩን ክብደት ለሚረዳ ሰውኮ በሲዋክ ፍቃደኛ መሆኗ ተልቅ የህሊና እዳ ነበር። አንድ ሰው በሲዋክ አግብቶ ሲፈታ ሲዋክ ብቻ ሰጥቶ ሊሸኛት ነው? በቃ የ5 ብር ሲዋክ ! ቻው?!

እርግጥ ነው ሸሪዐው ከተስማማችበት ውጭ ክፈል አይልም። ለዚህም ነው ሜንታሊትን ይጠይቃል ያልኩት። ይገናኛትም አይገናኛትም በኒካሕ ኖረዋል። በሐላሉ ማውራት በራሱ ሐያት ነበረኮ !

ሲዋክ ወርዉሮ የመፍታት ዝግመተ ህሊና ውስጥ ላለ ሰው የሰሓባን መህር ማውራት ምንና ምን ነው?

« ዚና በተስፋፋበት ዘመን መህርን አታብዙ !» የሚለው ዳዕዋ ሰሒሕ ነው! ግን ያሁን ዘመን ወጣት ከትዳር ያራቀው እውነት የመህር መግዘፍ ነው? ! በሲዋክ አግባኝ የሚሉትም ሳይጠፋ ትዳርን የሚሸሹትም ያንኑ ያህል ናቸው! መህር አንድ ጊዜ ተወስኖ የሚከፈል ለዚያውም በዱቤ መከፈል የሚችል ሆኖ ሳለ ወጣቱን ከትዳር ያራቀው መህር ነው? !

መህርን ቀስ ብሎ እንዲከፍል መፍቀድ በራሱ መህርን ማቅለል ነበረኮ ። ዐፍው ማለቱም እንዳለ ሆኖ። ነገር ግን ሃለፊነትና ህሊናዊ ማመዛዘኛ የሌለበት ሲዋክ ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልገዋል ለማለት ነው። የጀሊሉ ብይን እንዲህ ነው ፦ «ሴቶችንም መህሮቻቸውን በደስታ ስጡ፡፡ ለእናንተም ከእርሱ አንዳችን ነገር ነፍሶቻቸው ቢለግሱ መልካም ምስጉን ሲኾን ብሉት፡፡ » (አንኒሳእ 4)

ለመህር ዋጋውን እናስቀምጥ! ከዚያ ከፊሉን ወይም ሙሉውን ተወው ካለችህ ውለታዋን ካለመርሳት ጋር ሐላል ነው ተጠቀመው። ከዚያ ውጭ ግን መህርን ሲዋክ ማድረጉ ልጂቱን በቅናሽ እንዳገኛት የሚሰማው ካደረገው ይህ የሱናንም ክብር ዋጋ ማሳጣት እንዳይሆን የግል ስጋቴ ነው!

ሁሉም ውለታ የሚውለው እርሱ ዘንድ ባለው ነገር ነው። ሴቷ መህሯን ዐፍው ካለችህ ቢያንስ እርሷ ዐፍው ያለችንን መጠን ያለው ገንዘብም ይሁን ቁስ ስጦታ በማበርከት ብንመልስስ? ሴቱን ብቻ ውለታ ዋይ ወንዱን ደግሞ ውለታ ተቀባይ ብቻ እንዲሆን የፈረደው ማን ነው?
ሴቶች በሲዋክ እያላችሁ ወጣቱን አታዳክሙ
ከወደዳችሁት መህሩን ያልተጋነነ አድርጋችሁ ከፈለጋችሁ ዐፍው በሉት! ስንፍና አታስተምሩት!

ስለ ግንኙነት ማንሳት የተፈለገበት አንድ ሰው ሳይገናኝ የፈታትን ሴት የሚሰጣት ግማሽ መህሯን ስለሆነ ነው ።

አላህ በተከበረ ቃሉ እንዲህ የላል፦ «ለእነርሱም መወሰንን በእርግጥ የወሰናችሁላቸው ስትኾኑ ሳትነኳቸው በፊት ብተፈቷቸው ካልማሩዋችሁ ወይም ያ የጋብቻው ውል በእጁ የኾነው (ባልየው) ካልማረ በስተቀር የወሰናችሁት ግማሹ አላቸው፡፡ ምሕረትም ማድረጋችሁ ወደ አላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ በመካከላችሁም ችሮታን አትርሱ፤ አላህ

የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና፡፡ » (አልበቀራህ 237)

(ከፌስቡክ ግድግዳ ላይ ወዲህ ያመጣሁት)

Telegram „ @ismaiilnuru

2 months, 2 weeks ago

በሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ለማጋራት ይህን የምስል ጥራት ፋይል ያውርዱ!

5 months, 3 weeks ago

ሀማስ ከኢራን ጋር የሚያደርገውን አጋርነት ለማውገዝ "የዑመርና የአቡበክር ሰዳቢዎች ጋር እየተሞዳሞደ" እያሉ ሲያወግዙ የነበሩ «ሰለፍዮች»

ቢን ሰልማን በዚህ አመት ለቀጢፍ ሺዐዎች በይፋ ሰሃቦች የሚሰደቡበት፣ ሑሰይኒያ ተእዚያ የሚከበርበትና አላህ ላይ በግልፅ ሽርክ የሚፈፀምበትን መድረክ ሲፈቅድና በወጠኒያ ወንድማማችነት ስሌት ከለላና ጥበቃ ሲያደርግ ቢያዩም ማውገዝ አይደለም ማመን አልፈለጉም።

እዛ ሰፈር ሐቅ በዞረበት እንዞራለን ማለት ይህ ነው!

የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/ismaiilnuru

5 months, 3 weeks ago
5 months, 4 weeks ago

በሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ለማጋራት ይህን የምስል ጥራት ፋይል ያውርዱ!

8 months ago

«ግፋችሁን ለዓለም እናሳያለን!»

ይህ ወጣት ነቅቷል ይባላል እንጅ እንደተኛ ነው። በሙስሊሙ ላይ በደልና ግድያ ሲፈፀም እንደማስፈራሪያ «ግፋችሁን ለዓለም እናሳያለን!» በማለት ቪዲዮና ምስሎችን ያጋራል። በዚህም የሚፈለገው ዓለም በመንግስት ላይ ተፅእኖ በማሳደር ከዚህ ድርጊቱ እንዲታቀብ ለማድረግ ነው። ይህ ግን ዓለምን ካለማወቅ የሚመጣ ችግር ነው።

ዓለም የበደለኞች መናሃሪያ ነች።ዓለም ላይ የረከሰ ደም የሙስሊሞች ደም ነው። የሰው ልጅን ደም ለማድረቅና እንባ ለማበስ ተብለው የሚቋቋሙ ድርጅቶች በሙሉ የሙስሊሙ ደም እንደማይመለከታቸው ሙስሊሙ ገና አልተረዳም።

የሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ የፀጥታው ምክር ቤት፣ እምባ ጠባቂ ተቋም ወዘተ የሚባሉ ሁሉ በስማቸው የዋህ ሙስሊሞችን ለመሸወድ የተቋቋሙ በእውነታቸው ግን በሙስሊሙ ላይ የተሰለጡ መዶሻዎች መሆናቸውን ሙስሊሙ ገና አልተገነዘበም።

ዓለም በየቀኑ ጋዛ ውስጥ የሚጨፈጨፉ ሙስሊም ህፃናትና ሴቶችን ለድፍን 70 አመታት ያህል እንደፊልም እየተመለከተ ነው። በሊቢያ፣በየመን፣ በዒራቅ ሚሊዮን ሙስሊሞች በአሰቃቂ ግድያ ህይወታቸውን ያጣሉ።

ሶሪያ ―ባጙዝ ከተማ― በአንድ ለሊት ብቻ ስጋን ሳይሆን አጥንትን በሚበጣጥሰው ነጭ ፎስፎረስ ከ3000 በላይ ሙስሊሞች ተጨፍጭፈዋል።ይህ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ዓለም የበርማ ሙስሊም ህፃናት ላይ እጆቻቸውን ዘርግተው በሞተር ሳይክር ሲነዳባቸው አይቷል።

ዓለም በመካከለኛው አፍሪካ ሙስሊሞች በቢላዋ ልክ እንደበግ ጉድጓድ ተቆፍሮላቸው ሲታረዱ አይቷል።ዓለም ጋንታናሞ ሙስሊሞች ብቻ ታስረው የሚሰቃዩበት እስር ቤት መሆኑን ያውቃል።

አንድ እግር ኳስ ተጫዋች ጉንፋን ሲያመው መግለጫ የሚያወጣው ዓለም የዓለም ሙስሊሞች ደም ለርሱ የጉንፋን ያህል ህመም የለውም!

ታድያ ሁለት ሰው ተገድሎብህ ገዳዮችን «ለዓለም አሳይባችኋላሁ» ብሎ መዛት እንዴት መንቃት ሊሆን ይችላል? (ሁለት ሰው ከነርሱ አንፃር ለማለት እንጅ ለኛማ ከግማሽ ነፍስ በታች ያለች አንዲት ጥርስ ብትወልቅ በምትኳ ቅጣት አንድ ጥርስ የሚወለቅላት አካል ነች) ግደል ብሎ አባቱ የላከውን ልጅ ለአባትህ እናገርብሃለሁ ብትለው ምን ማለት ነው? ?

ገዳይህ ከዓለም ጋር የሚግባባበት ቋንቋ ያንተ ደም ሆኖ ሳለ ለዓለም እናገርብሃለሁ ማለትህ ስሜት ይሰጣልንዴ ሐቢቢ?

ዓለም ብትጮህ ብትፈራገጥ አይሰማም ። ዓለም አሁን ላይ ለሙስሊሞች ምቹ አይደለችም። ያ ቢሆንማ ረሱላችን ﷺ በመህዲ መምጣት አያበስሩንም ነበር! የመህዲ መምጣት አላማውኮ ለሙስሊሞች ፍትህን ማስፈን ነው!

«(ምድርን/ዓለምን) በፍትህና በፍትህ ይሞላታል በግፍና በበደል ከሞላች በኋላ» አሉ ሰይዳችን የመህዲን መምጣት ኣላማ ሲነግሩን። ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ ዐለይሂ!

በርግጥ ከመህዲ በፊት በርሳቸው መንሀጅ ላይ የምትፀና የኸሊፋ ስርአት እንደምትዘረጋ ገልፀዋል። ስለዚህ ሙስሊሙ በሸሪዐ እንጅ ፍትህ እንደማይገኝ ዓለም ለሙስሊሙ ባይተዋር እንደሆነች ከነዚህና መሰል ነብያዊ ሀዲሶች በመገንዘብ ንቃተ ህሊናውን ሊያሻሽል ይከጀላል።

ሙስሊሞች ፍትህ ሊሰፍንላቸውና ሰላማቸው ሊረጋገጥ የሚችለው አንዱ በነብያዊ መንሀጅ በምትዘረጋ የኺላፋ ስርአት አለያም በመህዲ መምጣት እንጅ አሁን ላይ አለም በምትዘወርበት የኩ$ፍር ፖለቲካ ስርአት እንዳልሆነ ጠንቅቀው ሊያውቁ ተገቢ ነው።

ቴሌግራም ፦ t.me/ismaiilnuru

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago