TEAM HUDA

Description
"أَفَلَا تَعْقِلُونَ"
"አታስተነትኑምን?"

አንብቡ! ራሳችሁን፣ በዙሪያችሁ ያሉትን ነገሮች፣ ሌሎች ሰዎችን፣ ፅሁፎችን.... አንብቡ! አስተንትኑ! ጠይቁ!

Big thanks for joining!

All team huda!
We recommend to visit

Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 8 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 3 weeks, 1 day ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች

? ውጤቶች

? የጨዋታ ፕሮግራሞች

? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 months, 2 weeks ago

3 months, 1 week ago

*     

የፈገግታ ሃይል

የፊትዎ አገላለጽ (Facial ecpression) ስሜትዎን እንደሚለውጥ ያውቃሉ

ፈገግታ ጥሩ ስሜት ውስጥ ባትሆንም እንኳን አእምሮህን የበለጠ ደስተኛ እንድትሆን እንደሚያታልልህ ታውቃለህ? እሱም “የፊት አስተያየት መላምት” ወይም 'Facial Feedback Hypothesis' ይባላል። እናም አእምሮህ በአንተ ላይ የሚጫወተው ሃይለኛ ተንኮል ነው።

ፈገግ ስትል፣ ወደድክም ባትፈልግም አእምሮህ ደስተኛ መሆንህን የሚጠቁሙ ምልክቶችን ይቀበላል፣ ይህ ደግሞ ስሜትህን ይጨምረዋል። . የሚገርመው ደግሞ ትንሽ ፣ የግዳጅ ፈገግታ እንኳን depression ወይም  ጭንቀትን ለመቀነስ ይረዳል ፣ ይህም የበለጠ ዘና ያለ እና አዎንታዊ ስሜት እንዲሰማዎት ያደርጋል። ሁኔታው ምንም ይሁን ምን ለእምሮህ ትንሽ ደስታን እንደመስጠት ያህል ነው።

እናም ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው 😊በሚቀጥለው ጊዜ የድካም ስሜት በሚሰማችሁ ጊዜ ይህን ቀላል ሆኖም ውጤታማ ዘዴ ሞክሩት። ፈገግ ..... መጀመሪያ ላይ ትንሽ ግራ የሚያጋባ ቢመስልም አእምሮህ ዝም ብሎ ሊይዝ እና ስሜትህን ሊለውጠው ይችላል። እናም አስታውሱ፣ ደስታን ማስመሰል ብቻ አይደለም - ለራስህ የተፈጥሮ መነሳት እና ቀኑን ብሩህ ማድረግ ነው!

JOIN
👇👇👇👇👇👇👇👇

@factandfiction1
@factandfiction1

-----------------------------------------

5 months, 3 weeks ago

Because they got alot of report on the above channal they proceed to this new one. We will not stop reporting untill they stop mocking by our Quran‼️*‼️*‼️**

Report their YouTube channel ⚠️****

https://youtube.com/@officialquranicsongs?si=et-vaE3gi_LD1-yE

And here their telegram channal?****

https://t.me/QuranicSongs

5 months, 3 weeks ago

*?SERIOUS ACTION NEEDED FROM ALL RIGHT NOW?*

This channel has appeared in YouTube called B Quranic Songs that combines music with the Holy Quran. Whoever can report this channel should do so until it is closed.**

REPORT THIS HERETIC CHANNEL THAT DISTORTS THE QURAN! ⚠️‼️

ارجوا التبليغ عن هؤلاء الزنادقه قندره عليهم

https://youtube.com/@quranicsongs?si=-YXoOKuPtmGj1RdO

6 months ago

....አንድ የጌታሽ ዱንያ ላይ፣ ሁለቴ መጣን እንል ዘንድ ለትዝታ....
.
.
"*ስካር
ከምሽቱ 6:07

<ኧረ ልጅቷ ዛሬ በጤናዋም አይደለች! ምን ነክቷት ነው።> ቅድም ጀምራ የምትስቀውን እንስት ግራ በመጋባት ውስጥ ያይዋታል። ስተፈልግ ደሞ እየሳቀች ታለቅሳለች። በአፏ አንድ ነገርን ከመደጋገም ውጭ ለሚጠይቋት ጥያቄ ምንም መልስ አልሰጥ ብላቸዋለች። <ሰክራ ነው> ብለው ጥለዋት ሄዱ። ከማንም በፊት ለድሮ ሚስጥረኛዋ ጨረቃ መናገር ነበረባትና እነሱ ከመሄዳቸው ወደ ሚስጥረኛዋ እየተመከተች መናገር ጀመረች።

< ሰማሻቸው ጨረቃዬ! ሰከረች አሉኮ ሃሃሃሃ ለነገሩ ምን ይበሉ እኔን ያሰከረኝ ነገር መች ገብቷቸው። ልክ ናቸዋ ሰክሪያለሁኮ፣ ግን ጠጥቼ አይደለም የሰከርኩት። እያሳቀ የሚያስለቅሰኝ ስካር የደስታ ስካር ነው። ለካ ደስታም ያሰክራል። ታውቂያለሽ! እስከዛሬ ተናድጄ፣ ታምሜ፣ አዝኜ፣ ተከፍቼ፣ ናፍቄ ነበር እንቅልፍ የማጣው ዛሬ ግን በተለየ ሁኔታ በደስታ ሰክሬ ነው።> ፈገግታ ምስልን የተላበሰችው ጨረቃ እሷም በደስታዋ የተደሰተች ትመስላለች። ንግግሯን ቀጠለች < ጨረቃ ግን አልገረመሽም! ብዙ ነገር በአንዴ እንደዚህ ብስራት በብስራት ሲሆን? በራስሽ ብስራት በጣም ተደስተሽ ደስታሽን የምታካፍያቸው ሁሉ ሲደሰቱ ስታዪ ደሞ ምን ያክል ደስታሽ እንደሚጨምር። ከዛም ደሞ እንሱን ያስደሰታቸውን ሲያካፍሉሽ፣ በነሱ ደስታ ስትደሰቺ ሱብሃንንን… ታውቂለሽ በአንድ ወቅት ለኔ ቅርብ የሆነው ወንድሜ "ችግሮች ጫፍ ሲነኩ መፈቻቸው ይቃረባል" ብሎኝ ነበር። ከቀናት በፊትኮ በዚሁ ሰአት ጭንቄን ላሰማሽ ተቀምጬ ነበር። የአሁኑ ደስታዬ ደሞ በቃ ጭንቅ ውስጥ ማለፍ ምንም አንዳልነበር ያሳየኛል። እና እንደዚህ ሁኖ በደስታ ብሰክር ይፈረዳል ወይ? ለካ አንዳንዴም ከማዘን ይልቅ የኢላሂ ባሪያ በመሆን ብቻ መደሰትም የሚገባ ነው። > ምላሽ ሳትጠብቅ እየተፍለቀለቀች ከተቀመጠችበት ተሳች። ከማንም በፊት ምስጋና ለሚገባው ጌታ መስገጃዋ ላይ ተደፍታ ልታመሰግነው!

" ألهم لك الحمدْ كما ينبغي لجلال وجهك و لعظيم سلطانك "

ረቡዕ 19/12/13*"

@Re_Ya_Zan

6 months, 1 week ago

እየደከምክ ግን ላለመውደቅ በመፍጨርጨር ውስጥ ሳለህ የማይደርስልህ፣ የማያስተውልህ ወዳጅ የወደቅክ ቀን ሊያስተዛዝንህ ብቅ ይላል። የመውደቅ እንጂ ይዞ የመቆየት ህመም የሚያም አይመስለው ይሁን አሊያ ስትወርድ አንድኛውን አላቅስሐለሁ ብሎ ይሁን ብለህ ጠርጥር። እንጂ መውረድህ እፎይታ ሰጥቶት ከንፈር ይመጥልኛል ስትል አትጠርጥር።

አውቃለሁ እያነባህ የደስታ የሚመስላቸው ሰዎች እንዳሉ፤ እየታገልክ ቀና ያልከውን ከኩራት የሚመድቡት እንዳሉ ይገባኛል። ያለፍከው መከራ ልብህን እንደወንፊት አሳስቶ ቶሎ እንደሚከፋህም።
ግን....
መታገልህን የሚረዳ፣ በቁም ውስጥህ እየተበላ እንደሆነ የሚያየው አሏህ አይበቃህም? ሊፈርድብህ ሳይሆን ሊሰማህ የተዘጋጀው አሏህ፤ ብስራቱን ሊሰድልህ ጥቂት ትቀርበው ዘንድ አንተን መጠበቁ አይበቃም ?
ትንሽ ታገስ። የተስፋን ክር የያዝክበቱ እጅህ ከጌታው የሆነን መረዳት እስኪያገኝ ድረስ ታጋሽ ሁን!

@Re_Ya_Zan

7 months ago

ማናችን እንሆን...ከወንጀል የጠራነው በየትኛው መንገድ ይሆን መልካም ሰሪ ብቻ የሆነው በይፋም ሆነ በድብቅ ስንት ወንጀሎችን እንሰራለን...ነገር ግን የኛ ሩህሩና አዛኝ የሆነው አላህ ወደ እሱ በቀረብን ቁጥር ሁሉንም ወንጀላችንን ይምረናል እንደ ሰው ድጋሚ ሳያነሳ ወንጀላችንን ሁሉንም በምህረቱ ያልፍልናል ታዲያ ይሄን የመሰለ ጌታችንን ማመፅ እንዴት ቀላል ሆነ...?
.
.
@Re_Ya_zan

7 months, 2 weeks ago

እድሜ

ልጅነት የተለየ አለም አለው። ደስታ፣ ጨዋታ፣ መቦረቅ፣ መደባደብ… ከኛ ከትልቆቹ አለም እጅግ ይለያል። በጣም ጣፋጭ የማይገኝ የሚናፍቅ ጊዜ ነው "ኧረ ልጆች ልጆች እንጫወት በጣም፣ ከእንግዲህ ልጅነት ተመልሶ አይመጣም…" እያልን ትርጉሙን ሳናውቀው እየዘመርን ቦረቅንበት። ትልቅ መሆን እንደተመኘን ነፃነት ያለው እየመሰለን እየጓጓንለትም አደግን። ነገር ግን ስናድግ ትልቅነት እንዳሰብነው የሚናፈቅ አለም ሁኖ አላገኘነውም። ልጅ ሁነን እጃችን ላይ ትንሽ ነገር ከቧጨረን ሳምንቱን እንደ ህመምተኛ እጄን ነካብኝ፣ አያስበላኝም፣ አያስተኛኝም ብለን እንዳልቀበጥን ሁሉ፣ አሁን መች እንደቆሰለ ራሱ የማናውቀው ብዙ ቁስል ሰውነታችንን ሞልቶታል። መች እንደቆረጥነው ሳናውቅ ረጥቦን ስንመለከተው እየደማ እንደሆነ የምናውቅባቸው አጋጣሚዎች ጥቂት አይደሉም። በማደግ ውስጥ አለመታመም ኑሮ ወይስ የውስጣችን ህመም በዝቶ ይሆን ሲቆስል የማትታወቀን ባይገባኝም ትልቅነት ግን የሚያጓጓ ጊዜ አልነበረም።

በትልቅነት ውስጥ አዕምሯችን ይበሰልም አይብሰልም ሀላፊነቶችን የመወጣት ግዴታ ይኖርብናል። አሁን ላይ እያንዳንዱ ጥቃቅን ስህተት "ልጅ ናት አታውቅም" ተብሎ አይታለፍልንም። "ትልቅ አልደለች እንዴ?!" ብሎ ተቆጪው ወቃሹ ብዙ ነው። የስኬት መንገዶች ላይ ድሮ ልጅ እያለን የማናውቀውን "ምቀኛ" የሚባል ቃል እንማራለን። በየምንገዱ ማልቀስ ላገኙት ሁሉ መዘርገፍ የማያዋጣ ነገር ይሆናል። ድሮ ልጅ ስለሆንን "እንዳያስቡ!" ተብለን የተደብቅናቸውን ችግርና ፈተና የሚባሉ ነገሮችን በተግባር እንማራለን። ከዛም ትልቅነት ያስጠላናል፣ የምንነፋረቅበት እቅፍ ይናፍቀናል። ወደ ልጅነት መመለስን ብንሻም በምኞት ውስጥ ስንዋልል ቁሞ የሚጠብቅ እድሜ የለንም። ከኋላችን እርጅና ያሳድደናል አሁን ከምንኖረው የባሰ የሆነ እድሜ። ቁጭ ብሎ ወጣትነትን እያስታወሱ ራሳችንን የምንወቅስበት እድሜ። መለስ ብለን ስናስበው ብንመለስበት ብዙ ማሳካት የምንችልበት እንደሆነ እንዲሰማን የሚያደርግ፣ አሁን ብዙ ያደከመንን ፈተና "ለዚህ ነው?" ብሎ የሚያስንቅ እድሜ ወደፊት ይጠብቀናል። ምኞት ብቻ ሁነን መስሪያ ጉልበቱን የምናጣበት፣ ለነገ ብለን የገፋነው ሁሉ ተጠራቅሞ የሚጠብቅብን፣ አንገፋው ወደፊት የለን…አንሰራው አቅሙ የለን… እንዲሁ ሁነን እንባክናለን። ከዛም ለምን ወጣትነት ላይ ፈተና እና ችግር እንደሚበዛ ይገለጥልናል። የተሻለ የእርጅና ዘመን ላይ መኖር እንችል ነበር። ነገር ግን ነጋችንን ሳናቅድ ኑረነዋልና ያተረፍነው ነገር ምን እንደሆነ አይገባንም። ከዛም ዳግም ለምን ወጣትነቴን ሳልጠቀምበት የሚል ቁጭት እናስከትላለን። ይህን የሚያውቁ አዛውንቶችም በቻሉት መጠን ሊመክሩን ይጥራሉ። ሁሉም ባለፈበት እንድናልፍ አይመኝልንም። ትንሽ የሚንቀሳቀስ ወጣት ሲያዩ ይደሰታሉ። ሁሉም ወጣቱን ህዝብ ይፈልገዋል፣ ለስኬት አስፈላጊ እንደሁነ ስለሚያውቅ ያለፈውን እድል ወጣቱን ተጠቅሞ እንዲሳካለት ይለፋል። ምክንያቱም አስቦበትም ይሁን ሳያስብበት ሀላፊነትን የተሸከመው ወጣት እሱ ብቻ እንደሚያሳካው የሚያውቁት እድሜውን ያለፉት ብቻ ናቸውና። እናማ… ህመሙ፣ ችግሩ፣ ሀላፉነቱ ቢበዛም ሁሉን ችሎ ትልቅ ቦታ የሚደርሰው የወጣትነት ሀይል ያለው ብቻ ነውና ችለን ነጋችንን መገንባት ትልቁ ስኬታችን ነው። የእድሜያችን ፈተና ይህ ስለሆነ!

@Re_Ya_Zan

7 months, 2 weeks ago

በምድር ላይ ባለህ ቆይታም ከመልካሞች ጋር ተወዳጅ...እነርሱ ከመካከላቸዉ በጠፋህ ጊዜ ፈላጊዎችህ ናቸዉ፣ መንገድ ስተህ ባዩህ ጊዜም ይመልሱሃል፣ በተዘናጋህ ጊዜ ያነቁሃል፣ በራቅካቸዉ ልክም ይናፍቃሉ፣ ከጌታቸዉ ጋር በተንሾካሾኩም ቁጥር ስምህን አይረሱም...?

@Re_Ya_zan

9 months ago

ንጋት...

ሲነጋ አይኖች ሲከፈቱ፣ አዲስ ቀን ብቅ ያለ ይመስላል። ነገር ግን ንጋት ሁሌ አዲስ ተስፋ አይደለም። የትናንቱን ኮተት ሰብስቦ የሚመለስ፣ ፀሀይ መውጣቷ ብቻ የሚለየው ዳግማው ትናንትም ይሆናል። እድሜያችንም የነዚህ ቀናት ጥርቅም ነው። ዳግማዊ ትናንቶች በየቀኑ ሲደጋገሙ ህይወታችን ወጥ ይሆናል። ዛሬዎችን ማጣት ህይወትን ይበልጥ አሰልችና የሚያስመርሩ ያደቸዋል። በነዚህ ቀናት ስናልፍ አልፎ አልፎ ብቅ የሚሉ አዳዲስ ንጋቶች፣ አዲስ ቅርፅ ያለው ዛሬን ሲሰጡን ትላልቅ የደስታ ቀናት እናልፋለን። የደስታ ቀናችንንም አንድ ብለን ከቆጠርናቸው ብዙ ዳግማዊ ትናንቶች ጋ ደምረን አንድ እርምጃ እንደተንቀሳቀስን ሁሉ.... ዳግም ወደቆጠራ ተመልሰን ሁለት እንላለን። እድሚያችንም ይበልጥ ያጥርብናል። ብዙ የተቃጠለ እድሜም እንዳለ ይሰማናል። ዳግማዊ ትናንቶችን መደምሰስ ባንችልም ግን ከትናንቱ የተወሰነ ልዩነት ለማምጣት ብለን እስካልተነሳን ድረስ አዳዲስ ዛሬዎች ይበልጥ እየራቁን ይመጣሉ። ስለዚህ ቢያንስ ትናንትን ከዳግማዊ ትናንት ለመለየት የቀኑን አጀማመራችንን እንለውጠው ወይንም አጨራረሳችንን። አንድን ቀን ሁለቴ ላለመኖር ያክል ብቻ…

@Re_Ya_zan

We recommend to visit

Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 8 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 3 weeks, 1 day ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች

? ውጤቶች

? የጨዋታ ፕሮግራሞች

? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 months, 2 weeks ago