Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚

Description
ይህ የኖህቶኤል ሀሳቦች የሚንፀባረቁበት ቻናል ነው። የምትስማሙባቸውን ለወዳጆ ሼር ያድርጉላቸው።🙏

@Noahtoael

በማንበብ ብቁ እና ጤናማ እውቀት ያላቸውን ትውልድ እናፍራ!

በዚህም ቻናል.!

፦አጫጭር አዝናኝ እና አስተማሪ ታሪኮች
፦ተከታታይ ታሪኮች
፦ትረካዎች
፦ግጥም እና ስነፅሁፎች
.......ያገኛሉ!
Advertising
We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

● Welcome to Ethio music Channel

➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !

Last updated 2 weeks, 1 day ago

🇪🇹 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ ቆየት ያሉና አዳዲስ👇👇

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት 🎻 የበገና መዝሙራት  
👑 የቅዱሳ መዝሙራት ⛪️ የንግስ መዝሙራት
💍 የሠርግ መዝሙራት 🌦 ወቅታዊ መዝሙራት መገኛ


📢ለ ማስታወቂያ ስራዎች @Miki_Mako

1 month, 2 weeks ago
እስኪ ዛሬ ያጋጠመኝን አንድ ታሪክ ልንገራችሁ፣ …

እስኪ ዛሬ ያጋጠመኝን አንድ ታሪክ ልንገራችሁ፣ ፈጣሪ እንዳልጠፋ ልጅ ሰጠኝ ስላለቺኝ አንዲት ልጅ፡
.
የሆስፒታል Ward ዉስጥ ያገኘዋት አንዲት ልጅ ነዉ እንዲ ያለቺኝ
.
ህይወት ምን እንዳስተማረኝ ልንገርሽማ ስትለኝ፣ ጆሮዬን ሰጠዋት
.
ታውቂያለሽ ፈጣሪን በጣም አስከፍቼዋለሁ ብዙ ጊዜ ሳጠፋ ቆይቻለሁ፣ እሱ ግን ሁሌም አብሮኝ ነበር አልራቀኝም ከቁጣ የራቀና ምህረቱም የበዛ ነዉ፣ ብዙ ልክ ያልነበሩ ነገሮች በህይወቴ ላይ ሰርቻለሁ፣ ለክፋቴ ምላሽ ሳይሰጠኝ ብዙ መንገድ ተጉዣለሁ፣ በዛ ብቀጥል ኖሮ ግን እጠፋ ነበረ፥
.
ከዛ ወደ ሆዷ ጎንበስ እንዳለች ፈገግ ብላ ፈጣሪ ግን እንዳልጠፋ ብሎ ልጅ ሰጠኝ አለቺኝ፣ አያቹ ምን አይነት አምላክ እንደሆነ፡ እኛ ሰዎች ሩቅ ሆነን የሰዎችን ህይወት እያየን የእጇን ነው የሰጣት እያልን ከንፈር ለመምጠጥ እንቸኩላለን ፣ እነሱ ግን ፈጣሪ እንዳልጠፋ ይሄን ሰጠኝ ይላሉ፣ ሌላን ሳይነቅፉ መኖር ታላቅ ብቃት ነው፣ የሌሎችን ስህተት አውጥቶ ሰውን ማሳነስ ራሳቸውን የማግዘፊያ አማራጭ ላደረጉ ሰዎች ግን በጣም ቀላል ነው፥
.
ፈጣሪ እንደ ሰው አይደለም፣ ሁሌም የስህተት መጨረሻም መውደቅ አይሆንም፣ አንድ አንዴ በሰራናቸዉ ስህተቶች ውስጥ በረከት ይኖራል፣ እስቲ ህይወታቹን ቃኙት በየትኛዉ ጥፋታቹ በረከት አፍሳቹሀል ከምንስ ተመልሳቹሀል?

1 month, 2 weeks ago
1 month, 2 weeks ago

ከዮቶር መፅሀፍ የተወሰዱ ሀሳቦች...

-ሰላም ካላቸው ወይ ያሰቡበት ላይ ደርሰዋል ወይ የሚሄዱበት የላቸውም
-ነፍሳችንና ስጋችን የሚያዜሙት ዜማ ህብረት ከሌለው ውበትም ሆነ መልዕክት ሊኖረው አይችልም
-ብዙ ሰዎች የራሳቸው ማንነት ላይ ከማተኮር ይልቅ የሌሎች ሰዎች ሰዎች ማንነት ላይ በማተኮር እድሜያቸውን ያባክናሉ
-አብረን ያፈካነው ቀን እኮ ነው አንቺን የገለፀሽ። እነዚህ ሰዎች የዚ ቀን ፀሀይ ሲያበራሽ ነው የተመለከቱሽ። እንደኔ በጨለማ ውስጥ አብረውሽ ሊጓዙ የሚችሉ አይነት አይደሉም
-ጀግና ጥሩም ሆነ መጥፎ ያው ጀግና ነው
-እውነትን እየተረዳህ በመጣህ ቁጥር ስቃይ ከውስጥህ ይሟታል ብላ ነፍሴ ሹክ አለቺኝ
-ምንም ብወደው ልኖርበት የማልፈቅደው ቤት ውስጥ እየተላተምኩ እየተፈጠፈጥኩ ከምኖር ልኖርበት የምፈቀደውን ሌላ ቤት መስራት ይጠበቅብኛል
-ከንቱ ፍራቻ ብለን የጠራነው የሰው ልጅ ደመ ነብሱን ከማዳመጥ ስለቦዘነ በራሱ ላይ የፈጠረው የፍራቻ ስሜት ነው
-ካለሁበት ተነስቼ አንድ እርምጃ ወደፊት በተራመድኩ ቁጥር የጨለማው ግድግዳም ወደኋላ አንድ እርምጃ ይሸሻል
-ፍራቻዬን በድርጊት አሸንፌዋለሁ
-እናንተ ወጣቶች የቁሳዊው አለም ሰዎች ናችሁ እኛ ሽማግሌዎቹ ደግሞ የመንፈሳዊው አለም ሰዎች ነን
-በእናንተ ውስጥ እርካታና ሰላም ጠፍቷል። ብዙ ትሮጣላችሁ እንጂ የእርካታን ደጅ አትረግጡም
-የሰው ልጅ አስቀድሞ በነፍሱ በሰውነቱ እና በማንነቱ  ላይ ቀድሞ ካልሰለጠነ ምኑን ነው ሰለጠነ የምንለው? ቁሳቁሱን ነው?
-በመንፈስ ስትሰለጥን በማንነትህ ላይ ስልጣን ይኖርሀል
-ሀይልና ገንዘብን ቅድሚያ ባደረገ ግስጋሴ ውስጥ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻ ይነግሳል
-ሰዎችን ጥገኛ የማያደርግ ምስጢራዊ እገዛ መልካም ነው
-ሁሉም ነገር በለውጥ ውስጥ የሚያልፈው እኮ በፍቅር ሳቢያ ነው
-እጅህ ላይ ያሉትን ተአምራት ሳትጠቀም ሌላ ተአምር ከሰማይ ለምን መጠበቅ ያስፈልግሀል
-የሰው ልጅ እምነት እርግጠኝነት ይጎድለዋል
-የአንድ እቃ ወይም ጉዳይ ዋጋ የሚለካው ባረፈበት ሰው ማንነት ላይ ነው
-ሀሳባችን በራሱ የህወታችንን ጉዟችንን የሚቀርፅ ሀይል ነው
-ራሳችንን በሌላኛው ሰው ቦታ ላይ አድርጎ ማሰብ ጉድለትን ማረሚያ መንገድ ነው
-ፍቅር ነፍስን ከነፍስ ከማቆራኘት አቅም እንዳለው አታውቂም?
-በገፍ ታፍሶ የተሰጠሽን ፍሬ ሳስተሽ ስለማትጠቀሚበት የምታባክኚው ይበዛል። ተቆጥቦና ተቆጥሮ የተሰጠሽ ፍሬ ግን ውድ ነው።
-ህይወት በጣም ትገርማለች በdestiny ላይ የቱጋር እንኳን ስህተት እንደፈፀምክ ሳይገባህ እንዲሁ ፊትህ ያገኘኸውን ብቻ ዝም ብለህ ትኖራለህ

1 month, 2 weeks ago
ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚
1 month, 2 weeks ago
የተሻለውን እወቅ

የተሻለውን እወቅ

አንድ ወቅት እንደዚህ ሆነ አንዲት ወፍ እና አንዲት ንብ እየተጫወቱ ሳለ ወፊት ብዙ ግዜ በሃሳቧ የሚመላለሰውን አንድ ጥያቄ ለታታሪዋ ንብ ጠየቀቻት "አንቺ! በብዙ ልፋት እና መከራ ጥረሽ ግረሽ የምትሰሪውን ማር ሰዎች ያለ ምንም ድካም ወስደው ሲጠቀሙበት አታዝኚም ወይ?" አለቻት።

ንቧም ስትመለስ "በፍፁም አላዝንም ምክንያቱ ሹም ሰዎች የሰራሁትን ማር ሊወስዱት ይችላሉ እንጂ በውስጤ ያለውን የማሩን አሰራር ጥበብ ማንም ከእኔ ውስጥ ሊወስደው አይችልም።"

አሳ እንዴት እንደሚጠመድ ሳይነግሯቼ ሐይቅ ውስጥ አሳ እንዳለ እና አሳ ማስገሪያው ሰተዋችሁ ቢሄዱ ለእናንተ ጥቅም የለውም ስለዚህ
የሻለውን እወቁ!!

ኖህቶኤል ነኝ

ለወዳጆ ሼር ያርጉ

https://t.me/Noahtoaels_Idea

1 month, 3 weeks ago

A struggle is a struggle
.
ሽንኩርት ሲከትፍ ቢላዋ የቆረጠዉ እና እንጨት ሲፈልጥ እጁ የተቆረጠ ሰዉ ሁለቱም “ምን ሆነህ ነዉ?” ቢባሉ “እጄ ተቆርጦ ነዉ” ይላሉ፥
.
ባለ ሽንኩርቱም፡ ባለ መጥረቢያዉም ይደማሉ፣ ይቆስላሉ፡ ቁስላቸዉን ያስታምማሉ፥
A struggle is a struggle

©️Tikusbiskut

1 month, 3 weeks ago
1 month, 4 weeks ago
ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚
1 month, 4 weeks ago

**ለምንድነው ሁሉም ነገር ስለእኛ በተምሳሌት ተመስሎ የሚታየኝ?

ዛሬ ጠዋት እኮ ነው ሰፈር ውስጥ ቁጭ ብዬ የሰፈር ልጆች ሲጫወቱ አየሁ "ልጅ ለመፈለግ መጥተናል" እያሉ ገና 20 አመቴን በቅጡ ሳልደፍን "እርጅና መጣና ድቅን አለ ፊቴ" እያልኩ በታዛቢ አይን ፈገግ ብዬ አያቸዋለሁ።

ልጆቹ የሚፈልጓትን ልጅ መረጡና ይሆናል ያሉትን ልጅ ጎትቶ እንዲያመጣት ወሰኑበት ከዛ "ከማር ከወተት ይሻላል መጓተት" ብለው ተጓተቱ። ፊታቸው ላይ ላለመወሰድ፥ ላለመሸነፍ ያለው ጭንቀት ያስታውቃል መጨረሻ ላይ ወንዱ አሸንፎ ወደ ራሱ ቀጠና አስገባት ግን ያው እሱም በቂጡ ዘጭ ማለት አልቀረለትም ነበረ።

እሷም እምባዋ መጥቶ "በሀይል ጎትቶኝ እኮ ነው" አለች ከወደቀበት ሳይነሳ "እኔም ላለመሸነፍ ብዬ ነው" አላት ልጆች አይደሉ ጨዋታቸውን ቀጠሉ።

እኔ ግን ገረመኝ እኛስ ላለመሸነፍ ብለን አይደለ ሁለታችንም የተሸነፍነው? ቢያንስ የልጆቹ ጨዋታ ይሻላል አንድ አሸናፊ ነበረው።**

2 months, 1 week ago

Letter 8
The inventions are getting weird and crazy but they all make sense even slightly. But robot partner…
I remember how disgusted I was when I hear about it, I mean there are billions of people in the world and they buy robots as partner?
And then I found you, the perfect masculine to be paired with. and the least favorite person for my toxicity. When the first time in my life, I was worried about another male beingness than myself and then you make me realize maybe the robot wasn’t that bad idea.
And then I rethink about having robot partner… I mean you can’t hurt it; it can’t break your heart; it doesn’t have norms and society to worry about.
Maybe there exists millions…billions of people but every of them with their own problems I mean but for the robots you just need charger
The robots are not busy they are just yours they don’t have family you are supposed to impress you don’t have to care about what they think cuz they don’t.
Above all, they don’t have emotions they don’t feel love, hate, anger or hunger they just exist man?!you know what I mean?? They won’t give you those memories that you always struggle from.
But you what’s the point of partner then? Without the pain, without those excruciating memories, without those stomach-full butterflies where is the beauty of life?
Just lets be able to say “thank you for the pain you make me suffer from because you can’t enjoy love without the pain you know why? Love is just another type of pain the pain you enjoy the pain you don’ t want to get rid of.
Ohh man!!! Love…the path is always unique and the experience is wild and adventurous fuck those cold robots and be able to fall in love and be the loser but in love losing is also winning since you’ve got the pain and the butterflies anyway

We recommend to visit

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

● Welcome to Ethio music Channel

➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !

Last updated 2 weeks, 1 day ago

🇪🇹 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ ቆየት ያሉና አዳዲስ👇👇

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት 🎻 የበገና መዝሙራት  
👑 የቅዱሳ መዝሙራት ⛪️ የንግስ መዝሙራት
💍 የሠርግ መዝሙራት 🌦 ወቅታዊ መዝሙራት መገኛ


📢ለ ማስታወቂያ ስራዎች @Miki_Mako