Books only!
This channel is created for books sharing To widen your mind and to get books easily We have more than 2000 amharic and english books !
Join and share @Books_worldd
አስተያየት @BooksWorlddd_bot !
@books_worlddd መወያያ ግሩፕ
#share
➡️ በቻናላችን የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች
➲የአቂዳ ኪታቦች
➲የፊቅህ ግንዛቤዎች
➲የሱና ኡለማዎች ፈትዋ
➲ወቅታዊ ምክሮች
➲የቁርአን ቂርአትና ሌሎችም
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Last updated 5 months, 4 weeks ago
?"እውቀት የነብያት ውርስ ነው። ኡለሞች ደግሞ የነብያት ወራሾች ናቸው። እውቀትን እና የእውቀትን ባለቤቶች መውደድ የነብያትን ውርስ እና ወራሾችን መውደድ ነው።
?በደረጃ የሚለቀቁ
1:-ነህው
2:-ሶርፍ
3:-ተጅዊድ
4:-ተፍሲር
5:-ፍቅህ
6:-አቂዳ
7:-መንሀጅ
8:-ሀዲስ
9:-ሲራ
10:-ሙስጦለህ
11:-ቀዋኢደል ፍቅህ
12:-ኡስሉል ፊቅ
13:-አህላቅ ወል አዳብ
14፡-ስለሴቶቻችን
15:-ንፅፅር
Last updated 2 months, 3 weeks ago
`አንድ ድሃ ኬክ ሻጭ ወደ ታዋቂው ግሪካዊ ቢሊየነር ኦናሲስ (በቅፅል ስሙ የነዳጅ ታንከሮች ንጉስ) ወደሚባለው ባለሃብት ጋር ቀረበና ኬክ እንዲገዛው ጠየቀው። ኦናሲስ አንድ ሳንቲም አውጥቶ ሻጩን እንዲህ አለው። "ጎፈር ወይስ ሰው? ከተሸነፍኩ በኪሴ ውስጥ ያለውን ሁሉንም ገንዘብና አንድ የቼክ ፊርማ እሰጥሃለው። ከተሸነፍክ ደግሞ የተሸከምከውን ኬክህን በጠቅላላ ጠረጴዛው ላይ ታስቀምጣለህ።"
ሻጩም እንዲህ ሲል መለሰ፡- -ጌታዬ እኔ ድሃ ነኝ፤ ያለኝን ሁሉንም ኬክ ከሰጠው ዛሬ ቤተሰቤን መመገብ አልችልም።
ኦናሲስ ወደ ኋላ በመዞር ጀርባውን ለነጋዴው ሰጥቶ እንዲህ አለ፡-`ኬክ ሻጩ ተወልዷል ፥ ኬክ ሻጩ ይሞታል..
😎
በእድሜ የገፋች አንዲት አሮጊት ሴትዮ ገንዘብ ለማውጣት ወደ ባንክ ሄደችና የባንክ ቡኳን ለገንዘብ ያዡ እየሰጠች
10 ዶላር ማውጣት እፈልጋለሁ
`አለችው።
ካሸሪውም፡-
"ከ$100 በታች ገንዘብ ለማውጣት እባክዎን ኤቲኤም ይጠቀሙ።"
አሮጊቷም```ለምን?```
ካሸሪውም በቁጣ የባንክ ቡኩን መልሶ እየሰጣት "እነዚህ መመሪያዎች ናቸው፤ እባክዎን ከኋላ የሚጠብቁ ብዙ ደንበኞች አሉ! ሌላ ትዕዛዝ ከሌለ መንገድ ይልቀቁልኝ!"
️️አሮጊቷ ለጥቂት ሰኮንዶች ዝም ካለች በኋላ የባንክ ቡኩን ወደ ካሸሩ እየመለሰች፦```እባክህን አካውንቴ ውስጥ ያለውን ገንዘብ በሙሉ ማውጣት ብትረዳኝ!```
ካሸሪውም አሮጊቷ በአካውንቷ ያስቀመጠችውን ገንዘብ ሲመለከት በጣም በመገረም እንዲህ አላት፦"በአካውንቱ ውስጥ 500,000 ዶላር አለ እና ባንኩ በአሁኑ ጊዜ ያን ያህል መጠን የለውም ነገ ተመልሰው መምጣት ይችላሉ?"
ሴትየዋም በመቀጠል ምን ያህል ገንዘብ ወዲያውኑ ማውጣት እንደምትችል ጠየቀች ገንዘብ ተቀባዩ፦ "ማንኛውም መጠን ቢኖር የሚቻለው እስከ 30,000 ዶላር ብቻ ነው።"
አሮጊቷም ሴትዮ ይህንን ስትሰማ እንዲህ አለችው፦```ይሁን መልካም አሁን 30,000 ዶላር እንድወስድ ብትፈቀድልኝ?```
ካሸሪውም በንዴት ወደ ካዝናው ተመልሶ 20 እና 10 ዶላር ቁልል አውጥቶ አስር ደቂቃውን 30,000 ዶላር በመቁጠር አሳለፈ። ከዚያም ገንዘቡን እየሰጠ እንዲህ አላት፦"ተጨማሪ የማደርግላችሁ ነገር አለ?"
አሮጊቷም በእርጋታ ከተቀበለችው ገንዘብ 10 ዶላር መዝዛ ቦርሳዋ ውስጥ እያስገባች እንዲህ አለች፡-`አዎ ጌታዬ $20,990 ወደ አካውንቴ ማስገባት እፈልጋለሁ።
አስተምሮቱም፡- ከአረጋውያን እና ልምድን ከተካኑ ሰዎች ጋር እልህ አትጋባ ህይወታቸውን በመማር አሳልፈዋልና
😑
በጊዜ ብዛት የሚያዋጣትን የለየች የሚያዘልቃትን መሰብሰብ የያዘች ከአሁን አሁን አያትና ወደፊት እንደሷ እንዳልሆን እሰጋለሁ።
እሷንስ መኖር አይደል እንደዚህ ያደረጋት፣ እድሜ አይደል ጎራ ያስለያት ፣ ጊዜ አይደል የጣላት።
.
.
ማን ያቃል እኔም እንደሷ መጠንከር ያቃታት ያቺ ሴት እሆን ይሆናል።
ጊዜ ብዙ ያስተምረናል ፣ አዙሮ አዙሮ ግን ያየነውን ፣ የታዘብነውን ያንኑ ያደርገናል፤
ጉርሻ
የከንፈሯን ደርዞች በጣቶቼ እዳስሳቸዋለሁ። ይህ የሚሆነው ራት እየተመገብን ሳጎርሳት ነው። ላጎርሳት ስል ለመጉረስ ከንፈሮቿን ገርበብ ስታደርጋቸው። ልቤ አብሮ ይከፈታል። ያንጊዜ ምግብ የጠቀለሉ ጣቶቼ በዐየር ላይ እንዳቆምኳቸው ክብነት ዋሻ ያስመሰለው ከንፈሯ ላይ ዓይኖቼ ይላተማሉ። ንዝረት በሙሉ አካሌ ላይ ደሜን ተክቶ ይዘዋወራል። ሲነዝረኝ ጉርሻው ከአፏ ሳይደርስ ይንጠባጠባል።
"አካሌዋ! አንተኮ ጉርሻህ በባህር እንደሚያቋርጡ ስደተኞች ነው። ከአፌ ሳይደርስ መንገድ ላይ ተንጠባጥቦ ያልቃል" ብላ ትተርበኛለች። እንደገና ሌላ ጉርሻ ጣቶቼ ያሳድዳሉ። አሁንም እየተንጠባጠቡ ሄዶ አፏን ይሞላሉ።
" ጉርሻህ ይጨንቃል ሆኖም እወደዋለሁ" ትለኛለች። ጉርሻ ቃል ነው። በአጎራረሴ ውስጥ ደግሞ መልዕክት አለ። ይህን ደግሞ እሷ አትረዳም ። አጎርሳታለሁ..ታላምጣለች..ትውጣለች..እጠግባለሁ።ወደቤቷ ትገባለች። በቃ።
አንድ ቀን ታዲያ እንደሁሌው የራታችን ማዕድ ላይ ሳጎርሳት እንዲህ ጠየቀችኝ (ለመጠየቅ ምክንያቷን የጉርሻ አምላክ ይወቀው)
" አካሌዋ! ምንድነው ጉርሻ?"
ጉርሻ ማለትማ ... ፍቅር፣ ህብራዊነት፣ ደስታ አብሮነት ጋሻነት ስስት ጉጉት የሚገለፁበት የስሜት ዓውድ ነው።
" ጣዕሜዋ! አልገባኝም " አለቺኝ አየር ላይ ተንጠባጥቦ ያለቀውን ጉርሻዬን እያላመጠች።
" በአጭሩ ጉርሻ ማለት መገለጫ ያገኘ ስሜት ነው" አልኳት
ይኸው ከዚህ በኋላ ራት ከበላን አጎርሳታለሁ ታላምጣለች ትውጣለች እጠግባለሁ። ቁርስ በልተን ነው የምንለያየው።
አካሌ🫶
በርግጥ መሳካት አለመሳካቱ ላይ እርግጠኛ አደለሁም ግን እሞክራለሁ፤ ይከብዳል፣ይደክማል አውቃለሁ ግን እሞክራለሁ የልቤን ምኞት ለፈጣሪዬ ነግሬ በቃሉ በረታለሁ በቃ ከዛ የመጣው ይምጣ ባንዱ መንገድ ባይሄድልኝ ሌላ አላጣም፤ እጄን አጣጥፌ አልተክዝም።
ስሞክር ይረዳኝም አይደል🤲🏼
ምንም ነገር ሳይለኝ ከተለየኝ ከ 8 ወራት ብኃላ በቀደም ደወለልኝ።ስልኬን አንስቼ ስመለከተው ያልተመዘገበ ስልክ ነበር ስልክ ቁጥሩን አተኩሬ ሳጤን የማውቅው መሰለኝ ብልጭ ያለልኝን ሀሳብ እውነትነቱን ለማረጋገጥ ባለማመን ከእጅ ቦርሳዬን ውስጥ መታወቂያዬን አውጥቼ ቁጥሩን አመሳሰልኩት ልክ ነበርኩ እራሱ ነው(ድንገት መታወቂያዬ ቢጠፋ እንኳ ብዬ ከራሴ ቁጥር ተዕዩ የሱን ቁጥር ነበር ያስቀመጥኩት)።የሰው ልጅ ግን ልርሳ ካለ ግዜ ይፈጃል እንጂ ይረሳል አይደል?!የእሱን ቁጥርኮ ከራሴ ቁጥር እኩል ነበር በቃሌ የማውቀው ዛሬ ግን ለማስታወስም ተቸገርኩ ምንድነው ግን እየተሰማኝ ያለው? ፍቅር፣ጥላቻ፣ናፍቆት፣ንዴት ወይስ ሁሉም በአንድነት? አላውቅም!...ይህን ሁሉ ሳብሰለስል ስልኩ ጥሪው አብቆቶ በድጋሚ መጥራት ጀመረ አነሳሁት "እረሳሽኝ አይደል?" በሚል ወቀሳ ተቀበለኝ እንዲህ አይነቱን ሰው ምን ይሉታል እንግዲህ? ምንም ሳይነግረኝ በማላውቀው ምክንያት እንደተለየኝ፣እርሱን ላገኝበት የምችላቸውን መንገዶች ሁሉ ሆን ብሎ በአንድ ቀን እንደዘጋጋብኝ፣ግራ ገብቶኝ ይገኛል ብዬ ያሰብኩት ቦታ ሁሉ ሂጄ እንዳጣውት፣በአጋጣሚ መንገድ ላይ አግኝቼው መገረሜ ሳይለቀኝ እንደማንኛውም የማይተዋወቅ ሰው ባላየ እንዳለፈኝና መገረሜን እጥፍ እንዳደረገው ሁሉንም በአምሮዬ በምልሰት ቃኘዋቸው....ከአፌ የወጣው ግን "ዛሬ ከየት ተገኘህ?" የሚለው ብቻ ነው። "ካለሁበት ቦታ ነዋ" ብሎ እንደዘበት መልሶልኝ ሌላ ወሬ ጀመረ።
የትም ሂዶ ሲመጣ ቁጭ ብዬ እንደምጠብቀው በጣም እርግጠኛ ነው።ከአንዴም ሁለቴ ተመሳሳዩን አድርጎ መጥቶ ስለተቀበልኩት ዛሬም ሲመጣ እጄን ዘርግቼ አሰፍስፌ እንደምቀበለው ነው የሚያስበው ንግግሩም የሚያሳብቀው ይህንኑ ነው።አንዳንድ ሰው ከትላንት ስህተቱ አይማርም ዛሬም ሌላ ተመሳሳይ ስህተት ለመስራት ሲሽቀዳደም እግሩን ውልፍት አይለውም...come on man! ህይወት እኮ አንዳንዴ ሁለተኛ እድል አትሰጥም!።እኔ እርሱ በሄደበት ወቅት መገፋቱን ተቋቁሜ ያለ ሰው በድል መቆም ችያለው ዛሬም ለመኖር ከእግዚያር በቀር እርሱ እንደማያስፈልገኝም እንዲሁ።ማንም ለማንም የመኖርና የመቀጠል ዋስትና ሊሆን አይችልም፡ቀድሞውኑ በእርሱ ላይ እምነት መጣሌ ስህተት ነበር ዛሬ ይህ እውነት ሲገባኝ ብቻዬን ነገሮችን ማድረግ ችያለው ዳ...ዲ እያልኩ ጀምሬም ቢሆን አሁን ላይ እሯጭ ነኝ።
ብዙ ጉዳዬችን አንስተን ካወጋን ቡሃላ "በአንቺ ከራሴወ በላይ እርግጠኛ ነበርኩ እንደምትጠብቂኝ አውቅ ነበር ይህን ህብረት ድጋሚ እንደትላንት እናድሰዋለን ያጠፋውትንም እክስሻለሁ!" አለ ሙሉነት በሚነበብት ድምፀት ሃሃሃሃሃ ይቅርታና ድጋሚ አብሮ መቀጠል ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ይቅር ብዬዋለው ግን ደግሞ ትላንት ተሸመድምጄ እንድወድቅ ደግሞ ደጋግሞ ጉድጓድ ከማሰልኝ ሰው ጋር ቁጭ ብዬ የወዳጅነት ቡና አልገባበዝም! ሁልግዜም ቀና ብለው አሻግረው ለተመለከቱ የተሻለ ነገር አለ። ዛሬ ላይ የሱ መኖር በእኔ ህይወት ውስጥ ቅንጣት ታህል ጥቅም የለውም መንገዳችን ለየቅል ሆኗል። እኔ ዛሬ ላይ እንጂ እሱ ትላንት ትቶኝ በሄደበት ቦታ ላይ አይደለሁም ስለዚህ በዙ ነገሮች ተቀይረዋል።ይህን አስረግጬ ነግሬው ተሰናበትኩት።
Cheers🥂 ለአዲሱ መንገዳችን
ተወዳጆች ሆይ!! ቸር ዋሉ
[ የህይወት መርሆዎች በተለያዩ ፈላስፎች አንደበት ]
*1. የበለጠ ለማወቅ ጣር (Platonism)
መልካም ሰው ሁን (Aristotelianism)
ራስህን ቻል (cynicism)
ዛሬ ተደሰት ነገ ለራሱ ይጨነቅ (hedonism)
ራስህን ከስቃይ አግልል (epicureanism)
ምክንያታዊ ሁን መቀየር ማትችለው ነገር አያስጨንቅህ (stoicism)
የግለሰብ ነጻነትን አክብር (classical liberalism)
ሌሎች እንዲያደርጉልህ ምትፍለገውን ነገር ለሌሎች አድርግ (kantianism)
የምትፍለገውን ነገር አድርግ ምክንያቱም ህይወት ትርጉም የለውም (nihilism)
ሃሳብህ ላይ ሳይሆን ተግባርህ ላይ ትኩረት አድርግ (pragmatism)
የፈጣሪህን አላማ ኑር (Theism)
ያንተ ውስኔ ያንተን ህይወት ይመራል (Existentialism)
13.የህይወት ትርጉም ምንድነው እያልክ
አትፈላሰፍ፣ ዝም ብለህ ኑር (Absurdism)
ለሰው መድሃኒቱ ሰው ነው (humanism)
ህይወት ትርጉም የለውም አነተ ትርጉም ካልሰጠኸው logical (positivism)
ሰዎችን ሁሉ እኩል ውደድ (Mohsim)
ከቅንጦት የጸዳ ተራ ህይወት የበለጠ ትርጉም አለው (Confucianism)*
- የቱን ህግ ወደዳችሁት?
መናገር ፈልጋችሁ ግን ቃል አጥሯቹ አያውቅም? .... ማለት የፈለጋችሁት ሌላ ሆኖ ግን ተቃራኒ response ሲደርሳችሁ ያለው feeling ughh..... አንደሰማን ሳናመዛዝን ግን ባናወራ ምን አለበት ቆም ብለን ብናስብ... ምነው? ለምን? ብለን በእርጋታ ብናጤን ምን ይጎልብናል..... ሁሉም ያማረውም process ላይ ያለውም ሚፈርሰው እኮ በዚ ባህሪያችን ነው...... ለመፍረድ በመቸኮል.... በመሰለን ተርጉመን በመረዳታችን..... ጊዜ ሰተን ለማዳመጥ ባለመሞከራችን ብዙ ብዙ...
እስኪ ስለሷ አውራኝ አልኩት ብወደውም ስለሷ ሲያወራ ፊቱ የሚፈካው መፍካት፣
ጉንጮቹ ቀይ የሚሆኑት ነገር፣ ቃላት ፍለጋ የሚጨነቀውን መጨነቅ ማየቱ ያስደስተኛል፣
ሊናገር ሲጀምር የአይኑ ብሌን ቅርፁን ሲለውጥ አስተዋልኩ፣ ሰው እንዴት በዚህ ልክ ሰው ይወዳል?
ታድላ....
እርጋታ ዝምታ አይደለም። የቱጋ ዝም ማለት እንዳለብን ማወቅ ነው። የሁሉም መልስ ያለው ሁሉንም ጥያቄ ጠይቆ የጨረሰ ነው። የቱን መምረጥ እንዳለበት የሚያውቅ፤ ችላ ባለው ትርምስ ውስጥ እርጋታ የልቦናው በር ይጎበኘዋል። ጠቢብ ግን ባንቀላፉት መኃል መንቃትን ፥ ከብዙ ሰው ጫጫታ ዝምታን ይሰርቃል
Books only!
This channel is created for books sharing To widen your mind and to get books easily We have more than 2000 amharic and english books !
Join and share @Books_worldd
አስተያየት @BooksWorlddd_bot !
@books_worlddd መወያያ ግሩፕ
#share
➡️ በቻናላችን የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች
➲የአቂዳ ኪታቦች
➲የፊቅህ ግንዛቤዎች
➲የሱና ኡለማዎች ፈትዋ
➲ወቅታዊ ምክሮች
➲የቁርአን ቂርአትና ሌሎችም
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Last updated 5 months, 4 weeks ago
?"እውቀት የነብያት ውርስ ነው። ኡለሞች ደግሞ የነብያት ወራሾች ናቸው። እውቀትን እና የእውቀትን ባለቤቶች መውደድ የነብያትን ውርስ እና ወራሾችን መውደድ ነው።
?በደረጃ የሚለቀቁ
1:-ነህው
2:-ሶርፍ
3:-ተጅዊድ
4:-ተፍሲር
5:-ፍቅህ
6:-አቂዳ
7:-መንሀጅ
8:-ሀዲስ
9:-ሲራ
10:-ሙስጦለህ
11:-ቀዋኢደል ፍቅህ
12:-ኡስሉል ፊቅ
13:-አህላቅ ወል አዳብ
14፡-ስለሴቶቻችን
15:-ንፅፅር
Last updated 2 months, 3 weeks ago