Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ እንኳን ለኢድ አል‐አድሀ በዓል አደረሳችሁ!
*?*?? ሙግቱ አበቃ! ???
?????? ?????
ምዕራፍ 8⃣ ?????? 8⃣
?ክፍል 8⃣0⃣
ድርሰት እና ዝግጅት :- በይበልጣል ተሾመ**
በአንድ ትልቅ መኖሪያ ቤት ውስጥ፤ ሶፋ ላይ ትርሲት እና ጌች እየተሳሳቁ እየተጫወቱ ነው።
"ሔኖክ እንዲ ዓይነት ቀሽም አልመሰለኝም ነበር"
"ተይ እንጂ አንቺ፣ የቀሸመው እኮ ላንቺ ብሎ ነውኮ"
"ሚያገኘኝ መስሎት ነውኮ፤ እያማረው ይቀራል"
"በቃ! ከዚህ በኋላ ይበቃናል! ከዚህ በኋላ እቃቃው ያበቃል፣ ኑሯችንን በሰላም እንኑር"
ድንገት በሩ ተበረገደና አቤኑ እና አባቱ ገቡ። ትርሲት ደንግጣ ቆመች። ጌችም በአግራሞት ይመለከታቸው ጀመር።
የኤቤኑ አባት "ህሊናችሁ እንዴት አስችሏችሁ ነው? እንዴትስ ብታስቡ ነው በሰው ገንዘብ የተንደላቀቀ ኑሮ ምትኖሩት። እኔ ለፍቼ የሰራሁትን ሀብት ነጥቀሽ ልጁን ጥለሽልኝ ሄድሽ፤ አንቼ አምጠሽ የወለድሽው ረግጠሽ የሄድሽውን ልጅ እኔ አልተውኩትም። ከወሰድሽብኝ ንብረት እሱ በልጦብኛል። ግን አሳፋሪዎች ናችሁ" አለ።
ጌች ደንግጦ ከተቀመጠበት ተነሳ። "ምንድነው ትርሲት? እውነት ነው?" አለ። የአቤኑ አባት "ኧረ ባክህ! ከአቶ ምንተስኖት ጋር ተባብራችሁ ሴት እየላካችሁ ሀብት እንደምትነጥቁ ማላውቅ መሰለህ?" አለው። ጌች "ትርሲት! ልጅሽ ነው?" ብሎ ጠየቃት። የአቤኑ አባት ክትክት ብሎ ሳቀ። "እንዲ በቀላሉ አንፋታትም፤ በቅርቡ የእጃችሁን ታገኛላችሁ!" ብሎ አቤኑን ይዞ ሄደ።
ጌች ሶፋው ላይ ቁጭ አለ። "ምንም ነገር መስማት አልፈልግም። ከዛሬ ጀምሮ እዚህ ቤት እንዳላይሽ" አለ።
ሜሮን በቤቷ ውስጥ በጣም እየተኳኳለች ነው። ኤልዲ ቁጭ ብላ እያቻት "አብራሃም ጋ ነው ወይስ ባምላኩ ጋ ነው ምትሄጂው?" አለች። ሜሮን "ሴት ልጅ ምንጊዜም መዋብ ግዴታዋ ነው" አለች። ኤልዲ ሳቅ አለችና "ተይው ባክሽ አውቄአለሁ" አለች። ሜሮን "በይ እናቴ አንቺ አውሪ" ብላ ቦርሳዋን ይዛ ወጣች።
ከሰዓታት በኋላ.....
ኤሊያስ የታገተበት ክፍል ውስጥ። ቹቹ ስልክ ይዞ ለኤሊያስ እያሳየው። "ክፈተው!" አለ። ኤሊያስ ከፈተው። ቹቹ ስልኩን መነካካት ጀመረ። አሁንም አሳየውና "ክፈተው!" አለ። ኤሊያስ "እንዴ! ይሄኮ የግል ሚስጥር ነው" አለ። ቹቹ "ክፈተው!" አለ በድጋሚ። ኤሊያስ ከፈተው። ቹቹ መመልከት ጀመረ። "ቹቹ መጥቻለሁ" የሚል ቀጠን ያለ ድምፅ ተሰማ። ቹቹ "ግቢ!" አለ። በፌስታል የተቋጠረ ምግብ ይዛ ኤልዲ ወደእነቹቹ መጣች።
?ምዕራፍ ስምንት ተጠናቅቋል ?**
ከጥቂት ቀናት እረፍት በኋላ ዘጠነኛውን ምዕራፍ ይዘን እንመጣለን።**
??? @saq_tera ???
??*? ሙግቱ አበቃ! ?*??
?????? ?????
ምዕራፍ 8⃣ ?????? 8⃣
?ክፍል 7⃣9⃣**
ድርሰት እና ዝግጅት :- በይበልጣል ተሾመ
ዳዊት ቢሮው ውስጥ ቁጭ ብሎ ስልክ እየሞከረ ነው። በተደጋጋሚ ይሞክራል፤ ግን አይነሳለትም። ሜሮን ቢሮውን ከፍታ ገባች። "ምንድነው? ምን ሆነህ ነው?" አለች። ዳዊት ስልኩን እያሳያት "ይሄንን ቁጥር ታውቂዋለሽ?" ብሎ ጠየቃት። እሷም በጥርጣሬ ከተመለከተች በኋላ "ቆይ ቆይ" አለችና ስልኳ ውስጥ መፈለግ ጀመረች። "አሀ ምንድነው? የአቶ ዳንኤል ስልክ አይደል" አለች። ዳዊት ደነገጠ።
አብራሃም ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ። ከፊት ለፊቱ ወደ 18 የሚጠጋ ዕድሜ ያለው ታዳጊ ጋር ያወራል።
"ለመጀመሪያ ጊዜ ናቲን ያየሁት ትያትር ሲሰራ ነበር። እኔም ትያትር ተምሬ ስለነበር እንዲያሰራኝ ጠየቅኩት። ጆን፣ ከምሬን ነው ምልህ ገና ሜሮንን ሳያት ነበር ወዲያውኑ እማዬ ትዝ ያለችኝ። ስለሷ ስሰማ ደግሞ የበለጠ ተደነቅኩ። ከስራ የተባረረችው በባምላኩ ምክነያት ነበር። ግን ወደ ትልቅ ስራ ነበር የተቀላቀለችው። ዳዊትን ለማዳን ብላ ራሷን ብቻ ሳይሆን እኔንም በአቶ ዳንኤል ስራ ውስጥ ከተተችኝ። እኔ ግን ዳዊትን ለማዳን ሳይሆን ለሷ ስል ነበር ስራውን የተቀበልኩት። እሷ ግን ልታየኝ አትፈልግም" አለ።
ከፊትለፊቱ የቆመው ታዳጊ "ለምን ወደቤተሰቦቿ አትሄድም? ሴት ልጅ ቤተሰቦቿን የሚንከባከብላትን ወንድ ትወዳለች ይባላል" አለ። አብራሃም "እንዴ! ደግሞ ይሄንን የት ሰማኸው?" አለው ተገርሞ። ልጁም "አይ! ከኔ የልምድ ልውውጥ ላቀብልህ ብዬ እንጂ ለሌላ አደለም" ሲለው አብራሃም የሶፋውን ትራስ አንስቶ ወረወረበት። "ጭራሽ፤ ሴት ማሳደድ ጀመርክ?" አለው ፈገግ እያለ።
አቶ ምንተስኖት በቢሮአቸው ውስጥ ቁጭ ብለዋል። አንድ ወፈር ያለ ወጣት ቢሮውን ከፍቶ ገባ። "አለቃ! አንዳንድ ፍንጮች ኤሊያስ እንደታገተ እያሳዩ ነው" አለ። አቶ ምንተስኖት "እሱ ምንም መረጃ አለመኖሩን ብቻ አረጋግጡልኝ! ስለሱ ደህንነት አይመለከተኝም" አሉ።
በአንድ ትልቅ መኖሪያ ቤት በር በኩል አቤኑ ና የአቤኑ አባት ተያይዘው ገቡ። የመኖሪያ ቤቱን በር ከፍተው ሲገቡ ሶፋው ላይ የተቀመጠችው ትርሲት ደንግጣ ቆመች። አጠገቧ የነበረው ጌችም በአግራሞት ይመለከታቸው ጀመር።
.
.
.
.
. . ....... ???????? ... ይቀጥላል
??? @saq_tera ???
?*?*? ሙግቱ አበቃ! ???
?????? ?????
ምዕራፍ 8⃣ ?????? 8⃣
?ክፍል 7⃣8⃣
ድርሰት እና ዝግጅት :- በይበልጣል ተሾመ**
ሆቴል ውስጥ አብራሃም እና ሜሮን ፊት ለፊት እየተያዩ ተቀምጠዋል። ረጋ ባለ ድምፅ የክርክር ንግግር እየተነጋገሩ ነው።
እሱ ተረጋግቶ ሲያናግራት እሷ በንዴት ትመልስለታለች።
"ለምንድነው ቆይ ያልተረዳሽኝ?"
"ምንድነው ልረዳህ? ታውቀኛለህ ከዚህ በፊት?"
"ይኸው ተዋወቅን አይደል። እኔ ደግሞ ወደድኩሽ"
"እኔኮ የራሴ የሆነ ህይወት አለኝ። ያምሀል እንዴ?"
"ተይ ሜሪዬ"
"አታቆላምጠኝ፣ በሙሉ ስሜ ጥራኝ፤ ይኸውልህ የኔ ወንድም እኔና አንተን ያገናኘን ስራ ነው። ስራችንን ደግሞ ጨርሰናል። ሌላ ስራ ካገናኘን ጥሩ! አለበለዚያ ግን ምንም ማድረግ አልችልም"
"እኔኮ ያኔም አቶ ዳንኤል ጋር የተስማማውት ስራውን ብዬ ሳይሆን ላንቺ ስል ነበር"
"እሱ አይመለከተኝም፤ ግን ዋናው ነገር አልተቀበልኩህም"
ብላ ከተቀመጠችበት ተነስታ ሄደች።
ሜሮን ወደ ቤቷ ሄደች። እንደገባች ሶፋው ላይ ቁጭ አለችና መጣራት ጀመረች። "ኤልዲ......ኤልዲ .... ኤልዲ"። ዕድሜዋ 18 የሚገመት፣ ቀይ፣ መልከመልካም፣ ፀጉሯን ፈርዛ ወደኋላ ለቀቅ ያደረገች። ቀጠን ያለች ወጣት ነጭ ቱታ እና ነጭ ቲሸርት ለብሳ ወጣች።
ሜሮን "ምነው ፈንዲሻ መሰልሽ" አለቻት። ኤልዳ ፈገግ እያለች "አንቺ የተጠበስሽው እያለሽ ነው እንዴ እኔ ፈንዲሻ ምመስለው" ስትል ሜሮን ኮስተር አለች። "ምን እያልሽ ነው?" አለቻት። ኤልዳ "ተይ ባክሽ" አለችና ሄዳ አጠገቧ ተቀመጠች። "አሁን ሁሉንም ነገር መስማት እፈልጋለሁ። እንዲ ስላበደልሽ ልጅ" አለች ኤልዳ። ሜሮን "ስለማን?" ብላ ጠየቀቻት። ኤልዳ ፈገግ እያለች "ስለአብርሽ ነዋ" አለች። ሜሮን ደነገጠች። "ማን ነገረሽ?" አለቻት ኮስተር ብላ። ኤልዳ "አንቺን ፍለጋ እዚህ ድረስ መጥቶ ነበር" አለች።
ሔኖክ በቤቱ ቁጭ ብሎ ስልክ እያወራ ነው።
"ይኸውልህ ሔኖክ ከዚህ በኋላ ተጠንቀቅ"
"አይ አባ እኔማ ያኔ እራሱ ናቲ ሲነግረኝ እምቢ ብዬ ነው እንጂ"
"አሁን ስማኝ፣ እኛ ወደኢትዮጵያ ልንመለስ ነው። ያው እዚህ ያለውን ለወንድሜ አስረክበናል። አሁን ኑሯችንን በኢትዮጵያ ልናረግ ልንመጣ ነው"
"ዋው፣ ደስ ይላል አባ፣ እና መች ልትመጡ ነው?"
"እሱን አሳውቅሀለው"
"እሺ አባ"
ሜሮን ሶፋው ላይ ቁጭ ብላ ኤልዳ ደግሞ እግሯን ሰቅላ ጭንቅላቷን የሜሮን እግር ላይ አርጋ የሜሮንን ዓይን ወደላይ ታያለች። ሜሮን እየነገረቻት ነው።
"ድንገት ባምላኩ ላይ የተደፋ ቡና ነበር ከስራዬ ያስባረረኝ። እኔ ከስራዬ ስባረር ወደ ሌላ ትልቅ ስራ ገባው። ዳዊትን አገኘሁ። ዳዊት መልካም ሰው ነው። ግን ቶሎ የመበሳጨት ችግር አለበት። እዛ ስገባ ባምላኩን ሰራተኛ ሆኖ አገኘሁት። ያን የመሰለ የትልቅ ባለሀብት ልጅ ሆኖ እዚ እንዴት ተቀጥሮ ይሰራል ብዬ ሳስብ፣ ለካ የዳዊትን አባት የገደለው ሰው ዳዊትንም እንዳይገድለው ሊታደገው ነበር የመጣው። ደግሞ ዳዊትን ሚታደገው ከገዛ አባቱ ነበር። ይህንን ስሰማ በጣም ደነገጥኩ። ማመን ተሳነኝ። አብራሃምን አልጠላውም። ግን ባምላኩ በኔ ልዩ ቦታ አለው" በማለት ተናገረች።
ኤልዳ "ባምላኩ ምትዪው የቹቹ ወንድም ነው አይደል" አለች። ሜሮን "ቹቹን ታቂዋለሽ እንዴ?" ብላ ጠየቀቻት። ኤልዳ "አዎ፣ አንዴ ታግቶ እያለ። በአጥር ዘልሎ የአቤኒ አባት ሊስትሮ ላይ ወረደና። እኛ ጋር ምግብ በልቶ፣ ተጫውቶ ቆይቶ ነበር የሄደው" አለች
.
.
.
.
. . ....... ???????? ... ይቀጥላል
??? @saq_tera ???
*?*?? ሙግቱ አበቃ! ???
?????? ?????
ምዕራፍ 8⃣ ?????? 8⃣
?ክፍል 7⃣7⃣
ድርሰት እና ዝግጅት :- በይበልጣል ተሾመ**
ቹቹ በእጁ መዶሻ ይዟል። ሄዶ የኤሊያስ አፍ ላይ ያለውን ፕላስተር አነሳው። ወዲያው ኤሊያስ መለፍለፍ ጀመረ። "ኧረ እባክህ ስለፈጠረህ..." ሲል ቹቹ "አፍህን ዝጋ! የፈጠረህን የት ታቀዋለህ? እሱን ብታውቀው ኖሮ ይህን አታደርግም ነበር" አቸው። ኤሊያስ "ቆይ ከኔ ምንድነው ምትፈልገው? የፈለግከውን ንገረኝና ከቻልኩ ልስጥህ" አለ። ቹቹ በማላገጥ ስሜት ሆኖ "ካልቻልከውስ?" አለ። ኤሊያስ "ካልቻልኩማ ከየት አመጣዋለው?" አለ እየፈራ።
በአቶ ምንተስኖት ሆቴል ውስጥ ዳዊት ከአለማየሁ እና ከሰለሞን ጋር ቁጭ ብሎ እያወራቸው ነው። "ማነው ገንዘቡን ዳዊት ነው የወሰደው ብሎ የነገራችሁ?" ብሎ ጠየቃቸው። ሰለሞን "ስሄድ፣ ንጉሴ የሚባል ሰው ወደ ከተማ ገብቶ ሀብታም ሆነ ሲሉኝ፤ ደግሞም በአጭር ጊዜ ውስጥ ሀብታም መሆኑን ሳስብ በቃ እርግጠኛ ሆንኩ" አለ። አለማየሁ "ግን ዳዊት አባትህ እንዴት....." አለ።
ዳዊትም "በ7 ዓመቴ ነበር ወደዚህ የመጣነው። ያኔ እዚህ እንደመጣ መጀመሪያ የተዋወቀው ከአቶ ምንተስኖት ጋር ነበር። ከዛ አብረው ስራ ጀመሩ። አባቴ ውጪ ሄደ። በመሐል አንዴ ብቻ ለጥቂት ቀን መጣ። ከዛ ተመልሶ ሄደ። ግን፣ ተመልሶ ወደውጪ ላይሄድ ለመጨረሻ ጊዜ ሲመጣ ይሄ አረመኔ በላው" አለ።
አለማየሁ "ማነው?" አለ። ዳዊት "ምንተስኖት ነዋ" ሲል ወዲያው የስልክ መልዕክት ገባለት። <ለአለማየሁ ምንም አይነት ነገር እንዳትነግረው> ይላል። ዳዊት ደነገጠ። አለማየሁ "አንዴ መታጠቢያ ቤት ደርሼ ልምጣ" ብሎ ሄደ። ዳዊት ቀስ ብሎ ተከተለው። አለማየሁ እንደደረሰ ስልኩን አውጥቶ ደወለ። "አቶ ምንተስኖት፣ ዳዊት የአባቱ ገዳይ እርስዎ እንደሆኑ አውቋል" አለ።
.... ከውጪ ሆኖ ዳዊት እየሰማው ነበር።
.
.
.
.
. . ....... ???????? ... ይቀጥላል
??? @saq_tera ???
?*?*? ሙግቱ አበቃ! ???
?????? ?????
ምዕራፍ 8⃣ ?????? 8⃣
?ክፍል 7⃣6⃣
ድርሰት እና ዝግጅት :- በይበልጣል ተሾመ**
በዳዊት መስሪያ ቤት መግቢያ በር ላይ አለማየሁ የሰለሞን እግር ላይ ተደፍቶ እየለመነው ነው። ሰለሞን በድንጋጤ ውስጥ ሆኖ "ተነስ እንጂ አሌክስ እንዴ" ይለዋል። አለማየሁ እዛው እንደተንበረከከ "ይቅር በለኝ ይቅር ካላልከኝ አልነሳም" አለ። ሰለሞን "እሺ ብዬሀለው" ሲለው ተነሳ።
አቶ ምንተስኖት በቢሮአቸው ውስጥ ሆነው መግቢያው ጋ ከቆመው ወፍራም እና ጥቁር ወጣት ጋር ይነጋገራል። "አለቃ! ኤሊያስ ጠፍቷል። ይመለሳል ብለን ብንጠብቅም ሊመጣ አልቻለም። ስልኩ ሲጠራ አይነሳም ነበር አሁን ግን ጭራሽ ጠፋ" ብሎ ሲናገር አቶ ምንተስኖት ደነገጡ። "ያኔ ከባምላኩ ቪዲዮውን ስታመጡ፣ እሱ ጋ የቀረ ነበር?" ብለው ጠየቁት። ወጣቱ "አይ አይ፤ ሙሉውን ለእርስዎ እንደሰጠ ነው የተናገረን፤ እኛን ዋሽቶን ካልሆነ በቀር ምንም እሱጋ የቀረ ነገር የለም" አለ። አቶ ምንተስኖት "በደምብ ፈልጉት!" አሉ።
አለማየሁ በዳዊት ቢሮ ውስጥ ተቀምጦ ከዳዊት ጋር እየተነጋገረ ነው።
"ዳዊት የእውነት ጥፋቱ የኔ ነበር"
"ችግር የለውም አልኩህኮ"
"እና ከልብህ ይቅር ካልከኝ በቃ ወደቀድሞው ስራዬ መመለስ እፈልጋለሁ"
"ማለት? የቱ ነው ያንተ የቀድሞ ስራ?"
"እዚሁ አንተጋ ጥበቃነቱ ይሻለኛል፤ ሌላ ምንም መሄጃ የለኝም"
ዳዊት ጥቂት ደቂቃ አሰበ። "እሺ ፤ እንማከርበትና አሳውቅሀለው" አለ።
ባዶ ምንም ነገር የሌለበት ቤት ውስጥ ቹቹ ወንበር ላይ ተቀምጧል።
"እናቴና ወንድሜን በጣም ነው ምወዳቸው፤ በነሱ ከመጣብኝ ማንንም አልምርም፣ አባቴ እንኳ ቢሆን፤ ያኔ ከመወለዴ በፊት ከቤታችን ሁለት ሰዎች ገንዘብ ሰርቀው ጠፉ። ገንዘቡን ደግሞ ዳዊት ይዞት መጣ። ከአባቴ ጋርም ተገናኙ ሰሩ። አባቴ ግን በጣም ራስ ወዳድና ስግብግብ ስለነበረ የዳዊትን አባት ገደለው። ታዳያ፣ ለአባቱ ያልተመለሰ ለዳዊት ይመለሳል? በፍፁም። እናም ባምላኩ ሊያድነው መጣ። ባምላኩን ወንጅለው አሳሰሩት። በእጁ የያዘውንም መረጃ ወሰዱ።
.
.
.
.
ስለዚህ፣ ይህንን መረጃ እኔ እፈልገዋለሁ። መረጃውን የወሰድከው አንተ ነህ። መረጃውን ስጠኝና ልፍታህ" አለ።
ከፊትለፊቱ ባለ ጠረጴዛ ላይ ኤልያስ ጥፍንግ ተደርጎ ታስሮ አፉ በፕላስተር ታፍኖ ቁጭ ብሏል።
.
.
.
.
. . ....... ???????? ... ይቀጥላል
??? @saq_tera ???
*?*?? ሙግቱ አበቃ! ???
?????? ?????
ምዕራፍ 8⃣ ?????? 8⃣
?ክፍል 7⃣5⃣
ድርሰት እና ዝግጅት :- በይበልጣል ተሾመ**
በእነ ናቲ ቤት ውስጥ። አቶ ምንተስኖት ደንግጠው ቆመዋል። ማርታ በንቀት ዐይን እያየቻቸው ነው። "ምንድነው ጉዱ?" አሉ አቶ ምንተስኖት በድንጋጤ ተሞልተው። ማርታ "አንተ ንገረን እንጂ፣ ዐይን በጨው ታጥበህ ትመጣለህ?" አለች። አቶ ምንተስኖት "ዳዊት" ብለው ዳዊትን ጠሩት። ዳዊት በብስጭት ተሞልቶ ዝም ብሎ ያፈጣቸዋል። አቶ ምንተስኖት "ምን ሆናችኋል?" አለ። አብራሃም ግራ ተጋብቶ ሁሉንም ያያቸዋል። ባምላኩ፣ ዳዊት፣ ሜሮን ቹቹና ማርታ ኮስተር ብለው አቶ ምንተስኖት ላይ ማፍጠጥ ጀመሩ።
አቶ ምንተስኖት በፍጥነት እርምጃ እየተራመዱ ቤቱን ለቀው ወጡ። አብራሀም እንደደነገጠ ነው። ሌሎቹ ጠቅላላ ክትክት ብለው ሳቁ። "የታባቱ!" አለች ማርታ።
ሔኖክ እና ማሕሌት በካፌው ውስጥ ተቀምጠው እየተነጋገሩ ነው።
"እስካሁን የኔን ነገርኩህ! አሁን ደግሞ ያንተን ንገረኝ" ብላ ጠየቀችው ማሕሌት።
"እናት እና አባቴ የሚኖሩት ውጪ ሀገር ነው፤ እዚህ ሀገር የሚመረት ብስኩት ወደውጪ እየሄደ እንዲከፋፈል ነው ሚሰሩት። የሚሰሩበት ዋና መስሪያ ቤቱ ደግሞ ዳዊት የሚባል ልጅ አለ፤ የሱ ነው። እና የዳዊት አባት አቶ ምንተስኖት ከሚባሉ ሰው ጋር ነበር ስራቸውን የጀመሩት። ግን እንደተጀመረ ወዲያው ወደውጪ ሄደው የማከፋፈሉን ስራ ተያያዙት። ከዚያም ከአባቴ ጋር ተገናኙና አብረው መስራት ጀመሩ። የዳዊት አባት ገና ኢትዮጵያን ከመርገጣቸው ሳምንት እንኳ ሳይሞላ ተገደሉ"
በማለት ሲነግራት። ማሕሌት ግራ ተጋብታ "እንዴ አሁን የነገርከኝ እኮ የአባትህን እና የወዳጆቹን ታሪክ ነው። እኔኮ የጠየቅኩት ስላንተ ነው" አለችው።
ሔኖክ ቀጠለና "እሺ፣ አግብቼ ነበር፣ ግን ውሸታም እና ሌባ ሴት ነበረች። ከሀዲ ዘራፊ ናት" ሲል አቋረጠችው። "ኧረ ተው! አሁንም ያንተን ትተህ የድሮ ሚስትህን ባህሪ እየነገርከኝ ነው!" አለች።
"ስሜታዊ ሆኜ ነው"
"ስሜትህን ገታ አድርገዋ፣"
"እሺ አደረግኩት እንበል፤ ስለምን እንድነግርሽ ፈልገሽ ነው?"
"ያንተ የስራ ድርሻ ምንድነው?"
"በፊት የእነዳዊት መስሪያቤት ነበርኩ አሁን ግን ለቅቄያለሁ። በራሴ ቆሜያለው"
"ከሚስትህ የወለድከው ልጅ ነበረህ" ብላ ጠየቀችው ፈራ ተባ እያለች። ሔኖክ "አይ የለኝም" ሲል ማሕሌት በረጅሙ ተነፈሰች። ሔኖክ ፈገግ አለ። ማሕሌትም ፈገግ እያለች ታየው ጀመር።
.
.
.
.
. . ....... ???????? ... ይቀጥላል
??? @saq_tera ???
?*?*? ሙግቱ አበቃ! ???
?????? ?????
ምዕራፍ 8⃣ ?????? 8⃣
?ክፍል 7⃣4⃣
ድርሰት እና ዝግጅት :- በይበልጣል ተሾመ**
ማሕሌት። ቀይ፣ መካከለኛ ተክለሰውነት ያላት፣ ዕድሜዋ ወደ 25 ሚጠጋ፣ ቆንጆ እና መልከመልካም ሴት።ካፌ ተቀምጣለች። እንዲህ ብላም ትናገራለች። "ከ5 ዓመት በፊት ነበር ከሀገር የወጣሁት። ከሀገር የወጣሁት ከእናቴ ጋር ነበር። አባቴ ከሀገር መውጣት አይፈልግም። ለዛ ነበር ከእናቴ ጋር የሄድኩት። አሁን ግን አባቴን ፈልጌ ነው የመጣሁት። የሚያግዘኝን እፈልጋለሁ። አባቴን ማግኘት አለብኝ። አባቴ ያስፈልገኛል"
ናቲ ሶፋ ላይ በጋቢ ተከናንቦ ተኝቷል። ከጎን ባለው ሶፋ ላይ ባምላኩ፤ ዳዊት እና ሜሮን ተቀምጠዋል።
በበሩ በኩል አቶ ምንተስኖት ገቡ። ዳዊት ደንግጦ ከተቀመጠበት ተነሳ። አቶ ምንተስኖት "እንዴት ናችሁ? ተሻለው እንዴ?" አሉና ከነሜሮን ፊት ለፊት ባለው መቀመጫ ቦታ ተቀመጡ። ቀና ብለው ሲያዩ ዳዊት ቆሞ ግራ በመጋባት ስሜት እያፈጠጣቸው ነው። "ምነው ዳዊት ተቀመጥ እንጂ" አሉ። ባምላኩ ቀስ ብሎ የዳዊትን እግር ረገጠ። ዳዊት ደንገጥ አለና ተቀመጠ።
አሁንም በሩ ተከፈተና አብራሃም በፌስታል ብርቱካንና ሙዝ ይዞ ገባ። አቶ ምንተስኖትን እንዳየ ደንግጦ በእጁ የያዘውን ፌስታል ጣለው። ብርቱካንና ሙዙ ተዘረገፈ።
ቹቹ ከውስጥ ወጣ። ማርታም ተከትላው መጣች። አቶ ምንተስኖት ከተቀመጡበት ተነሱ።
ካፌ የተቀመጠችው ማሕሌት ማናገሯን ቀጥላለች። "አሁን ግን አባቴን እንዳገኝ አንተ ትረዳኛለህ" አለች። ከፊት ለፊቷ የተቀመጠው ሔኖክ በፈገግታ ተሞልቶ "በጣም እረዳሻለው" አለ።
.
.
.
.
. . ....... ???????? ... ይቀጥላል
??? @saq_tera ???
*?*?? ሙግቱ አበቃ! ???
?????? ?????
ምዕራፍ 8⃣ ?????? 8⃣
? ክፍል 7⃣2⃣
ድርሰት እና ዝግጅት :- በይበልጣል ተሾመ**
አለማየሁ በሆስፒታል ውስጥ እየተራመደ፣ አንድ የቆመ የህክምና ባለሙያ አጠገብ ሄዶ ቆመ። "ዶክተር! ናትናኤል የሚባል ታካሚ እዚህ ገብቶ ነበር እና የት እንዳለ ማወቅ ፈልጌ ነበር" አለው። የህክምና ባለሙያው ትኩር ብሎ አይቶት "ገብቶ ነበር! ግን ዛሬ ወጥቷል" አለ። አለማየሁ "አመሰግናለሁ" ብሎ ወጣ።
ሔኖክ ከሁለት ወፋፍራም ወንዶች ፊት ለፊት ቆሞ እያናገራቸው ነው።
"ከጀርባዋ ማን እንዳለ በደምብ አጣሩ። በደምብ! በፍፁም እንቅስቃሴያችሁን ማንም ማወቅ የለበትም። ማንም ይሁን ማን በጥራጥሬ ዐይን ነው ምታዩት። ወንድሜ ናቲ ቢሆን እንኳ ይጠረጠራል። እያንዳንዱን እንቅስቃሴዋን ተከታተሉ" አለ።
ባምላኩ ወደ ዳዊት ስራ ቦታ ሄደ። እንደደረሰ የዳዊት ቢሮ ውስጥ ገባ። ዳዊት ተቀምጧል። ባምላኩ ግራ በመጋባት "ምንድነው እንደዚ አቻኩለህ የጠራኸኝ?" አለ። ዳዊት ረጋ ብሎ "ተቀመጥ!" አለው። ባምላኩ ተቀመጠ። ዳዊት ተነሳና የቢሮውን በር ቆለፈውና ቁልፉን ነቀለ። ባምላኩ መደንገጥ ጀመረ።
ዳዊት ሽጉጥ አወጣ። ባምላኩ መንቀጥቀጥ ጀመረ። ዳዊት ወደ ባምላኩ ደግኖ "የአባቴን ገዳይ ንገረኝ!" አለ። ባምላኩ" እእእ......እኮ ተረጋጋና .. ሽጉጡን አስቀምጠው" አለ። ዳዊት "ትነግረኛለህ ወይስ አትነግረኝም" አለ። ባምላኩ "እሺ........ አባትህን የገደለው........ ..............
.
.
.
.
. . ....... ???????? ... ይቀጥላል
??? @saq_tera ???
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад