Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 8 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 3 weeks, 1 day ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 months, 2 weeks ago
እስኪ ልጠይቅሽ
`እስኪ ልጠይቅሽ
ውስጤን ከገለጥሽው
እንዴት ተረዳሽው?
እንዴት አነበብሽው?
ያን ዝብርቅርቅ አለም
የገፄን ሙንጭርጭር
አንቺም እንደሌላው
ተውሽው ወይ በጅምር
ወይስ
በልባድ ገመትሽኝ
ደረሽ ድምዳሜ?!
ሰጠሽኝ ስያሜ?!
አልሽኝ ውስጡን ለቄስ....
እስኪ በይ ንገሪኝ
ውስጤን ከገለጥሽው
እንዴት ተረዳሽው?
እንዴት አነበብሽው`?
ሰውን በውጪያዊ ገፅታው ልንፈርደው አንችልም። የሰውንም ውስጣዊ ገፅታ መረዳት አዳጋች ይሆናል ምክንያቱም ሰው ምድር ላይ ካሉ ውስብስብ ፍጥረቶች አንዱ ነው።ስለዚህ ውስጡን ለፈጣሪ እንተወው።
*ፀጋሽ እዳሽ
አልቅሰሻል መንታ መንታ
ሲቃ ይዞሽ ላይገታ
ብለሻል ቆላ ደጋ
ከእኔጋ....
በጀርባ አዝለሽ
በባዶ እግርሽ
እኔው ሸክምሽ እኔው ጌጥሽ
እንዴት ነው ግን አንቺስ ግብርሽ?!
የኔ ቡጭር ላንቺ ቁስል
የኔ ልብልብ ላንቺ ክስል
ለህመሜ መድሃኒቱን ስታስሺው ያለድካም
ያሳለፍሽው አይነገር አይለካም
ስንት አለፍኩኝ ባንቺ ፍዳ
እኔ.....
ያንቺው ፀጋ ያንቺው እዳ
ከየት ምድር እሱ አፈራሽ
ካንቺው ፈጥሮኝ ለኔው ሰራሽ
አዳንሽኝ ተንከራተሽ
ቁልቁል ወርደሽ ዳገት ወጥተሽ
አለም ፈካ ሰላም ሞላኝ
በመከራሽ እኔ ደላኝ
ኑሪልኝ ሺ....
አይደል ስልሳ አይደል ሰባ
ለምልሜያለሁ ባንቺው እንባ።
በኛ ለኛ ለተንከራተቱ እናቶቻችን*
ፅድቅና ኩነኔ
በጥምቀቱ ማግስት ብዬ ነበር ብቅ፣
ግማሹም ላንቺ ነው የቀረውም ለፅድቅ፣
ከቅዱስ ሚካኤል ደብር የዮዘገሊላ ለት፣
ደምቀሽ ባገር ልብሱ አምረሽ ባገር ጥለት፣
ከዝማሬው መሃል ስታሸበሽቢ፣
እኔን አታስቢ......፣
ከወረቡ መሃል ስትውረገረጊ ስትይ ወዝ ወዝ፣
ፈሰሰልሽ ልቤ እንደ ግዮን ወንዝ።
ኧረ ተይ ገድቢው ድንበር ሳይሻገር፣
ኋላ.....
የኛ ነው እንዳይሉሽ ገብቶ ባዕድ ሃገር።
እንደልማዳቸው......፣
እኔ ግን....፣
እኔማ ነበር አመጣጤ
ነበር አወጣጤ....
በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ልመታ
አንቺን በእይታ
በፀሎት ከጌታ
ዳሩ ግን.....
ወይ አይቼ አልጠገብኩ
ወይ ከፀሎቱ አልሆንኩኝ፣
ለ12 እግዚኦ 15 ቆጠርኩኝ።
ተኮነንኩልሻ፣
ተይ ቀልቤን መልሻ።
ይሁና.....
አይ አንተ መልአኩ
አሁን ምን ይሉታል....
ካልጠፋ ፈተና እሷን በኔ ላይ መላኩ
እንጃ!!
አንተ ታውቀዋለህ
....
እናማ እልሻለሁ....
እኔስ አንዴ ተኮነንኩኝ በአንቺ በኩል ልፅደቅ፣
አብረን ባንወጣም ነይ አብረን እንጥለቅ።
ሎሚ ልገዛ ብል
ዋጋው ጣራ ነካ
ኮብል እንዳልይዝም
ለደረትሽ ሳሳሁ
ከመሳሳት በላይ
ድንጋይ ሸክም ሰጋሁ
ቢያደርገኝ
የቴክኖ ተማሪ
የበርሃው ኗሪ
በእንቧይ ተከብቤ
እንደው ከጭፍጨፋ
ተረፍረፍ ያለውን በፌስታል ሰብስቤ
የጥምቀት ለት ወጣሁ
ታቦታቱን ልሸኝ
እግረ መንገዴንም
ያቺን ሸጊት ላገኝ
ያንን ሁላ እንቧይ እንደው ተሸክሜ፣
ስፈልጋት ውዬ ሳስሳት ከርሜ፣
ሳላገኛት መጣሁ ደጁን ተሳልሜ።
የኔ ሞናሊዛ
ሞናሊዛ ምልሽ፣
በውበትሽ ከቶ እንዳይመስልሽ፣
ሞናሊዛ ምልሽ......
አስደንቆኝ አይደል የገፅሽ ማማሩ፣
ድንቅ አፈጣጠሩ፣
ሞናሊዛ ምልሽ ....
ለዚህ ነው ይኸውልሽ....
ውበት ባንቺ ቢፈስ
ቢሞላሽ የማያልቅ ጥፍጥና፣
ነፍስ ያልዘራ ሰው ላይ
ምን ሊያረግ ቁንጅና።?
ሰማንያው ምን በላው???
ተስፋ አርጌ ነበር
ምስራች ሲነገር
ታዲያ ምን ያረጋል
ለድስት የተባለው በወረቀት ሲቀር
ተስፋ አርጌ ነበር
ሆዴን ሰፋ ሰፋ
ዛሬ እንዲህ ልከፋ
በመቶ ብር ዋጋ
ቁጥር ተለወጠ
ድስቱ ግን እዛው ነው
ድሮን የመረጠ
ተስፋ አርጌ ነበር
ተስፋዬን ሰው በላው
የኛን ድስት ቸገረው
የነሱ እየደላው
ሃያውስ አለ አሉ
ሰማንያው ምን በላው???
ብእሬ እንደፃፈችው!!
የምግብ ሜኑ ተስተካክሏል ተብሎ ላልተስተካከለልን የግቢ ተማሪዎች በብእሬ የተፃፈ የስሞታ ግጥም?
ሲተካ በጋው በክረምቱ
ቦታ ሲለቅ ቀንም ለምሽቱ
ሰላም የተባለው ሲሆንበት ነውጥ
አፍሪካም ወግ ደርሷት መሪ ስትለዋውጥ
ሞትኩኝ በመናፈቅ
ሞትኩኝ በመጠበቅ
ውበትሽ መች ይሆን
ስልጣኑን የሚለቅ?!
Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 8 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 3 weeks, 1 day ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 months, 2 weeks ago