Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

አል –ፈቂር ኢለሏህ ( ሷድቅ አወል) አልወራቢይ

Description
أقــول الحــق ولو كـان مـــرا
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago

3 weeks, 1 day ago

The Virtue of Friday:

‎Ibn al-Qayyim رحمه الله
‎"Friday is the day of worship, its comparison to other days like the comparison of the month of Ramadan to other months and the hour in it is like the Night of Decree in Ramadan."

‎[Zaad Al-Ma’aad | 1398]

3 weeks, 1 day ago
3 weeks, 1 day ago

🔸 الرد على ابن منور بعنوان "تَنْوِيرُ الظُّلُمَاتِ وَالْحَوَالِكِ فِيْ شَطَحَاتِ وَتَمْيِيعَاتِ ابْنِ مُنَوَّرِ الْهَالِكِ"

የሙነወር ልጅ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ዐባስ መስጂድ ላይ ባደረገው ተልቢስ ላይ የተሰጠ ምላሽ!

በዩንቨርሲቲው ሰለፊዮች መስጂድ ላይ በሸዋል 16 የተሰጠ ምላሽ!

🎙 በወንድም፦ አቡ ዘከሪያ ሙሀመድ አል-ወልቂጢይ

t.me/Deawaaselefiyah
t.me/Deawaaselefiyah

1 month ago

አ/አወል  ኢልያስ ጀይላኒን ሲያወድስ አይ ውዳሴ አይደለም የሂወት ታሪክ ነው ያወራው ይላል ይህስ የሱ ትልቁ ቅጥፈት አይደለምን የሚገርም ሰው ነው አላህ ይምራው

1 month ago

ቀጣፊው አ/አወል ሙሀመድ ሰዒድ የተጠየቀውን ጥያቄ ሁሉ መልስ ሰጥቷል ይላል እዩት ይህ ዉሸታም ሰውዬ እራሱ እየቀጠፈ ሌሎችን ዋሺ ያስብላል። በሱቤት ሙመይዓ ማለት ተቃሩበል አድያን(የሀይማኖቶች አንድነት)  ሲኖር ነው  ምነኛ የሚገርም ፍጡር ነው። ስለሚከተላቸው ሰዎች ሲወራለት ስለኔ ይላል ወይ ከነሱ ጠራሁ አይመለከተኝም አይልም ከነሱ ሁኖ የነሱ ስም ሲጠራ ስለሚሸነፍ( ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልምና) ሰውዬው ተወዛግቧል።

1 month ago

አ/አወል የመርከዙ ሰዎች ከኢኽዋኖች እና ከሱፍዮች  የተስማሙበትን ድሮ ኢኽዋኖች የሁደይብያ ስምምነት የአሀኖቹ የኢትዮጵያ አሊሞች የአንድነትና የትብብር ሰነድ ብለው አዘጋጅተው መስማማታቸዉ እንደ አ/አወል የተጃጃለ አስተሳሰብ ከበፊቱ የተሻሻለ ነው ይለናል። መቼ ነው የቢድዓና የሱና ባለቤቶች አንድ የሚሆኑት የዞረበት እንጂ አያሻማም መቼም አንድ አይሆኑም

1 month, 1 week ago

#ከሸዋል 6ቀን (ስድስቶን) የመፆም አይቀሬነት፣             እና
#የሚመጡ_ምክንያቶችን
,      #የሚያስዎግድ_ትውስታ!!


አሰላሙ ዓለይኩም ወረህመቱላህ ወበረካትሁ የተከበራችሁ ሙስሊም  የሱና ወንድም እህቶች አባትና እናቶች በቅድሚያ አልሐምዱሊላህ እንኳን አላህ ለስድስቶ ፆም በሰላም አደረሰን እያልኩ በመቀጠልም ከላይ ከርእሱ እንደተመለከታችሁት የስድስቶን ፆም ለመፆም አይቀሬ ስለ መሆኑና ልብ ላይ የሚመላለሱ እንቅፋቶችን የሚያዳፍን ትውስታየን ነው የማቀርብላችሁ!
በርግጥ ፆሙ ከተጀመረ በኋላ ዘግይቼ በመምጣቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ! በመሆኑም ቀድማችሁ ቁርስ ያልበላችሁ የሱና ፆም ከነጋ በኋላ ረፋድ ላይም መነየት ስለሚቻል አሁን መነየት (ማሰብ) ትችላችሁ! አይ አስቀድማችሁ የበላችሁ ደግሞ በሸዋል ወር ሙሉውን የስድስቶን ፆም መፆም ስለሚቻል ቀጣይ የማስታውሳቸውሁን እንመልከት።
መቼም አብዛሃኞቻችሁ እንደምታውቀት ረመዳንን ፁሞ ከሸዋል ስድስት ቀኖችን (ስድስቶን) የጨመረ ልክ አመቱን እንደፆመ ነው። ይህ ማለት ደግሞ በደረጃ ቢለያዩም የአመቱ ቀሪ ክፍሎችን በመሸፈን ረገድ  ስድስቶም ልክ እንደ ረመዳን ቦታ አላት ማለት ነው።
ስለዚህም ወደ ዋናው ጉዳያችን ስንመለስ ከሚነሱ ማዳከሚያዎች ውስጥ እየጠቀስን መፍትሔዎቻቸውንም ጭምር እናያል።
-ያነን ውድ ወር ረመዳንን ነበርነበት ብለህ ስድስቶን እንዳትዘናጋ! አዎ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በረመዳን ጥፋቶችን ከመስራት ያልተቆጠብኩና በዛ ወቅት ያልተጠቀምኩ፣ አሁን ምን ለውጥ ላመጣ ነው? የሚል ከባድ የሰይጣንን ወጥመድ እንዳትከተል! ለዚህም በመጀመሪያ ይሄን አስታውስ
{{فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرًّا يَرَهُ }}
{{የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡ የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡}}
[ ሱረቱ አል-ዘልዘላህ: 7 - 8 ]

ሥለዚህ በእርግጥ እንደ ረመዳን ባይሆኑም ሌሎችን ትልልቅ ነገሮች ወይም ትልልቅ ወቅቶችን ረመዳን አለፈኝ ብለህ ትተዋለህን? አላህኮ የብናኝ ክብደት ያህል የሆነች ሥራን ትንሽ ናት ብሎ አይተውም። ደግሞ የፈለገ ቢገዝፍ እርሱ ሊምረው ይችላል። ትልቅ መልካም የሰራህ የመሰለህ ሥራህ ደግሞ  ተቀባይነትን ያላገኘ ሊሆን ይችላል። ታዳ ማንኛውን ምሮልህ ማንኛውን እንደሚቀበልህ ታውቃለህ?
ስለዚህ መቸም ቢሆን በሠራሀው ጥፋት ተፀፀት እንጅ ሥራየ ተቀባይነት አያገኘም ብለህ ተስፋ በመቁረጥ ሌሎች ወንጀሎችን መቀጠልና መልካም ሥራዎች መተው የለብህም። በመልካም መሽቀዳደም ረመዳን እስካለ ብቻ ሳይሆን ህይዎትህ እስካለች ድረስ ሰበብ አድርስ ተስፋ አትቁረጥ!! አላህ የፈለገውን ሰሪ ነው
{{ إن ربك فعال لما يريد }} {{ጌታህ የሚሻውን ሠሪ ነውና፡፡ }}     [ ሱረቱ ሁድ - 107 ]
-ሌላው የምግብ ውደታና በረመዳን ምክንያት የተከሰተ የምግብ ናፍቆትን ተከትሎ የሚመጣ ነው። ይህ ደግሞ አነሰም በዛም ትላንት ዒድ ስንበላ ሰንውል ይሄ ነው እንደ ሲበሉ መዋል ወይኔ ፆሜ ብለን በምናስብበት ደረጃ ደርሰን ልኩን አውቀነዋል። ምናልባትም ዛሬ ያልፆማችሁም ሲበሉ ከመዋል እርካታ ይልቅ የፆም እርካታ በብዙ እጥፍ እንደሚለይ አመዛዝናችሁ ከአሁን በኋላ ስድስቶን አጥብቃችሁ ለመፆም ወስኑ! እንፁም; በተረፈ አላህ ይገዘን!!
-ሌላው ወር ረመዳንን ሰይጣን ጋር ሲነፋፈቅ የቆየ፣ረመዳን ሲዎጣለት የተደሰተ፣የስድስቶ ፆም የሞት ያህል የምትከብደው ካለ ይህ በጣም ከባድ ቢሆንም  ነገር ግን ሰይጣንን አመት ሙሉ አብሮት ሊኖር ነው። ነፍሱ እርክት የምትለበትን ነገር ሁሉ ሊያሰራው ካሰራው በኋላ እንደገና መፀጸት ሰይጣን ጋር ጭቅጭቅ አመቱን ሙሉ ክፍት ነው። ሥለዚህም ሌላው ቢቀር ለማያመልጠው ሰይጣን ቦታ ሳይሰጥ ለሚያመለጠው ታላቅ ዒባዳ ቅድሚያ ቦታ ሰጥቶ መጠናከር አለበት። ይህችን ወቅት በህይወታችን መቼም አናገኛትም። በርግጥ ሰይጣን የያዘውን ርካሽ ነገር በጣም ወድና ነገ የማይገኝ አስመስሎ ያቀርባል። ይህም ሰውየውን ጀሀነም ይዞት እስሚዎርድ ድረስ  አይላቀቀውም።
-ሌላው አሁንም ብዙዎቻችን ላይ እንቅፋት የሚሆንብን ምክንያት በወንደ ላጤዎች የሚበዛ ሲሆን እንኳን ስድስቶን ረመዳንም ራሱ የሚያፆመኝ አጥቼ ሴት የለኝ ብዙውን ስሁር ሳልበላ እየዋልኩ ብዙውን ደግሞ ፊቴ ድመት እስከሚመስል እንደ ሴት ምድጃ ለምድጃ እየተጭሮቀሮኩ ነው ያሳለፍኩት የሚል ሲሆን ለዚህም በመጀመሪያ ረመዳንን ወሩን ሙሉ በዛ መልክ ካሳለፍክ ለስድስት ቀን የዚህን ያህል ከከበደህ ስድስቶን የሰጠሃት ከብርና ግምት ስላነሰ ነውና ተስተካከል አለበለዚያ ሰይጣን ነገራቶችን ቆልሎብሀል አዑዙ ቢላህ ብለህ ስድስቶህን ፁም።
ሌሎችም ምክንያቶች ሊኖሩብህ ይችላሉ ምክንያቶችን ትተህ ስድስቶችን ፁም።

#ሳጠቃልል፦ ሌላው መንቃት ያለብን የሴት ልጅ ሀይድን ይመስል አይቀሬ ምክንያት ካልሆነ ሸዋል እስከሚያልቅ ቀስ ብየ እጨርሳለው በሚል እሳቤ አልፎ አልፎ ባንፆምና ከነገ ጀምሮ በተከታታይ ስድስቱን ቀን ብንፆም የተሻለ ነው። ምክንያቱም
1/ ነሻጣ ይኖረዋል።
2/የፆም ልምዳችን ሳይጠፋ መፆማችን ቀላል ያደርግልናል።
3/አብዘሃኛውን ሰው የሚፆመው በዚህ ወቅት ስለሆነ ብቸኛ ሳንሆን እንደሰው እንሆናል። ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል!

አብዱረህማን ዑመር
ሸዋል 2 / 1443 ሂጅራህ
https://t.me/Abdurhman_oumer/2701

Telegram

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

#ከሸዋል 6ቀን (ስድስቶን) የመፆም አይቀሬነት፣ እና #የሚመጡ\_ምክንያቶችን , #የሚያስዎግድ\_ትውስታ!! ***〰******〰******〰******〰******〰******〰******〰******〰******〰******〰*** አሰላሙ ዓለይኩም ወረህመቱላህ ወበረካትሁ የተከበራችሁ ሙስሊም የሱና ወንድም እህቶች አባትና እናቶች በቅድሚያ አልሐምዱሊላህ እንኳን አላህ ለስድስቶ ፆም በሰላም አደረሰን እያልኩ በመቀጠልም ከላይ ከርእሱ እንደተመለከታችሁት የስድስቶን ፆም ለመፆም አይቀሬ…

1 month, 1 week ago
1 month, 1 week ago

ወቅታዊ አንገብጋቢ ትምህርት
➪➬➫➩➧

ርዕስ፦ ⬇️
〖ዘካተል ፊጥርን በተመለከተ ስፋ ያለ ማብራሪያ

🎙 للشيخ أبي طلحة أبي ذر بن حسن الولوي «حَفِظَهُ اللَّهُ»
🎙 በሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን አቡ ጦልሃ ሀፊዘሁሏህ
https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha/5358

3 months, 1 week ago

🎤    እኛ ያልነው ካላላችሁ ይሉናል !!!!! ።

በአሁኑ ጊዜ በጣም እየተነዛ ያለ ብዥታ አለ ። እሱም ሙመዪዓዎች ወጣቱን ለመንሸንገልና ሙሪዶቻቸውን ባሉበት ለማፅናት አስበው የሚነዙት ብዥታ ሲሆን እሱም ኢብኑ መስዑዶች የቢዳዓ አንጃዎች ናቸው የሚለውን ብይን ዋጋ ለማሳጣትና እየሄድበት ያለውን ሰለፍያን የተቃረነ አካሄድ የሰለፎች አካሄድ ለማስመሰል የሚደረግ ሩጫ ነው
     ይህ ብዥታ ( እኛ ያልነውን ካላላችሁ ይሉናል ) የሚለው በጥቅሉ ሲታይ ሰዎችን የሚያስበረግግ ይመስላል ። ነገር ግን በዚህ ብዥታ ላይ ሶስት ነገሮችን ማጤን ግድ ይላል ።
1– ተብለናል ባዮቹ እነማን ናቸው ? 
2 – ባዮቹስ እነማን ናቸው ?
3 – አባባሉስ ትክክል ነው ወይስ አይደለም የሚሉትን ማጤን ።
1 – ተብለናል ባዮቹ እነ ኢብኑሙነወር ናቸው ። እኛ ያልነው ካላላችሁ ተብለናል የሚሉት ኢብኑ መስዑዶች የቢዳዓ አንጃዎች ናቸው የሚለው ነው ። በመጀመሪያ ደረጃ ማንም ሰው እኔ የእገሌን ተቋም የቢዳዓ ተቋም ነው ብዬዋለሁ ወይም እገሌን ሙብተዲዕ ነው ብዬዋለሁ አንተም በል ማለት አይችልም ። ምክንያቱም ጉዳዩ ሸሪዓዊ ብይን ስለሆነ ሸሪዓዊ መረጃ ያስፈልገዋል ።
    ተብዲዕ ሸሪዓዊ ብይን ስለሆነ ሸሪዓዊ መረጃ ሳይኖር ብይን መስጠት በሸሪዓ ላይ ወሰን ማለፍ ነው የሚሆነው ።
     ይህ ማለት አንድ ተቋም ወይም ግለሰብ የሚያራምደው አቋም ከቁርኣንና ሐዲስ እንዲሁም ከሰለፎች ስምምነት የወጣና እነዚህን ጥሶ የተገኘው አካል በሰለፎች ሚዛን የቢዳዓ ተቋም ወይም ሙብተዲዕ የሚያሰኘው ከሆነ ብቻ ነው ይህ ብይን የሚሰጠው ።
      የኢብኑ መስዑዶች አካሄድ ቁርኣንን ሐዲስንና የሰለፎችን ኢጅማዕ የጣሰ መሆኑን በተለያየ ጊዜ በመረጃ ለማረጋገጥን የሞከርን ቢሆንም ሙሪዶቻቸውና እንባ ጠባቂዎቻቸው አላየንም አልሰማንም ብለው ንትርክ ያነሳሉ ። ለማናኛውም በተጠናከረና መረጃው ተሰባስቦ በያዘ መልኩ የቀረበውን የወንድማችን አቡ ዐብዱራሕማን የተመጠነ ማረጋገጫ የሚለውን ይመልከቱ :–

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/bahruteka/3042

–  የመርከዝ ኢብ መስዑድ ሰዎች ከማን ጋር እየሰሩ እንደሆነና የተዘፈቁባቸው ሙኻለፋዎችን የሚያጋልጥ ምላሽ ።  አብረዋቸው የሚሰሯቸው አሕባሽ ፣ ሱፍይና ኢኽዋን መሪዎች ማንነት በሚገርም ማስረጃ ።
– ኢልያስ አሕመድ የሚያወድሰው ዶክተር ጀይላን ድብቅ ማንነት ።
– የመርከዙ ሰዎች የደስታ መግለጫ ያዥጎደጎዱላቸው መጅሊሱን የሚመሩ ሰዎች ጉድ እና ሌሎችም ድብቅ ሚስጢሮች በመረጃ የተጋለጡበት ነው።
  ወንድማችንን አቡ አብዱራሕማንን አላህ ስራውን ይቀበለው ።

–  የመርከዝ ኢብ መስዑድ ሰዎች ከማን ጋር እየሰሩ እንደሆነና የተዘፈቁባቸው ሙኻለፋዎችን የሚያጋልጥ ምላሽ ።  አብረዋቸው የሚሰሯቸው አሕባሽ ፣ ሱፍይና ኢኽዋን መሪዎች ማንነት በሚገርም ማስረጃ ።
– ኢልያስ አሕመድ የሚያወድሰው ዶክተር ጀይላን ድብቅ ማንነት ።
– የመርከዙ ሰዎች የደስታ መግለጫ ያዥጎደጎዱላቸው መጅሊሱን የሚመሩ ሰዎች ጉድ እና ሌሎችም ድብቅ ሚስጢሮች በመረጃ የተጋለጡበት ነው።
  ወንድማችንን አቡ አብዱራሕማንን አላህ ስራውን ይቀበለው ።
     እነ ኢብኑ ሙነወር እኛ ያልነውን ካላላችሁ እየተባልን ነው የሚሉት ከኢብኑ መስዑዶች ለመከላከልና ሰዎችን ከጭብጥ ለማውጠት የሚያደርጉት ሙከራ ነው ።
    ምናልባት ሙኻለፋው የሰለፎች ኢጅማዕን የጣሰ ባይሆን ኖሮ የሚቻቻሉበት ነው ይባል ነበር ። ነገር ግን ሙኻለፋው መሰረታዊ የዓቂዳ ሙኻለፋዎችን የሰበሰበ ሆኖ ሳለ ይን የግለሰብ እይታ አድርጎ ማቅረብ ምን እንደሚባል ግራ ይገባል ።
2 – ብለዋል የሚባሉት ሸይኽ ዐ/ሐሚድና ሸይኽ ሐሰን ገላው እንዲሁም አብረዋቸው ያሉት መሻኢኾችና ዱዓቶች ናቸው ። ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ማንም በጀማዐም ይሁን በተናጠል እኔ ያልኩት ካላልክ ማለት አይችልም ። ይህን ሊል የሚችለው የሱፍይ ወይም ሺዓህ ሸይኽ ነው !!!!!።
    የሰለፍይ ሸይኽ አላህ ያለውን እንዲሁም መልእክተኛው ያሉትን ነው የሚለው ። መረጃ ሙብተዲዕ ነው ያለውን ሙብተዲዕ ነው ይላል ያላለውን አይልም ቢልም ተቀባይነት የለውም ።
      ኢብኑ መስዑዶችን በተመለከተ የቢዳዓ አንጃ ናቸው ማለት እየአንዳንዱን ሙንተሲብ ሙብተዲዕ ነው ማለት አይደለም ተላዙምም የለውም ። እነኢብኑ ሙነወር ጅምላ ጭፋጨፋ ነው የሚሉት እነርሱም ተብሊጎች የቢዳዓ አንጃዎች ናቸው ኢኽዋኖች የቢዳዓ አንጃዎች ናቸው ሲሉ ጅምላ ጭፍጨፋ ላይ ነበሩ ማለት ነው !!!!! ። ከዚህ በላይ የሰለፍ ዑለሞች ጀህምዮችና ራፊዳዎች ካፊሮች ናቸው ሲሉ አዕያኖችን ባጠቃላይ እንደማይፈልጉበት ግልፅ ነው ። አሁንም ኢብኑ መስዑዶች የቢዳዓ አንጃዎች ናቸው ሲባል አዕያኖችን ባጠቃላይ ማለት አይደለም ። ይህ በጣም ወሳኝ ነጥብ ስለሆነ ሊታወቅ ይገባል ።
3 – እኛ ያልነው ካላልክ የሚለው አባባል ትክክል ነው ወይስ አይደለም ? 
    ይህ አባባል በዚህ መልኩ በልቅ ከሆነ ትክክል አይደለም ። ነገር ግን ባዮቹ በማያሻማና ግልፅ በሆነ መርህ ላይ የኻለፈን አካል በመረጃ ካሉት ይህን መቀበል ግድ ነው ። ምክንያቱም ሸሪዓ ያለውን መቀበልና በስራ ላይ ማዋል ግድ ስለሆነ ።
    ወደ ነባራዊው ሁኔታ ስንመጣ የኢብኑ መስዑዶች ሙኻለፋ ሁለት ሰለፍዮች የሚጨቃጨቁበት ጉዳይ አይደለም ። ምናልባት በሰለፍያ መዝሀብ ላይ በቂ እውቀት የሌላቸው ካልሆኑ በስተቀር ።
      ሰለፍዮች ሆይ በመርከዙ ሰዎች ጉዳይ ልትጠራጠሩ አይገባም ሙኻለፋቸው እንደ ጠዋት ፀሀይ ፍንትው ብሎ የሚታይ ታላላቅ መርሆችን የጣሰና ከሰለፍያ የሚያስወጣ ነው ።

🔹 ከመረጃ ማጠናከሪያ ጋር በድጋሚ የተለቀቀ

https://t.me/bahruteka

Telegram

ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

***🔷*** የተመጠነ ማረጋገጫ – የመርከዝ ኢብ መስዑድ ሰዎች ከማን ጋር እየሰሩ እንደሆነና የተዘፈቁባቸው ሙኻለፋዎችን የሚያጋልጥ ምላሽ ። አብረዋቸው የሚሰሯቸው አሕባሽ ፣ ሱፍይና ኢኽዋን መሪዎች ማንነት በሚገርም ማስረጃ ። – ኢልያስ አሕመድ የሚያወድሰው ዶክተር ጀይላን ድብቅ ማንነት ። – የመርከዙ ሰዎች የደስታ መግለጫ ያዥጎደጎዱላቸው መጅሊሱን የሚመሩ ሰዎች ጉድ እና ሌሎችም ድብቅ ሚስጢሮች በመረጃ…

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago