Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

AGARO MUSLIM STUDENT'S JEMEA🕌

Description
.
.
.
.

ስህተቶች ስተገኙ አስታከክሉን በረከሏሁ ፊኩም አዳራ ግን አተሰደቡ  በአደብ
@Riihu_bot



👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@nejashi_jemea_group
We recommend to visit

.
.
.
.

ስህተቶች ስተገኙ አስታከክሉን በረከሏሁ ፊኩም አዳራ ግን አተሰደቡ  በአደብ
@Riihu_bot



👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@nejashi_jemea_group

Last updated 3 weeks, 6 days ago

Foto/Dokumenta

Last updated 1 month, 2 weeks ago

3 weeks, 6 days ago

ያ አህባቢ በመልካም ዱዓቹ አትርሱን ባረከ አላሁ ፊኩም

✍️Rihu
اللهم إنك عفوٌ تُحِبُ العفوَ فاعفُ عنّا

♡ ㅤ  ⎙ㅤ  ⌲        ✉️   
   ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ʳⁱʰᵘ ⁱˢˡᵃᵐⁱᶜ ᵖᵒˢᵗ

3 weeks, 6 days ago

👉ልክ እንደ አፍቃሪ አቀራረብ
አላህን ስትቀርበው ሀዘንህ የቱንም ያህል
ቢሆንም በእዝነቱና በፍቅሩ አብቃቅቶህ
ያስደስትሃል   ⇄ ለአላህ ሁን
ህይወት ለአንተ ትሆናለች ።
♡ ㅤ  ⎙ㅤ  ⌲        ✉️   
   ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ʳⁱʰᵘ ⁱˢˡᵃᵐⁱᶜ ᵖᵒˢᵗ

1 month ago

🌙 የጎዳና ኢፍጣር🌙

🖌 በኢልያስ አሕመድ

በቅድሚያ ይህን ፕሮግራም ለማሰናዳት በቅንነት የሚለፉ ግለሰቦችና ድርጅቶችን አላህ የኒያቸውን እንዲሰጣቸው እንለምናለን፤ ከዚህ በታች ያለው አጭር ፅሑፍ የልፋታቸው መሰረት የተስተካከለ እንዲሆን ታስቦ በተቆርቋሪነት የተከተበ ነው።
              ››››› ‹‹‹‹‹

በህብረት ማፍጠር ሁለት አይነት አፈፃፀሞች ሊኖሩት ይችላል፦

1ኛ/ ለማፍጠር መሰባሰቡን ዋና ኢላማ ሳያደርጉ በተወሰኑ አጋጣሚዎች በህብረት ማፍጠር ሲሆን ይህም እንደማይወገዝ ግልፅ ነው።
ለምሳሌ፦ ለሰላት ወደ መስጂድ የመጣውን ስብስብ ወይም ድሆችን በአንድ ቦታ ለማስፈጠር የሚኖረው መሰባብሰብ ተቃውሞ ሊነሳበት አይችልም። ዘመድና ጓደኛን ጠርቶ በጋራ ማፍጠርም እንደተራ ግብዣ ሊታይ ይችላል። ፆመኛን ማስፈጠርን አስመልክቶ የተወራውን ምንዳ ለማግኘት ከታሰበ ደግሞ እንደ እሳቤው የተወደደ ሊሆን ይችላል።

ብዙ ዑለማዎች የፈቀዱትም በዚህኛው ምድብ የሚካተተውን ነው።

2ኛው/ ለኢፍጣር መሰባሰቡ ራሱ እንደ ዋና ግብ ታልሞና ይህንንም በሚያሳብቁ ተግባራት ታጅቦ በስፋት የሚተገበር አፈፃፀም ሲሆን ይህ የቢድዓ መገለጫን ሊላበስ ይችላል።

በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለመደው የጎዳና ኢፍጣር ይህንን ይዘት እንደተላበሰ ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል፦

👉 እንደ በዓላት የሚጠበቅ ህዝባዊ ኩነት መሆኑ፣ (Grand Iftar 1, 2 እየተባለ ዘንድሮ 4ኛው ላይ ደርሰናል!)

👉 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የበድር ዘመቻ የተካሄደበት የረመዳን 17ኛው እለት ለዚህ አመታዊ መሰባሰቢያ እንዲሆን በተደጋጋሚ መመረጡ፣

👉 ሰዎች በነቂስ ወጥተው እንዲታደሙ ሰፊ ጥሪ መደረጉ፣

👉 በታዳሚያን ብዛት ከሌሎች አገራት ጋር ፉክክር ውስጥ የተገባበት መሆኑ፣

እና ሌሎች አባሪ ሂደቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ።

የነዚህ ሂደቶች ስብስብ ተግባሩን ራሱን የቻለ አዲስ የሙስሊሞች ይፋዊ ምልክት (ሺዓር) እያደረገው ነው።

📌 ታላቁ ኢማም #ኢብኑ_ተይሚያህ በዲን ውስጥ ስለሚጨመሩ የፈጠራ በዓላት በሚያብራሩበት አውድ ስለ በዓላት ምንነት ሲያስረዱ የሚከተለውን ይላሉ፦
«“ዒድ” (በዓል) በተለመደ መልኩ ለሚደጋገም ሁሉን አቀፍ መሰባሰብ የሚሰጥ ስያሜ ሲሆን በየአመቱ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ ወይም በተመሳሳይ ሁኔታ (በውስን ቀናት) የሚመላለስ ነው።
በዓል የተወሰኑ ነገሮችን አቅፎ ይይዛል፤ ከነሱ መካከል፦
እንደ ዒድ አል-ፊጥር እና እንደ ጁሙዓ የሚመላለስ ቀን፣ (በቀኑ) መሰባሰብ፣ ይህን ተከትለው የሚመጡ አምልኳዊ ወይም ልማዳዊ ተግባራት ይገኛሉ።
በዓል በውስን ቦታ የተገደበ ሊሆን ይችላል፤ ያልተገደበም ሊሆን ይችላል፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ (በነጠላ) ዒድ ሊሰኙ ይችላሉ....
“ዒድ” የሚለው ቃል ለእለቱና በውስጡ ላለው ተግባር ጥምረት የሚሰጥ ስም ሊሆን ይችላል፤ ይህም አብዛኛው (አጠቃቀሙ) ነው።»
[“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (1/496 – 497)]

📌 በሌላ ቦታም እንዲህ ብለዋል፦
«ከተደነገጉት መሰባሰቦች ውጪ ሳምንታት፣ ወራት፣ ወይም አመታት በተደጋገሙ ቁጥር የሚደጋገም  መሰባብሰብን በቋሚነት መያዝ ለአምስቱ ሰላቶች፣ ለጁሙዓ፣ ለሁለቱ ዒዶችና ለሐጅ ከመሰባብሰብ ጋር ይመሳሰላል፤ ፈጠራና አዲስ ተግባር ማለት ይህ ነው!))
[“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)]

📌 አለፍ ብለውም እንዲህ ይላሉ፦
«ከነዚህ (ከተደነገጉት) መሰባሰቦች ባሻገር የሚለመድ ተጨማሪ መሰባሰብ ከተጀመረ አላህ ከደነገገውና ካፀደቀው ፈለግ ጋር የሚመሳሰል ይሆናል …. - ለብቻው የሆነ ግለሰብ ወይም ውስን ስብስቦች አንዳንዴ ከሚሰሩት በተለየ መልኩ!))
[“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/144)]

ይህ ማብራሪያ ሰዎች በየውስን ጊዜ በታወቀ ቀጠሮ የሚፈፅሙት ህዝባዊ ስብስብ እንደ በዓል ባይታቀድ እንኳ በዓላዊ ይዘትን እንደሚላበስ ያሳያል።

አንድ ነገር በጥቅሉ የሚፈቀድ፣ ብሎም የሚደነገግ ከመሆኑ ጋር በአፈፃፀሙ ረገድ የሚኖሩ ተጓዳኝ ነገሮች ብይኑ እንዲቀየር ሊያደርጉ ይችላሉ።
📌 ታዋቂው ዓሊም #ኢብኑ_ደቂቅ_አል_ዒድ አንዳንድ ሸሪዓዊ አፈፃፀሞችን ለመተግበር በደካማ የሐዲሥ ዘገባ ላይ ስለመመርኮዝ የሚነሳውን ውዝግብ አስመልክቶ እንዲህ ይላሉ፦
«የ“መውዱዕ” (የተቀነባበረ የውሸት ሐዲሥ) ክልል ውስጥ ያልገባ ደዒፍ (ደካማ) ከሆነ በዲን ላይ አዲስ ይፋዊ ምልክት “ሺዓር” የሚፈጥር ከሆነ ይከለከላል፤ ካልሆነ ደግሞ ምልከታ የሚቸረው ይሆናል...» [“ኢሕካሙ’ል-አሕካም” (1/501)]

👉 አንድን ተግባር እንደ “ሺዓር” ከሚያስቆጥሩት የአፈፃፀም ሂደቶች መካከል ሰዎች ተጠራርተው የሚሰባሰቡበት ኩነት መሆኑ ነው፤ በተለይ እንደ ዒድ ሰላት በጎዳና/በአደባባይ ላይ የሚተገበር ከሆነ!
ይህን የሚያብራራ አንድ ምሳሌ እንጥቀስ፦

ሰዎች በተሰባሰቡበት አጋጣሚ አንዳንዴ ዱዓ ማድረግ የሚቻል ከመሆኑ ጋር ይህን በህብረት ለመፈፀም መጠራራትን ብዙ የኢስላም ሊቃውንት አይደግፉም።
📌 #አል_ኢማም_አሕመድ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፦ «ሰዎች ተሰባስበው አላህን መለመናቸውና እጃቸውንም ማንሳታቸው ይጠላል?»
እርሳቸውም፦
«مَا أَكْرَهُهُ لِلْإِخْوَانِ إذَا لَمْ يَجْتَمِعُوا عَلَى عَمْدٍ إلَّا أَنْ يَكْثُرُوا»
= «ሆን ብለው ካልተሰባሰቡ ለ(ዲን) ወንድማማቾች አልጠላውም – ካልበዙ በስተቀር!»

📌 #አል_ኢማም_ኢስሓቅ ኢብኑ ራሀወይህ ሲጠየቁም ተመሳሳይ መልስ ሰጥተዋል።

«ካልበዙ በስተቀር» ሲሉ ልማድ በማድረግ እስካልተበራከቱ ድረስ ማለታቸው እንደሆነ ጠያቂው (ኢስሓቅ ኢብኑ መንሱር) ተናግረዋል!
[“መሳኢሉ’ል-ኢማሚ አሕመድ ወኢስሓቅ” (9/4879)፣ “ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)]፣
“አል-ኣዳብ አሽ-ሸርዒይ-ያህ” ሊ’ብኒ ሙፍሊሕ (2/103)]

👉 ስለሆነም ነገሩ ከዚህ በላይ ሳያድግ መግታቱ አስፈላጊ ነው።
ይህ ከዚህ በፊት የተስተዋሉ የአፈፃፀም ግድፈቶችን ከግምት ሳናስገባ የምንደርስበት መደምደሚያ ሲሆን፤ ያለ በቂ ምክንያት መንገድ መዘጋጋት፣ አግባብ ያልሆነ የወንድና የሴት መቀላቀል፣ የሴቶች ምስል በሚዲያ የሚሰራጭበት ቀረፃ፣ ሴቶች በምሽት መንገላታታቸው፣ በሙዚቃ መሳሪያ የታጀበ "ነሺዳ"፣ የምግብ ብክነት እና መሰል ጥፋቶች የሚታከሉበት ከሆነ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል።

አዎን! ፕሮግራሙ ከዚህ በፊት ሞራላዊ ጥቅምን አስገኝቶ ሊሆን ይችላል፤  ነገር ግን በውስጡ ከላይ የጠቆምነውን አመዛኝ ጉዳት ማካተቱ ለመታቀብ በቂ እንደሆነ አስባለሁ።

አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው።

ረመዳን 15/1445
@Rihu_islamic_post

2 months, 3 weeks ago

ፈተና መብዛቱ ለኸይር ነው

አብሽር አሏህ ፈተናን ባንተ ላይ ማፈራረቁ ስለጠላህ አይደለም። ነብያችን - ﷺ - የቲም ነበሩ። እናታቸውን በ6አመታቸው አጥተዋል ፤ ርቧቸው ድንጋይ ሆዳቸው ላይ አስረዋል ፤ ሌላም ብዙ ፈተና ደርሶባቸዋል። ታዲያ አሏህ ጠልቷቸው ነው ብለህ ታስባለህን? በጭራሽ.
°
እንደውም በተቃራኒው እንደሚወድህ አመላካች ነው። ነብያችን - ﷺ - ይህን ስላሉ ፦ [ አሏህ ህዝቦችን ከወደደ ይፈትናቸዋል። ] (ሙስነድ ኢማሙ አሕመድ ፥ 23623). በሌላም ሐዲስ ላይ [ ከሰዎች ሁሉ በላእ የሚበረታባቸው ነብያቶች ናቸው ከዛም ደጋግ የአሏህ ባሪያዎች ናቸው። ] (ሲልሲለት አስሶሒሓህ ፥ 144).
°
አማኝ በሆነ ሰው ላይ ፈተና  መብዛቱ አሏህ ለሱ መልካምን ነገር እንዳሰበለትም አመላካች ነው። ረሱል - ﷺ - እንዲህ ብለዋል ፦ [ አንድን ሙስሊም ከድካምም ይሁን ከበሽታ ከጭንቅም ይሁን ከሐዘን ከችግርም ይሁን ከጭንቀት ሙሲባ አይደርስበትም ከምትወጋው የሆነች እሾህም ብትሆን አሏህ በሷ አማካኝነት ከወንጀሉ ቢያፀዳው እንጂ። ] (ሶሒሁል ቡኻሪ ፥ 5641). አሏህ ፈተናን ታግሰው እሱ ከሚወዳቸው ባሪያዎቹ ያድርገን።

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄  🍃
@Rihu_islamic_post
@Rihu_islamic_post

3 months ago

አምስቱ የወጣቱ ችግሮች ሊቀረፉ ይገባቸዋል! ካልሆነ ግን የቀጣዩ ትውልድ ሁኔታ እጅግ በጣም ያሰጋል!

ወደ ኣኺር ዘመን በተጠጋን ቁጥር ነገሮች እየተቀየሩ ችግሮችም እየተባባሱ ይሄዳሉ ይህን ያልተረዳ ሰው አዳዲስ ነገሮች በመጡ ቁጥር ሲታለልና ሲከተላቸው ይታያል።

ሐቁ ግን " ጥሩና መልካም ነገር ሁሉ የሚገኘው በሰላሙ ዘመን በሰላም ከጌታቸው ጋር የተገናኙ ሰዎችን የሰሓቦችንና ተከታዮቻቸውን ብቻ ፈለግ በመከተል ነው።"

የዘመኑ ወጣት ይህንን መሰረት በመዘንጋቱ በርካታ ስህተቶች ላይ ሲወድቅ እናያለን ከነዚህም በጥቂቱ፦

1) ትንሽ ሲያውቁ ሁሉንም ያወቁ መስሎ ራስን ሰማይ መስቀልና በራስ መደነቅ።

2) ሐቅን በሰዎች መለካትና ከሚያደንቁት ሰው በስተቀር ሌላን ሐቅ ከማንም አለመቀበል እንዲሁም ሰዎችን ከአላህና ከመልእክተኛው ይልቅ በግለሰቦች ላይ እንዲንጠለጠሉ ማድረግ፣ ከዚህም አልፎ እነሱ የሚያደንቁት ሰው ጭራሽ ከስህተት የተጠበቀ አድርጎ መቁጠርና ስህተቶቹን አለባብሶ ማለፍ።

3) መካሪዎችና ተናጋሪዎች ወጣቱ እራሱ የሚመርጠውንና የሚፈልገውን ዓይነት ንግግር ብቻ እንዲናገሩ መሻት፣ ይህ ካልሆነ ችግር መፍጠርና ተገንጥሎ መውጣት።

4) ወሬኛነትና ነገር ማመላለስ፣ ከሰሙት አልፎ ያልሰሙትን ሁሉ ማውራት ይህ ማለት ደግሞ እንዲህ ማለት ነው እያሉ የማይመስሉ ነገሮችን ልክ እንደሆነ ነገር አድርገው ለማሳየት መሞከርና በዚህም ሰውን ስራ ማስፈታት።

5) ኢባዳ ላይ መድከምና አኼራን መዘንጋት ዲን ወሬ ብቻ እስኪመስል ድረስ መልካምና ማራኪ ንግግሮችን እየተናገሩ ስራ ላይ ግን ተቃራኒ መሆን !ዚክር፣ ዱዓ፣ ሰላተል-ለይል፣ ዝምድናን መቀጠል፣ የተቸገረን መርዳት፣ የታመመን መጠየቅ፣ መላ ሰውነትን ከሐራም መጠበቅና ሰዎችን ከንግግር ይልቅ በተግባር ወደ ዲን መጣራትና መተው ወዘተ መልካም ባህሪያትና የግል ጥንካሬ ማጣት!

እነዚህና መሰል የወጣቱ ችግሮች ሊቀረፉ ይገባቸዋል ካልሆነ ግን የቀጣዩ ትውልድ ሁኔታ እጅግ በጣም ያሰጋል

ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን

Click and like

በቴሌ ግራም ለመከታተል
@Rihu_islamic_post

3 months ago
4 months, 4 weeks ago

Asslamualeykum
Werametulahi
Weberekatu
ውድ ያ አጋሮ ሙስሊም ተማሪዎች

5 months ago

የጀመዓው ሴክተሮችና የስራ ድርሻዎቻቸው የነጃሺ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አምስት ዋና ዋና ዘርፎች (Sectors) አሉት። 1.የዳዕዋና ኢርሻድ ዘርፍ (D`awa and Ershad Sector) 2. የአካዳሚክ ዘርፍ (Academic Affairs’ Sector) 3. የማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ (Sector of Social Affairs) 4. የውጭ ጉዳይ ዘርፍ (Sector of External Affairs) …

5 months ago

🔴 👉 ጓደኛ

→ክፍል ሦስት (③)

↝በጓደኛሞች መካከል የሚኖሩ የግንኙነት ዓይነቶች↜

⇨ ጓደኛሞቾ እንድ የጋራ ነፍስ ወይም ሕይወት ያላቸው ሁለት አካላት ናቸው፡፡»

⇨ ጓደኛህን ንገረኝና ማን እንደሆንክ እነግረሃለሁ፡፡»

⇨ ከማንና የት እንደምትውል ንገረኝና ማንነትን እነግርሃለሁ፡፡»

ኢስላም ለጓደኝነት ትልቅ ቦታን ሰጥቷል፡፡ ግና የጓደኝነት መሠረቱና መነሻው ለዓለማዊ ጥቅም ሳይሆን ለአላህ(ﷻ) ሲባል የሚመሠረት ንጹሕ ኢማናዊ ጉድኝት መሆን አለበት፡፡ ለአላህ(ﷻ)ተብሎ በሰዎች መካከል የሚመሠረት ጓደኝነትም ትልቅ ምንዳ እንዳለውና ኢስላምም አብዝቶ ያዘዘበት ነው፡፡ ለአላህ(ﷻ)ሲሉ የሚጎዳኙ ሰዎች የሚያገኙትን ምንዳ በተመለከተ ↝ነብዩ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡-

«አላህ (ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)(በሐዲሠል ቁድስ)እንዲህ ይላል፡-እነዚያን ለኔ ልቅና ብለው የተዋደዱትን፣ የኔ ጥላ እንጂ ሌላ ጥላ በሌለበት (በትንሳኤው)ቀን በዐርሽ ጥላ ሥር
አድርጋቸዋለሁ፡፡»(አሕመድ)

ምንም እንኳን ኢስላም ያወደሰው፣ ያዘዘውና ዕውቅናን የሚሰጠው ኢማናዊ ጓደኝነትን ቢሆንም ግና በሰዎች መካከል የተለያዩ ዓይነት ጉድኝቶች እንደሚኖሩ ይታወቃል፡፡ ይህንኑ አስመልከቶ ታላቁ ዓሊም ኢማም ኢብኑል ቀይም(ረሂመሁሏህ)እንዲህ ይላሉ፡-

በጓደኛሞች መካከል ሁለት ዓይነት ግንኙነቶች አሉ፡- የመጀመሪያው ዓይነት በማህበራዊና ጊዜን አብሮ በማሳለፍ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ግን ከጥቅሞቹ ይልቅ ጉዳቶቹ ያመዝናሉ፡፡ ከነዚህ ጉዳቶች መካከልም ዝቅተኞቹ የልብ መበከልና የጊዜ ብክነት
ናቸው፡፡ ሁለተኛው ዓይነት እርስ በርስ ለመረዳዳት ሲባል የሚደረግ ግንኙነት ነው፡፡
በዚህም አንዱ ሌላውን በእውነትና በሶብር አደራ ይባባላሉ፡፡ ይህ በላጩ ዓይነት ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን አሁንም ሦስት ጉዳቶች በውስጡ አሉበት፡፡ እነዚህም፡-
☞1/ አንዱ ሌላውን መደለሉ/መሸንገሉ፤
☞2/ ከልክ በላይ ወረኛ የመሆን እግዝማሚያ እና
☞3/ በሂደት የዚህ ዓይነት ግንኙነቶች ልማድ ወይም ተራ ይሆናሉ፡፡ ከዚህም የተነሳ ዓላማቸውን ለማሳካት ይሳናቸዋል፡፡ (አል-ፈዋኢድ)

ዓሊሙ ሲያከሉበትም፡-

«ባጠቃላይ የማህበራዊ ጉድኝቶች ውጤት ከምንጩ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ወደ መጥፎነት ለተዘነበሉ ነፍሶች የጓደኝነታቸው ውጤትም መጥፎ ይሆናል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ወደ መልካምነት ለተዘነበሉ ነፍሶች የጓደኝነታቸው ውጤትም መልካም ይሆናል። ምንጩ መልካም ከሆነ፣ በርግጠኝነት ፍሬዎቹም መልካም ይሆናሉ፡፡ ምክንያቱም ንጹሕ ነፍሶች ምሪታቸውን የሚያገኙት ከጌታቸው ነውና፡፡ እኩይ ነፍሶች ግን ምሪታቸውን የሚወስዱት ከሸይጧን ነው፡፡
ከዚህም የተነሳ ↝ አላህ(ዐዝ-ዘ ወጀል-ለ)መልካም ሴቶችን ለመልካም ወንዶች፣ መጥፎ ሴቶችን ግን ለመጥፎ ወንዶች በማድረግ አቆራኝቷቸዋል፡፡

Surah An-Nur (النّور), verses: 26
🌺 🌸 🌼

ٱلْخَبِيثَٰتُ لِلْخَبِيثِينَ وَٱلْخَبِيثُونَ لِلْخَبِيثَٰتِ وَٱلطَّيِّبَٰتُ لِلطَّيِّبِينَ وَٱلطَّيِّبُونَ لِلطَّيِّبَٰتِ أُو۟لَٰٓئِكَ مُبَرَّءُونَ مِمَّا يَقُولُونَ لَهُم مَّغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ

መጥፎዎቹ ሴቶች ለመጥፎዎች ወንዶች መጥፎዎቹ ወንዶችም ለመጥፎዎቹ ሴቶች የተገቡ ናቸው፡፡ ጥሩዎቹ ሴቶችም ለጥሩዎቹ ወንዶች ጥሩዎቹ ወንዶችም ለጥሩዎቹ ሴቶች የሚገቡ ናቸው፡፡ እነዚያ(መጥፎዎቹ) ከሚሉት ነገር ንጹሕ የተደረጉ ናቸው፡፡ ለእነርሱ ምህረትና መልካም ሲሳይ አላቸው፡፡
🌺 🌸 🌼
👉 👉 ይቀጥላል 👈 👈

ኢንሻ አላህ በቀጣይ ጥሩ ጓደኛ መምረጥ በሚል እርዕስ እንደተለመደው ውድ የሆነ መልዕክት ይዤላችሁ እመጣለሁ።

በዚህ ውድ መልዕክት አላህ እንዲያስጠቅመን እማፀነዋለሁ።
ሌሎችም ፁሁፉን አምብበው ትምህርት እየወሰዱበት ስለሆነ ይሄን ውድ መልዕክት ብዙ ሰዎች አልደረሳቸውም እና ለአላህ ብለን በቻልነው ፁሁፉን ለማሰራጨት እንሞክር።
👉ቢያንስ በውስጥ መስመር ለምናውቃቸው እንላክላቸው።
ለመልካም ነገር አይደከምም።!
ባረከላሁ ፊኩም
اللهم صل وسلم علي سيدنا محمد

👇 👇 👇
Join us On
TelegraM Channel
👇 👇 👇 👇
@Rihu_islamuc_post
@Rihu_islamuc_post

6 months, 2 weeks ago

Add Add add የቻላቹትን ያክል....... [لَا يُكَلِّفُ ٱللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا] : አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፡፡ እስኪ 2000 member እንግባ🏃‍♂🙏 Group 👇👇👇 https://t.me/nejashi_jemea_group

We recommend to visit

.
.
.
.

ስህተቶች ስተገኙ አስታከክሉን በረከሏሁ ፊኩም አዳራ ግን አተሰደቡ  በአደብ
@Riihu_bot



👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@nejashi_jemea_group

Last updated 3 weeks, 6 days ago

Foto/Dokumenta

Last updated 1 month, 2 weeks ago