Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

Description
የቀድሞ አበው እና እመት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ጥበብ...
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @behlateabew 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆

https://t.me/+RICJUxY54uwNbPXe
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 месяц назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 месяц назад

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 2 недели, 1 день назад

1 month ago

"የጥበብ አገሯ ወዴት ነው? ጥበብ ግን መድኃኒታችን ነው።በሥጋው መሥዋዕትነት ያዳነን ፣ በደሙም ፈሳሽነት የተወዳጀን፣ለመንግሥቱም የመረጠን፣ ለዘለዓለሙ።"
ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ

1 month, 1 week ago

"ቤተክርስትያንን መርዳት ከፈለክ ሌሎችን ለማረም ከማሰብ በፊት በቅድሚያ እራስን ማስተካከል ይበጃል። እራስህን ካስተካከልክ አንድ የቤተክርስትያን ክፍል ዳነ ወይም ተስተካከለ ማለት ነው። ሁሉም ሰው ይህን ማድረግ ከቻለ ቤተክርስትያን ጤናማ ትሆናለች። ስለዚህ ላስተዋለው ሰው ሌሎች ላይ መፍረድ እጅግ በጣም ቀላል ነው እራስን ማስተካከል ግን ጥረት ይጠይቃል።"

#ቅዱስ_ፓሲዮስ

1 month, 2 weeks ago

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ዳዋ ጥሳ ፣ ተራራ ቧጣ ፣ ቋጥኝ ፈልፍላ ፣ የእምነት እና የታሪክ ቦታዎችን የመሥራት ብቃት ፣ ችሎታ ፣ መንፈሳዊነት እና መለኮታዊ ኃይል አላት ።

መስቀል አደባባይ እንዲህ ዛሬ ያም እየተነሳ የእኔ ነው ያም እየተነሳ የእኔ ነው ከማለቱ በፊት ጉቶውን ነቅላ አረሙን አርማ ስትጠቀምበት የኖረችው ይኸችው መከረኛዋ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ናት ።

አሁንም ቤተ ክርስቲያናችን የሆነ በረሃ ላይ ሄዳ እንደ መስቀል አደባባይ ዓይነት በዓላቶቿን የምታከብርበት ቦታ ብታዘጋጅ ይኸንኑ ያዘጋጀችውን ቦታ ሊቀራመቷት የሚመጡ አይጠፋም ።

ዝንጀሮ እና ጦጣ ሁል ጊዜ ያልዘራውን ያጭዳል ያላበቀለውንም ያለ ይሉኝታ ይበላል ። ቅድስት እናታችን ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችንም ይኸ ነው የገጠማት ።

ጊዜ የሚባል ፍትሐዊ ዳኛ አለ !

Zekaryas Kiros

2 months, 4 weeks ago

«እግዚአብሔር የእለት እለት ምግባቸውን ይሰጣቸው ዘንድ
ስለ ተራቡና ስለተጠሙ ሰዎች እንማልዳለን።
እግዚአብሔር ፈጽሞ ያረጋጋቸው ዘንድ ስለ አዘኑና ስለ ተከዙ
ሰዎች እንማልዳለን።
እግዚአብሔር ከእስራታቸው ይፈታቸው ዘንድ ስለ ታሰሩ ሰዎች
እንማልዳለን ።
እግዚአብሔር ትዕግሥትን ፣ በጎ ትምህርትንም ይሰጣቸው ዘንድ
የድካማቸውንም ፍጹም ዋጋ ይሰጣቸው ዘንድ ስለተሰደዱ ሰዎች
እንማልዳለን ።»
በእንተ ቅድሳት

3 months ago
ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
3 months ago
ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
3 months ago

ሰማያት ሳይዘረጉ፤
የየብሱ ፊት ሳይታይ፤
ተራሮች ሳይቆሙ፤
የአየር ርዝመት ሳይከፈት፤
ቀላያት ጥልቅ ሳይሆኑ፤
የውሃ ምንጮች ሳይፈሉ፤
የወንዙም ጎርፎች ሳይፈሱ፤
ነፋሳት ሳይነፍሱ፤
ብልጭልጭታውም ሳይመላለስ፤
መባርቅት ሳይመዘዙ፤
ነጐድጓድም ሳይሰማ፤
የደመናትም ግዘፍ ሳይሳብ፤
ብርሃናት ሳያበሩ፤
ጨለማ ሳይጋረድ፤
መዓልትም ብርሃን ሳይበራ፤
ሌሊትም ሳይፈጠር፤
ፀሓይ የመዓልትን፣ ጨረቃም የሌሊትን ርዝመት ሳይገዛ፤
ከዋክብት ሳይብለጨለጩ፤
መናፍስት ሳይነቃነቁ፤
መላእክትም ሳይፈጠሩ፤
በባሕሪይህ የነበርክ!

ተራሮችንና ኮረብቶችን በሚዛን የመዘንክ፤
ውኆችን በእፍኝ የሰፈርክ፤
ከተራሮች ከፍታ በላይ ከፍ ያልክ፤

አንስርት የማይደርሱብህ ረጅም፤
ዓሦች የማይዋኙህ ጥልቅ፤

አልጫውን ያጣፈጥከው ጨው፤
ጨለማን ያሳደደከው ብርሃን፤
ዓለምን ሁሉ ያበረኸው ፋና፤

ሁሉን የምትመረምር፤
አንተ ግን በማንም የማትመረመር፤

ከሁሉ የተሰወርህ፤
ሁሉ ግን በአንተ ዘንድ የተገለጠ

አንተ!
ሳትደክም ሁሉን ትሸከማለህ፤
ሳታጎድል ሁሉን ትመግባለህ፤
ሳትተኛ ሁሉን ትጠብቃለህ፤
ሳትነጥፍ ሁሉን ታረካለህ፤
ሳትዘነጋ ሁሉን ታስባለህ፤
ቸል ሳትል ሁሉን ትሰማለህ፤
ሳትቀበል ለሁሉ ትተዋለህ፤
አንተ የሁሉ ጌታ ነህና።

በእውነት አንተ የሁሉ አምላክ ነህ ።
አንተ የሁሉ ንጉሥ ነህ ።
አንተ ሁሉን የያዝህ ነህ ።
አንተ ሁሉን የምትገዛ ነህ ።
አንተ ሁሉን የምታድን ነህ ።
አንተ የሁሉ መድኃኒት ነህ ።
አንተ ሁሉን የምትጠብቅ ነህ።
አንተ ሁሉን የምትመግብ ነህ።
አንተ በእውነት የሁሉ ገዥ ነህ።

የእኛ ጌታ፤
የሁላችን ከፍታ፤
የሕይወታችን አንድምታ፤
የነፍሳችን እርካታ፤

የውድቀታችን ትንሣኤ፤
የመረበሻችን ሰላም፤
የሕመማችን መፈወሻ መድኃኒት፤

የመመኪያችን ዘውድ፤
የደኅንነታችን ፋና፤
የሕይወታችን መሠረት፤
የቤታችን ጉልላት፤
የማንነታችን ሁሉ ውበት እና ጌጥ የሆንከው መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ!

አቤቱ ልዕልናህን ማመስገን የሚቻለው ምን አፍ ነው!?
ምንስ ከንፈር ነው!?
ምንስ አንደበት ነው!?
ለአንተ ምስጋና
ለመንግሥትህም ምስጋና
ለአባትህ ኃይል ክብርና ምስጋና
ከጽንዕ ጋራ ከአንተና ከወለደህ ከአባትህ ጋራ ለሚተካከል ሕፀፅ ለሌለበት መንፈስ ቅዱስ ይገባል
ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን!!!

3 months ago

ደጉ ሳምራዊ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ደጉ ሳምራዊ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ሳምራዊ ማለት ሀገር ጠባቂ ማለት ነው፥ እየሱስ ክርስቶስም እረኛችን ጠባቂያችን ነው፤ ዮሐ 10፥11 ፣1ኛ ጴጥ 2፥24። ሀገር ጠባቂ ሀገርን የሚጠብቀው ራሱን ለሞት አሳልፎ በመስጠት ነው፥ እየሱስ ክርስቶስም እኛን በነፍስም በሥጋም የጠበቀን ራሱን ለመስቀል ሞት አሳልፎ ሰጥቶ ነው፤ ደጉ ሳምራዊ ቊስለኛውን በሩቅ አይቶ አዘነለት ፥ቀርቦም በቊስሉ ላይ ወይንና ዘይት አፈሰሰለት፤ ወይኑ፦ የቊስለኛውን ደም እንዲያቆምለት እንዲያደርቅለት ነው። ቊስል ቶሎ የሚደርቀው ከላይ ነው፥ ወዲያውም እየተሰነጣጠቀ ያሰቃያል፤ ለዚህም መከላከያ እንዲያለሰልስለት ዘይቱን አፍስሶለታል። ጌታችንም በሩቅ ማለትም በሰማይ መንበሩ ተቀምጦ ቊስለኛውን አዳም በዓይነ ምሕረቱ አየው፥ ገጸ ምሕረቱን መለሰለት፤ ቀረበውም። (ባሕርዩን ባሕርይ አደረገ ፥ የባሕርዩ መመኪያ ከሆነች ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ ነስቶ፥ ተዋሕዶ ሰው ሆኖ ተወለደ)። ወይን እንደማፍሰስ፦በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ፥ ሥጋውን ቆረሰለት ደሙን አፈሰሰለት። ጌታችን የጸሎተ ሐሙስ ዕለት ወይኑን በጽዋ አድርጎ፦ «ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው፤» ያለው ለዚህ ነው። ማቴ 26፥27።
እንደ ዘይት ደግሞ የመንፈሰ ቅዱስን ጸጋ ሰጥቶታል። ይኽንን በተመለከተ ቅዱስ ዳዊት፦«ወይን (የክርስቶስ ደሙ) የሰውን ልብ ደስ ያሰኛል፥ ዘይትም ፊትን ያበራል፥ (መንፈስ ቅዱስ ሰውን ብሩኅ መልአክ ያስመስለዋል) ፥ እህልም (የክርስቶስ ስንዴ ሥጋው) የሰውን ጉልበት (ነፍስን) ያጠናክራል።» ብሏል። መዝ 103፥15 ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስም፦ «እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋልና ሁሉንም ታውቃላችሁ።» ያለው ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ነው።
ደጉ ሳምራዊ ከአህያው ወረዶ ቊስለኛውን ማስቀመጡ የሚያመለክተው፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ መንበሩ መውረዱንና የአዳምን በሰማይ መንበሩ ማስቀመጡን ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፦ «በኢየሱስ ክርስቶስ በሰማያዊ ሥፍራ ከእርሱ ጋር አስቀምጠን፤» ያለው ይኽንን ምሥጢር ይዞ ነው። ኤፌ 2፥7። ምክንያቱም በተዋሕዶ አምላክ የሆነ ሥጋ በሰማይ የእሳት መንበር ተቀምጧልና።
ደጉ ሳምራዊ፦ ያከመውን ቊስለኛ ለእንግዶች ቤት ጠባቂ ማስረከቡ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ፈሳሽነት ያከማቸውን ምእመናን ለመምህራን የማስረከቡ ምሳሌ ነው።ቅዱስ ጴጥሮስን፦«ግልገሎቼን አሰማራ፥ ጠቦቶቼን ጠብቅ ፥ በጎቼን አሰማራ፤» ያለው ለዚህ ነው። ዮሐ 21፥15። ሁለት ዲናሮች ደግሞ የሁለቱ ማለትም የብሉይ ኪዳንና የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ምሳሌዎች ናቸው። የሰው ሕይወቱ የሚጠበቀው
በእነዚህ ነውና። በሁለት ዲናር የተመሰሉ ቅዱሳት መጻሕፍት ምግበ ነፍስ ናቸውና። ቅዱስ ዳዊትም፦ «ቃልህ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው፤ ከማርና ከወለላ ይልቅ ጣፈጠኝ።» ብሏል። መዝ 118፥103።
ደጉ ሳምራዊ የእንግዳ ቤት ጠባቂውን፦ «ከሁለት ዲናር በላይ ብታወጣ እኔ በተመለስኩ ጊዜ እከፍልሃለሁ፤» አለው እንጂ፥ «ዋጋ የለህም፤» አላለውም። ይህም የሚያመለክተው፦ መምህራን የተሰጣቸውን፦ ሁለት ዲናር (ብሉይ ኪዳንን እና አዲስ ኪዳንን) ይዘው ፥ የምእመናንን ሕይወት ለመጠበቅ ሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍትን ቢጽፉ፥ ጌታ ሲመጣ የድካማቸውን ዋጋ እንደሚከፍላቸው ነው። ቅዱሳን ሊቃውንት፦ መጽሐፍ ቅዱስን ለማብራራት ፥ ንባቡን በመተርጐም ፥ ምሥጢሩን በማራቀቅ አያሌ መጻሕፍትን ጽፈዋል። እነዚህም አዋልድ መጻሕፍት ይባላሉ። የቅዱሳት መጻሕፍት ልጆች ማለት ነው። የገድል የድርሳን እና የተአምር መጻሕፍት ቊጥርም ከአዋልድ መጻሕፍት ነው። እነርሱም የእግዚአብሔር ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንደፈጸሙ፥ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን የሚያሳይ ነው። መጻፍ ማጻፍም ፥ መስማት ማሰማትም ዋጋ አለው። እንግዲህ በተሰጡን ሁለት ዲናሮች ሥራ እንድንሠራ ፥ ሌሎችንም ቅዱሳት መጻሕፍት በመጻፍና በማጻፍ እንድንመክርና እንድንመክር ፥ የተሰጠንን አደራ እንድንጠብቅ ፥ በዚህ ዓለም ተዋርደን ምእመናን የሚከብሩትን ግብር ይዘን እንድንገኝ፥ የሚያዝን ልቡና እንዲሰጠን ፥ የምናቆስል ሳይሆን የቆሰሉትን የምናክም እንዲያደርገን፥ የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን አሜን።
©ምንጭ፦ ሶልያና አስፍው-

👉https://t.me/behlateabew
https://t.me/+RICJUxY54uwNbPXe

3 months, 1 week ago

" ... የአሕዛብን ምድር በመስቀልህ ዕርፍ አርሰው የቃልህን መዝገብ በዓለም ዳርቻ ሁሉ ስለዘሩ ስለ ሐዋርያት፤ ድል ስለነሱ አምነው ንጹሐን ስለሆኑ ስለ ሰማዕታትም ሁሉ። ተኩላዎች እንደ በግ ስለበሏቸው ስለ መንጋህ። .... በመልካም ቃል ዋጋቸውን ይቀበሉ ዘንድ ላንተ ሰውነታቸውን አሳልፈው ስለሰጡ ገድላቸውን ጨርሰው በበጎ ስም ስለ ገቡ ስለ ቅዱሳንህም ሁሉ"

ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ

3 months, 1 week ago

++ አበው ስለ እመቤታችን ዕረፍት እንዲህ አሉ ++

‹ሌሎች በድንግልና የኖሩ ሴቶች 'ለሞት የሚሆኑ ልጆችን አንሰጥህም" በማለት ሞትን ተቃወሙት፡፡ ድንግል ማርያም ግን አንድ ልጅ በመውለድ በልጅዋ ሞት ራሱ እንዲሞት አደረገችው፡፡ ከዐለት ጋር እንደተጋጨ የተፈረካከሰው በማሕፀንዋ ፍሬ ነውና ሞት ወደ እርስዋ ሲቀርብ ተብረከረከ›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

‹‹ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው … በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው … በዚህች ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው … በዚህች ቀን ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ … አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት [የተለያየ] ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ›› ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ (Homily on the Dormition)

‹‹የቃሉ አገልጋዮችና ምስክሮች የነበሩት ሐዋርያት በሥጋ የወለደችውን የእናቱን ዕረፍትና እርስዋን የሚመለከቱ የመጨረሻዎቹን ምሥጢራትም ማየት ነበረባቸው፡፡ ይህም የሆነው የክርስቶስ የዕርገቱ የዓይን ምስክሮች እንደሆኑ ሁሉ የወለደችውም እናቱ ወደዚያኛው ዓለም ለሸጋገርዋ ምስክሮች መሆን ስላለባቸው ነው›› ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ (aka Doctor of Dormition)

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
አስተ ር እዮ ማርያም
ጎተበርግ ስዊድን

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 месяц назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 месяц назад

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 2 недели, 1 день назад