Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

ETHIO MEDICAL TRAINING AND CONSULTANCY PLC (CPD CENTER )

Description
#CPD_Center
⭐️092 1785903
⭐️091 2441527
⭐️094 7473333

#ንፋስ_ስልክ_ጎተራ_ራሚ_ህንፃ_2ኛ_ፎቅ_ላይ ያገኙናል።
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 2 days ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago

3 weeks, 1 day ago
[#CPD\_Training\_ማክሰኞ\_ይጀምራል](?q=%23CPD_Training_%E1%88%9B%E1%8A%AD%E1%88%B0%E1%8A%9E_%E1%8B%AD%E1%8C%80%E1%88%9D%E1%88%AB%E1%88%8D)

#CPD_Training_ማክሰኞ_ይጀምራል

ETHIO_MEDICAL_TRAINING_CENTER

#የፊታችን_ማክሰኞ_ሚያዚያ_22_ጀምሮ
#BASIC_lIFE_SUPPORT (BLS) ስልጠና እንጀምራለን።

#15CEU ይይዛል።

ስልጠናው ለማንኛውም የጤና ባለሙያዎች  የሚሰጥ ስለሆነ በ 0921785903 ደውለው ይመዝገቡ።

#ሰልጣኞች
➯ ሀኪሞች
➯ ነርሶች
➯ ፋርማሲዎች
➯ ለላብ ባለሙያዎች እና ለሌሎችም የሚሆን
https://t.me/ethiomedicaltrainingplc
ባሉበት ሁነው ይደውሉ!!! ይመዝገቡ።
0921785903
አድራሻ፦ ጎተራ ንፋስ ስልክ ማሞ ባቡር  ፌርማታ ሲደርሱ ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ

3 weeks, 3 days ago
[#CPD\_Training\_ነገ\_ጧት\_ይጀምራል](?q=%23CPD_Training_%E1%8A%90%E1%8C%88_%E1%8C%A7%E1%89%B5_%E1%8B%AD%E1%8C%80%E1%88%9D%E1%88%AB%E1%88%8D)

#CPD_Training_ነገ_ጧት_ይጀምራል

ETHIO_MEDICAL_TRAINING_CENTER

#የፊታችን_ቅዳሜ_ሚያዚያ_19_ጀምሮ
#Pain_management ስልጠና እንጀምራለን።

#15CEU ይይዛል።

ስልጠናው ለማንኛውም የጤና ባለሙያዎች  የሚሰጥ ስለሆነ በ 0921785903 ደውለው ይመዝገቡ።

#ሰልጣኞች
➯ ሀኪሞች
➯ ነርሶች
➯ ፋርማሲዎች
➯ ለላብ ባለሙያዎች እና ለሌሎችም የሚሆን
https://t.me/ethiomedicaltrainingplc
ባሉበት ሁነው ይደውሉ!!! ይመዝገቡ።
0921785903
አድራሻ፦ ጎተራ ንፋስ ስልክ ማሞ ባቡር  ፌርማታ ሲደርሱ ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ

3 weeks, 4 days ago

የድህረወሊድ እንክብካቤ (postnatal care)
👨‍👦👨‍👦👨‍👦👨‍👦👨‍👦👨‍👧👨‍👧👨‍👧👨‍👧👨‍👧👨‍👧👨‍👧👨‍👧

ዩቲዩብ ላይ ገብታችሁ ሰብስክራይብ ያላደረጋችሁልን ቤተሰቦች ሰብስክራይብ አድርጉልን። ሰርቲፋይ ለመሆን ብዙ ሰብስክራይብ እና ብዙ ሰዓት ይቀረናል። ላላወቃችሁ ደግሞ በዩቲዩብ ጀምረናልና ጎራ ብላችሁ እዩን።
ሊንኩ 👇👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCM2HMbAuepuSrLQGVvhLUHw

አንድ ሴት ከወለደች በኋላ ሊደረግላት የሚገቡ ሙያዊ እገዛ ፣ ምክር እና  አስተምሮ የድህረ ወሊድ እንክብካቤ እንለዋለን።
ይህም ከወለደችበት ደቂቃ አንስቶ እስከ አርባ አምስተኛ ቀን ድረስ የሚደርስ ሲሆን እንደ እርግዝና ጊዜ ሁሉ ለእናት ጤና አስጊ የሆኑ ችግሮች ጎልተው የሚታዩበት ወቅት ስለሆነ እና
ለተወለደው ጨቅላም የተለዪ አደገኛ ሁኔታዎች ሊከሰቱ ስለሚችል ክትትል እና እንክብካቤ ማድረግ ብልህነት ነው።

ውስብስብ ችግሮቹ ምንድናቸው?
በዚህ ወቅት የሚፈጠሩ ቸግሮች በርግዝና ጊዜ የነበሩ አልያም አዲስ የተፈጠሩ ሊሆኑ ይችላሉ። ከእነዚህም መካከል
• የማህፀን ኢንፌክሽን
• ደም መፍሰስ
• ግፊትና ማንቀጥቀጥ
• የጡት ህመም
• የቁስል መፈታት
• ፊስቱላ
• የሳንባ ምች
• የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
• ኪንታሮት
• የደም መርጋት

አደገኛ ምልክቶች ምንድናቸው?
በእናት ወይም በልጅ ላይ የሚከሰቱ ዋናዋና የጤና ችግሮች ሲታዩ ያለምንም ቅድመሁኔታ ወደ ወለድሽበት  ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ህክምና ማድረግ ያሻል።

የእናት አደገኛ ምልክቶች
1. ትኩሳት
2. ከፍተኛ ራስ ምታት እና የአይን ብዥታ
3. የሰውነት አብጠት
4. የሽንት ወይም ሰገራ አለመቆጣጠር
5. ራስ መሳት
6. የጡት እብጠትና ህመም
7. ሳል እና አየር ማጠር
8. ሽታ የለው ፈሳሽ በማህፀን መኖር

የልጅ አደገኛ ምልክቶች
1. የፈጠነ አተነፋፈስ
2. ጡት አለመጥባት
3. የማያቋርጥ ለቅሶ
4. ትኩሳት
5. የሰውነት ቢጫ መሆን
6. የሽንትና ሰገራ አለመውጣት
. 👇👇👇👇👇👇👇
ይቀጥላል
በድህረ ወሊድ ወቅት የሚጠቅሙ
ተጨማሪ ምክሮች

#አመጋገብ
ከወሊድ በኋላ ገንቢ እና ጠጋኝ ምግቦችን መመገብ የተለመደ እና የሚበረታታ ጉዳይ ሲሆን አትክልት እና ፍራፍሬ ጨምሮ ጤነኛ አመጋገብ ማዘውተር ተገቢ ነው።
ቅባት፣ ጮማ፣ጨውና ቅመማቅመም ማብዛት ለጤና መታወክ ስለሚያጋልጥ መጠንቀቅ ያሻል።
በኦፕራሲዮን ከወለደች በአንዳንድ ማህበረሰብ ስጋ እና የወተት ተዋፅዖ መውሰድ ቁስል እንዳይድን እንዲያመረቅዝ ያደርጋል የሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ ስለሆነ ኦፕራሲዮን ያደረገሽን ሃኪም በፅሞና መከታተል ወይም መጠየቅ ተገቢ ነው።

#ቀጠሮ
ከወለድሽ በኋላ ክትትሉ ስለሚቀጥል በ7ኛ ቀን እና በ45 ቀን አንቺ እና ልጅሽ በወለድሽበት ጤና ተቋም መታየት መልካም ነው።

#እንቅስቃሴ
በብዙ ማህበረሰብ አራስ ቤት ውስጥ እንድትወሰን እነዳትንቀሳቀስ ጓዳ ውስጥ እንድትሆንና ተከልላ እንድትቀመጥ የሚደረጉ ሲሆን የማይበረታታ እና ያረጀ ፋሽን ስለሆነ ቤት ውስጥ መጠነኛ መደበኛ እንቅስቃሴ እንድታደርግ አየር እና የፀሃይ ብርሃን እንድታገኝ ያስፈልጋል።
ባለመንቀሳቀስ ምክንያት የደም መርጋት ፣ ኢንፌክሽን፣ የሆድ ድርቀት እና የአጥንት መሳሳት ሊከሰት ይችላል።
አራሷ በሚመቻት መጠንና ሰዓት እንድትንቀሳቀስ ማበረታታት ያስፈልጋል።

#የአካል ንፅህና
በማህፀን የወለደች እናት በወለደችበት ቀን ገላዋን መታጠብ የምትችል ሲሆን በደንገጡር ታግዛ ካልሆነም ተቀምጣ እንድትታጠብ ይመከራል።
በኦፕራሲዮን ከወለደች ደግሞ ከ72 ሰዓት በኃላ መታጠብ እንደሚቻል ሳይንስ ያስቀምጣል።

#የመራቢያ አካላት ንፅህና
የመራቢያ አካል ላይ የተደረገ መለስተኛ ቀዶጥገና ካለ በቀን 4-6 ጊዜ ለብ ባለውሃ ለ10ቀናት ያህል መታጠብ ያስፈልጋል።
ጨው እና ዲቶል እንዲሁም ሌሎች በሃኪም ያልታዘዙ ባዕድ ነገሮች መጨመር ወይም መቀባት ለኢንፌክሽንና ለቁስል መፈታት ስለሚያጋልጥ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

#የረካቤ ስጋ
ከወሊድ በኋላ የመራቢያ አካላት ቁስለት ብግነት እና እብጠት ከዳነ አና አንቺ የግንኙነት ፍላጎት ካለሽ ግንኙነት አይከለከልም። ይህም ከ4-6ሳምንት በኋላ እንደሆነ ሳይንስ ቢያስቀምጥም በተለያየ ቤተ እምነቶች ከ45ቀናት በኋላ እንደሚፈቀድ ተቀምጣሉ።

#የወሊድ መከላከያ
አንድ ሴት ከወለደች በኋላ ከ45ቀናት ጀምሮ እርግዝና ሊከሰት ይችላል። ምንም እንኳን የወርአበባ ባይመጣም ጡት ብቻ የምታጠባም ቢሆን መቶበመቶ እርግዝና ሊከላከል ስለማይችል አስቀድሞ መጠንቀቅ ግድ ነው።

#የልጅ ክትባት
ከወለድሽ በኋላ ወዳውኑ የሚሰጡ ክትባቶች ልጅሽ ማግኘቱ ካረጋገጥሽ በኋላ የቀጣይ ቀጠሮ ይዘሸ መሄድን አትርሺ
ልጅሽ እንደተወለደ ፣ 45 ቀኑ ፣ በ10 ሳምንቱ ፣ በ14 ሳምንቱ፣ በ6 ወሩ እንዲሁም በ9 ወሩ ክትባት መውሰድ እንዳለበት አስታውሺ
ክትባቶቹ ከፖሊዮ፣ ከኩፍኝ ፣ከቲቢ ፣ ከተቅማጥ ፣ ከሳንባምች ፣ ከቴታነስ ፣ ከጉበት ቫይረስ ፣ ከማጅራት ገትር ፣ ከትክትክ እና ሌሎች አደገኛ ህመሞች እንደሚከላከል አስቢ።

#የልጅ እጥበት
ያለጊዜው የተወለደ ልጅ ከሆነ ማጠብ ሙቀት ከሰውነቱ እንዲባክን ስለሚያደርግ በቂ ኪሎ እስከሚያገኝ በዋይፕስ መጥረግ ይቻላል። በጊዜው የተወለደ ለልጅ ከሆነ ግን ከተወለደ 24 ሰዓታት በኋላ ሞቅ ባለ ቤት ውስጥ ለብ ባለ ውሃ አጥቦ በንፁህ ጨርቅ በማድረቅ አቅፎ ማሞቅ ያስፈልጋል።

#የጡት ማጥባትና የልጅ አመጋገብ
ከተወለደ ደቂቃ እስከ 6ወራት የእናት ጡት ብቻ መስጠት ለልጁ ጤንነትና ተመጣጣኝ እድገት ወሳኝ ሚና አለው። ውሃ መስጠት ፣ ቂቤ ማላስ እንዲሁም ስኳር በጥብጦ ማጠጣት የመይደገፉ ኋላቀር አሰራሮች መሆናቸው አውቀሽ ለ6 ወራት ጡት ብቻ መጥባትን ልማድ እናድርግ።

#ፀሃይ ማሞቅ
ከወለድሽ 7-10ቀናት ጀምሮ ልጅሽን የፀሃይ ብርሃን በየቀኑ ማሳየት ያስፈልጋል። ልጅሽን ምንም ሳትቀቢ የጠዋት ፀሃይ 30-40ደቂቃ ማሞቅ እድገቱ የተስተካከለ እና አጥንቱ የጠነከረ እንዲሆን ያደርጋል።

ማጠቃለያ፦  ሳይንሳዊ ዳራ ከሌላቸው አጉል አስተሳሰቦች ተላቀን የነቃና ጤነኛ ማህበረሰብ ለመፍጠር ሁላችንም የድርሻችን እንወጣ።
ዶ/ር ነጋልኝ መቻል

https://t.me/jossiale2022

2 months, 3 weeks ago
[#CPD](?q=%23CPD)

#CPD
Ethio Medical Training Center

#የካቲት_19_ማክሰኞ  የሚጀምር የCPD ስልጠና

ስልጠናው ለማንኛውም የጤና ባለሙያዎች  የሚሆን ነው። 
ኮሩሱ፦ #Community_First_Aid ሲሆን #900ብር ነው።
• 15CEU የያዘ ሰርተፍኬት በአንድ ዙር ስልጠና ያገኛሉ።
#ሰልጣኞች
➯ ሀኪሞች
➯ ነርሶች
➯ ፋርማሲዎች
➯ ለላብ ባለሙያዎች እና ለሌሎችም የሚሆን
https://t.me/ethiomedicaltrainingplc
ባሉበት ሁነው ይደውሉ!!! ይመዝገቡ።
0921785903
አድራሻ፦ ጎተራ ንፋስ ስልክ ማሞ ባቡር  ፌርማታ ሲደርሱ ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ

2 months, 3 weeks ago
CPD ስልጠና፦ ART ላይ!!!

CPD ስልጠና፦  ART ላይ!!!

#ART (Comprehensive HIV Care) training  ለምትፈልጉ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ

➩ ስልጠናው የCPD ማዕከል ከሆኑ የመንግስት ሆስፒታሎች ጋር በትብብር ይሰጣል።
➩ በግሩፕ ለምትመጡ 10% ቅናሽ እናደርጋለን።

#ለመመዝገብ
👇👇👇👇👇
➩ 0921785903 ላይ ይደውሉ።
https://t.me/ethiomedicaltrainingplc

2 months, 3 weeks ago
[#CPD\_ነገ](?q=%23CPD_%E1%8A%90%E1%8C%88) \_ጧት

#CPD_ነገ _ጧት

#የCPD_ስልጠና_ቅዳሜ_የካቲት_16_የሚጀምር

ኢትዮ ሜድካል ትሬኒንግ ሴንተር
➩ የሚጀምርበት ቀን #ቅዳሜ_የካቲት16
➩ ስልጠናው፦ #Syndromic_Management_of_Sexual_Transmitted_Diseases (STI)ነው።

➩ ለማንኛውም ጤና ባለሙያ ይሆናል።
#ክፍያ ለ15 CEU =900ብር ብቻ

👉 ቦታ ሳይሞላ ማስታወቂያውን እንዳዩ ደውለው ወይም ሙሉ ስም ቴክስት በመላክ ይመዝገብ።
0921785903 ላይ ይደውሉ። ወይም መልዕክት ያስቀምጡ!!!!
https://t.me/ethiomedicaltrainingplc

4 months, 4 weeks ago
Ethio Medical Training Center

Ethio Medical Training Center

#ከታህሳስ_16/2016 የሚጀምር የCPD ስልጠና

ስልጠናው ለማንኛውም የጤና ባለሙያዎች  የሚሆን ነው። 
ኮሩሱ፦ #Adolescent_and_youth_health (AYH) ነው።
• 15CEU የያዘ ሰርተፍኬት በአንድ ዙር ስልጠና ያገኛሉ።
#ሰልጣኞች
➯ ሀኪሞች
➯ ነርሶች
➯ ፋርማሲዎች
➯ ለላብ ባለሙያዎች እና ለሌሎችም የሚሆን
https://t.me/ethiomedicaltrainingplc
ባሉበት ሁነው ይደውሉ!!! ይመዝገቡ።
0921785903
አድራሻ፦ ጎተራ ንፋስ ስልክ ማሞ ባቡር  ፌርማታ ሲደርሱ ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ

5 months ago

#መልካም_ዜና
ሸር ያድርጉ!!! ለሚመለከታቸው ሁሉ ያድርሱ!!!

➩ ውሎአቹሁ በመንግስት ወይም በግል መስሪያ ቤቶች የሆነ ወይም በግል ስራችሁ ላይ የተጠመዳችሁ በሙሉ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የጤና ችግሮች ዙሪያ በአማረኛ ቋንቋ በቂ ግንዛቤ (ስለበሽታዎቹ ጥልቅ ማብራሪያ) እየሰጠን እንገኛለን።
➩ ስልጠናውን መውሰድ በእጅጉ ጠቃሚ ነው። የአኗኗር ዘይቤን በማስተካከል በሽታዎችን ለመከላከል፣ ተጠቂም ከሆኑ በቀላሉ ለመቆጣጠርና ለመዳን፣ የማይድን ከሆነም ጉዳት እንዳያደርስ ለማድረግና ቀለል ያለ ህይዎትን ለመምራት ያስችለዎታል።
➯ ስለበሽታዎች በቂ ግንዛቤ መያዝ የችግሩ መፍቻ ዋና ቁልፍ ነው።
#ስልጠና_የምንሰጥባቸው_የበሽታ_አይነቶች
1. የስኳር በሽታ
2. ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት
3. የሪህ በሽታ
4. የደም ቅባት መጠመር
5. ውፍረት እንደት እንደሚቀነስ
6. ካንሰርን በተመለከተ
7. መካንነትን በተመለከተ
8. እርግዝናን በተመለከተ
9. የኩላሊት፣ የጉበት፣ የልብ ችግሮችን በተመለከተ
10. የጨጓራና አንጀት ችግሮችን በተመለከተ
11. ጭንቀት፣ ውጥረት እና ፍራቻን አስመልክቶ
12. ማንኛውም የስነ አእምሮ ችግር በተመለከተና ሌሎችንም ጭምር እንደፍላጎታችሁ....
#የስልጠና_ጊዜ

➩ ከሰኞ አሰከ አርብ ከምሽቱ 12 :00 - 1:30
➩ ቅዳሜና እሁድ ሙሉ ቀን (በመረጡት ከሰዓት ወይም ከጧቱ ፈረቃ) ይሆናል።
#ለመመዝገብና_ቦታ_ለመያዝ
0921785903
አድራሻ ጎተራ ማሳለጫ ማሞ ሰፈር ራሚ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ

5 months ago

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድ የኢንፎ ሄልዝ ሴንተር ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ?

✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️
ዛሬ ስለ ሄፓታይተስ "ቢ" ወይም የጉበት በሽታ አይነት "ቢ" ስለሚባለው እናወራለን። ሁላችሁም ስለምታደምጡን እናመሰግናለን ቀጥታ ወደ ሀተታየ ልግባ።

🗣️🗣️🗣️🗣️🗣️🗣️🗣️🗣️🗣️🗣️🗣️🗣️🗣️🗣️🗣️
በመጀመሪያ ግን ጉበት ስለሚባለው የሰውነት ክፍል ጥቂት ነገር ማለት ይኖርብኛልና ከሱ ነው የምንጀምረው።

@በትልቅነቱ በቀዳሚነት የሚታወቅ በቀኝ የላይኛው የሆድ ክፍል ላይ የሚገኝ ዋና የሰውነት አካል ክፍል ነው ጉበት። ጤናማ የሆነ ጉበትን በእጃችን ዳሰን ለማግኘትም ሆነ ለማወቅ እንቸገራለን። ምክንያቱም ጉበታችን የቀኝ የሳንባ ክፍልን ወደላይ ገፋ በማድረግ በጎድን አጥንቶች ጭምር የተሸፈነ በመሆኑ ነው። በመልኩ ቀላ ያለ ወይም በቀይ እና በቢጫ ቀለም መሀል የሚገኝ ሲሆን ክብደቱ እስከ ሶስት ፓውንድ ይመዝናል።

🔋🔋🔋🔋🔋🔋🔋🔋🔋🔋🔋🔋🔋🔋🔋🔋
• ጉበት የሰውነታችን #ባትሪ እና ዋና #የጉሙሩክ ጣቢያም ነው በመባል ይታወቃል። ለዚህም ማብራሪያ እናቅርብ ከተባለ በመጀመሪያ የምንበላውን እና የምንጠጣውን ነገር አይን ያየዋል። "ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል ፤ አፍ የሚጎርሰውን እጅ ይመጥነዋል" (1) እንደሚባለው ከአይን እና እጅ ያለፈው ጎጅ ነገር በምላስ አማካኝነት ወደ ሆድ እንዳይገባ ይደረጋል። (2) ለዛም ነው መሮን፣ እጅግ ጣፍጦን ወይም ጎምዝዞን ቋቅ ብሎን የምንተፋው። ከአፋችን አምልጦ የገባውን ደግሞ ጨጓራ ውስጥ ያለው አደገኛ አሲድ እንዳልነበር ያደርገዋል። (3)በመቀጠል በቀጭን አንጀት አማካኝነት አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ ጠቃሚ ነገሮች ናቸው የተባሉትን እየመጠጠ ወደ መጨረሻው የማጣሪያ እና ፍተሻ ጣቢያ ይልካል። (4) እርሱም ጉበት ነው።(5) ማንኛውም የበላነው እና የጠጣነው ነገር ይህን ሂደት አልፎ ጉበት ጋ ከደረሰ በኋላ በየአይነቱ እየተፈተሸ፣ እየተጣራ፣ እየተመጠነ፣ መወገድ ያለበት እየተወገደ፣ መርዛማውን እያከሸፈ፣ አስፈላጊውን ንጥረ ነገር እያመረተ፣ ከበዛው ላይ ቀንሶ በማስቀመጥ፣ ያነሰው ላይ ከስቀመጠው ላይ ጨምሮ ወደ ልብ በመላክ ለሁሉም የሰውነት አካል ክፍል እንድደርስ ይደረጋል።

✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️✌️
#የጉበት_ጥቅሞች
🐠 ከቀጭን አንጀት ጠቃሚ ንጥረ ነገር ይዞ የመጣን ደም ወደቀረው የሰውነት አካል ክፍል ሳይሰራጭ ያጣራል። ይፈትሻል።
🐠 ማርዛማ የሆኑ ኬሚካሎችን ኢመርዛማ ያደርጋቸዋል።
🐠 በአፍ የሚወሰዱ መድሀኒቶችን በሚፈለገው መንገድ ያደቃቸዋል።
🐠 ስብን፣ ቅባትን፣ አልኮልን፣ ኮሌስትሮልን የሚፈጭ ኬሜካል ያመርታል።
🐠 ቫይታሚን "ኬ" እና ሌሎች ደም ቀጥኖ እንዳይደማ የሚያደርጉ ፕሮቲኖችን ያመነጫል።
🐠 ኮሌስትሮል፣ አላስፈላጊ ሆርሞን፣ አላስፈላጊ የሀሞት ፈሳሽ እና ተረፈ መድሀኒቶች እንድወገዱ ያደርጋል።
🐠 ስኳርን፣ ቫይታሚኖችን እና ጠቃሚ ማዕድናትን በውስጡ ያጠራቅማል።
🐠 የበዛ አልኮል ወደ ሰውነት እንዳይሰራጭ ያደርጋል።
🐠 በደም ውስጥ ያሉ መርዛማ ንጥረነገሮችን ያከሽፋል። ያጣራል። ከዚህ ተግባሩ የተነሳ ጉበታችን ለተለያዩ ችግሮች ወይም ጉዳቶች በቀላሉ ተጋላጭ ይሆናል።

ለምሳሌ፦ ለጉበት ኢንፌክሽን፣ ለጉበት ካንሰር፣ ለጉበት መበጣጠስ፣ ለጉበት መስባት፣ ውሀ መቋጠር፣ የጉበት ስራ ማቆምና ሌሎችም ችግሮችን መዘርዘር ይቻላል። እዚህ ላይ አውቀን ማለፍ ያለብን ነገር ቢኖር በምንበላውና በምንጠጣው ነገር የጉበትን ጤንነት መወሰን እንደምንችል ነው። ጉበት ይቅርታን አብዝቶ የሚቸር 90% አካሉን አጥቶ ሳለ በቂ ህክምናና እንክብካቤ ከተሰጠው ወደነበረበት ሊመለስ የሚችል ድንቅ የሰውነት አካል ክፍል ነው። ለማንኛውም ጉበት እንድህ ይላችኋል፦ እባካችሁ መጠኑ የጨመረ አልኮል አትጠጡብኝ😭 በምትኩ ብዙ ውሀ ላኩልኝ😁 እያለ ነው። ይሄ ቀልድ አይደለም!!!

ወደዛሬው እርዕሳችን ልግባ...
👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌
#የጉበት_ኢንፌክሽን_አይነት "ቢ" ይህም ሄፓታይተስ "ቢ" እየተባለ የሚጠራው ነው። ሄፓታይተስ ቢ በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ የጉበት ኢንፌክሽን አይነት ነው። በጊዜ መኖሩ ካልታወቀ እና እንደ አስፈላጊነቱ እየታየ ህክምና ካልተወሰደ ደግሞም የአኗኗር ዘይቤን ከቫይረሱና ከጉበት ባህሪ ጋር ማጣጣም ካልተቻለ ለህይዎት እጅግ አስጊ በሽታ ነው።

@የጤና ክትትል ካልተደረገ፣ ህክምና ካልተወሰደ እና የአኗኗር ዘይቤ ካልተቀየረ ለጉበት መበጣጠስ እና ለጉበት ካንሰር የማጋለጥ እድሉ ከፍተኛ ነው። ከፍ ሲልም ጉበትን ከአገልግሎት ውጭ አድርጎ ለሞት ያደርሳል።

🌎🌍🌍🌍🌍🌍🌍🌍🌍🌍🌍🌍🌍🌍🌍🌍
• ይህ የጉበት ቫይረስ በአለማችንም ሆነ በሀገራችን እጂግ ብዙ ሰዎችን የሚያጠቃ አደገኛ ተዛማች ቫይረስ ነው። በ2019 የአለም ጤና ድርጅት እንዳወጣው መረጃ ከሆነ 296ሚሊዎን ሰዎች ከቫይረሱ ጋር ይኖራሉ። በየአመቱ ደግሞ 1.5 ሚሊዎን የሚደርሱ ሰወች እንደ አድስ ሲያዙ በየአመቱ 820ሺ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ህይዎታቸውን ያጣሉ።
👎👎👎👎👎👎👎👎👎👎👎👎👎👎👎
በጣም ጥሩው ዜና በዚህ ቫይረስ ከተጠቁት መሀል 90-95% የሚሆኑት ሰዎች እያወቁም ይሁን ሳያውቁ በ6 ወር ውስጥ ሙሉ በሙሉ ከበሽታው ይድናሉ። ስለዚህ እርስዎም ሳያውቁት ታመው ድነው ይሆናል። ይህ ግን ከ5 አመት በታች ያሉ ህፃናትን አያካትትም። ለእነርሱ ተገላቢጦሽ ነውና!
• 5-10%የሚሆኑት ደግሞ የረጅም ጊዜ ተጠቂ ይሆናሉ። ይህንን ልዩነት የሚያመጣው ቫይረሱን የመከላከል አቅም መለያየት ነው።

• ለረጅም ጊዜ ተጠቂ ከሚሆኑት(5 -10%ዎቹ) መሀል ከ 70 - 80% የሚሆኑት ቫይረሱ በውስጣቸው እንዳለ አውቀው አስፈላጊውን ጥንቃቄ፡ ክትትልና ህክምና ካደረጉ በህይዎታቸው የሚፈጠር ብዙ ችግር የለም። ቀሪዎቹ 20 - 30% የሚሆኑት ደግሞ በተለያየ ምክንያት ለጉበት ካንሰር እና ለጉበት መበጣጠስ ተጋልጠው በአጭር ወይም በረጅም ጊዜ ለሞት ይዳረጋሉ። ባጠቃላይ ስናየው ከመቶ ሰው 2 ወይም 3 ሰው ማለት ነው።

• በዚህ መሰረት ሄፓታይተስ "ቢ" በሁለት ይከፈላል። የአጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ ተብሎ። የአጭር ጊዜ የሚባለው አንድ ሰው በቫይረሱ ከተያዘበት ቀን አንስቶ እስከ ስድስት ወር ያለውን ጊዜ ሲሆን 90 - 95% የሚሆኑት ሰዎች የሚገኙበት ነው። የረጅም ጊዜ የምንለው ግን በስድስት ወር ውስጥ ከሰውነት ሳይጠፋ ሲቀር እና ለረጅም አመታት ወይም እድሜ ልክ በሰውነት ውስጥ መኖርን ሲቀጥል ነው። 5 - 10%የሚሆኑት ሰዎች የሚገኙበት ክፍል ማለት ነው። ከነዚህ ውስጥ 1% የሚሆኑት በየአመቱ ከቫይረሱ ነፃ የመሆን እድል አላቸው።
📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌
በሄፓታይተስ "ቢ" የተጠቃ ሰው ሊያሳያቸው የሚችሉ ምልክቶችን ስናይ፦
• ብዙ ጊዜ ምርመራ ካላልተደረገ ሳይታወቅ ለአስርት አመታት የመቆየት እድል አለው። የጉበት 80 - 90% አካሉ እስኪጎዳ ላይታወቅ ይችላል። የተወሰኑት ሰዎች ላይ ደግሞ ጉበት ሳይጎዳም በመጠቃቱ ብቻ የሚያሳያቸው ምልክቶች አሉ። እየቆየ እና ጉዳቱ እየጨመረ ሲሄድ ምልክቶቹም በዚያው ልክ እየጨመሩ ይመጣሉ። እንደ አጠቃላይ ምልክቶቹን ስናይ ግን፦

5 months ago
[#መልካም\_ዜና](?q=%23%E1%88%98%E1%88%8D%E1%8A%AB%E1%88%9D_%E1%8B%9C%E1%8A%93)

#መልካም_ዜና
ሸር ያድርጉ!!! ለሚመለከታቸው ሁሉ ያድርሱ!!!

➩ ውሎአቹሁ በመንግስት ወይም በግል መስሪያ ቤቶች የሆነ ወይም በግል ስራችሁ ላይ የተጠመዳችሁ በሙሉ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የጤና ችግሮች ዙሪያ በአማረኛ ቋንቋ በቂ ግንዛቤ (ስለበሽታዎቹ ጥልቅ ማብራሪያ) እየሰጠን እንገኛለን።
➩ ስልጠናውን መውሰድ በእጅጉ ጠቃሚ ነው። የአኗኗር ዘይቤን በማስተካከል በሽታዎችን ለመከላከል፣ ተጠቂም ከሆኑ በቀላሉ ለመቆጣጠርና ለመዳን፣ የማይድን ከሆነም ጉዳት እንዳያደርስ ለማድረግና ቀለል ያለ ህይዎትን ለመምራት ያስችለዎታል።
➯ ስለበሽታዎች በቂ ግንዛቤ መያዝ የችግሩ መፍቻ ዋና ቁልፍ ነው።
#ስልጠና_የምንሰጥባቸው_የበሽታ_አይነቶች
1. የስኳር በሽታ
2. ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት
3. የሪህ በሽታ
4. የደም ቅባት መጠመር
5. ውፍረት እንደት እንደሚቀነስ
6. ካንሰርን በተመለከተ
7. መካንነትን በተመለከተ
8. እርግዝናን በተመለከተ
9. የኩላሊት፣ የጉበት፣ የልብ ችግሮችን በተመለከተ
10. የጨጓራና አንጀት ችግሮችን በተመለከተ
11. ጭንቀት፣ ውጥረት እና ፍራቻን አስመልክቶ
12. ማንኛውም የስነ አእምሮ ችግር በተመለከተና ሌሎችንም ጭምር እንደፍላጎታችሁ....
#የስልጠና_ጊዜ

➩ ከሰኞ አሰከ አርብ ከምሽቱ 12 :00 - 1:30
➩ ቅዳሜና እሁድ ሙሉ ቀን (በመረጡት ከሰዓት ወይም ከጧቱ ፈረቃ) ይሆናል።
#ለመመዝገብና_ቦታ_ለመያዝ
0921785903
አድራሻ ጎተራ ማሳለጫ ማሞ ሰፈር ራሚ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 2 days ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago